ገናኘ የሚነሱ አንድ አንድ ችግሮች አሉ፡፡ ከሚነሱት የሕግ እና የአሰራር ችግሮች መኃል ከላይ የተነካኩና የጸሐፊው ሀሳቦችም ጭምር ተገልጧል፡፡ የቀሩትን በችግርነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ነጥቦች ደግሞ አሁን እናነሳለን፡፡
1. ቼክን ለክፍያ እንዲቀርብ ሳይሆን ለዋስትና ወይም እንደመተማመኛ ነው የሰጠሁት የሚል መከራከሪያ ይነሳል በተለይም በወንጀል ጉዳይ ተጠያቂ ላለመሆን የሚነሳ ጥያቄ ነው፡፡ ከላይ ባነሳነው መከራከሪያ ነጥብ መሠረት የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 693 የማታለል ይዘት በድርጊት ውስጥ መኖሩ መረጋገጥ አስፈላጊ አይሆንም ባልነው መሠረት ቼኩ ለተከፋዩ የተሰጠው እንደዋስትና እንኳን ቢሆን በሂሳብ ውሰጥ በቂ ሂሳብ እስከሌለው ድረስ የወንጀል ተጠያቂነት ማስቀረት አይችልም፡፡ የማታለል ጉዳይ በዚህ ግንኙነት መኖሩ ግድ ነው የሚባል ከሆነ ግን የዚህን ዓይነት መከራከሪያዎች ሚዛን የሚደፉ ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን የሰበር መዝገብ ቁጥር 67947 ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሂሳብ ውስጥ በቂ ሂሳብ ከሌለ የወንጀል ተጠያቂነት እንደሚያስከትል አስቀጧል፡፡ ዝርዝር ጉዳዩን ወደታች እንመለከተዋለን፡፡
2. ሌላው መከራከሪያ ጉዳይ በቂ ሂሳብ ሳይኖር ቼክ ወጪ ከተደረገ በኃላ ባንኩ የአውጪውን የቼኩ ሂሳብ መዝጋት፡፡ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት ለ 3 ግዜ በቂ ሂሳብ ሳይኖረው ቼክ የፃፈ ግለሰብ በባንኩ ሂሳቡ እንደሚዘጋበት ያስቀምጣል፡፡ ሁለት መሰረታዊ ልዩነቶችን ግልፅ እናድርግ፡፡ የመጀመሪያው ሂሳቡ በባንኩ የተዘጋው ቼኩን አውጪው ከመስጠቱ በፊት እና ሂሳቡ ከመዘጋቱ በፊት የተሠጠ ቼክ ብለን ለሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ የመጀመሪያውን ሁኔታ ለሁለት በድጋሜ ከፋፍሎ ማየት ነገሩን የበለጠ ግልፅ ያደርገዋል፡፡ በዚህም መሠረት ቼኩ ቀድሞ ስለመዘጋቱ በባንኩ ለአውጪው የተነገረና በባንኩ ያልተነገረበት ሁኔታዎች ይኖራሉ፡፡ ሁለተኛውን ሁኔታም በድጋሜ ለሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ በዚህም መሠረት ለክፍያ ቼኩ በሚቀርብበት ግዜ በቂ ሂሳብ በአካውንቱ የነበረውና ያልነበረው ተብሎ ለሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያውን ሁኔታ ማለትም ቼኩ ወጪ የሆነው ቼኩ ከተዘጋ በኃላ ሲሆንና ባንኩም ለአውጪው ቼኩ መዘጋቱን የገለፀለት እንደሆነ ክፍያ ሊፈፀም የማይችልበት ሰነድ ነው የሰጠው ማለት ይቻላል፡፡ በዚህ ሁኔታም በድርጊቱ ውስጥ የወንጀል ተግባር መፈፀሙም ግልፅ ይሆናል፡፡ የተፈፀመው ወንጀል ግን አንቀፅ 692 የመታለል ወንጀል ነው፡፡ ምክያቱም ክፍያ ሊፈፀም እንደማይችልና ችኩ መዘጋቱን በመደበቅ ነው ቼኩን ፅፎ የሰጠው፡፡ ከባንኩ ጋር ያለው ስምምነት የተቋረጠ ስለሆነ ክፍያ መጠየቅ አይቻልም፡፡ ለሌላኛው እና አከራካሪው ጉዳይ ቼኩ መዘጋቱ ሳይገለፅለት ሂሳቡ ከተዘጋ በኃላ ቼክ ፅፎ የሰጠ እንደሆነ ምን ይከሰታል?በወንጀልስ ተጠያቂነት አለበት ወይ?