አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የኢኮኖሚ አሻጥር ምንነት እና ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ህጋዊ አንድምታዎቹ
*
የአንድ ሀገር እሴት መገለጫ መገኛው ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ መስተጋብሮች ናቸው፡፡ አንድ አገር አገር ሆኖ እንዲቀጥል ሶስቱ ዋና ዋና አምዶች ተጣጥመው እና ተመጋግበው መቀጠላቸው የግድ እና አስፈላጊ ነው፡፡ የኢኮኖሚ መዛባት ፖለቲካውን በእጅጉ የሚጫነው ሲሆን ፖለቲካው የተረጋጋ ባልሆነ ጊዜ ሁሉ ኢኮኖሚው ተፈጥሯዊ ዑደቱ ተስተጓጉሎ በማህበራዊ ዘርፉ ትርምስ ይፈጠራል፡፡ ስለሆነም የሀገር ምሰሶ የሆኑትን እነዚህ ሶስት እሴቶች መጠበቅ ማጎልበት እና ማሳደግ ትልቁ የመንግስታት ሚና ነው፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች መነሻ ኢኮኖሚው ሲፈተን መንግስትም ፈተናውን ለማለፍ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ማስተዋሉ የተለመደ ነው፡፡ በተለይም ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በሀገር ውስጥ እና በውጪ ያሉ ሀይሎች አሁን ያወጁትን የቃታ ጦርነት ከማወጃቸው በፊት የኢኮኖሚ ጦርነት በማወጅ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ አሻጥሮችን በመንደፍ እና በመተግበር መንግስትን ሲገዳደሩ የተስተዋለ ሲሆን የዚህ ውጤት ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት፣ መሰረታዊ የሆኑትን ጨምሮ የእቃና አገልግሎት ዋጋ ንረት እና እጥረት፣ የውጪ ምንዛሪ እጥረት፣ የስራአጥ ቁጥር መጨመር፣ የኑሮ ውድነት እና የመሳሰሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን አስከትሏል፡፡ እነዚህ ችግሮች በምላሹ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን በህዝቡ ላይ ቅሬታ እና ጉርምርምታን በመፍጠር መንግስቱ ደካማ ነው በአግባቡ እየመራ አይደለም ለሚሉ የውጪ እና የውስጥ ሃይሎች ፖለቲካዊ ትርፍ አስገኝቷል፡፡ ለመሆኑ ኢኮኖሚ ማለት ምን ማለት ነው፣ የኢኮኖሚ አሻጥርስ ምንድነው እንዴት ይፈፀማል ከህግ አንፃር እንዴት ይታያል የሚለው በዚህ አጭር ፅሁፍ ይዳሰሳል፡፡

ኢኮኖሚ ምንድነው?
ኢኮኖሚ /ምጣኔ ሃብት/ ማለት የአንድ ሃገር የምርት እና ፍጆታን በማመጣጠን ሀብት የሚተዳደርበት ስርአት ሲሆን ይህን ስርዓት የሚያጠናው ዘርፍ ደግሞ ኢኮኖሚክስ ይባላል፡፡ ኢኮኖሚክስ ከማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የሚመደብ የእቃዎችን አመራረት ክፍፍል እና አጠቃቀም የግለሰቦች፣ መንግስት እና ድርጅቶች ምርጫ፣ ሀብታቸውን የሚያወጡበት እና የሚጠቀሙበትን ሁኔታ ወዘተ--- የሚያጠና ዘርፍ ነው፡፡ በተፈጥሮ የሰዎች ፍላጎት ገደብ አልባ ሲሆን ያሉ ሀብቶች ደግሞ ውስን ናቸው ኢኮኖሚክስ እነዚህ ውስን ሃብቶች ፍትሀዊነት ባለው መልኩ እንዴት ሊከፋፈሉ እንደሚችሉ ያጠናል፡፡ ዘርፉ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን microeconomics እና macroeconomics በመባል ይታወቃሉ፡፡ የመጀመሪያው ስለውስን ነገሮች ለአብነት ስለ ግለሰቦች የንግድ ተቋማት የመሳሰሉትን በመለየት ስለምርታቸው ምርጫቸው ለገበያው የሚሰጡትን ምላሽ እና ውሳኔ አሰጣጣቸውን የመሳሰሉትን ያጠናል፡፡ ሁለተኛው የኢኮኖሚ ክፍል ዋና ዋና የኢኮኖሚ መመዘኛ ነጥቦችን መሰረት በማድረግ ጠቅላላ ኢኮኖሚውን ይገመግማል ያጠናል፡፡ የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ የሁለቱ ኢኮኖሚ ክፍሎች ውቅር ነው፡፡

የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ጤነኛ ነው የሚባለው ፍላጎት እና አቅርቦት የተጣጣመ ወይም በእንግሊዘኛው demand = supply ሲሆን ነው፡፡ ፍላጎቱ በዝቶ አቅርቦቱ ካነሰ ወይም አቅርቦቱ እያለ ከዋጋ አንፃር ተደራሽ ካልሆነ እንዲሁም አቅርቦቱ እያለ ፈላጊ ከሌለም ኢኮኖሚው ተፈጥሮአዊ ዑደቱን ጠብቆ በአግባቡ እየሄደ እንዳልሆነ ያሳያል፡፡
ሰዎች ተሰባስበው በአንድ አገዛዝ ስር መኖር ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር ጊዜ ድረስ የመንግስታት አንዱና ዋናው ሃላፊነት የሚያስተዳድሯቸውን ህዝቦች ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማስጠበቅ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ መንግስታት ህግ ከማውጣት አንስቶ እጥረት በሚስተዋልበት አጋጣሚ ሁሉ እቃዎችን በማቅረብ አገልግሎቶችን በመስጠት የህዝቡን ፍላጎት ለመሙላት እና ቅቡልነት ለማግኘት ሲጥሩ ይስተዋላል፡፡ የኢኮኖሚው ጤነኛ መሆን አለመሆን ለህዝቡ አስተዳዳሪ /መንግስታት/ በህብረተሰቡ ተቀባይነት ለማግኘት ወይም ላለማግኘት አይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

ኢኮኖሚ አገር እንደሀገር መንግስት እንደመንግስት እንዲቀጥል ያለው ሚና የጎላ ከመሆኑ አንፃር ስልጣን ላይ ባለ መንግስት ቅሬታ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከውስጥም ከውጪም ያሉ የመንግስቱ ተቃዋሚዎች ኢኮኖሚውን በመረበሽ መንግስትን ተቀባይነት ለማሳጣት እንደ አንድ የፖለቲካ መታገያ ስልት ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡ በሌላም በኩል ገንዘብ መሰብሰብ እና ብልፅግናን አላማ ያደረጉ በየደረጃው ያሉ ነጋዴዎች ያላግባብ ሀብት ለመሰብሰብ እና ይበልጥ ለመበልፀግ በማሰብ ኢኮኖሚው ጤነኛ ሆኖ እንዳይቀጥል የሚያደርጉ ተግባራቶችን የሚከወኑ ሲሆን ይህ በሙያው አጠራር የኢኮኖሚ አሻጥር /economic sabotage/ በመባል ይታወቃል፡፡

