አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የቀብድ ክፍያ ሲባል ምን ማለት ነው? አንዱ ወገን ለሌላኛው የቀብድ ክፍያ መፈፀሙ በህግ አግባብ በሰጪና በተቀባይ ላይ ምን ውጤት ያስከትላል ? በፍትሓብሄር ሕጋችን ህጋዊ አንድምታው ምን ይመስላል?
________________
https://telegram.me/lawsocieties
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የኢፌድሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌስቡክ ገጽ ተከታታዮቻችን ለዛሬ ቀብድ በፍትሓብሄር ህጋችን ያለውን ህጋዊ አንድምታ በተመለከተ አንድ ጥንቅር ልናስነብባችሁ ወደናል ከወዲሁ መልካም ንባብ ተመኝን፡፡

ቀብድ/ቃብድ ክፍያ ማለት?
-------------------------------
ቀብድ ከጥንት ጀምሮ ህብረተሰቡ ሲጠቀምበት የነበረ ሲሆን ብላክስ ሎው ዲክሽነሪ የቀብድ ክፍያ ሲተረጉም የቀብድ ክፍያ ማለት ውል መደረጉን ለማረጋገጥ ገዥ ለሻጭ የሚሰጠው ገንዘብ ወይም ዋጋ ያለው ዕቃ ማለት ነው ብሎ ይተረጉመዋል፡፡

በሀገራችንም የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1883 የቀብድ ትርጉም ሲያስቀምጥ አንድ ወገን ለአንዱ ወገን ቀብድ መስጠቱ በማያከራክር ሁኔታ ውል መደረጉን ያረጋግጣል በማለት ይገልፃል፡፡ ይሁን እንጂ በፍትሐብሔር ህግ ስለውል አፈፃፀም ድንጋጌዎች መሰረት በፅሁፍ ሊደረጉ እና በፍ/ቤት መዝገብ ወይም ውል የማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ፊት መሆን የሚገባቸው ውሎች በፅሁፍ ሳይረደጉ ቀረተው ቀብድ መሰጠቱ ብቻ ውል መፈፀሙ አያረጋግጥም፡፡

የቀብድ ክፍያን ምንነት የበለጠ ለመረዳት ይቻል ዘንድ በጉዳዩ ላይ የሚያጠነጥን አንድ ኬዝ እናስነብባችሁ፡- የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰ/መ/ቁ. 56794 በአመልካች አቶ ሳህለ ሙለጌታ በተጠሪዎች በእነ አቶ ሰለሞን ኤፌሬም ክርክር ላይ የሰጠውን የህግ ትርጉም መመልከት ተገቢ ነው፡፡

የጉዳዩ መነሻ ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አመልካች ለተጠሪዎች ቤት ለመሸጥ ተስማምቶ የቀብድ ክፍያ ከተቀበለ በኋላ አመልካች ውሉን መሰረዙ በደብዳቤ የገለፀ ሲሆን ተጠሪዎች በውሉ
መሰረት ቤቱን እንዲያስረክብ ይህ ቢታለፍ የቀብዱን አጠፌታ እንዲክፍል እንዲወሰን በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ አቅርበው አመልካች/ሻጭ ቀርቦ በመካከላችን ከረቂቅ ያለፈ በህግ ፊት የሚፀና የሽያጭ ውል የሌለ በመሆኑ ክስ ውድቅ እንዲደረግልኝ በማለት መልስ ሰጥቷል፡፡ ከፍተኛ ፍ/ቤቱም የፍትሐብሔር ህጉን የቀብድ ድንጋጌዎች በመጥቀስ በአመልካች/

በሻጭና በተጠሪዎች/በገዥዎች መካከል የሽያጭ ውል ያለ በመሆኑ በውላቸው መሰረት ሻጭ ቤቱን ያስረክብ ገዢዎችም ቀሪውን ክፍያ ይፈፅሙ በማለት ወስኗል፡፡

ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህንን የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ያፀናል፡፡ አመልካች በውሳኔው ቅር በመሰኘት ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በውል አዋዋይ ወይም በፍ/ቤት መዝገብ ሹም ፊት ያልተደረገ ውል አስገዳጅነት ያለውና የፀና ውል ነው በማለት በስር ፍ/ቤትና በይግባኝ ሰሚ ችሎት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ጥሰት አለበት፡፡

ውል አለ ቢባል እንኳን በውሉ አደራረግ ወቅት ተፅእኖ ያለበት በመሆኑ የቀበድን አጠፌታ እንድከፈል ያቀረበው ጥያቄ አግባብ አይደለም በማለት አመልክቷል፡፡

የሰበር ሰሚ ችሎት የስር ፍ/ቤት ተጠሪዎች ለአመልካች የቀብድ ገንዘብ የከፈሉ መሆኑና አመልካች ከተጠሪዎች የቀብዱን ገንዘብ የተቀበሉ በመሆናቸው ይህም የቤት ሽያጭ ውል መደረጉን በማያከራክር ሁኔታ እንደሚያረጋግጥ የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1883 በተደነገገው መሰረት ያደረገ በመሆኑ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስኗል፡፡

ከዚህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ቀብድ ሰጪ/ከፋይ ለቀብድ ተቀባይ የቀብድ ክፍያ መፈፀሙ በሲጪና በተቀባይ መካከል በቀጣይ የሚፈፀም/የሚጠናቀቅ ውል መኖሩን የሚያረጋግጥ መሆኑን መረዳት እንችላለን፡፡

እንዲሁም በፅሁፍ ሽያጭ ውል መሰረት ተደርጎ የቀብድ ክፍያ ከተፈፀመና ይህም በሁለቱ ወገኖች የታመነ ሆኖ እያለ በውልና ማስረጃ ባለመመዝገቡ ብቻ ውል የለም ማለት ከፍትሐብሔር ህጉ ቁጥር 1723 ዓላማ ጋር የሚሄድ አለመሆኑ ከዚህ ውሳኔ እና ከሰ/መ/ቁ 36887 መረዳት ይቻላል፡፡

በአጭሩ የቀብድ ክፍያ ማለት በተዋዋይ ወገኖች መካከል ውል መኖሩ እና ተዋዋይ ወገኖች በውሉ ለመገደድ ወይም ውሉን እስከ መጨረሻው ተከታትሎ ለመጨረስ ያለን ፍላጎት ለማሳየት ሲል በመያዣነት ቀብድ ሰጪ ለቀብድ ተቀባይ የሚሰጠው ክፍያ ነው፡፡ በዚህ ዓይነቱ ክፍያ ተዋዋይ ወገኖች መካከል የሽያጭ ወይም የአገልግሎት የውል ስምምነት መኖሩን፤ በቀጣይም ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች በውል ስምምነቱ ለመገደድ ያላቸውን ፍላጎት የሚገልጽበት ነው፡፡

ቀብድ ክፍያ ውጤት ምንድነው?
--------------------------------------
https://telegram.me/lawsocieties
በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1884 መሰረት ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ቀብድ ተቀባይ ውሉ ከተፈፀመ በኋላ የቀብዱን ገንዘብ መመለስ ወይም ውሉ ሲፈፀም ከጠቅላላው ክፍያ መቀነስ ያለበት መሆኑ ይደነግጋል፡፡

ሰለዚህ ለተዋዋይ ወገኖች የተወወ ቢሆንም ሌላ ስምምነት ካላደረጉ ውሉ ሲፈፀም የቀብድ ክፍያ እንደ ቅደመ ክፍያ ይቆጠራል ወይም ቀብድ ተቀባይ ለቀብድ ሰጪ ይመልሳል፡፡

ቀብድ ሰጪ ወይም ቀብድ ተቀባይ ውሉ ለመተው ቢፈልጉ ያለ ኃላፊነት/ግዴታ በፍ/ህግ ቁ. 1885 ስር ተደንጓል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት ሌላ ስምምነት ከሌለ በስተቀር ቀብድ ሰጪ የሰጠውን የቀብድ ክፍያ በመልቀቅ ውሉ መተው ይችላል፡፡

ቀብድ ተቀባይ ደግሞ የተቀበለውን ቀብድ አጠፌታ በመክፈል ውሉን መተው ይችላል፡፡ ቀብድ ሰጪና ቀብድ ተቀባይ ውሉን ሲያፈርሱ የሚከፈለው የቀብድ ክፍያ መጠን አንድ አይነት አይደለም፡፡ ቀብድ ተቀባይ የቀብዱን እጥፍ እንዲከፈል ህጉ ያስገደደው የተደረገው ውሉ ባለመፈፀሙ ምክንያት በሌላኛው ወገን (በቀብድ ሰጪ) ሊደረስ የሚችለውን ጉዳት እንደማካካሻ እንዲሆን በማሰብ ነው፡፡

ከላይ በተመለከት ነው የሰበር ክርክር ጉዳይን የቀበድ ውጤትን ለበለጠ ለመረዳት ስንመለከት ችሎቱ በውላቸው ላይ የተለየ ስምምነት የሌለ በመሆኑ በፍ/ህግ ቁጥር 1885 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት አመልካች/በቀብድ ተቀባይ የቀብዱን አጠፌታ በመክፈል ውሉን የማፍረስ መብት አላቸው፡፡

ስለሆነም በስር ፍ/ቤቶች ቀብድ የተከፈለበት ውል ሆኖ እያለ የፍ/ህግ ቁጥር 1885 ንዑስ አንቀጽ 2 ከግንዛቤ ሳይሰገቡ አመልካች/በቀብድ ተቀባይ ለተጠሪዎች ቤቱን እንዲያስረክብ እና የሽያጭ ውሉን እንዲፈፀም የተሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት ያለበት ነው፡፡

አመልካች ከተጠሪዎች የተቀበለውን ቀብድ ብር 206,000 /ሁለት መቶ ስድስት ሺህ ብር/ አጠፌታ አድርጎ ብር 412,000 /አራት መቶ አሥራ ሁለት ሺህ ብር/ ለተጠሪዎች በመከፍል የሽያጭ ውለን ማፍረስ ይችላል በማለት ወስኗል፡፡

ሰለዚህ ቀብድ ክፍያ በቀብድ ሰጪና በቀብድ ተቀባይ መካከል ውል መኖሩን ከማረጋገጥ በላይ ቀብድ ሰጪ ሆነ ቀብድ ተቀባይ በሕግ የተጣለባቸውን ግዴታና ኃላፊነት በመወጣት ማለትም ቀብድ ሰጪ ቀብድ ክፍያውን በመተው እንዲሁም ቀብድ ተቀባይ የቀብድ አጠፌታውን በመክፈል ውለታውን ማፈረስ ይችላሉ፡፡

ውድ አንባቢያን ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁን ጥንቅር በዚሁ አበቃን በቀጣይ በሌላ ርዕሰ ጉዳይ እስክንገናኝ ሰላም፡
https://telegram.me/lawsocieties
የወጣቶች የወንጀል ፍትሕ እና የክስ አጀማመር ህጋዊ አንድምታው ምን ይመስላል
--------------------------------------
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌስቡክ ገጽ ተከታታዬቻችን፤ እንዴት ናችሁ ለዛሬ የወጣቶች የወንጀል ፍትሕ እና የክስ አጀማመር ህጋዊ አንድምታው ምን ይመስላል በሚል አንድ ጥንቅር ልናስነብባችሁ ወደናል ከወዲሁ መልካም ንባብ ተመኘን፡፡

እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች በሕግ የተለየ ጥበቃ ይደርግላቸዋል። ይህ ጥበቃ በሕገ-መንግሥት፣ በቤተሰብ ሕግ፣ በውርስ ሕግ፣ በውል ሕግ፣ በወንጀል ሕግ፣ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ፣ በአሠሪና ሠራተኛ ሕግ፣ በአለም ዓቀፍ ስምምነቶች እና በሌሎችም በርካታ የይዘት ሕጎች ተደንግጎ የሚገኝ ነው። እነዚህ ሕጎች ከሞላ ጎደል የሚጋሩት ጉዳይ ከ18 ዓመት በታች ለሆኑት ሰዎች ይበልጥ በሚጠቅም መርህ የያዙ መሆናቸው ነው። በወንጀል የፍትሕ ሥርዓት ለወጣቶች እንዲሁም ለሕፃናት የሚደረገው ጥበቃ በወንጀል ሕጉ እና በሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተዘረጋውን ሥርዓት የሚያጠቃልል ነው። የወንጀል ሕጉ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶችን/ሕፃናትን በሦስት የእድሜ ክልሎች ማለትም ከ9 በታች፣ ከ9-15፣ ከ15-18 በመመደብ በተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች እንዲገዙ አድርጓል።

ወጣቶችን የሚመለከተው የሥነ-ሥርዓት ሂደት እንደዚሁ ከመደበኛው በይዘት የተለየ፣ ከሌሎች ታሳቢዎች የሚንደረደርና በሌሎች መርሆች የሚመራ ነው። ይህ ልዩነት ከሞላጎደል በሁሉም የሂደቱ ደረጃዎች የሚንፀባረቅ ነው። ስለሆነም ምርመራው፣ ክሱ፣ የመስማት ሂደቱና የማረም ሥርዓቱ የራሱ ገፅታዎች ያሉት ነው።

የወንጀል ፍትሕ ሂደት የሚመራው በዋናነት በወንጀል የሥነ-ሥርዓት ሕግ ነው። የሥነ-ሥርዓት ሕጉ የወንጀል ጉዳዮችን በማስመልከት ሦስት የተለያዩ ሀዲዶችን አስቀምጧል፤ አንድ መደበኛና ሁለት ልዩ ሥነ-ሥርዓቶችን። ሁለቱ ልዩ ሥነ-ሥርዓቶች የደንብ መተላለፍንና (አንቀጽ 167-180) የወጣቶችን ጉዳይ (አንቀጽ 171-180) የሚመለከቱ ሲሆን ሦስተኛው ከነዚህ ውጭ ያሉትን ሁሉንም የወንጀል ጉዳዮች የሚሸፍነው መደበኛው ሥነ-ሥርዓት ነው።