የሚሉት ጥያቄዎች መመለስ በተወሰነ መልኩም ቢሆን አስቸጋሪነት አለው፡፡ የወንጀል ተጠያቂነትን ለማስከተል እውቀት ወይም የጥንቃቄ ጉድለት(ቸልተኝነት)ይጠይቃል፡፡ ገንዘብ እንዳያስገባ ሂሳቡ ተዘግቷል በዚህ ሁኔታ አከራካሪና አጠራጣሪ ሁኔታ መፈጠሩን ማየት ይቻላል፡፡ በዚህ ሁኔታ ደግሞ ወደ ተከሳሽ ማድላት እንደሚኖርብን የወንጀል ሕግ አንደኛው መርህ ስለሆነ በወንጀል ጥፋተኛ ወዳለማድረጉ ማድላት ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ባንኮች የቼክ ሂሳብ ሲዘጉ የማሳወቅ አሰራርን የሚከተሉት፡፡ የማያሳውቁ ከሆነ ግን እራሱን የቻለ መከራከሪያ ነጥብ ሊሆን ይችላል ማለት ነው፡፡ በሁለተኛው ሁኔታ ግን ሂሳቡ የተዘጋው ቼኩ ወጪ ከሆነ በኃላ ከሆነ የማታለል ጉዳይ ለማቋቋም ያስቸግራል፡፡ በዚህ ሁኔታ መሆን የሚኖርበት ሂሳቡ በሚዘጋ ወቅት በቂ ሂሳብ ነበረው ወይስ አልነበረውም የሚለው ነጥብ ነው፡፡ በሂሳቡ ውስጥ በቂ ሂሳብ ካልነበረው አንቀፅ 693 ስር የወንጀል ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል፡፡ ምክንያቱም ቼኩ በቂ ሂሳብ እንዲኖረው የሚያስፈልገው ቼኩ ወጪ በሆነበት ወይም ለክፍያ በሚቀርብበት ግዜ ስለሆነ ወጪ ከተደረገ በኃላ በቂ ሂሳብ እንደሌለው የሚያሳይ ስለሚሆን የወንጀል ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል፡፡ ነገር ግን በሂሳቡ ውስጥ ሂሳቡ ሲዘጋ የነበረው ገንዘብ መጠን በቼኩ ላይ የተፃፈውን ለመሸፈን የሚያስችል ከሆነ ይህንን ቼክ በተመለከተ አውጪው በወንጀል ሊጠየቅ አይገባም፡፡ ምክያቱም የማታለል ጉዳይ የሌለበትና(አንቀፅ 692)የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትለው በቂ ሂሳብ በሂሳብ ውስጥ ያለመኖር ስለሆነ(አንቀፅ 693/1/ን በተመለከተ)፡፡ በዚህም አጋጣሚ ቼክ የፃፈና ሂሳቡ ግን ከባንክ ባለመከፈሉ ምክንያት የወንጀል ተጠያቂነት ያለ ቢሆንም ሁልግዜም ያለመሆኑን ያስገነዝባል፡፡ ይህ ማለት ግን የፍትሐብሔር ተጠያቂነትን በምንም መንገድ አያስቀርም(ያላግባብ ስለመበልፀግ በተደነገጉት የሕግ አንቀፆች መሠረት)፡፡
3. በቂ ሂሳብ እያለ ቼኩ ከተሰጠ በኃላ ለክፍያ ከመቅረቡ በፊት ቼኩን ማሳገድ፡፡ የንግድ ሕጉ አንቀፅ 857 ቼኩ ከመከፈሉ አስቀድሞ አውጪው እንዳትከፍል ብሎ የነገረው እንደሆነ ባንኩ የቼኩን ዋጋ አልከፍልም ለማለት ይችላል ብሎ በማስቀመጥ ይህንን መብት አድርጎ አስቀምጦታል፡፡ ከንግድ ሕጉ መረዳት እንደሚቻለው እንዳትከፍል ብሎ ለማዘዝ የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ እንኳን የለም፡፡ ይህንን በማድረጉ የወንጀል ተጠያቂነት ሊኖር ይችላል ብሎ መከራከር አይቻልም፡፡ በቂ ሂሳብ ሳይኖር ቼኩን ያሳገደው እንደሆነ ግን ቼኩ ለክፍያ በሚቀርብ ግዜ ብቻ ሳይሆን ወጪ ሲሆንም ጭምር በቂ ሂሳብ እንዲኖረው ስለሚያስፈልግ ይህ እንዳልነበረ የተረጋገጠ እንደሆነ ግን በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 693 መሠረት ተጠያቂ ሊሆን ይገባል ማለት ነው፡፡
4. ቅጣትን በተመለከተ በባንክ ሂሳቤ ውስጥ ያለኝ ገንዘብ ቼኩ ላይ ከተፃፈው ገንዘብ ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ ጉድለት ስለሆነ በልዩነቱ ልክ ነው መቀጣት ያለብኝ የሚል መከራከሪያ(ቅጣት ሲጣል በቅጣት አወሳሰን መመሪያው መሠረት የገንዘብ መጠንን ግምት ውስጥ አስገብቶ መጣል ስላለበት)፡፡ ይህንን በተመለከተ የገንዘብ መጠንን መሠረት በማድረግ ቅጣት እርከን እንደሚወሰን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ያመላክታል፡፡ ይህን ጥያቄ ለመፍታት በዋናነት መመሪያውን መጠቀም ይኖርብናል፡፡ በዚህም መሠረት መመሪያው በየትኛውም ድንጋጌው ላይ በቼኩ ላይ ስለተጠቀሰው ሂሳብ እንጂ ስለልዩነቱ የሚናገረው ነገር የለም፡፡ ሕጉንና መመሪያውን መሠረት በማድረግ ስለሚሰራና በሕጉም ላይ ሆነ መመሪያው ላይ ይህን የሚፈቅድ አሰራር ስለሌለ የዚህን ዓይነት ጥያቄ የሕግ መሠረት የለውም ተብሎ ሊታለፍ ይችላል፡፡