የኢኮኖሚ አሻር /Economic sabotage/ ምንድነው፡- ዳንኤል ፕሮቶር የተባሉ ኢኮኖሚስት ሲተረጉሙት Economic sabotage is the practice of undermining the economy of a nation. It is a tactic used to pressure governments. በማለት ይተረጉሙታል ወደ አማርኛው ሲመለስ የኢኮኖሚ አሻጥር የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ እንዳያድግ፣ ውጤታማ እንዳይሆን፣ አቅም እንዲያንሰው እና እንዲረበሽ የማድረግ ተግባር ነው፡፡
ይህ ተግባር መንግስት ላይ ጫና መፍጠሪያ ዘዴ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል እንደማለት ነው፡፡ አጥቂዎች ትኩረት አድርገው የሚነሱት ገበያውን ነው ዋናው ተግባራቸውም በገበያው ላይ የአቅርቦት እጥረት እንዲፈጠር ማድረግ ወይም የህብረተሰቡ የመግዛት አቅም እንዲዳካም ማድረግ ወይም ከሚፈለገው በላይ አቅርቦት እንዲኖር ማድረግ ወይም ፍላጎት እንዳይኖር ወይም እንዲቀንስ ማድረግ ወዘተ----ነው፡፡ ይህ ሁነት ገበያው ላይ እንዲገለፅ ከጀርባ አይነተ ብዙ አሻጥሮች ይሰራሉ፡፡ ገበያ በአግባቡ ካልተመራ የአንድን አገርን ኢኮኖሚ ለመጉዳት እና መንግስትን ለማዳከም አይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡

የኢኮኖሚ አሻጥር በሀገር ውስጥ ያለን መንግስት ከመጫን ባለፈ አንድ አገር የሌላኛውን አገር መንግስት በማጥቃት እጅ ለመጠምዘዝ ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡ የኢኮኖሚ አሻጥር እንደፖለቲካ መታገያ ጥቅም ላይ ከዋለ ብዙ ዘመናትን ያስቆጠረ ሲሆን አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በአለማቀፍ ደረጃ በሁሉም ሀገሮች ተግባራዊ ሆኖ ይገኛል፡፡ በተለይም ኃያላን አገሮች ከነሱ ጥቅም ተቃራኒ ሆኖ በሚቆም መንግስት ላይ የመጀመሪያው የሚወስዱት እርምጃ በኢኮኖሚ አሻጥር መንግስቱን ማዳከም ሲሆን አሻጥር የሚፈፀምበት መንግስት አሻጥሩን መቋቋም ሲያቅተው ታዛዥ መንግስት ሆኖ ይቀጥላል አልያም በህዝባዊ አመፅ እንዲወገድ ይደረጋል፡፡ በቅርቡ በሰሜን አፍሪካ አገራት የታየው እና ብዙውን የአካባቢው አገራት የፖለቲካ ስርዓት የቀየረው አረብ ስፕሪንግ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ከፍተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መነሻ በኃያላኑ አገራት ተደርሶ ስፖንሰር የተደረገ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል የለም ሰፊው ህብረተሰብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ አይደለም የሚል አጀንዳ የተሸከሙ ወጣቶች ያነሱት ተቃውሞ ነው፡፡
የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
INSA

1. የይለፍ-ቃልዎን ደህንነት ማረጋገጥ

#_የፌስቡክ አካውንቶን ለሌላ ማንኛውም የኦንላይን አገልግሎት ላይ አይጠቀሙ፤

#_ የይለፍ-ቃልዎን በፍፁም ለሌላ ሰው አያጋሩ፤

#_የሚጠቀሙበት የይለፍ-ቃል ለመገመት አዳጋች የሆነ፣ በፍጹም የእርሶን ስም እና የተለመዱ ቃላትን ያልያዘ ሊሆን ይገባል፤

#_የይለፍ-ቃልዎ ፣ኢ-ሜይልዎን፣ የስልክ ቁጥሮን ወይም የልደት ቀንዎን በፍፁም የሚጠቀም መሆን የለበትም፤

2. የሚያስሱትን ድረ-ገጽ መረጃ በፍጹም አያጋሩ

#_አጥቂዎች ፌስቡክ የሚመስል የሐሰት ገጽ ፈጥረው በኢ-ሜይል አድራሻዎና በይለፍ ቃልዎ እንዲገቡ ሊጠይቁዎ ይችላሉ፤

#_ሁልጊዜም መረጃ የሚያስሱበትን ድረ-ገጽ URL ትክክለኝነት ያረጋግጡ፤
አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ www.facebook.com በማፈላለጊያው ላይ በመጻፍ ወደ ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ለመመለስ ይሞክሩ፤