ሀ የክስ አጀማመር (setting justice in motion)
ወጣቶችን የሚመለከት የወንጀል ምርመራ በልዩ ሥርዓት የሚመራ ነው። እንደሚታወቀው በመደበኛ የወንጀል ጉዳዮች የፍትሕ ሂደት የሚጀምረው ማንም ሰው በሚያቀርበው ክስ ወይም አቤቱታ መነሻነት ነው (አንቀጽ 11) ። አቤቱታ ወይም ክስ ማቅረብ መብት ቢሆንም በፍትሐብሔር ሂደት እንደሚደረገው ክሱን ወይም አቤቱታውን ቀጥታ ለፍርድ ቤት ማቅረብ አይቻልም። ክስ ወይም አቤቱታ ማቅረብ የሚቻለው ለፖሊስ ነው።

በመሆኑም የወንጀል የፍትሕ ሂደት የክስ አቀራረብ፣ ማስረጃ አሰባሰብና አቀርረብ ከፍትሐብሔሩ የተለየ ነው። በፍትሐብሔር የሙግት ሂደት ማስረጃ ማሰባሰብም ሆነ ለፍትሕ ተቋማት የማቅረብ ኃላፊነት በዋናነት የከሳሽና የተከሳሽ ነው። በመሆኑም ግለሰቦች (ከሳሽና ተከሳሽ) የራሳቸውን ጉዳይ የሚመለከት ማስረጃ የማሳባሰብ እንዲሁም ለፍርድ ቤት የማቅረብ የግል ኃላፊነት አለባቸው። የወንጀል የፍትሕ ሥርዓቱ ከዚህ በተለየ ሁኔታ ማስርጃ የማሰባሰቡም ሆነ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ ከግል ወደ መንግሥት ኃላፊነት በማዘዋወር ግለሰቦች ከዚህ ኃላፊነት ነፃ እንዲሆኑ አድርጓል። በዚህ መሠረት ሕጉ በወንጀል ጉዳዮች ሪፖርት የማቅረብ መብት ለዜጎች ሲሰጥ ሪፖርቱን የመቀበል፣ የመመዝገብ እና የማጣራት ሥልጣንና ኃላፊነት የፖሊስ አካላት እንዲሆን አድርጓል። በመሆኑም የወንጀል ጉዳይ የሚጀምረው ለፖሊስ በሚቀርብ ክስ ወይም አቤቱታ መነሻነት ነው።

"ማናቸውም የወንጀል ክስ (ቁጥር 11) ወይም የክስ አቤቱታ (ቁጥር 13) ለፖሊስ ወይም ለዓቃቤ ሕግ ማቅረብ ይቻላል። አካለመጠን ባላደረሰ ወጣት ላይ የሚቀርብ ክስ ወይም የክስ አቤቱታ በቁጥር 172 መሠረት መቅረብ አለበት"
በማለት የመደበኛውና የወጣችቶ ጉዳይ በተለያየ ሥርዓት እንደሚጀምር ያሳያል። አንቀጽ 172 በሌላ በኩል ወጣት አጥፊዎች በወንጀል ገብተው ሲገኙ ጉዳዩ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሳይሆን ወደ ፍርድ ቤት የሚቀርብ መሆኑን ይደነግጋል።
አንቀፁ"አካለ መጠን ያልደረሰ ወጣት በወንጀል ነገር ውስጥ ገብቶ በተገኘ ጊዜ ፖሊሱ፣ ዐቃቤ ሕጉ፣ ወላጁ ወይም ሞግዚቱ በቅርብ ወደሚገኘው የወረዳ ፍርድ ቤት ወድያውኑ ይዞት ይቀርባል" በማለት ይደነግጋል። ከዚህ ድንጋጌ ይዘት በግልፅ መገንዘብ እንደሚቻለው የወጣቶች ጉዳይ የሚጀምረው ክስን ለፍርድ ቤት በማቅረብ ነው።

በመደበኛው ሂደት ፖሊስ የሚቀርብለትን ክስ ወይም አቤቱታ ተቀብሎ ምርመራውን የመምራት ሥልጣን ሲኖረው በወጣቶች ጉዳይ ላይ ወይም ከ9 አመት በታች፣ ከ9-15፣ ከ15-18 የእድሜ ክልሎች ውስጥ ባሉ ወጣት አጥፊዎች ላይ ይህ ሥልጣን አልተሰጠውም፣ ይህ ሥልጣን የተሰጠው ለፍርድ ቤቶች ነው። ስለዚህ ፖሊስ ገና ከጅምሩ በእነዚህ የእድሜ ክልሎች ውስጥ የሚገኙት የወንጀል ጉዳይ የሚያስተናገድበት እድል የለም።

በአጠቃላይ ፖሊስ ወጣቶቹን ወድያውኑ ወድ ፍርድ ቤት ከመውሰድ ያለፈ ሌላ ተግባር የለውም። ከዚህ ቀጥሎ እንደምንመለከተው ፖሊስ ክሱንም ሆነ አቤቱታውን ተቀብሎ የምርመራ መዝገብ የመክፈት ኃላፊነት ስለሌለበት በጉይዩ ላይ ማንኛውንም አይነት የምርመራ ሥራ የማከናወንም ተግባር አይጠበቅበትም። በመርህ ደረጃ ምርመራ የማከናወን አደራ የተሰጠው ለፖሊስ ተቋም ቢሆንም ሕጉ ወጣቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ይህ ኃላፊነት ለፍርድ ቤት እንዲሆን ይደነግጋል፡፡

ውድ አንባቢያን ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁን ጥንቅር በዚሁ አበቃን በቀጣይ ክፍል በወጣት አጥፊዎች ላይ ማስረጃዎች እንዴት ይሰበሰባሉ የከስ አቀራረብ ሂደት ምን ይመስላል በሚሉና በመሰል ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ጥንቅር ወደ እናንተ እናደርሳለን በቀጣይ እስክንገኛኝ ሰላም፡፡
መረጃውን ያገኘነው ከአቢሲኒያ ሎው ድህረ-ገጽ ነው፡፡
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
#NewsAlert ‼️

#Ethiopia : ከዛሬ ጀምሮ ከቤት ውጪ በሁሉም ቦታዎች ማስክ የማድረግ ግዴታን የሚጥል መመሪያ ፀደቀ! ከዛሬ ጀምሮ ከቤት ውጪ በሁሉም ቦታዎች ማስክ የማድረግ ግዴታን የሚጥል መመሪያ መፅደቁን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።

"ለራስ፣ ለቤተሰብ፣ ለወገን እና ለሀገር ብለን ከሌሎች ስህተት በመማር ጥንቃቄአችንን ከበፊቱ በላይ እናጠናክር" ብለዋል ወይዘሮ አዳነች በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት።

ህብረተሰቡ ለራሱ ሲል በመንግስት እና በባለሞያዎች የሚተላለፉትን የጥንቃቄ መመሪያዎች ችላ ሳይል እንዲተገብርና ለህግ አስከባሪው አካል እንዲታዘዝም አሳስበዋል።
ተጠርጣሪ በዋስ እንዲለቀቅ ፍርድ ቤት የሚሰጠው ትዕዛዝ እና አፈጻጸም!
-------------------------------------------------

በቁጥጥር ስር የዋለ ማንኛውም ተጠርጣሪ በዋስ እንዲለቀቅ ፍርድ ቤት የሚሰጠዉ ትዕዛዝ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስትና በሌሎች ህጎችም ጭምር የተረጋገጠ መብት ቢሆንም ትዕዛዙ ሳይፈጸም ሊቆይ የሚችሉበት በሕግ የተደገፉ ምክንያቶች አሉ፡፡

ሰላም የፌስቡክ ገጻችን ተከታታዮች እንደምን አላችሁ ዛሬ የፍርድ ቤት ትእዛዝና አፈፃፀሙን በተመለከተ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዋስትና ተፈቅዶላቸዉ የሚለቀቁበትንና ተጠርጣሪዎች ሳይለቀቁ የሚቆዩበትን አግባብ ህጋዊ ማዕቀፉን መሰረት አድርገን በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ጉደታ ቀንዓን አናግረን ያዘጋጀንላችሁን ፅሁፍ ወደ እናንተ ልናደርስ ወደናል መልካም ንባብ! ከሦስቱ የመንግስት አካላት ወይም ክፍሎች መካከል አንዱ የዳኝነት አካል ነው፡፡

በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 78 (1) መሰረት የተቋቋሙት ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ የዚሁ ህግ አንቀጽ 79 (1) በግልጽ ደንግጎታል፡፡
ፍርድ ቤቶች በዚሁ የዳኝነት ስልጣናቸው አለመግባባቶች በስምምነት ካልተፈቱ ወይም የወንጀል ጉዳይ ክስ ሲቀርብለት ተከራካሪ ወገኖችን በማከራከር መፍትሔ/ውሳኔ የሚሰጡ ሲሆን በፍርድ ቤት የሚታዩ ጉዳዮችም የፍታብሔር ወይም የወንጀል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ፍርድ ቤት በክርክር ሂደት ዉስጥ ለዉሳኔ አሰጣጥ እንዲመቸዉ የተለያዩ ትዕዛዞችን ይሰጣል፡፡ ትዕዛዞቹ አንድ ሰው ወይም አካል የተጠቀሰውን ድርጊት እንዲፈፅም ወይም እንዳይፈፅም የሚሰጥ አቅጣጫ ሲሆን እነዚህ ትዕዛዛት ተከሳሽ፣ ከሳሽ፣ ምስክር ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ መጥሪያ መስጠት፣ የእግድ ትዕዛዝ (ንብረት፣ የሰው እንቅስቃሴ ሊሆን ይችላል፣ ማስረጃዎች እንዲቀርቡ ወይም ምስክሮች ፍርድ ቤት ቀርበዉ እንዲያስረዱ፣ የመያዣ ወይም የመልቀቂያ ትዕዛዝ፣ የአፈፃፀም ትዕዛዝ እና ሌላ ለክስ መስማት ሂደት የሚያስፈልግ ትዕዛዝ ሊሆን ይችላል፡፡ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዴት ይፈፀማል የሚለዉን ጉዳይ ስንመለከትም ትዕዛዙ በራሱ በፍርድ ቤት ወይም በተከራካሪ ወገኖች ወይም በፖሊስ ትዕዛዙን ለሚፈጽመው ሰው ወይም አካል ሊደርስ ይችላል፡፡ ትዕዛዙ በፍቃደኝነት ሊፈጸም ይችላል፡፡ ሆኖም በፍቃደኝነት ካልተፈፀመ በማስገደድ (የአስፈፃሚ አካል/ፖሊስ እገዛ በመጠየቅ) የሚፈፀም ይሆናል፡፡

ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት ትዕዛዛት ባልተከበሩበት ሁኔታ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑ ሁሉም አካላት ትዕዛዛቱን የማክበር ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በፍርድ ቤት የተሰጠን ትእዛዝ ወይም ዉሳኔ አለመፈፀም የፍትሐ ብሔር እና/ወይም የወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡ የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ ማክበር ለህግ ተገዥነትን ወይም በህግ የበላይነት ማመንን የሚያሳይ ነው፡፡ በተጨማሪም የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ ማክበር ህብረተሰቡ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ያለውን አመኔታ እንዲያድግ ያደርጋል፡፡
በተቃራኒው የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ አለማክበር የህግ የበላይነትን የሚሸረሽር እና ህገ-ወጥንት የሚያስፋፋ በመሆኑ ያለ በቂ ምክንያት የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ አለማከበር በፍትሐ ብሔርና ወንጀል ህጎች ሥነ-ሥርዓት ላይ የተቀመጡ የትዕዛዝ አለማከበር ውጤቶች ተፈፃሚ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለአብነት በማስገደድ ማስፈፀም፣ የእስር እርምጃ (ፍ/ስ/ስ/ህግ ቁ. 389 እንደተቀመጠው) በተለይ በችሎት ጉዳዮች ላይ አለመታዘዝ በፍርድ ቤት መድፈር ወንጀል ሊያስቀጣ ይችላል፡፡

በተጨማሪም በወንጀል ሕግ ላይ የተቀመጡ የፍርድ ቤት ትዕዛዝን አለመፈጸምን የሚመለከቱ የወንጀል ድንጋጌዎች መሰረት ተጠያቂነትን ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ይሁንና ተጠርጣሪው የተጠረጠረበት ወንጀል በዋስትና መለቀቅን የማያስፈቅድ ሲሆን ወይም በሌላ በሥነ-ሥርዓት ህጉ በተቀመጡት ምክንያቶች ተጠርጣሪው በዋስትና ከሚለቀቅ በእስር ላይ መቆየቱ ፍትሃዊ ውሳኔ ለማሰጠት የሚረዳ (በቀጣይ ላይቀርብ የሚችል አይነት ሲሆን፣ ወይም ማስረጃ የሚያጠፋ፣ ሌላ ወንጀል ሊፈጽም የሚችል እንደሆነ) ከነኚህ እና ሌሎች ምክንያቶች አንጻር የተጠርጣሪው በዋስትና መለቀቅ ላይ ፖሊስ ወይም ዐቃቤ ህግ ቅሬታ ያለው እንደሆነ ይግባኙን ጉዳዩን ቀጥሎ ላለው ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡

ፍርድ ቤቱም ይግባኝ ጥያቄውን ከተቀበለ በኋላ ተገቢ መሆኑን ሲያምን አከራክሮ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በስር ፍርድ ቤት ተሰጥቶ የነበረው ትዓዛዝ ሳይፈጸም ታግዶ እንዲቆይ ሊያዝ ይችላል፡፡ ይህ የሆነ እንደሆነ የዋስትና መብቱ ተጠብቆለት የነበረው ተጠርጣሪ በእስር ላይ ሊቆይ ይችላል፡፡ ይሁንና ይግባኙን የመረመረው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ካጸና ተጠርጣሪው ወዲያውኑ ሊለቀቅ ይገባል፡፡ በሌላ በኩል በወንጀል ተጠርጥሮ ከተያዘ በኋላ ፍርድ ቤቱ በዋስ እንዲለቀቅ የፈቀደለት ተጠርጣሪ በሌላ የወንጀል ጉዳይ የሚፈለግ ወይም በሌላ ወንጀል የተጠረጠረ ከሆነ በማቆያ እንዳለ ሊቆይ ይችላል፡፡

በዚህ ምክንያት በአንድ ወንጀል ተጠርጥሮ የዋስትና መብት ከተፈቀደለት በኋላ ተጠርጣሪው ሳይለቀቅ በመቅረቱ ምክንያት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አልተከበረም ሊያስብል አይችልም፡፡ ይሁንና በዚህ ምክንያት በእጁ ያቆየው ፖሊስ ስለ ተጠርጣሪው አቆያየት ትዕዛዝ ለማሰጠት ፍርድ ቤት ሊያቀርበው የሚገባ ስለመሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ከነዚህ ምክንያቶች ውጭ የዋስትና መብቱ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተጠብቆለት እያለ ትዕዛዙን በመጣስ ተጠርጣሪው በእስር ላይ እንዲቆይ ያደረገ ማንኛውም ሰው ከተጠያቂነት የሚድን አይሆንም፡፡

ስለሆነም ህብረተሰቡ ሊያዉቀዉ የሚገባው ጉዳይ ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቅ ትዕዛዝ የሰጠበት ሰዉ ሕጋዊ በሆኑ ሌሎች ምክንያቶች መሰረት በእስር እንዲቆይ የሚደረግበት ሁኔታ እንዳለ እና ከዚህ ባለፈ በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎች ማጣራት እና በዋስ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ተሰጥቶላቸው ያልተለቀቁ ሰዎች በእስር ላይ የቆዩበት ምክንያት ከላይ ከተነሱት ምክንያቶች አንጻር በተገቢው ታይተው እንደሆነ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም መንገድ ያለ አግባብ ታስሮ ያለ ሰው ካለ ነባራዊ ሁኔታዎች ቦታዉ ላይ በመገኘት ጉዳዩን ማየትና መመርመር ያስፈልጋል፡፡
ለአንድ አገር የፍትህ ስርዓት መጎልበት ሕግን አክብሮ መንቀሳቀስ ተገቢ ሲሆን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲኖር ሕጉ በሚፈቅደዉ መሰረት ሕጋዊ እስከሆነ ድረስ መመራት እንደሚያስፈልግና ይህንን አለማድረግ ግን ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑን አዉቆ ህጉ በሚፈቅደዉ መሰረት መሰራት አለበት የእንግዳችን መልእክት ነዉ፡፡
Via Federal General Attorney
@lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የፌደራል ጠቅላይ ዕቃቤ ሕግ

የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ (preliminary objection) ሲባል ምን ማለት ነው?
______________________
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የፌስቡክ ገጻችን ተከታታዮች ብዙውን ጊዜ በዜና አውታሮች ፍርድ ቤቱ በነ እገሌ የክስ ሂደት ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ለመስማት ቀጠሮ ሰጠ ሲባል እንሰማለን ለመሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ሲባል ምን ማለት ነው? ለዛሬ በዚሁ አርዕሰት ላይ እናንተን ያስተምራል ያልነውን ጥንቅር ወደናንተ ልናደርስ ወደድን ተከታተሉን፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ተከሳሹ ስለ ክሱ ማመልከቻ ፎርም ወይም በክስ ማመልከቻ የተገለፀውን ነገር የሚቃወምበት ስርዓት ነው፡፡የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አላማ ፍርድ ቤት እና ተከራካሪ ወገኖች ወደ ክርክሩ ፍሬ ነገር ሳይገቡ መነሳት ያለባቸውን ነጥቦች በማንሳት ውሳኔ በመስጠት ጊዜ መቆጠብ ነው፡፡ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊነሳባቸው የሚችሉ ነጥቦች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የክሱን ይዘት በተመለከተ ሊቀርብ ይችላል፡፡ይህም ማንኛውም የክስ ማመልከቻ ቀንና ዓመተ ምህረት የተፃፈበት እና የተፈረመበት እንዲሁም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እንዲገልፅ ያስፈልጋል፡፡እነዚህም ተከሳሽ የተከሰሰበት ወንጀል እንዲሁም የወንጀሉ መሰረታዊ ነገር እና ሁኔታዎች፤ወንጀሉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ስፍራ ተገቢ በሆነ ጊዜም በደል የደረሰበት ሰው ስም ወይም ወንጀሉ የተፈፀመበት ንብረት፣ተከሳሽ ድርጊቱን በመፈፀም የተላለፈው የህግ አንቀጽ መያዝ አለበት፡፡ክሱ ግልፅ እና የተከሳሽን የመከላከል መብት የማያጣብብ መሆን አለበት፡፡
በመሆኑም እነዚህ ነገሮች ግልፅ ባልሆኑ እና ባልተሟሉ ጊዜ ተከሳሽ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማንሳት ይችላል፡፡ በተጨማሪ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 130/2 ስር የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚያስነሱ ነገሮች ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡
• ተከሳሽ በዚሁ ነገር ክስ በሌላ ፍርድ ቤት ተጀምሮ በቀጠሮ ያለ መሆኑ
• በዚሁ ክስ ከዚህ በፊት ተከሶ ነፃ የወጣ ወይም የጥፋተኝነት ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑ
• ክስ የቀረበበት ወንጀል በይርጋ ህግ የታገደ ወይም ምህረት ወይም ይቅርታ የተደረገለት መሆኑ ከተረጋገጠ፡፡ ይርጋ ማለት አንድ የወንጀል ድርጊት ተፈፅሞ ክስ ለማቅረብ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ማለት ነው፡፡በወንጀል ህግ አንቀጽ 219 ስር እንደተደነገገው የይርጋ ዘመን የሚታሰበው የቅጣት ማከበጃ ወይም ማቅለያ ሁኔታዎች ግምት ውሰጥ ሳይገቡ በወንጀል ህጉ ልዩ ክፍል የተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት መሰረት በማድረግ ነው፡፡የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው ጥፋተኛው የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመበት አንስቶ ነው፡፡ለምሳሌ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ወንጀሉ በተፈፀመ በአስር አመት ውስጥ ክስ መቅረብ አለበት፡፡አስር አመት ካለፈ ግን ክስ ማቅረብ አይቻልም ማለት ነው፡፡
• ከሌሎች ወንጀለኞች ጋር በተከሰሰ ጊዜ እና ለብቻው ተነጥሎ ክሱ ባይታይለት የሚጎደው መሆኑን፣
• ክሱን ለማቅረብ በህጉ መሰረት ፈቃድ ያልተሰጠ መሆኑ ለምሳሌ ተከሳሽ በአለም አቀፍ ህግ ዲፕሎማቲክ ኢሙኒቲ የማይከሰስ እንደሆነ፣
• በሌላው ችሎት የቀረበው ክስ ሳይፈፀም በዚህ የወንጀል ክስ ሊሰጥ የማይገባ መሆኑ፣
• ለፈፀማቸው ተግባሮች ኀላፊ አለመሆን ፤ለምሳሌ የተከሳሽ አድሜ ከዘጠኝ አመት በታች ከሆነ፣ በወንጀል ህግ አንቀጽ 48 ላይ እንደተመለከተው ማንም ሰው በእድሜ ፣ በህመም ፣ባልታሰበ የእድገት መዘግየት ወይም ጥልቅ በሆነ የአዕምሮ የመገንዘብ ችሎታ መቃወስ ወይም የወንጀል ድርጊት በሚፈፅምበት ጊዜ የድርጊቱን አይነት ወይም ውጤት ለመገንዘብ ወይም በዚህ ግንዛቤ መሰረት ራሱን ለመቆጣጠር በፍፁም ያልቻለ ሲሆን ኢ-ኃላፊ ስለሚሆን አይቀጣም፡፡
ከላይ የተዘረሩት ነጥቦች ባጋጠሙ ጊዜ ተከሳሽ እራሱ ወይም ጠበቃ ካለው በጠበቃው አማካኝነት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ሊያነሳ ይችላል፡፡
ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ሲጠይቀው ተከሳሹ የክሱን ማመልከቻ ወዲያውኑ ካልተቃወመ በቀር ቆይቶ እንዲህ ያለውን መቃወሚያ ነገሩ በሚሰማበት በሌላ ጊዜ ሊነሳ የሚችለው ፍርድ ቤቱን የሚፀና ፍርድ ለመስጠት የሚያግደው ከሆነ ብቻ ነው (ወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.130/3)፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ተከሳሽ አንድ ጊዜ ተከሶ በተቀጣበት ወንጀል ድጋሚ ሊከሰስ እንደማይገባ ይህም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባይነሳም በማንኛውም ጊዜ ሊነሳ እንደሚችል የሚያሳየንን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 72304 የሰጠውን ውሳኔ እንደ አብነት ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
ጉዳዩ ባጭሩ ተከሳሽ በስር ፍርድ ቤት በቀላል አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሶ ከተቀጣ በኃላ ተበዳይ በመሞታቸው ዐቃቤ ህግ ድጋሚ በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ክስ ሲያቀርብ ተከሳሽ እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሳያነሳ ቀርቶ በኃላ በተመሳሳይ ወንጀል ድጋሜ ያለመከሰስ መብት principle of double jeopardy ይነካል ማለቱ ተገቢ አይደለም ብሎ የተከራከረበት ጉደይ ነው፡፡
ሰበር በውሳኔ ዝርዘሩ ላይ እንዳስቀመጠው “ አንድ ሰው በወንጀል ህግ እና ስነ ስርዓት ተከሶ የመጨረሻ ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ጥፋተኛ ሆኖ ተቀጥቷል ወይም ነፃ ተለቋል የሚለው መከራከሪያ በመጀመሪያ የወንጀል ክስ የክስ መቃወሚያ ሆኖ መቅረብ ያለበት መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 130 የተደነገገ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የቀረበው የክስ መቃወሚያና ማስረጃ በመመርመር ውሳኔ መስጠት ያለበት መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 131 ተደንግጓል፡፡ሆኖም አንድ ተከሳሽ በወንጀል ተከሶ በመጨረሻ ፍርድ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በተቀጣበት የወንጀል ድርጊት በድጋሜ ያለመከሰስ ያለመጠየቅ መብት መሰረታዊ እና ህገ መንግስታዊ መብት በመሆኑ ክርክሩ በሚካሄድበት በማናቸውም ደረጃ ሊነሳ የሚችልና በማስረጃ ተረጋግጦ በተገኘ ጊዜ ፍርድ ቤቶች ተቀብለው ብይን ሊሰጡበት የሚገባ መሆኑ በውሳኔው አስፍሯል፡፡
ከመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ጋር ሊምታታ የማይገባው መቃወሚያ በማለት ተከራካሪ ወገኖች እንደ አስፈላጊነቱ ዐቃቤ ሕግም ይሁን ተከሳሽ በክርክር ወይም ምስክር በሚሰማበት ጊዜ ጣልቃ የሚገቡበት ስነ ሥርዓት ነው፡፡
ለምሳሌ ምስክር በሚሰማበት ጊዜ ለምስክሩ በዋና ጥያቄ ላይ መሪ ጥያቄ ቢቀርብ ወይም ምስክሩ ከተመለከተው ወይም ከሚያውቀው ነገር ባሻገር ግላዊ አስተያየቱን ወይም ግምቱን እንዲሰጥ ቢጠየቅ ወይም ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ ጥያቄ ቢጠየቅ ተከራካሪ ወገኖች መቃወሚያ አለኝ ብለው ፍርድ ቤቱን በማስፈቀድ ምስክሩ መልስ እንዳይመልስ ማድረግ ይችላሉ፡፡
ውድ አንባቢያን ለዛሬ ካዘጋጀንላችሁ ጥንቀር በጉዳዩ ዙሪያ ዕውቀት እንደጨበጣችሁ ተስፋ እናደርጋለን በቀጣይ በሌላ ፕሮግራም እስክንገናኝ መልካሙን ሁሉ ተመኝን ሰላም፡፡
https://t.me/lawsocieties
የጥብቅና ፍቃድ ለማውጣት መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች!
________
ሰላምጤና ይስጥልን የኢፊዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌስቡክ ፔጅ
ተከታታዮቻችን በምን እንጠይቅልዎ አምዳችን ስር ከተነሱት ጥያቄዎች አንደኛዉ
ጠበቃ ለመሆን መሟላት ያለባቸዉን መስፈርቶች በተመለከተ ማብራሪያ
እንዲሰጥበት በጠየቃችሁን መሰረት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ
አሰጣጥና ምዝገባ አዋጅ 199/1992 ዋቢ አድርገን የሚከተለዉን ፅሁፍ
አዘጋጅተናል፡፡ መልካም ንባብ!
የጥብቅና አገልግሎት በሕግ ሙያ የሠለጠነና ሰፊ ልምድ ያለው፤የፍርድ ቤት
አሠራርን ጠንቅቆ የሚያውቅ፤የታማኝነት፤የቅንነትና የእውነተኝነት መንፈስን
የተላበሰ ሰው ለሕግ የበላይነትና ለፍትሕ መስፈን ከፍትሕ አካላት ጐን
በአጋዥነት የሚሰለፍበት ሙያ በመሆኑ፤በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለመሥራት
የሚችሉ ጠበቆችን ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ሁኔታ በተሟላ መልኩ በሕግ
መደንገግ በማስፈለጉ፤የጥብቅና ሥራ የሚሠሩ ሰዎችን የሙያ ብቃት ደረጃ
ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር የተመጣጠነ ለማድረግ በሥራው ለመሠማራት
የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን ከፍ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤በኢትዮጵያ
ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥትአንቀጽ55(1) መሠረት
የሚከተለው ታውጇል።
ፈቃድ ለማግኘት ስለሚቀርብ ማመልከቻ
=============================
1.የጥብቅና ፈቃድ ለማግኘት የሚቀርብ ማመልከቻ ለዚሁ ተግባር በሚኒስቴሩ
በተዘጋጀ ቅጽ ተሞልቶይቀርባል፡፡
2.አመልካቹ ከማመልከቻው ጋርየሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ ይኖርበታል፡-
ሀ/የትምህርት ማስረጃውን፤
ለ/ከቀድሞ አሠሪው ስለ ሥነምግባሩ ወይም ስለ ሥራ አፈጻጸሙ የሚገልጽ
ደብዳቤ፤
ሐ/እንደአስፈላጊነቱ ፈቃድ ለማግኘት የሚሰጠውን የሙያ መግቢያ ፈተና
ማለፉን የሚያሳይ ማስረጃ፣
መ/የፈቃድክፍያመፈጸሙንየሚያሳይማስረጃ፣
ሠ/የሙያ ኃላፊነት መድን ዋስትና መግባቱን የሚያሳይ ማስረጃ፣
ረ/ሌሎች በሚኒስቴሩ የሚጠየቁ ማስረጃዎች፤ማቅረብ አለበት፡
3.በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) (ሐ) የሚቀርብ ሠርተፊኬት ዋጋ የሚኖረው
ፈተና ማለፉ በታወቀ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከቀረበ ብቻ ነው፡፡
ፈቃድ ስለመስጠት
=============
1.ሚኒስቴሩ የጥብቅና ፈቃድ ማመልከቻ በአንቀጽ 4 መሠረት ተሟልቶ
ሲቀርብለት ከ30 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ተገቢውን ውሣኔ መስጠት
አለበት፡፡
2.በፈቃዱ ላይ የሚጠቀሱት የሚከተሉትን ይጨምራል፤
ሀ.የጠበቃውን ሙሉ ስምና ዜግነት፣
ለ/መደበኛ የመኖሪያና የሥራ አድራሻ፣
ሐ/የፈቃዱንዓይነት፣መ/የፈቃድሰጭውን ስምና ፊርማ።
3.ቋሚ ሥራ ላለው ሰው የጥብቅና ፈቃድ አይሰጥም።
የፈቃድ ዓይነቶች በሚኒስቴሩ የሚሰጡ የሚከተሉት ሦስት ዓይነት የጥብቅና
ፈቃዶች ይኖራሉ፤
ሀ/የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ፣
ለ/የፌዴራል ማናቸውም ፍርድቤት ጥብቅና ፈቃድ፣እና
ሐ/የፌዴራል ልዩ የጥብቅና ፈቃድ፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥብቅና ፈቃድ
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የፌዴራል
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ ይሰጠዋል፡
1.በሕግ ዕውቅና ካገኘ የትምህርት ተቋም በዲፕሎማ በሕግ
የተመረቀ፣የኢትዮጵያን መሠረታዊ ሕጐች የሚያውቅና በሙያው ቢያንስ
የአምስት ዓመት ልምድ ያለው ወይም በሕግ በዲግሪ የተመረቀ፣የኢትዮጵያን
መሠረታዊ ሕጐችየሚያውቅና በሙያው ቢያንስ የሁለት ዓመት ልምድ ያለው፣
2.ለፍትሕ ሥራ አካሄድ መልካም ሥነ ምግባር ያለው፣
3.ለደረጃው የሚሰጠውን የጥብቅና መግቢያ ፈተና ያለፈ
4.ምግባረ ብልሹነትን በሚያመለክት ወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ፤
5.የሙያ የኃላፊነት መድኅን ዋስትና መግባቱን የሚያሳይ ማስረጃ ያቀረበ፡
የፌዴራል ማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የፌዴራል
ማናቸውም ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ ይሰጠዋል፡
1.በሕግ ዕውቅና ካገኘ የትምህርት ተቋም በሕግ ዲግሪ የተመረቀ፣የኢትዮጵያን
መሠረታዊ ሕጐች የሚያውቅና በሙያው ቢያንስ የአምስት ዓመት ልምድ ያለው፡
2.ለፍትሕ ሥራ አካሄድ መልካም ሥነምግባር ያለው፣
3.ለደረጃው የሚሰጠውን የጥብቅና መግቢያ ፈተናያለፈ፣
4.ምግባረ ብልሹነትን በሚያመለክት ወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ፣
5.የሙያ የኃላፊነት መድኅን ዋስትና መግባቱን የሚያሳይ ማስረጃ ያቀረበ፡፡
የፌዴራል ልዩ የጥብቅና ፈቃድ
======================
1.የኅብረተሰቡን አጠቃላይ መብትና ጥቅም ለማስከበር የሚሟገትና
ከዚህበታችየተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያሟላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የፌዴራል
ልዩ የጥብቅና ፈቃድ ይሰጠዋል፤
ሀ/በሕግ ዕውቅና ካገኘ የትምህርት ተቋም በሕግ በዲግሪ
የተመረቀ፣የኢትዮጵያንመሠረታዊ ሕጐችየሚያውቅና በሙያው ቢያንስ የአምስት
ዓመት ልምድ ያለው፤
ለ/ከሚወክለው የህብረተሰብ ክፍል ወይም ደንበኛ ምንም ዓይነት ክፍያ
የማይቀበል፣
ሐ/ፀባዩ ይህን ኃላፊነት ለመቀበል ተስማሚ የሆነ፤
መ/ምግባረ ብልሹነትን በሚያመለክት ወንጀል ተከሶያ ልተቀጣ፡፡
2.የጥብቅና ፈቃድ ያለውማንኛውም ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ1
የተገለጹትን የሚያሟላ ከሆነ ልዩ የጥብቅና ፈቃድ ሳያስፈልገው አገልግሎት
መስጠት ይችላል፡፡ነገር ግን ይህን ግልጋሎት ከመስጠቱ በፊት ሚኒስቴሩን
ማሳወቅ አለበት፡፡
የፈቃድ እድሣት
1.የጥብቅና ፈቃድ በየአመቱ መታደስ አለበት፡፡
2.ፈቃድ ለማሳደስ የሚቀርብ ማመልከቻ ፈቃዱ የሚያገለግልበት የአንድ ዓመት
ጊዜ ከማለቁ ከአንድ ወር በፊት መቅረብ አለበት፡፡
3.አመልካች በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣው ደንብ የሚወሰነውን የማሳደሻ
ክፍያ ይከፍላል ዉድ አንባቢያን ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለጋችሁ በፅሁፋችን
ምንጭ አድርገን ከወሰድነዉ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ አሰጣጥና
ምዝገባ አዋጅ 199/1992 ማንበብ እንደምትችሉ ለመጠቆም እንወዳለን
ሰላም!
https://telegram.me/Ethiopian_Legal_Advocate
የቅጣት ማክበጃ ምክንያት (aggravating circumstance)
--------------------
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ የፌስቡክ ገጽ ተከታታዮቻችን እንዴት ናችሁ ለዛሬ አንድ ሰው በማወቅም ይሁን ባለማዎቅ በሰራው ወንጀል ፍርድ ቤት ቀርቦ በሚከራከርበት ሰዓት ዐቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃ ምክኒያቶችን አቀረበ ሲባል እንሰማለን ለመሆኑ የቅጣት ማክበጃ ምክኒያቶች ምንድን ናቸው?
የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች በሁለት ይከፈላሉ እነኚህም ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት እና ልዩ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ለዛሬ ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶችን በተመለከተ ያዘጋጀንላችሁ አጭር ገለጻ እነሆ….ከወዲሁ መልካም ንባብ ተመኝን፡-
ጠቅላላ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች የምንላቸው በወንጀል ህጋችን በአንቀጽ 84 ስር የተዘረዘሩት ናቸው፡፡
የወንጀል ህጋችን አንቀጽ 84(1) ከፊደል ተራ ሀ-ሠን እንደሚከተለው ተመልክተናቸዋል፡፡