5. አጠቃላይ ቼኩ ላይ ያለው እና የተፃፈው ነገር ከፊርማው ውጭ የእኔ ስላልሆነ ቼኩ አያስገድደኝም በወንጀልም አልጠየቅም የሚል መከራከሪያ፡፡ የንግድ ሕጉ አንቀፅ 827 ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ ቼኩን ያወጣው ሰው ፊርማ ከሚለው በስተቀር ሌሎቹን አውጪው እራሱ እንዲፅፋቸው የሚያስገድድ አይደለም፡፡ ስለዚህ ሌላ ሰው ሌሎቹን ነገሮች ፅፎለት ከተመለከተ በኃላ ፊርማውን ካኖረ በተፃፈው ነገር ተስማምቷል ሕጉም ሌሎቹን ፅሁፎች እራሱ እንዲፅፍ ስለማያስገድዱ በቼኩ በፍትሐብሔርም ሆነ በወንጀል ተጠያቂነት ሊኖርበት ይገባል፡፡ ነገር ግን ማስተዋል ያለብን በሌላ በኩል አውጪው በቼኩ ላይ ፊርማ ብቻ አኑሮ ለሌላ ሰው ከሰጠው ሰነድ እንጂ እንደ ቼክ እንደማይቆጠር ሕጉ ያስቀምጣል፡፡ ስለዚህ በዚህ ሁኔታ ቼክ ተብሎ ለመጠየቅ ያስቸግራል፡፡ ስለዚህ ፅሁፉን ማንም ይፃው ማን ዋናው ነገር አውጪው የተፃፈውን ነገር ተመልክቶ ፊርማውን

የምስክሮች ቃል መመዘኛ መንገዶች
⚖️በበርካታ ክርክሮች ላይ የሰው ምስክሮች በማስረጃነት ተጠቅሰው የሚሰሙ ሲሆን የተሰሙት ምስክሮች የተያዘውን ጭብጥ ምን ያህል አስረድተዋል ለማለት እና የተሻለ ያስረዳውን ለመለየት ግምት ውስጥ የሚገቡ መመዘኛዎች ግን ግልፅ ባለመሆናቸው በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች የማስረጃ ምዘና መርህን መሰረት በማድረግ ውሳኔዎችን ሲገለባብጡ ይታያል።
💥በክርክር ሂደቶችም አንድን ፍሬ ነገር ለማስረዳት የተጠሩ የግራ ቀኙ ምስክሮች ቀርበው ሲመሰክሩ የከሳሽም ለከሳሽ፤ የተከሳሽም ለተከሳሽ በሚያስረዱበት ጊዜ ሌሎች ማጣሪያ ማስረጃዎች ከሌሉ ዳኞች እውነተኛውን ምስክር ለመለየት ሲቸገሩ ማየት የተለመደ ነው። ብዙ ጊዜም ዝምድናንና ፀብን ብቻ እንደ መለያ መስፈርት ሲጠቀሙም ይስተዋላል። አንዳንዶች ደግሞ የቃላት ልዩነትና መመሳሰልን ብቻ መሰረት ያደርጋሉ።
💥በዚህ ፅሁፍም በተከራካሪ ወገን የተቆጠሩ የሰው ምስክሮች የሰጡት የምስክርነት ቃል ፍሬ ነገሩን በማስረዳት ረገድ ያላቸውን ተዓማኒነት ለመመዘን ግምት ውስጥ መግባት ያለባቸውን መስፈርቶች ለመግለፅ እንሞክራለን።
1# 🇪🇹ዕድልና አጋጣሚን መሰረት በማድረግ የምስክሮችን ቃል መመዘን
ምስክሮች የሰጡት ቃል ትክክለኛነት ከሚመዘንባቸው መስፈርቶች መካከል አንዱ ዕድልና አጋጣሚ ነው።ማለትም ምስክሩ ቀርቦ የመሰከረው ቃል እርሱ እንደሚለው ለመስማት፣ ለማየት.... ወዘት እንዴት ቻለ? በሚል መጠየቅ ያስፈልጋል። ይህ ጥያቄ አግባብነቱ ለፍትሀብሄርም ለወንጀልም ጉዳዬች ሲሆን ከጊዜ፣ ከቦታ እና ድርጊቱ ሲፈፀም ከነበረው የምስክሩ ባህሪ አንፃር ሊታይ የሚገባውንነው።
ድርጊቱ የተፈፀመበት ቦታ ማስረጃን ለመመዘን ከፍተኛ ድርሻ አለው። ምስክሩ ያስረዳው ድርጊት የተፈፀመበት ቦታ ሊገኝ የቻለበት ዕድልና አጋጣሚ መመርመር ይገባዋል። ይህም ምስክሩ የሚሰጠውን ቃል የሚያውቀውን ወይም ግምቱን እንደሆነ ለመለየት ይረዳል።
ከጊዜ አንፃር ምስክሩ ድርጊቱ በተፈፀመበት ቦታ ሊገኝ መቻልና አለመቻሉን፣ ቢገኝም እንኳ ለመለየት መቻልና አለመቻሉን ለማረጋገጥ ይረዳል። ከዚህ በተጨማሪ ድርጊቱ ሲፈፀም ምስክሩ ዝም ብሎ የመከታተሉን ሁታ የተለመደና ያልተለመደ መሆኑንም በመለየት የምስክሩን ትክክለኛነት ለመመዘኛ መጠቀም ይቻላል።
2# 🇪🇹ቀጥተኛ የሆነና ያልሆነ የምስክር ቃል ምዘና