#_ ከሜታ /Meta/ ወይም ፌስቡክ የሚላክሎትን ኢ-ሜይል በፍጹም ለሌላ ሰው አያጋሩ፣ በተለይም ስለ አካውንቶ ምስጢራዊ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ፤

#_ስለፊሺንግ ጥቃት እና ጠንካራ የይለፍ-ቃል አጠባበቅ ላይ ያለዎትን እውቀትና ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

3. ኮምፒውተርዎን ለሌላ ሰው የሚያጋሩ ከሆነ የፌስቡክ አካውንቶን ዘግተው መውጣትዎን /Log Out/ ማድረግዎን አይዘንጉ፤

#_ኮምፒውተርዎን ዘግተው ሳይወጡ ወይም መሣሪያዎን ያዋሱ ከሆነም ከርቀት እንዴት መውጣት /Log Out Remotely/ እንደሚችሉ ይወቁ፤

#_ከርቀት ሆነው ለሌላ አካል ካዋሱት ኮምፒውተር ላይ ለመውጣት(log out) ለማድረግ ወደ ፌስቡክ "Security and Login Setting" ሲገቡ ከዚህ በፊት ይገቡባቸው የነበሩ መሣሪያዎችን ዝርዝር የሚያቀርብልዎ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሚፈልጉት መሣሪያ ላይ "Logout" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን መውጣት ይችላሉ፤

4. ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄ ሲላክልዎ አይቀበሉ

#_ጠላፊዎች ሰዎችን ለማጥመድ ሲፈልጉ ሀሰተኛ አካውንት ሊፈጥሩ ይችላሉ፤

#_የጠላፊዎች ጓደኛ መሆን ምን አልባት የእርሶን የፌስቡክ የፊት ገጽን /Timeline/ ሊበክሉ፣ የተለያዩ ጉዳዮችን በገጾ ላይ ሊያጋሩ ወይም በካይ መልዕክቶችን በመልዕክት መቀበያዎ ሊልኩብዎ ይችላሉ፤

5. ከበካይ ሶፍትዌሮች እራሶን ይጠብቁ

#_አጥፊ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተሮች፣ ሰርቨሮች /Server/ ወይም የኮምፒውተር ኔትወርክ ላይ ጉዳት ሊጥሉ ይችላሉ፤

#_የተበከለ ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ምን ዓይነት ባህሪያት እንደሚያሳዩ እና እነዚህን በካይ ሶፍትዌሮችን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ በሚመለከት ያለዎትን እውቀት ያዳብሩ፤

#_ማፈላለጊያዎትን በየጊዜው ያዘምኑ፣ አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን እና የማፈላለጊያ ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ፤

6. አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን /Links/ ከሚያውቁት ጓደኛ ወይም ድርጅት እንኳ ቢላክልዎ ከመክፈት ይቆጠቡ

#_እነዚህ በፌስቡክ ወይም በኢ-ሜይል የሚላኩ ማስፈንጠሪያዎች /Links/ ሊሆኑ ይችላሉ፤

#_ፌስቡክ ወይም Meta የይለፍ-ቃሎን በኢ-ሜይል እንዲያስገቡ በፍጹም እንደማይጠይቅዎ ይወቁ፤

#_አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያ ሲያጋጥሞ ለፌስቡክ ሪፖርት /report it/ ያድረጉ፤

7. ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ መንገዶችን ይተግብሩ

#_ከማይታወቁ አድራሻዎችና መሣሪያዎች ወደ አካውንትዎ የመግባት ሙከራ ሲደረግ የጥቆማ መረጃ እንዲደርሶ /get alerts about unrecognized logins/ ያድረጉ፤

#_ባለሁለት ደረጃ የማንነት ማረጋገጫ ዘዴ /Set up two-factor authentication/ ይጠቀሙ፤

#_ሌሎች የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የፌስቡክ Help & Support ላይ በመግባት ያለዎትን ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

https://t.me/GudayAsfetsami
#Share
Muktarovich O.