ሀ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው በከሀዲነት ወይም በወስላታነት ወይም በወራዳነት ወይም መጥፎ አመልን በሚያሳይ ምቀኝነት፣ጥላቻ፣ ስግብግብነት፣ መጥፎ ነገርን ለመስራት ወይም ሰውን ለመጉዳት ፍጹም ፍቃደኛ በመሆን ወይም በተለየ ክፋት ወይም በጨካኝነት እንደሆነ ይላል
ወንጀል ታስቦ ወይም በቸልተኛነት ሊፈጸም ይችላል፡፡ከላይ የምንመለከተው ወንጀልን አስበው እና ሆነ ብለው የሚፈጽሙ ሰዎች በፈጸሙት ወንጀል ማግኘት ካሰቡት ያልተገባ ብልጽግና በተጨማሪ ወንጀሉን ለማድረግ ካነሳሳቸው ወይም ምክንያት ከሆናቸው ነጥብ አንጻር የወንጀል አድራጊውን አደገኛነት የሚያመላክት እንደሆነ ፍ/ቤቶች ከላይ በተዘረዘሩት የማክበጃ ምክንያቶች መሰረት ቅጣትን ሊያከብዱ ይችላሉ፡፡በዚህ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ስር የተለያዩ ምክንያቶች የተዘረዘሩ ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት ቅጣትን ለማክበድ ከመካከላቸው የአንዱ መሟላት በቂ ነው፡፡ይህም ማለት ተከሳሽ ወንጀሉን ያደረገው በከሃዲነት ወይም በወስላታነት ወይም በምቀኝነት ወይም በጥላቻ ከሆነ ከነዚህ መካከል አንዱ በወንጀል አድራጊው ወንጀል አደራረግ ውስጥ ከተገኘ በቂ ነው ማለት ነው፡፡እምነቱን በጣለበት ወዳጁ ላይ፣ በተበዳዩ ላይ ባለው የግል ጥላቻ ወይም በምቀኝነት(ጥቅም ለማግኘት ብቻ ሳይሆን አንድ ሰው ጥቅም እንዳያገኝ በማሰብ) ወዘተ ወንጀልን ማድረግ በአብነት ሊነሱ ይችላሉ፡፡

ለ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው ስልጣኑን፣ ተግባሩን ወይም የተጣለበትን እምነት ወይም ሀላፊነት ያለአግባብ በመገልገል እንደሆነ
ባለስልጣናት ወይም የመንግስትን ስራ ለመስራት ወይም ለመምራት ስልጣን ወይም እምነት የተጣለበት ሰው ስራውን በታማኝነት እና በቅንነት መፈጸም አለበት፡፡በተጨማሪም ይህንኑ ስልጣን ተገን በማድረግ ለራሱም ሆነ ለሌላው ጥቅም ለማስገኘት ወይም በሌላ ሰው ጥቅም ወይም መብት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ አንድን ወንጀል ከፈጸመ ቅጣት ሊከብድበት እንደሚገባ የወንጀል ህጉ ይደነግጋል፡፡ይህ የሆነበት ምክንያት ሰዎች ስራ ፈጻሚዎች የሚነግሯቸውን ወይም እንዲያደርጉ የሚያዟቸውን ነገር ሁሉ ስለሚቀበሉ እና ትዕዛዙን መቀበል ካልቻሉ ደግሞ የሚፈልገውን አገልግሎት ላናገኝ እንችላለን ከሚል የአማራጭ ማጣት ሀሳብ ምክንያት ለጉዳት ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡ወንጀል አድራጊውም እምነት ሲጣልበት እምነቱን ወይም አደራውን በተገቢ መንገድ መወጣት አለበት፡፡

ስራውን የሠጠው ሰው እምነቱን የጣለበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ጠባቂ የሌለው በመሆኑ ስልጣኑን ወይም ሀላፊነቱን ለግል ጥቅሙ ለማዋል አይችልም፡፡ሰነዶችን በህገ-ወጥ መንገድ ለማይገባው ሰው የሰጠ የመዝገብ ቤት ወይም የአገልግሎት መስጫ ተቋም ሰራተኛ፣ ሌላውን ሰው ከህጋዊ ቅጣት ወይም ክፍያ ለማዳን ሲል ወንጀልን የፈጸመ የትራፊክ ፖሊስ ወይም መርማሪ ፖሊስ እና የመሳሰሉት በምሳሌነት ሊነሱ ይችላሉ፡፡በመሆኑም ከላይ የጠቀስነውን ሁኔታ ተሟልቶ ሲገኝ እንደ አንድ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ተወስዶ ቅጣትን በአንድ እርከን ከፍ ሊያደርግ የሚችል ምክንያት ነው፡፡