ቀጥተኛ ማስረጃ ቀጥተኛ ካልሆነ ማስረጃ የተሻለ አስረጅነት አለው ብሎ መገመት ስህተት ሊሆን ይችላል። ፍሬ ነገሩ ቀጥታ በሆነ ሁኔታ አውቃለሁ የሚል ምስክር አካባቢያዊ ሁኔታዎችን ገልፃ ከሚያስረዳ ማስረጃ የተሻለ አስረጅነት አለው ብሎ መደምደም አይቻልም። ዋናው ቁም ነገር የቀረበው ማስረጃ ከብዙ አጋጣሚዎች አንፃር ሲመዘን የሚኖረው የአስረጅነት ብቃት እንጂ ቀጥተኛ መሆን አለመሆን ላይ አይደለም።
በአይን አየሁ የሚለው ምስክር ቃሉ ሲመዘን ከግል ፍላጎቱ፣ ከጥላቻ ወይም ከዝምድና እንዲሁም ጉዳዩን ለማወቅ ካለው አጋጣሚ አንፃር ሲታይ እውነተኛ ላይሆን ይችላል። ቀጥተኛ ያልሆነ ማስረጃም ቢሆን ከሌሎች ተጨማሪ ማስረጃዎች ጋር ተጣምሮ ሲታይ እምነት የሚጣልበት ሆኖ ልናገኘው እንችላለን።
#3 🇪🇹የምስክሮች ቃል አንድነትና ልዩነት መሰረት መመዛን
የምስክሮች ቃል የእርስ በእርስ ግንኙነት ሲመረመር አንዱ ምስክር ከሌላው ምስክር ቃል ጋር ብቻ በማገናዘብ ሳይሆን አንዱ ምስክርም ቢሆን በዋና ጥያቄ፣ በመስቀለኛ ጥያቄ እና በድጋሜ ጥያቄ የሰጠው ቃል ትስስርና ተያያዥነት እንዱሁም የምስክሩ ቃል ከሌላ ዓይነት ማስረጅ ( ሰነድና ኢግዚቢት) ማስረጃ ጋር ያለው ግንኙነት መታየት ይገባዋል።
የምስክሮች ቃል ልዩነት መኖር ምስክሩን አጠራጣሪ፣ ሀሰተኛ እና የማይታመን የሚያደርገው ሲሆን ነገር ግን ሲመዘንና ሲወሰን የሰወችን የግንዛቤ ደረጃ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይኖርበታል። ከዚህ በመነሳት ከሰዎች የግንዛቤ ደረጃ ልዩነት አንፃር የምስክር ቃል ልዩነት ሊኖር ስለሚችል ፍርድ ቤቶች ልዩነቱ በጉዳዩ ላይ ለውጥ የሚያመጣ ጉልህና መሰረታዊ መሆንና አለመሆኑ ሊታይ ይገባል።
በአንፃሩ የምስክሮች ቃል መመሳሰል የተሻለ ግምት የሚሰጠው ቢሆንም ስለተመሳሰለ ብቻ በእርግጠኝነት እውነት ነው ብሎም መደምደም አይቻልም። ስለዚህ ማስረጃው ተመሳሳይ ቢሆንም እንኳን መገምገምና መመዘን አስፈላጊ ነው።
#4 🇪🇹ጥቅም ያላቸው ምስክሮች የምስክርነት ቃን ምዘና
ምስክሮቹ ከተከራካሪ ወገኖች ጋር ባላቸው ፀብ፣ ዝምድና ወይም የተለየ የጥቅም ተጋሪነት፣ ወገንተኘትና ሌላ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች በጉዳዩ አወሳሰን ላይ የተለየ ፍላጎት ሊኖራቸው ስለሚችል የሚሰጡት የምስክርነት ቃል ምዘና በጥንቃቄ ሊታይ የሚገባው ነው። ዝምድና ያለው ሁልጊዜ ይወግናል ፀብ ያለው ደግሞ ያጠቃል ብሎም መደምደም አይቻልም።
ስለዚህ ፍርድ ቤቶች ፀብ ወይም ዝምድና ያላቸውን፣ የራሳቸው ተከራካሪዎችን፣ የአብሮ አባሮችና የጥቅም ተካፋዬችን ምስክሮች ቃል ሲመዝን ይመሰክሩበታል ከተባለው ፍሬ ነገር ወይም ጭብጥ አካባቢያዊ ሁኔታ አንፃር ማየትና የተሰጠው የምስክርነት ቃል እውናተኛ መሆኗን ወይም ለመጥቀም ወም ለመጉዳት በማሰብ የተቀነባበረ ወይም የተጋነነ መሆኑን ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል። ለመመስከር የተነሱበት ምክንያትም መታየት ይገባዋል።
#5🇪🇹 ልዩ መደብ ያላቸው ምስክሮች ቃል ምዘና
ህፃናት የሚሰጡት የምስክርነት ቃል የተሻለ ተዓማኒነት ያለው ቢሆንም በሌሎች ተፅዕኖ ስር የመውደቃቸው ሁኔታ ከፍተኛ በመሆኑ እና ድርጊቱ የተፈፀመበትና የሚመሰክሩበት ጊዜ ልዩነት ከዕድሜያቸው የማስታወስ ችሎታ አንፃር ስጋት ስለሚፈጥር የሚሰጡት ቃል ከሌሎች ምስክሮች ቃል ጋር ተገናዝቦ በጥንቃቄ ሊመዘን ይገባል።
በዕድሜ የገፉ ሰዎች ምስክርነት ቃልም ከማስታወስ ችሎታ መድከም ጋር ተያይዞ ችግር ሊኖር ስለሚችል ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር ተደግፎ መታየት ይኖርበታል።