ሐ/ ወንጀለኛው በቀድሞ ጥፋተኛነቱ ወይም ወንጀልን ማድረግ ሙያ ወይም ልማድ አድርጎ መያዙ፣ ወይም የወንጀሉ አፈጻጸም ዘዴ፣ ጊዜ፣ ቦታና የአፈጻጸም አኳሀን፣ በተለይም በሌሊት ወይም በሽብር ወይም በሁከት ለአደጋ ሽፋን ወይም በጦር መሳርያ ወይም በሌላ አደገኛ መሳርያ ወንጀሉን በማድረግ የተለየ አደገኝነቱን አሳይቶ እንደሆነ
በዚህ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ስር ሶስት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ እነኚህም፡-ወንጀልን ማድረግ ሙያው ወይም ልማዱ አድርጎ መያዝ ወንጀል አፈጻጸም ዘዴ፣ጊዜ፣ቦታ እና የአፈጻጸም አኳሀን ወንጀልን በጦር መሳርያ ወይም በሌላ አደገኛ መሳርያ መፈጸም ናቸው፡፡

ወንጀል ማድረግን ሙያው ወይም ልማድ አድርጎ መያዝ ማለት ተከሳሹ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት ተመሳሳይ ወይም የተለያዩ ወንጀሎችን በማድረግ የሚታወቅ እና ፍርድ ቤቶች የዚህን ሰው ጉዳይ ተመለክተው በሚሰጡት የመጨረሻ ውሳኔ ጥፋተኛ እያሉት ቅጣት የጣሉበት እና በማረሚያ ቤት ገብቶ የእስር ጊዜውን አጠናቆ ከወጣ በኋላም ወንጀልን ማድረግ ባለማቆም ወንጀልን ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡የወንጀል ህጉ በአንቀጽ 67 ስር ስለደጋጋሚነት ያስቀመጠው ድንጋጌ የተካሳሹን የቀድሞ ባህሪ በቅጣት ማክበጃነት ልንጠቀም እንደምንችል ይደነግጋል፡:

ሌላው ወንጀል አድራጊው ወንጀሉን ለማድረግ አስቀድሞ በማሰብ ተጎጂው እራሱን እንዳይከላከል ወይም ሰው እንዳይደርስለት ወይም ማስረጃ እንዳይገኝበት ለየት ያለ ቦታ በመምረጥ፣ ወይም ሰው በማይንቀሳቀስበት በሌሊት ጨለማን ተገን በማድረግ የፈጸመው እንደሆነ ወይም የወንጀል አድራጊውን አደገኛነት በሚያሳይ ጨካኝነት ወይም በተለየ ስልት ወንጀልን ከፈጸመ፡፡ሌሊት የሚለው ሀረግ ከስንት ሰዓት ጀምሮ እንደሆነ አሻሚ ቢሆንም በተለምዶ ፍርድ ቤቶች ከሌሊቱ 6፡00-12፡00 ድረስ ያለውን የጊዜ ገደብ በሌሊትነት ወስደው ቅጣት ያከብዱበታል፡፡

ሶስተኛው ምክንያት ወንጀልን ለመፈጸም ወንጀል አድራጊው የተጠቀመባቸው መሳርያዎች ናቸው፡፡ ወንጀልን ለመፈጸም ጥቅም ላይ የሚውል መሳርያ የወንጀል አደራረግን ከባድነት ያሳያሉ፡፡በመሆኑም በእጅ ወይም በዱላ የውንብድና ወንጀልን የፈጸመ ሰው እና የስለት ወይም የጦር መሳርያዎችን ተጠቅሞ ይህንኑ ወንጀል የፈጸመ ሰው የወንጀል ማድረግ አደገኛነቱ እኩል ሊሆን አይችልም፡፡በመሆኑም ተከሳሽ ወንጀሉን ለመፈጸም የተጠቀመው መሳርያ በወንጀል ማቋቋሚያነት በልዩ ህጉ ካልተወሰደ በስተቀር በቅጣት ማክበጃ ምክንያትነት ይወሰዳል፡፡
መ/ ወንጀለኛው ወንጀሉን ያደረገው ወንጀል ለመፈጸም በተደረገ ስምምነት መሰረት ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን ወይም ወንጀል ለመፈጸም ከተቋቋመ ቡድን ጋር በመስማማት ወይም አባል በመሆን ይልቁንም እንደ ወንጀል ቡድን ሹም ወይም አደራጅ ወይም መሪ በመሆን እንደሆነ
በየትኛውም ምክንያታዊ አስተሳሰብ በአንድ ሰው መብት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በተናጠል እና በቡድን ወይም ከአንድ በላይ በመሆን መፈጸሙ በተጎጂው ስነልቦና ላይ የሚያደርሱት ተጽዕኖ አንድ ሊሆን አይችልም፡፡በመሆኑም ወንጀልን ለመፈጸም ከሌላው ጋር ወይም ለዚሁ አላማ ከተደራጀ ቡድን ጋር በአባልነት በመስማማት ወንጀልን ማድረግ ቅጣትን ሊያከብድ የሚችል በቂ ምክንያት ነው፡፡
የሀገራት አለምአቀፍ ግንኙነት መርሆች
---------------------

ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፌስቡክ ገጽ ተከታታዮቻችን እንዴት ናችሁ ለዛሬ የሀገራት አለማቀፍ ግንኙነት መርሆዎች ምንድን ናቸው በሚለው ላይ አንድ ጥንቅር ወደ እናንተ ልናደርስ ወደናል ከወዲሁ መልካም ንባብ ተመኝን፡፡

1. የሀገራት ግንኙነትና የሚመራበት ህግ ማዕቀፍ

የአለም ሀገራት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ግንኙነት ይፈጥራሉ፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት የአለም ሀገራት የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር በጋራ የሚሰሩበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ የሀገራት ግንኙነት በኢኮኖሚ፣ ንድግ፣ በፖለቲካ ወይም በፀጥታ ዘርፍ በትብብር መስራት ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይችላል፡፡

በሀገራት መካከል የሚደረግ ማናቸውም ግንኙነት የሚገዛው በአለምአቀፍ ህግ መሰረት ነው፡፡አለምአቀፍ ህግ ደግሞ የራሱ የሆኑ መርሆዎች፣ መብቶችና የሀገራት ግዴታዎች ያሉት ሰፊ ማእቀፍ ነው፡፡ አለምአቀፍ ህግ በተለያዩ የአለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፎች ገዢ የሆኑ ድንጋጌዎችና ደንቦች አሉት፡፡የአለም አቀፍ ህግ ምንጭ በዋናነት የሀገራት የፅሁፍ ስምምነት (ሁለትዮሽም ሆነ ባለብዙ)፣ የዳበረና የታወቀ ልማድ፣ ጠቅላላ መርሆች እና እነዚህን የሚያረጋግጡ አለምአቀፍ ፍርዶችና የታወቁ ምሁራን ፅሁፎች ናቸው፡፡

2. የሀገራት ግንኙነት መርሆች ምንድን ናቸው?

እንያንዳንዱ ሀገር ትልቅም ሆነ ትንሽ፣ ደሀም ሆነ ባለፀጋ እኩል መብትና ግዴታ አለው፡፡ በተጨማሪም የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤትና የሚያስተዳድረው ግዛት አንድነት የማይደፈር፣ በሀገሩ ያሉ ሰዎችና ንብረት ላይ ሙሉ ስልጣን ያለው ነው፡፡ ከዚህም አንፃር የሚከተሉት የታወቁና የተጠበቁ የአለምአቀፍ ህግ ግንኙነት መርሆች ናቸው፡- ሁሉም ሀገራት እኩል መሆናቸው፣ ሀገራት ሉዓላዊ ስልጣን ያላቸው መሆናቸው፣ አለምአቀፍ ግንኙነቶችን በቅን ልቦና ማድረግ፣ በአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ማንም ጣልቃ መግባት አለመቻሉ፣ በአለምአቀፍ ግንኙነት ራስን በመከላከል ካልሆነ በቀር ሀይልን አለመጠቀም፣ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ሀገራት ግንኙነታቸውን እና በተለያዩ ጉዳዮች ያሉ ትብብራቸውን ለማሳለጥ በሁለትዮሽ ግንኙነትም ይሁን በባለብዙ ዘርፍ ግንኙነት በጋራ እየሆኑ አለምአቀፍ እና አህጉራዊ ድርጅቶችን መስርተው በጋራ ለመስራት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ የማናቸውም ሀገራት ግንኙነት ከላይ በተመለከቱት አጠቃላይ የአለምአቀፍ ህጎች እና መርሆች የሚገዙ ናቸው፡፡ ማናቸውም ሀገር የሌላው ሀገር ሉአላዊነት፣ የግዛት አንድነት፣ የፖለቲካ ነፃነት፣ እኩልነት ማክበርና እና በውስጥ ጉዳይ ከመግባት መቆጠብ አለባቸው፡፡ አንድ ሀገር ከሌላ ሀገር ጋር ግንኙነቱ የሻከረ እንደሆነ ወይም አለመግባባት የተፈጠረ እንደሆነ ይህን ለማስተካከል ሰላማዊ በሆነ መንገድ በቀጥታ ወይም ሶስተኛ ወገንን ጨምሮ መነጋገርና ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት ከመጣር በዘለለ በሌላ ሀገር ጉዳይ ጣልቃ መግባት አይችሉም፡፡

በሌላ አገላለፅ በአንድ ሀገር ውስጥ አንድን ወገን መደገፍ ሌላውን መቃወም ወይም አንድ መንግስት ይህን አድርግ ይህን አታድርግ በማለት ኢኮኖሚያዊ ወይም ፖለቲካዊ ጫና ወይም ማእቀብ በመንግስት ላይ ማድረግ በአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ በቀጥታ ጣልቃ መግባት ማለት ነው፡፡ አንድ ሀገር በሌላ ሀገር ውስጥ ጉዳይ ላይ በራሱም ሆነ ሌሎች ሀገራት ጫና እንዲያደርጉበት፣ እንዲያገሉት ወይም ግንኙነት እንዳያደርጉ ማድረግ ግልፅ የሆነ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት እርምጃ እና የአለም አቀፍ ህግ ጥሰት ነው፡፡ ነገር ግን ሀገራት ከእነዚህ መርሆች ውጭ የተለያዩ ምክንያቶችን መነሻ በማድረግ በሌላ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ሲገቡ እና የተለያዩ ጫናዎችን ሲፈጥሩ ይስተዋላል፡፡ በተለይም ግብዣ ሳይቀርብና ፈቃድ ሳይሰጥ በአንድ ሀገር የውስጥ አስተዳደር ጉዳይ በመግባት እንዲህ አድረጉ ወይም እንደዚህ አታድርጉ በማለት በውስጥ ጉዳይ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ጫና ለመፍጠር የሚደረግ ጥረት አለምአቀፍ ህግን የጣሰ ተግባር ነው፡፡

በሌላ በኩል ሀገራት በፈቃዳቸው ያቋቋሙት እና አባል የሆኑበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋነኛ አላማዎች ወይም ተግባራት መካከል አለምአቀፍ ሰላምና ፀጥታ ማስጠበቅ፣ የሀገራትን ወዳጅነት በሉአላዊ እኩልነት ላይ ተመስርቶ ማራመድ፣ የኢኮኖሚ ማህበራዊና ባህላዊ ችግሮችን ለመፍታትና ሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር በትብብር መስራት ይገኙበታል፡፡ ከዚህ አንፃር በአንድ ሀገር ያሉ ሁነቶች አለምአቀፍ ሰላምና ጸጥታን የሚመለከቱ ከሆኑ ወይም በሁለት ሀገራት መካከል ያለ ግንኙነት አለምአቀፍ ሰላምና ፀጥታን የሚያደፈርስ ከሆነ ጉዳዩን በመመልከት ህጋዊ የሆነ መፍትሄ የመስጠት ሀላፊነት ይኖረዋል፡፡ አባል ሀገራትም በዚህ ማእቀፍ ውስጥ ለመስራት ይችላሉ፡፡

የሀገራት ግንኙነት ሊመራ የሚገባው በዚህ ማዕቀፍ ቢሆንም በአንድ ሀገር ውስጥ ሊከሰት የሚችለው ችግር አለምአቀፍ ሰላምና ፀጥታን የሚመለከቱ ጉዳዮች ባልሆነ ጊዜ የሀገራትን ግንኙነት መርሆችን ተከትሎ መንቀሳቀስ ላይ የወጥነት ችግር እና መርህን መሰረት አለማድረግ እንደ ችግር ይታያል፡፡ አለምአቀፍ ሰላምና ፀጥታን የሚመለከት ችግር ባጋጠመ ጊዜ የግጭቶች አካሄድ አለምአቀፍ ህግን ያከበረ እንዲሆን እና ወደ ጎረቤት ሀገሮች ግጭቶች እና ችግሮች ተስፋፍተው አካባቢያዊ ሰላምና ፀጥታን የሚያደፈርስ እንዳይሆን የመከታተልና የመደገፍ ስራ እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያሉ ተቋማት ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ ከዚህም አንፃር ቢሆን የተባበሩት መንግስታት በጉዳዩ የሚመለከተው በአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ሳይሆን ሀገራት የገቡትን አለምአቀፍ ግዴታ ከማክበራቸው አንፃር እና የሀገራት እርምጃ ከአለም አቀፍ ሰላምና ፀጥታ መጠበቅ ላይ ከሚኖረው ተፅእኖ አንፃር ብቻ ሊሆን ይገባል፡፡

በሌላ በኩል የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የሚያጋጥሙ ቢሆን የአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ እና አለምአቀፍ ግዴታን የመወጣት ጉዳይ ነው፡፡ የሰብአዊ መብት ጥሰት ከፍ ያለ እና ስርአታዊ (systemic) መልክ ያለው ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ችግሩን ለመቅረፍ ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ የሚጋብዝ ከሚሆን ውጪ አለምአቀፍ ሰላምና ፀጥታን የሚያናጋ እስካልሆነ ድረስ በስልጣኑ ስር የሚወድቅ ጉዳይ አይሆንም፡፡ በተመሳሳይ የሰብአዊ እርዳታ በምግብም ሆነ መጠለያ በስፋት ማስፈለጉ የአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ቢሆንም አለምአቀፍ ህብረተሰቡ ድጋፍ የማድረግ ሰብአዊ ግዴታ አለበት፡፡ ከዚህ አንፃርም የተባበሩት መንግስታት ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ አንድን ሀገር ይህን አድርግ ይህን አታድርግ ለማስባል የሚበቃ አይደለም፡፡ ወደእዚህ ደረጃ ከፍ ሊል የሚችለው ችግሩ አለምአቀፍ የሰላምና ፀጥታ ችግር ወደ መሆን ደርሷል ወይም ሊደርስ ይችላል የሚባል ሲሆን ብቻ ነው፡፡