የኤክስፐርት የሙያ ምስክርነት ቃልም ቢሆን የተዋጣላት በቂ ማስረጃ ተደርጎ የሚወሰድ ሳይሆን ስለሙያ አስተያየቱ ትክክለኛነት የቀረቡ ማረጋገጫዎች፣ የእውቀት ምንጩ ከሌላ ያረጋገጠው ወይስ ራሱ ያወቀው፣ ያለው ገለልተኝነት እና የእውቀት ደረጃው ጭምር መታየት ይኖርበታል።
via Henok Taye
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

የወንጀል ምርመራ ትርጉምና ጠቀሜታ
====================
መንግሥት ወንጀል ምርመራና የወንጀል ክስ የማቅረብ ተግባር ሙሉ በሙሉ በውክልና ለግለሰብ ወይም የህግ ሰውነት ላለው ድርጅት አሳልፎ ለመስጠት የማይችልበትና በርካታ ምክንያቶች እንዳሉ ግልፅ በመሆኑ ምክንያቶቹን መዘርዘር አያስፈልግም፡፡
በመሆኑም መንግሥት በአንድ አካባቢ ወንጀል የተፈፀመ ስለመሆኑ አጠርጣሪ ሁኔታዎች ሲኖሩ ጉዳዩን የማጣራት ወንጀል የተፈፀመ ስለመሆኑ መረጃ ሲደርሰው መረጃና ማስረጃ የማሰባሰብና የወንጀል ምርመራ የማከናወን ግዴታና ሀላፊነት አለበት፡፡ ስለሆነም በአንድ አካባቢ ወንጀል ስለመፈፀሙ አጠራጣሪ ሁኔታ ወይም ወንጀል ስለመፈፀሙ መረጃ ሲደርሰው መረጃውን የሚቀበል እና የወንጀል ምርመራ ማከናወን የመጀመሪያው ተግባር ነው፡፡ ይኸም መንግሥት የሚያከናውነው የወንጀል ምርመራ የራሱ የሆነ ግብና ዓላማ አለው፡፡ ስለሆነም ስለ ወንጀል ምርመራ መሠረታዊ ግብና ዓላማ ለመረዳት በመጀመሪያ የወንጀል ምርመራ ትርጓሜና ጠቀሜታ ምንድን ነው? የሚለውን ነጥብ አንስቶ መወያየቱ የጎላ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
“የወንጀል ምርመራ” መሠረታዊ ትርጉም ስንመለከት የአማርኛ ቋንቋ መዝገበ ቃላቶች የወንጀል ምርመራ ለሚለው ፅንሰ ሃሣብ የተሟላ ትርጉም ሰጥተው እናገኝም፡፡ ይህንንም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት ኢንስቲቲዩት በ1993 ዓ.ም ባሣተመው መዝገበ ቃላት ለመረዳት ይቻላል፡፡ መዝገበ ቃላቱ “የወንጀል ምርመራ ማለት ሕገ ወጥ የሆኑ ተግባራትን እንደ ሌብነት ግድያና የመሳሰለው ጥፋት በደልና ስህተቶችን የምርመራ ሥራ ማከናወን” ማለት ነው በሚል ቁንፅል ትርጓሜ ሰጥቶት እናገኛለን፡፡ በአንፃሩ በእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላቶች ውስጥ የወንጀል ምርመራ /Criminal Investigation/ የሚለውን ፅንሰ ሃሣብ መሠረታዊ ምንነት ልዩ ባህሪያትና ዓላማ የሚያቅፋቸውን ተግባራት ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ የሚገልፅ ትርጓሜ ተሰጥቶት እናገኛለን፡፡
የወንጀል ምርመራ /Criminal Investigation/ የሚለው ፅንሰ ሃሣብ በእንግሊዝኛ የህግ ማዝገበ ቃላት የሰጠውን ትርጓሜ ስንመለከት “Criminal Investigation is a process of establishing that the crime is committed, identifying and apprehending the suspect, recovering the stoen property if any, and assisting in the prosecution of a person charged with crime’ የሚል ትርጓሜ ሰጥቶት እናገኛለን፡፡ ይህንን ትርጓሜ በትኩረት ስንመረምረው የሚከተሉትን መሠረታዊ ነጥቦች ያካተተ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
1. #የወንጀል ምርመራ በራሱ ግብ ሣይሆን የግብ ማሣካት ሂደት መሆኑ