በመሆኑም ሀገራት በአለምአቀፍ ግንኙነታቸው አንዱ የሌላውን እኩልነት እና ሉአላዊነት ማክበር፣ በቅን ልቦና ግንኙነቶችን ማድረግ፣ በሌሎች ሀገሮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባትና ጫና አለማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት በበኩሉ የስልጣንና ሀላፊነት ወሰኑን በሚገባ በመጠበቅ አለምአቀፍ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ማተኮር እና የአባል ሀገራትን እኩልነት እና ሉአላዊነት ማክበርና ማስከበር ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም ሀገራት አለምአቀፍ ግዴታቸውን ለመወጣት የሚያደርጉትን ጥረት የመደገፍ እና ሰብአዊ ድጋፍ የማድረግ አለምአቀፍ ግዴታውን በተቻለ መጠን ለመወጣት ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡
Forwarded from ሕግ ቤት
ሰላም እንዴት ናችሁ
~~~~
የዘንድሮውን የአብክመ ፍትህ ማሰልጠኛ መግቢያ ፈተና በተመለከተ በግል በርካታ አካላት ስትጠይቁኝ ስለነበር መረጃውን እነሆ!
.
.
በአብክመ የፍትህ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ተቋም ባለፈው ለምዝገባ ጥሪ አቅርቦ በተለያዩ የዞኑ ፍትህ መምሪያዎች ምዝገባ መከናወኑ ይታወሳል።ፈተናውም ህዳር 8 እንደሚሰጥ ተገልፆ ነበር።ነገር ግን በወቅታዊ ጉዳይ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።መረጃውን በኔትወርክ ም/ት ተደራሽ ማድረግ ባይቻልም በተቋሙ የፌስቡክ ገፅ እንደሚለቀቅና አድስ ነገር ሲኖር ተቋሙ በተለመደው አሰራር ግልፅ ማስታወቂያ የሚያሳውቅ ይሆናል።
.
.
መልካም ጊዜ ለሁላችን!!!!
የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
INSA

1. የይለፍ-ቃልዎን ደህንነት ማረጋገጥ

#_የፌስቡክ አካውንቶን ለሌላ ማንኛውም የኦንላይን አገልግሎት ላይ አይጠቀሙ፤

#_ የይለፍ-ቃልዎን በፍፁም ለሌላ ሰው አያጋሩ፤

#_የሚጠቀሙበት የይለፍ-ቃል ለመገመት አዳጋች የሆነ፣ በፍጹም የእርሶን ስም እና የተለመዱ ቃላትን ያልያዘ ሊሆን ይገባል፤

#_የይለፍ-ቃልዎ ፣ኢ-ሜይልዎን፣ የስልክ ቁጥሮን ወይም የልደት ቀንዎን በፍፁም የሚጠቀም መሆን የለበትም፤

2. የሚያስሱትን ድረ-ገጽ መረጃ በፍጹም አያጋሩ

#_አጥቂዎች ፌስቡክ የሚመስል የሐሰት ገጽ ፈጥረው በኢ-ሜይል አድራሻዎና በይለፍ ቃልዎ እንዲገቡ ሊጠይቁዎ ይችላሉ፤

#_ሁልጊዜም መረጃ የሚያስሱበትን ድረ-ገጽ URL ትክክለኝነት ያረጋግጡ፤
አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ www.facebook.com በማፈላለጊያው ላይ በመጻፍ ወደ ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ለመመለስ ይሞክሩ፤

#_ ከሜታ /Meta/ ወይም ፌስቡክ የሚላክሎትን ኢ-ሜይል በፍጹም ለሌላ ሰው አያጋሩ፣ በተለይም ስለ አካውንቶ ምስጢራዊ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ፤

#_ስለፊሺንግ ጥቃት እና ጠንካራ የይለፍ-ቃል አጠባበቅ ላይ ያለዎትን እውቀትና ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

3. ኮምፒውተርዎን ለሌላ ሰው የሚያጋሩ ከሆነ የፌስቡክ አካውንቶን ዘግተው መውጣትዎን /Log Out/ ማድረግዎን አይዘንጉ፤

#_ኮምፒውተርዎን ዘግተው ሳይወጡ ወይም መሣሪያዎን ያዋሱ ከሆነም ከርቀት እንዴት መውጣት /Log Out Remotely/ እንደሚችሉ ይወቁ፤

#_ከርቀት ሆነው ለሌላ አካል ካዋሱት ኮምፒውተር ላይ ለመውጣት(log out) ለማድረግ ወደ ፌስቡክ "Security and Login Setting" ሲገቡ ከዚህ በፊት ይገቡባቸው የነበሩ መሣሪያዎችን ዝርዝር የሚያቀርብልዎ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሚፈልጉት መሣሪያ ላይ "Logout" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን መውጣት ይችላሉ፤

4. ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄ ሲላክልዎ አይቀበሉ

#_ጠላፊዎች ሰዎችን ለማጥመድ ሲፈልጉ ሀሰተኛ አካውንት ሊፈጥሩ ይችላሉ፤

#_የጠላፊዎች ጓደኛ መሆን ምን አልባት የእርሶን የፌስቡክ የፊት ገጽን /Timeline/ ሊበክሉ፣ የተለያዩ ጉዳዮችን በገጾ ላይ ሊያጋሩ ወይም በካይ መልዕክቶችን በመልዕክት መቀበያዎ ሊልኩብዎ ይችላሉ፤

5. ከበካይ ሶፍትዌሮች እራሶን ይጠብቁ

#_አጥፊ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተሮች፣ ሰርቨሮች /Server/ ወይም የኮምፒውተር ኔትወርክ ላይ ጉዳት ሊጥሉ ይችላሉ፤

#_የተበከለ ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ምን ዓይነት ባህሪያት እንደሚያሳዩ እና እነዚህን በካይ ሶፍትዌሮችን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ በሚመለከት ያለዎትን እውቀት ያዳብሩ፤

#_ማፈላለጊያዎትን በየጊዜው ያዘምኑ፣ አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን እና የማፈላለጊያ ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ፤

6. አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን /Links/ ከሚያውቁት ጓደኛ ወይም ድርጅት እንኳ ቢላክልዎ ከመክፈት ይቆጠቡ

#_እነዚህ በፌስቡክ ወይም በኢ-ሜይል የሚላኩ ማስፈንጠሪያዎች /Links/ ሊሆኑ ይችላሉ፤

#_ፌስቡክ ወይም Meta የይለፍ-ቃሎን በኢ-ሜይል እንዲያስገቡ በፍጹም እንደማይጠይቅዎ ይወቁ፤

#_አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያ ሲያጋጥሞ ለፌስቡክ ሪፖርት /report it/ ያድረጉ፤

7. ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ መንገዶችን ይተግብሩ

#_ከማይታወቁ አድራሻዎችና መሣሪያዎች ወደ አካውንትዎ የመግባት ሙከራ ሲደረግ የጥቆማ መረጃ እንዲደርሶ /get alerts about unrecognized logins/ ያድረጉ፤

#_ባለሁለት ደረጃ የማንነት ማረጋገጫ ዘዴ /Set up two-factor authentication/ ይጠቀሙ፤

#_ሌሎች የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የፌስቡክ Help & Support ላይ በመግባት ያለዎትን ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

https://t.me/GudayAsfetsami
#Share
Muktarovich O.
ውል ማለት ምን ማለት ነው ? የዉል አመሠራረት ሲባልስ በአገራችን የህግ ማዕቀፍ እንዴት ይታያል?
***
ሰላም ንዴትናችሁ ው የፌስቡክችን ተከታታዮ ለዛሬ ውል ሲባል ምን ማት ነው? የዉ አመሠራረት ባልስ በአገራን የህግ ማዕቀፍ እንዴት ይታያል በሚል አንድ የጹሁፍ ጥንቅር ወደ እናንተ ልናደርስ ወደድን መልካም ንባብ ተመኘን፡፡

የሰዉ ልጆች በዚች ምድር ላይ ሲኖሩ የተለያዩ ህጋዊ ውጤት ያላቸዉን ድርጊቶች ያከናዉናሉ፡፡ ለአብነትም ቤት ይከራያሉ ያከራያሉ፣ ጋብቻ ይፈፅማሉ፣ ንብረት ይሸጣሉ ይገዛሉ፣ ወዘተ፡፡ ህጋዊ ዉጤትም ከሚያስከትሉ ተግባራት አንዱ ውል ነዉ፡፡ ውል ሰዎች በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሕይወታቸዉ ዉስጥ ከሚያከናውኗቸው የግንኙነት መገለጫዎች አንዱ ሲሆን ከፍትሐብሔር ግዴታ አንዱ ዘርፍ ነው፡፡

ሰዎች በእለት ተእለት የኑሮ እንቅስቃሴያቸዉ ዉስጥ የተለያዩ ውሎችን ይፈፅማሉ፡፡ ወደ ሱቅ ሂደዉ ሸቀጥ ሲገዙ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመንቀሳቀስ ታክሲ ሲጠቀሙ፣ ለንግድም ሆነ ለመኖሪያ ቤት ሲከራዩ፣ ወዘተ፡፡ እኒህ የውል ግዴታ ዉስጥ የሚገቡት የማህበረሰቡ አካል የሆኑ ሰዎች ናቸዉ፡፡ በሌላ አባባል ውል የሚኖረዉ የውል ግዴታ ውስጥ የሚገቡ (የሚዋዋሉ) ሰዎች ሲኖሩ ነዉ፡፡ ሰዎች ስንል በፍትሐብሔር ህጉ መሰረት የተፈጥሮ ሰዎች ወይም ህጋዊ ሰዉነት የተሰጣቸው ድርጅቶች ናቸዉ፡፡ ውድ አንባቢያን ለመግቢያ ያክል ይህን ካልን አሁን ደግሞ የውልን ትርጓሜ እናያለን

ውል ማለት ምን ማለት ነው
ውል ምን ማለት ነዉ? የሚለዉን ስንመለከት የዘርፉ ሙሁራን እና የፍትሐብሔር ህጋችን የተቀራረበ ትርጉም ሰጥተውት እናገኛለኝ፡፡ በእዉቁ የህግ መዝገበ ቃላት ብላክስ ሎዉ ላይ “ዉል ማለት በሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በመካከላቸዉ አንድን ድርጊት ለማድረግ ወይንም ላለማድርግ በመስማማት ግዴታ የሚፈጥሩበት መንገድ ነዉ” ሲል ትርጉም ይሰጠዋል፡፡ ፕሮፌስር ጥላሁን ተሾመ የኢትዮጳያ የዉል ህግ መሰረተ ሀሳቦች በሚለዉ መፅሃፋቸዉ ዉስጥ “ዉል አንድን ግዴታ ወይም ከዚሁ ግዴታ የተያያዙ ሌሎች በርከት ያሉ ግዴታዎችን የሚያቋቁም ተግባርን የሚያመለክት አነጋገር ነዉ፡፡ በዚህ ግዴታ ባለገንዘብ የሆነዉ ወገን አንድ ነገር እንዲፈጸምለት የመጠየቅ መብት የሚኖረዉ ሲሆን ባለዕዳዉ ደግሞ አንድን ነገር የመፈጸም ግዴታ ይጠበቅበታል” በማለት አብራርተዉ ገልፀዉታል፡፡ እንዲሁም በፍትሐብሔር ህጋችን መፅሃፍ አምስት ስለ ግዴታዎች በሚደነግገዉ ክፍል አንቀፅ 1675 ላይ “ዉል ማለት ንብረታቸዉን የሚመለከቱ ግዴታዎችን ለማቋቋም ወይም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ባላቸዉ ተወዳዳሪ ግንኙነት በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መሀል የሚደረግ ስምምነት ነዉ” በማለት ትርጉም ሰጥቶታል፡፡

የዉል አመሠራረት
ከላይ እንደተገለፀዉ ዉል ስምምነት ነዉ፡፡ ነገር ግን ዉል ስምምነት ቢሆንም ከሌሎች ስምምነቶች የሚለየዉ ለአፈፀሙ ከበስተጀርባዉ የሕግ ድጋፍ ያለዉ ስምምነት መሆኑ ላይ ነዉ፡፡ ይህም ማለት ተዋዋይ ወገኖች የተስማሙበትን ነገር እንደ ስምምነታቸዉ ባይፈፅሙ ያልፈፀሙትን ነገር በህግ ተገደዉ እንዲፈፅሙ ይደረጋሉ፡፡ ይህም የሚያሳየን ዉል በተስማሚዎቹ አካላት መካከል እንደ ህግ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን ነዉ፡፡

ዉል በተወያይ ወገኖች መካከል ህጋዊ ዉጤት እንዲኖረዉ አስቀድሞ የዉል አመሰራረቱ ህጋዊ መስፈርቱን ማሟላት አለበት፡፡ በፍትሐብሔር ህጋችን ስለ ዉል አመሰራረት በሚደነግገዉ ክፍል አንቀፅ 1678 ላይ በግልፅ እንደተቀመጠዉ የሚፀና ዉል ነዉ ለማለት መሟላት ያለባቸዉን ሁኔታዎች አስቀምጧል፡፡ እነሱም፡
1ኛ. ዉል የሚፈፀመዉ ለመዋዋል ችሎታ ባላቸዉ ሰዎች መካከል መሆኑን፡፡ ይህም ማለት በህግ ፊት የሚፀና ዉል ለማድረግ ተዋዋዮች በህግ ችሎታ ያላቸዉ መሆን አለባቸዉ፡፡ በፍትሐብሔር ህጋችን ላይ ስለ ችሎታ በሚደነግገዉ ክፍል አንቀፅ 192 ላይ በመርህ ደረጃ ማንኛዉም ሰዉ በህግ ችሎታ እንደሌለዉ ካልተገለፀ በቀር ማንኛዉንም ህጋዊ ድረጊት ለማድረግ ችሎታ እንዳለዉ እንደሚቆጠር ተደንግጓል፡፡ በዚሁ ህግ አንቀፅ 193 ላይ እንደተደነገገዉ እድሜዉ ለአቅመ አዳም/ሄዋን ያልደረሰ/ሰች ወይም አይምሮዉ ህመም ያለበት ሰዉ ወይም በፍርድ ቤት የተከለከለ ሰዉ ችሎታ እንደሌለዉ ይቆጠራል፡፡ ከላይ እንደተገለፀዉ ዉል ህጋዊ ተግባር ነዉ ስለሆነም እድሜዉ ለአቅመ አዳም/ሄዋን ያልደረሰ/ሰች ወይም አይምሮዉ ህመም ያለበት ወይም በፍርድ ቤት የተከለከለ ሰዉ ዉል መዋዋል አይችልም፡፡

2ኛ. ዉል የሚፈፀመዉ በተወያያቹ ነፃ ፍቃድ ብቻ መሆኑ፡፡ ይህም ማለት ተወያይ ወገኖች ዉል ዉስጥ የሚገቡት ያለማንም ጫና አድራጊነት በራሳቸዉ ፍቃድ መሆን አለበት ማለት ነዉ፡፡ አንድ የዉል ግዴታ የተቋቋመ መሆኑ የሚረጋገጠዉ የተዋዋዮቹ ፈቃድ በህግ አግባብ መገለፁ ሲታወቅ ነዉ፡፡ ተዋዋዮቹ በመሀከላቸዉ በህግ ፊት የሚፀና ግዴታ ለማቋቋምና ይህም ግዴታ በሚያስከትለዉ ዉጤት ለመገዛት ስምምነት ያላቸዉ መሆኑ ይፋ ሲያደርጉ ፈቃዳቸዉን ገለፁ እንላለን፡፡ በፍትሐብሔር ህጉ አንቀፅ 1679 ላይ ይህን አባባላችን በሚያጠናክር መልኩ “ዉል ተዋዋዮች በገቡባቸዉ ግዴታዎችና እነዚህም አስገዳጅ እንዲሆኑ የተስሚ መብትን በሚገልፀዉ የፈቃድ መስጠት ላይ የተመሰረተ ነዉ” በማለት ተደንግጓል፡፡

3ኛ. ተወያይ ወገኖች የሚዋዋሉበት (ዉል ዉስጥ የሚገቡበት) ጉዳይ በእርግጠኝነት የሚቻል እና ህጋዊና ሞራላዊ ጉዳይ ላይ መሆኑ፡፡ የዉሉ ፍሬ ነገር በሰዉ ልጅ አቅም መፈጸም የሚችል እና ህጋዊና ሞራላዊ የሆነ መሆን አለበት፡፡ በሰዉ ልጅ አቅም መፈፀም የሚቻል ተግባር ማለት የሰዉ ልጅ በተፈጥሮዉ ማከናዉን የሚችለዉ ማለት ነዉ፡፡ ለአብነት የዉሉ ፍሬ ነገር እንደ እርግብ መብረር ቢሆን በሰዉ ልጅ ተፈጥሮ የማይቻል ተግባር ነዉ፡፡ ሌለዉ የዉሉ ፍሬ ነገር በህግ ያልተከለከለ ወይም ህገ-ወጥ እና በህብረተሰቡ ባህልና ወግ ተቀባይነት ያለዉ ነገር ላይ (በሌላ አባባል ከህብረተሰቡ ሞራል ጋር ያልተቃረነ ያልሆነ) መሆን አለበት፡፡ ለአብነት ፍሬ ነገሩ ሰዉ ለመግደል ቢሆን በህግ የተከለከለ ነዉ፡፡

4ኛ. የዉል አቀራረጹ ወይም አፃፃፉ በህግ (ፎርም) ተለይተዉ የተቀመጡ ወይም ተዋዋይ ወገኖች ተለይቶ እንዲቀመጡ ከተስማሙበት የዉል ጉዳይ በቀር የተለየ የዉል ፎርም የማያስፈልግ መሆኑ፡፡ በፍትሐብሔር ህጋችን አንቀፅ 1678(3) ላይ እንደተደነገገዉ በግልፅ በህግ ይህን የዉል ፎርም ተከተሉ ተብሎ ካልተደነገገ በቀር ተዋዋይ ወገኖች ዉላቸዉን በፈለጉት አይነት ማድረግ ይችላሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዚሁ ህግ አንቀፅ 1719(1) ላይ ተዋዋይ ወገኖች የመዋዋል ነፃነት እንዳላቸዉ ሁሉ የሚዋዋሉበትን ዉል አቀራረፅ የመወሰን ነፃነትም እንዳለቸዉ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በተለየ ሁኔታ በህግ ዉሉ በዚህ መልክ ይቀመጥ ካልተባለ በስተቀር ተዋዋዮቹ ወገኖች ዉላቸዉን በፈለጉት ፎርም ማድረግ ይችላሉ፡፡

ውድ አንባቢያን ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁን በዚሁ አበቃን በቀጣይ የቤት ኪራይ ውል ሲባል ምን ማለት ነው በአገራችን የህግ ማዕቀፍ እንዴት ይታያል በሚል አርዕስት አንድ ጥንቅር ከትበን ወደ እናንተ እናደርሳለን እስክንገናኝ መልካም ጊዜ ተመኝን ሰላም፡፡
https://t.me/lawsocieties
Secretariat of Addis Ababa City Council ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
👩 position:-
1: Documentation Officer
2: legal drafting specialty
3: IT Support Officer III
4: Website Administrator I
https://bit.ly/38713uP
📚ትምህርትዓይነትእናደረጃ:-accounting,communication-engineering,computer-engineering,computer-science,economics,electrical-engineering,information-science,information-system,information-technology,law,management,management-information-system-mis,software-engineering .
🇪🇹 የስራ ቦታ:-አዲስ አበባ
🧭የምዝገባ ጊዜ /Deadline/: እስከ መጋቢት 28 /2014 ዓ.ም
🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
jobs.amazonethiopia.com
🔰ወደፊት የምናወጣቸው የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎች በፍጥነት እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገጻችን እና የፌስቡክ ገጻችን ይወዳጁ!
ሰሞኑን "ፊያስ" በተባለ አድራሻው በማይታወቅ የኦላይን ማጭበርበሪያ ዘዴ ብዙዎች በየዋህነት ገንዘባቸውን ተበልተዋል። ይህ ትምህርት ሊሆነን ይገባል። አሁንም በኦላይን እያጭበረበሩ የሚገኙ ስላሉ ጥንቃቄ አድርጉ።

የአማራ ባንክ ተመርቆ እንደተከፈተ ያልተከፈተ የቴሌግራም ቻናል የለም። እነዚህ በአማራ ባንክ ስም የተከፈቱ የቴሌግራም ቻናሎች የመኖሪያ ቤት ሽልማት ይሰጣል ከዛ በፊት ግን ለ50 ወይንም ለ60 ሰው ሼር አድርጉ ይላሉ። ይህን መረጃ አምኖ ሼር የማያደርግ የለም።ለእነሱ የራሳቸውን የቴሌግራም ተከታይ ለማሳደግ የፕሮሞሽን ሥራ እየሰሩነው። አለፍ ሲልም ለሌላ ወንጀል ይጠቀሙበታል።

ለጎደኞቻችሁ ሼር የምታደርጉ ሰዎች ፍፁም ውሸት መሆኑን ልታውቁት ይገባል።
ፊደል የቆጠረ ሰው እንዲህ በአለ ነገር በቀላሉ መሸወድ የለበትም። ትክክለኛውን ገፅ ለማግኘት ይሄን ያህል የሚከብድ አይደለም። ወይንም በውስጥ መስመር መረጃውን ብትልኩ አጣርተን ትክክል መሆኑንና አለመሆኑን ማወቅ እንችላለን።
ከውጭ አገር አሜሪካ ሳይቀር ለእኔም አሰልቺ ማስታወቂያዎች በግል ደርሰውኛል።

ለማንኛውም አማራ ባንክ ምንም አይነት የቤት ሆነ የመኪና ሽልማት ማስታወቂያ አላወጣም እውነት ቢሆን እንኳን እንደሌሎቹ ባንኮች በቴሌቪዥን የምታዩት ነው የሚሆነው።

ትክክለኛው የአማራ ባንክ ቴሌግራም ይሄኛው ነው!!!

Telegram: https://t.me/Amhara_Banksc

የአማራ ባንክ የፌስቡክ ገፅ ይሄ ነው።
Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1