የወንጀል ምርመራ ጎን በጎን የሚፈፀሙ የተለያዩ ተግባሮችን የያዘ የሥራ ሂደት /Process/ መሆኑ ነው፡፡ የወንጀል ምርመራ ማከናወን በራሱ መሠረታዊ ግብ አይደለም፡፡ የወንጀል ምርመራ የተለያዩ ዓላማዎችን ለማሣካት የሚከናወን የሥራ ሂደት ነው፡፡ ለዚህም ነው የወ.መ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ 12 የወንጀል ምርመራ የሚጀመረው ወንጀል ስለመፈፀሙ ምክንያታዊ ጥርጣሬ ሲኖር መሆኑን የሚደነግገው በእኛ አገር የወንጀል ምርመራ መጀመር በራሱ እንደ አንድ ግብ የሚታይበትና በተለይም
የወንጀል ባህሪ በሌላቸው የፍታብሔር ጉዳዮች መነሻ በማድረግ ተጀምረው ጊዜና ጉልበት ከባከነባቸው በኋላ የሚመክኑ የምርመራ ሥራዎች መኖራቸው
ያለበቂ ምክንያት ሰውን በቁጥጥር ሥር ለማዋልና አስሮ ለማቆየት ሲባል ዓርብ ተጀምረው ሰኞ የሚቋረጡ ምርመራዎች
ወንጀል ከተፈፀመ በኋላ ተጠርጣሪውን ፍርድ ቤት በዋስ እስኪለቀው ድረስ የተወሰነ ደረጃ ከተራመደ በኋላ ከዚያ በኋላ የሚዘነጉና ተቋርጠው የሚቀሩ ምርመራዎች መኖራቸው ሲታይ የወንጀል ምርመራ መጀመርን በራሱ መሠረታዊ ግብ አድርጎ የመውሰድ የተዛባ አመለካከት እንዳለ ለመገንዘብ እንችላለን፡፡
2. #የወንጀል ምርመራ የሚከናወነው በመጀመሪያ ወንጀል የተፈፀመ መሆኑን ለማጣራት ነው፡፡ የወንጀል ምርመራ ከወንጀል ምርመራ የሚጠበቀው ወንጀል ለመፈፀሙ በተለያየ መንገድ መረጃ ሲደርስ በእርግጥ ወንጀሉ የተፈፀመ መሆኑ ወይም መረጃው በሀሰት ተቀነባብሮ የቀረበ የተባለው ወንጀልም ያልተፈፀመ መሆኑን ማረጋገጥ ነው፡፡ በእኛ አገር ምርመራ የማከናወን ስልጣን ያለው አካል /ፖሊስ/ ወንጀል ሰለመፈፀሙ ጥቆማ ሲደርሰው የምርመራ ሥራውን በእርግጥ የተባለው ወንጀል ተፈፅሟል ወይስ አልተፈፀመም የሚለውን ነጥብ በማጣራት አይጀምርም፡፡ ይልቁንም ወንጀሉ ስለመፈፀሙ እርግጠኛ ሣይሆንና ማስረጃ ሣያሰባስብ ወንጀሉን ፈፀሙ የተባሉትን ሰዎች በመያዝ ጥቆማ አቅራቢው ስለጉዳዩ ያውቃሉ ያላቸውን ምስክሮች ቃል በመቀበል ምርመራውን ጀምሮ የሚያጠናቅቅበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡
በዚህ ምክንያት ወንጀል ፈፅመዋል የተባሉት ሰዎች አላግባብ ተከስሰው ብዙ ጊዜ ከታሰሩ በኋላ ተፈፀመ የተባለው ወንጀል በሀሰት ተቀነባብሮ የቀረበ መሆኑን የተረጋገጠበት ሁኔታ በአማራ ክልል በተለያዩ ደረጃ ያሉ ፍርድ ቤቶች ከሰጧቸው ውሣኔዎች ለመረዳት ይቻላል፡፡
በአጠቃላይ አንድ መረጃና ጥቆማ የደረሰው ፖሊስ የቀረበለትን መረጃ በደፈናው ማመን የለበትም፡፡ በመረጃው የተገለፀው ወንጀል ተፈፅሟል ከሚል መደምደሚያ ላይም ስለጉዳዩ ማስረጃ ከማሰባሰቡና ከማጣራቱ በፊት መድረስ የለበትም፡፡ ስለሆነም መርማሪው ነፃና ገለልተኛ ሆኖ በመጀመሪያ በእርግጥ ወንጀሉ በትክክል ተፈፅሟልን? የሚለውን ነጥብ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ታዓማኒነት ያላቸውን መረጃዎች በማሰባሰብ ዕውነታውን መፈለግ ይገባዋል፡፡
3. #የወንጀል ምርመራ የሚከናወነው ተጠርጣሪውን ለመለየትና በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው፡፡ ስለሆነም የወንጀል ምርመራ የሚያከናውነው አካል ወንጀል መፈፀሙ ካረጋገጠ በኋላ ተጠርጣሪዎቹን ለመለየትና ለመያዝ የሚከናወን የሥራ ሂደት ነው፡፡ የአንድ ምርመራ እና የወንጀል የፍትህ ሥርዓት ውጤታማነት ተጠርጣሪዎቹን ለመለየትና ተጠርጣሪዎቹን በመያዝ አቅም ነው፡፡ በዚህ በኩልም ቀላል የማይባሉ ችግሮች መኖራቸውን የሚያመላክቱ መረጃዎች ስላሉ ትኩረት ሰጥተን ልንሠራ ይገባናል፡፡
4. #የወንጀል ምርመራ ሌላው ትኩረት በወንጅሉ የተወሰዱ ንብረቶች በአስቸኳይ ተከታትሎ መያዝና ማስመለስ ጭምር ነው፡፡ በመሆኑም ከላይ ከተገለፁት ተግባራት ጎን በጎን በወንጀሉ የተወሰደ ንብረት ለማስመለስ በትጋት መሥራትን ይጠይቃል፡፡ ይህንን በአግባቡ ማከናወን ሲቻል ብቻ ነው፡፡ “ማንም ሰው በወንጀል ሥራ ፍሬ ተጠቃሚ ሊሆን አይገባውም” የሚለውን መሠረታዊ መርህ ተግባራዊ ለማድረግ የሚቻለው፡፡
5. #የወንጀል ምርመራ አጥፊውን ለፍርድ ለማቅረብና የሚችል ማስረጃ ለማሰባሰብና በወንጀል ክስ፣ የሙግትና የፍርድ ሂደት አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ ነው፡፡ እዚህ ላይ አንድ አንድ መርማሪዎች ምርመራው ከተጠናቀቀ ዐቃቤ ሕግ ክስ ካቀረበ በኋላ የወንጀል ምርመራ መሠረታዊ ግብ እንደተሳካ አድርገው በተከሣሽ አቀራረብም ሆነ በምስክሮች አቀራረብ እኛን የሚመለከት አይደለም የሚል ክርክር ያቀርባሉ፡፡ አንድ ምርመራ ተከናውኖ ተከሣሹና ማስረጃዎች ፍርድ ቤት ቀርበው ተጠያቂ የማይሆን ከሆነ የወንጀል ምርመራ መሠረታዊ ግቡን አያሣካም፡፡ ሌሎች አገሮች ተከሣሽን በመክሰስና ጥፋተኛ ለማሰኘት የሚደረገው ዕገዛ የወንጀል ምርመራ አንደኛው ሂደት እንደሆነ “ Criminal Investigation is the process of assisting prosection of

በወንጀል ክርክር ወቅት የመስቀለኛ ጥያቄ መጠየቂያ መርሆችና ቴክኒኮች
===========https://t.me/lawsocieties
ዐቃቤህግ በመደበኛ የወንጀል ክስ ለመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ሲቀርብ ስለጉዳዩ በተለይም ስለምስክርነቱ አስቀድሞ ሳይዘጋጅ ማለትም ዕዉቀት ሳይኖረዉ ነዉ:: መስቀለኛ ጥያቄ ሂደት እንኳንስ ያለቅድመዝግጅት ዝግጅትም ተደርጎ አስቸጋሪ ሥራ ነዉ:: የመከላከያ ምስክሮች ከመዋሸት እስከ ሆን ብሎ አለማስታወስ ድረስ መሰናክል ሊፈጥሩ ይችላሉ:: በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደቱ ለዐቃቤህግ ተባባሪ ላይሆኑ ይችላሉ:: ስለዚህ ዐቃቤህግ በዚህ ሂደት ለማግኘት የሚፈልገዉን ምናልባትም ሊያገኝ የሚገባዉን ያለማግኘት ችግር ሊያጋጥመዉ ይችላል:: እንዲያዉም የራሱን ክስ ሊጎዳ የሚችል አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል:: ስለዚህ መስቀለኛ ጥያቄን ለማካሄድ ወይም ላለማካሄድ በከፍተኛ ጥንቃቄ መምረጥ አና ማካሄድ የግድ ነዉ:: ለዚህ ደግሞ አንዳንድ መርሆችንና ቴክኒኮችን ማወቅ ተገቢ ነዉ:: እነዚህ መርሆችና ቴክኒኮች በአሰራር ልማድ የምንፈጥራቸዉን ችግሮች ለማረም እገዛ ሊያደርጉ የሚችሉ ናቸዉ:: እነዚህን ቆየት ብለን የምናያቸዉ ሆኖ ከዚያ በፊት ስለመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ወሰን እና መጠን አንዳንድ ነገሮች እንይ::
በቅድሚያ ከላይ እንደተገለጸዉ መስቀለኛ ጥያቄ አስቸጋሪ ሂደት ነዉ:: አደጋዎቸ አሉት:: ስለዚህ መስቀለኛ ጥያቄ ማከሄድ ተመራጭ ላይሆን ይችላል:: መስቀለኛ ጥያቄ አለማካሄድ ምን ዉጤት አለዉ? በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 140 እንደተመለከተዉ መስቀለኛ ጥያቄ አለመጠየቅ በሌላዉ ወገን የተነገረዉን እንደማመን አያስቆጥርም:: ስለዚህ መስቀለኛ ጥያቄ ብዙም ባይደፈር ይመረጣል:: በተለይም የመስቀለኛ ጥያቄ ግብ ከሆኑት (የተቃራኒን ምስክርነት የማይታመን መሆኑን ማሳየት በክሱ ላይ የደረሰዉን ጉዳት ማስተካከል ወዘተ) አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ለማሳካት የምንችል ወይም ተገቢ ካልሆነ በቀር ወይም ምስክሩ ለጉዳያችን የምንፈልገዉ መረጃ ብቸኛ ምንጭ ካልሆነ በቀር መስቀለኛ ጥያቄ ማካሄድ የሚመከር አይደለም::