ትክክለኛ የዐማራ ባንክ የቲዊተር አድራሻ ይሄ ነው። https://twitter.com/Amharabanksc
እስካሁን በአጭበርባሪዎች ተሸውዳችሁ ለ60 ሰው ያሰራጫችሁ ሰዎች ይሄን ትክክለኛው መረጃ ለ100 ሰው ብታሳውቁ አትጎዱም። ለወደፊቱ ጥንቃቄ አድርጉ!!!

በሌሎችም የሪል እስቴት ስሞች፣ ድርጅቶች እና ታዋቂ ባለሀብቶች ስም የተከፈቱ የተለያየ አጓጊ ሽልማት አለው ሼር አድርጉ የሚሉ ብዙ የሀሰት የቴሌግራም ቻናሎች አሉ።

ጥንቃቄ ይጠብቅሃል ማስተዋል ይጋርድሀል።

እኛ ተሸውደን እና ተታለን ሰዎችን እዲታለሉና እንዲሸወዱ መንገድ አንክፈት።

#share ሼር በማድረግ እውነትን አጋልጡ

Via #አለ_ህግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
የፌድራል_ጠቅላይ_ዐቃቢ_ህግ_ማቋቋማያ_አዋጅ.pdf
550.9 KB
... የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ…
Proclamation No. 943/2016Federal Attorney General Establishment Proclamation
በማህበራዊ ሚዲያ ጥላቻና ሐሰት መልዕክት ስያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ

ወላይታ ሶዶ፤ ጥር፣15/2015 ዓ.ም በወላይታ ዞን በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ በማህበራዊ ሚዲያ ጥላቻና ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ህብረተሰቡን ስያወክ የነበረ ግለሰብ ሰባት ወርና 3 ሺህ እንድቀጣ ተወስኗል።

ተከሳሽ አቶ ዳሳለኝ ደግፌ የተባለ ግለሰብ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከለከልና ለመቆጣጠር የወጠውን አዋጅ .1185/2012 በመተላለፍ የተለያዩ ስያሜ ያላቸውን ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንት በመጠቀም ከአንድ ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ በተለያዩ ቀናትና ጊዜያት በህዝብና መንግሥት መካከል እምነት እንዳይኖርና ሁከትና ግጭት እንዲነሳ በማሰብ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ተከሳሹ ግለሰብ በአከባቢው የሚገኙ ግለሰቦች ስብዕና የሚነኩ፣ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎችና የመንግስት ተቋማትን ሰብዓዊ ክብራቸውን የሚነኩና ስማቸውን የሚያጠፉ በሀሰተኛ አካውንቶች ሐሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨቱም ተመላክቷል።

በቀን 29/01/2015 ዓ.ም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በተደረገው ብርበራ ዉጤት መሰረት ህዝብና መንግስትን የሚያጋጩ ጽሑፎችና መረጃዎች ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዟል።

ሀሰተኛ መረጃዎ በማሰራጨት ወንጀል ተከሶ ፍ/ቤት የቀረበ ሲሆን ግራ ቀኙ ስያክራክራ የቆየው የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍ/ቤት በቀን 15/5/2015 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹን ሆነ ሌላዉን ማህብረሰብ ያስተምራል ያለዉን በተከሰሱበት ድንጋጌ ጥፋተኛ በማለት በ3000 ብር መቀጮ ወይም የሰባት ወር እሥራት እንድቀጣ ወስኗል።
ወላይታ ሶዶ
https://t.me/lawsocieties
#news

የኢትዮዽያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ተ/ፕሬዚደንት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው የአፍሪካ ጠበቆች ማህበር (PALU) ም/ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ!!!
***********************

እ.ኤ.አ ከጁላይ 5 ቀን 2023 ጀምሮ በዛምቢያ ሀገር ሊቪንግስተን ከተማ እየተካሄደ ባለው 13ኛው የአፍሪካ ጠበቆች ማህበራት ህብረት ጉባኤ ከመላው አፍሪካ ፤ ከመካከለኛው ምስራቅ ፤ ከአውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ ክፍለ አህጉሮች የተውጣጡ ከ 250 በላይ የጠበቆች ማህበር ፕሬዝደንቶችና የአመራር አባላት ፤ አካባቢያዊ የባር አሶሲዬሽን መዋቅሮች ፤ አለም አቀፍ የጥብቅና ድርጅቶች ፤ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች ተወካዮች እና የሚመለከታቸው የመንግስት ሀላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ::

በዚሁ ጉባኤ ላይ ለህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች ለተደረገው ምርጫ የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበርን እየመሩ ያሉት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ከተወዳዳሪዎቹ ይልቅ ከአባል ሀገራቱ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት የአፍሪካ ጠበቆች ማህበር (PALU) ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው ተመርጠዋል::

አቶ ቴዎድሮስን በእጩነት እንዲወዳደሩ የጠቆመው 7 ሀገራትን በአባልነት ያቀፈውና ከ28,000 በላይ አባላት ያሉት የ East African Law Society ነው:: ቴዎድሮስ ከምስራቅ አፍሪካ ፤ ከደቡብ አፍሪካ እና ከማእከላዊ አፍሪካ ዞናት ሙሉ ድጋፍ ያገኙ ሲሆን ከምእራብና ሰሜን አፍሪካ ተወካዮች ደግሞ አብላጫውን ድጋፍ በማግኘት ሊመረጡ ችለዋል::

የአፍሪካ ጠበቆች ማህበራት ህብረትን በም/ፕሬዝደንትነት ለመምራት ኢትዮጵያዊ ሲመረጥ የመጀመሪያው ሲሆን ህብረቱ በአዲስ አበባ በተመሰረተበት ግዜ ከ21 አመታት በፊት አንጋፋው የህግ ባለሙያ አቶ ጌታቸው ቅጣው የህብረቱ ዋና ፀሀፊ ሆነው አገልግለዋል:: ላለፉት 18 አመታት በህብረቱ ከፍተኛ አመራር ላይ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ምንም አይነት ቦታ ማግኘት ሳይችሉ ቆይተዋል:: በአሁኑ ወቅት የህብረቱ ፕሬዚደንት ፈረንሳይኛ ተናጋሪው ካሜሮናዊው የህግ ባለሙያና ጠበቃ ሚ/ር ካሪ አብዶል ባጉይ ሲሆኑ የሴክሬታሪያቱ መቀመጫ በታንዛኒያ አሩሻ እንደሚገኝ ይታወቃል::

የኢትዮዽያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር

ሀምሌ 02 ቀን 2015ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤

#መረጃዎች በቶሎ እንዲደርሷችሁ ይፋዊ የፌስቡክ ገፃችንን በሚከተለው ሊንክ ይቀላቀሉ::

https://www.facebook.com/ethiopianbarassociation?mibextid=LQQJ4d
ለፌደራል ጥብቅና ሙያ ተፈታኞች የፈተና ውጤት

***********************

በፌደራል በማናቸውም ደረጃ ፍ/ቤቶች የተፈታኝ ጠበቆች ውጤት በአዋጅ ቁ.1249/2013 አንቀፅ 77 መሰረት በተቋቋመው የጥብቅና ሙያ የመግቢያ ፈተና ኮሚቴ Exam Committee ይፋ ተደርጓል:: የማለፊያ ነጥቡ 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ መሆኑን እንገልፃለን::

የማለፊያ ነጥቡን ያስመዘገቡ ተፈታኞች በአዋጁ አንቀፅ 79 መሰረት ለተቋቋመው የጥብቅና ፈቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ Licensing Committee ሰነዶቻቸውን በማቅረብ የሚመረመር እና የጥብቅና ሙያን ለመቀላቀል መስፈርቱን ላሟሉት ባለሙያዎች የፌደራል የጥብቅና ፈቃድ የሚሰጣቸው ይሆናል::

የጠበቆች ማህበር የማለፊያ ውጤቱን ላገኙ ተፈታኞች እንኳን ደስ አላችሁ! እያለ መስፈርቱን አሟልታችሁ ፈቃድ የምትወስዱ ባለሙያዎች ለሀገራችን የህግ ስርአት መዳበር ከፍ ባለ ስነምግባር ሀላፊነታችሁን እንደትወጡ በማሳሰብም ጭምር ነው::

መረጃውን #share በማድረግ ላልደረሳቸው እንድታሳውቁ እንጠይቃለን::

መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ የፌስቡክ ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ::

https://www.facebook.com/ethiopianbarassociation?mibextid=LQQJ4d

የኢትዮዽያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር

ነሀሴ 15 ቀን 2015ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤
የፌደራል ጠቅላይ ዕቃቤ ሕግ

የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ (preliminary objection) ሲባል ምን ማለት ነው?

__
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ
የፌስቡክ ገጻችን ተከታታዮች ብዙውን ጊዜ በዜና አውታሮች ፍርድ ቤቱ በነ እገሌ የክስ ሂደት ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ለመስማት ቀጠሮ ሰጠ ሲባል እንሰማለን ለመሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ሲባል ምን ማለት ነው? ለዛሬ በዚሁ አርዕሰት ላይ እናንተን ያስተምራል ያልነውን ጥንቅር ወደናንተ ልናደርስ ወደድን ተከታተሉን፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ተከሳሹ ስለ ክሱ ማመልከቻ ፎርም ወይም በክስ ማመልከቻ የተገለፀውን ነገር የሚቃወምበት ስርዓት ነው፡፡የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አላማ ፍርድ ቤት እና ተከራካሪ ወገኖች ወደ ክርክሩ ፍሬ ነገር ሳይገቡ መነሳት ያለባቸውን ነጥቦች በማንሳት ውሳኔ በመስጠት ጊዜ መቆጠብ ነው፡፡ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊነሳባቸው የሚችሉ ነጥቦች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የክሱን ይዘት በተመለከተ ሊቀርብ ይችላል፡፡ይህም ማንኛውም የክስ ማመልከቻ ቀንና ዓመተ ምህረት የተፃፈበት እና የተፈረመበት እንዲሁም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እንዲገልፅ ያስፈልጋል፡፡እነዚህም ተከሳሽ የተከሰሰበት ወንጀል እንዲሁም የወንጀሉ መሰረታዊ ነገር እና ሁኔታዎች፤ወንጀሉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ስፍራ ተገቢ በሆነ ጊዜም በደል የደረሰበት ሰው ስም ወይም ወንጀሉ የተፈፀመበት ንብረት፣ተከሳሽ ድርጊቱን በመፈፀም የተላለፈው የህግ አንቀጽ መያዝ አለበት፡፡ክሱ ግልፅ እና የተከሳሽን የመከላከል መብት የማያጣብብ መሆን አለበት፡፡
በመሆኑም እነዚህ ነገሮች ግልፅ ባልሆኑ እና ባልተሟሉ ጊዜ ተከሳሽ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማንሳት ይችላል፡፡ በተጨማሪ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 130/2 ስር የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሚያስነሱ ነገሮች ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡
• ተከሳሽ በዚሁ ነገር ክስ በሌላ ፍርድ ቤት ተጀምሮ በቀጠሮ ያለ መሆኑ
• በዚሁ ክስ ከዚህ በፊት ተከሶ ነፃ የወጣ ወይም የጥፋተኝነት ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑ
• ክስ የቀረበበት ወንጀል በይርጋ ህግ የታገደ ወይም ምህረት ወይም ይቅርታ የተደረገለት መሆኑ ከተረጋገጠ፡፡ ይርጋ ማለት አንድ የወንጀል ድርጊት ተፈፅሞ ክስ ለማቅረብ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ማለት ነው፡፡በወንጀል ህግ አንቀጽ 219 ስር እንደተደነገገው የይርጋ ዘመን የሚታሰበው የቅጣት ማከበጃ ወይም ማቅለያ ሁኔታዎች ግምት ውሰጥ ሳይገቡ በወንጀል ህጉ ልዩ ክፍል የተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት መሰረት በማድረግ ነው፡፡የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው ጥፋተኛው የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመበት አንስቶ ነው፡፡ለምሳሌ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ወንጀሉ በተፈፀመ በአስር አመት ውስጥ ክስ መቅረብ አለበት፡፡አስር አመት ካለፈ ግን ክስ ማቅረብ አይቻልም ማለት ነው፡፡
• ከሌሎች ወንጀለኞች ጋር በተከሰሰ ጊዜ እና ለብቻው ተነጥሎ ክሱ ባይታይለት የሚጎደው መሆኑን፣
• ክሱን ለማቅረብ በህጉ መሰረት ፈቃድ ያልተሰጠ መሆኑ ለምሳሌ ተከሳሽ በአለም አቀፍ ህግ ዲፕሎማቲክ ኢሙኒቲ የማይከሰስ እንደሆነ፣
• በሌላው ችሎት የቀረበው ክስ ሳይፈፀም በዚህ የወንጀል ክስ ሊሰጥ የማይገባ መሆኑ
• ለፈፀማቸው ተግባሮች ኀላፊ አለመሆን ፤ለምሳሌ የተከሳሽ አድሜ ከዘጠኝ አመት በታች ከሆነ፣ በወንጀል ህግ አንቀጽ 48 ላይ እንደተመለከተው ማንም ሰው በእድሜ ፣ በህመም ፣ባልታሰበ የእድገት መዘግየት ወይም ጥልቅ በሆነ የአዕምሮ የመገንዘብ ችሎታ መቃወስ ወይም የወንጀል ድርጊት በሚፈፅምበት ጊዜ የድርጊቱን አይነት ወይም ውጤት ለመገንዘብ ወይም በዚህ ግንዛቤ መሰረት ራሱን ለመቆጣጠር በፍፁም ያልቻለ ሲሆን ኢ-ኃላፊ ስለሚሆን አይቀጣም፡፡
ከላይ የተዘረሩት ነጥቦች ባጋጠሙ ጊዜ ተከሳሽ እራሱ ወይም ጠበቃ ካለው በጠበቃው አማካኝነት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ሊያነሳ ይችላል፡፡
ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ሲጠይቀው ተከሳሹ የክሱን ማመልከቻ ወዲያውኑ ካልተቃወመ በቀር ቆይቶ እንዲህ ያለውን መቃወሚያ ነገሩ በሚሰማበት በሌላ ጊዜ ሊነሳ የሚችለው ፍርድ ቤቱን የሚፀና ፍርድ ለመስጠት የሚያግደው ከሆነ ብቻ ነው (ወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.130/3)፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ተከሳሽ አንድ ጊዜ ተከሶ በተቀጣበት ወንጀል ድጋሚ ሊከሰስ እንደማይገባ ይህም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባይነሳም በማንኛውም ጊዜ ሊነሳ እንደሚችል የሚያሳየንን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 72304 የሰጠውን ውሳኔ እንደ አብነት ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
ጉዳዩ ባጭሩ ተከሳሽ በስር ፍርድ ቤት በቀላል አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሶ ከተቀጣ በኃላ ተበዳይ በመሞታቸው ዐቃቤ ህግ ድጋሚ በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ክስ ሲያቀርብ ተከሳሽ እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሳያነሳ ቀርቶ በኃላ በተመሳሳይ ወንጀል ድጋሜ ያለመከሰስ መብት principle of double jeopardy ይነካል ማለቱ ተገቢ አይደለም ብሎ የተከራከረበት ጉደይ ነው፡፡
ሰበር በውሳኔ ዝርዘሩ ላይ እንዳስቀመጠው “ አንድ ሰው በወንጀል ህግ እና ስነ ስርዓት ተከሶ የመጨረሻ ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ጥፋተኛ ሆኖ ተቀጥቷል ወይም ነፃ ተለቋል የሚለው መከራከሪያ በመጀመሪያ የወንጀል ክስ የክስ መቃወሚያ ሆኖ መቅረብ ያለበት መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 130 የተደነገገ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የቀረበው የክስ መቃወሚያና ማስረጃ በመመርመር ውሳኔ መስጠት ያለበት መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 131 ተደንግጓል፡፡ሆኖም አንድ ተከሳሽ በወንጀል ተከሶ በመጨረሻ ፍርድ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በተቀጣበት የወንጀል ድርጊት በድጋሜ ያለመከሰስ ያለመጠየቅ መብት መሰረታዊ እና ህገ መንግስታዊ መብት በመሆኑ ክርክሩ በሚካሄድበት በማናቸውም ደረጃ ሊነሳ የሚችልና በማስረጃ ተረጋግጦ በተገኘ ጊዜ ፍርድ ቤቶች ተቀብለው ብይን ሊሰጡበት የሚገባ መሆኑ በውሳኔው አስፍሯል፡፡
ከመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ጋር ሊምታታ የማይገባው መቃወሚያ በማለት ተከራካሪ ወገኖች እንደ አስፈላጊነቱ ዐቃቤ ሕግም ይሁን ተከሳሽ በክርክር ወይም ምስክር በሚሰማበት ጊዜ ጣልቃ የሚገቡበት ስነ ሥርዓት ነው፡፡
ለምሳሌ ምስክር በሚሰማበት ጊዜ ለምስክሩ በዋና ጥያቄ ላይ መሪ ጥያቄ ቢቀርብ ወይም ምስክሩ ከተመለከተው ወይም ከሚያውቀው ነገር ባሻገር ግላዊ አስተያየቱን ወይም ግምቱን እንዲሰጥ ቢጠየቅ ወይም ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ ጥያቄ ቢጠየቅ ተከራካሪ ወገኖች መቃወሚያ አለኝ ብለው ፍርድ ቤቱን በማስፈቀድ ምስክሩ መልስ እንዳይመልስ ማድረግ ይችላሉ፡፡
https://t.me/lawsocieties