ሆኖም ዘወትር እንደሚስተዋለዉ አንዳንድ ምስክሮች ባህሪያቸዉ ምንም ሳይጠየቁ መሄድ የለባቸዉም የሚያስብል ይሆናል:: በዚህ ጊዜ መስቀለኛ ጥያቄ ማንሳት የግድ ከሆነ ከላይ ሲባል እንደነበረዉ አደጋዉ የበዛ በመሆኑ መጠኑን ማሳነስ ይመከራል::
በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 137(3) ስር መስቀለኛ ጥያቄ በዋና ጥያቄ ጊዜ በተመለሱ ነገሮች ዉስጥ ያለዉን ስህተት አጠራጣሪ ወይም የማይታመን ቃል ለፍርድ ቤቱ ለመግለጽ ወይም ለማስተባበል የሚደረግ መሆኑ ተደንግጓል:: ስለዚህ ከዚህ የወጣ ጥያቄ ሲነሳ ተቃዉሞ ሊገጥም ይችላል:: ሆኖም በዋና ጥያቄ ከተፈጠረዉ ድንበር ወጥቶ መጠየቅ የሚቻልባቸዉ የተለዩ አጋጣሚዎች ይኖራሉ:: ለምሳሌ የምስክሩን ተዓማኒነት የሚመለከቱ ጥያቄዎች በዋና ጥያቄ ጊዜ ባይነሱም በጠቅላላዉ ምስክሩ የተናገረዉን ነገር ተዓማኒነት የሚመለከት ስለሚሆን ተቀባይነት ያለዉ አካሄድ ነዉ:: ለምሳሌ የተለመደዉ የተከሳሽ መከላከያ ክርክር (በወንጀሉ ጊዜ በወንጀሉ ቦታ አልነበርኩም) ሲቀርብ የሚነገረዉ ታሪክ የተፈጸመበትን ጊዜ ከወንጀሉ ጊዜ ጋር እንዲገጥም የማድረግ ነገር ስለሚኖር ምስክሩ ጊዜን በመለየት ረገድ ስላለዉ ችሎታ ለማረጋገጥ በዚህ ዙሪያ ጥያቄ ቢነሳ ሊከለከል አይገባም:: ምስክሩ ተዓማኒነቱ ምን ያህል እንደሆነ ለማሳየት የሚረዳ በመሆኑ ተገቢ ነዉ::
ከተዓማኒነት ጋር በተያያዘ ምስክሩ በነገሩ ዉስጥ ያለዉ ጥቅም ወይም ፍላጎት ሊታለፍ የማይገባዉ ነጥብ ነዉ:: ምስክሩ የሚሰጠዉ ምስክርነት ከነገሩ ዉስጥ ካለዉ ጥቅም ወይም ፍላጎት የተነሳ ከዕዉነት የራቀ ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ በነገሩ ዉስጥ ጥቅም እንዳለዉ ማሳየት በሰጠዉ ምስክርነት ላይ ዕምነት እንዲታጣ ሊያደርግ ስለሚችል በዋና ጥያቄ አልተነሳም ተብሎ ቀሪ ሊደረግ አይገባም::
አንዳንዴ ምስክሩ ራሱ ለመስቀለኛ ጥያቄ በሚመልስበት ጊዜ በዋና ጥያቄ ጊዜ ላልተነሱ ሀሳቦች መንገድ ሊከፍት ይችላል:: በዚህ ጊዜ ምስክሩ ራሱ ባነሳዉ ነገር ላይ ሌላ መስቀለኛ ጥያቄ የማይጠየቅበት ምክንያት አይኖርም:: ስለዚህ ዐቃቤህግ እነዚህን አጋጣሚዎች በንቃት መጠባበቅ ይገባዋል፣ ለዚህም ምስክርነቱን በሚገባ ማዳመጥ ይኖርበታል፡፡
ከጭብጥ ከመዉጣት ሌላ በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት የማይፈቀድ ነገር ምስክርን ማስፈራራት እና ማንጓጠጥ ነዉ:: ምስክሩ ዐቃቤህግ የሚፈልገዉን እንዲል መገደድ የለበትም:: ይህን ማድረግ የሚቻለዉ ክህሎት በተሞላዉ የአጠያየቅ ዘዴ መሆን አለበት:: አዘዉትሮ በፍርድቤቶች በሚደረግ ክርክር ጊዜ የሚስተዋል በህግ ባለሙያዎች (ዐቃብያነህግ ጠበቆች ዳኞች) የሚባል አንድ ነገር አለ:: ምስክሩ እነዚህ ባለሙያዎች እንደፈለጉት ወይም ዕዉነት ነዉ ብለዉ እንደሚያስቡት ሳይናገር በቀረ ጊዜ በሃሰት መመስከር በወንጀል እንደሚያስቀጣ ይነግሩታል:: ይህ ነገር ማስፈራራት ከመሆኑ በተረፈ ነገሩ ተሰምቶ ሳያልቅ እና ምስክሩ የተናገረዉ ሃሰት ይሁን ዕዉነት ሳይረጋገጥ በጉዳዩም ላይ በምስክሩም ላይ ፍርድ የመስጠት ያህል ይሆናል:: ከዐቃቤህግ የህግ ጠባቂነት ሚና አኳያም የሰዉን መብት የሚደነግጉ ህጎችን የመጣስ ዉጤት ይኖረዋል::
የመስቀለኛ ጥያቄዎች ባህሪያት (መሪ ጥያቄ)፡-- ይህ የጥያቄ አይነት በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ዉስጥ በህግ የተፈቀደ ቢሆንም ዐቃቤህግ (ሌሎች ባለሙያዎችም) ሲጠቀሙበት አይስተዋልም:: በርግጥ ይህ የጥያቄ አይነት ስለሚያስከትለዉ መልስ ማወቅን ስለሚጠይቅና ዐቃቤህግ ደግሞ ከላይ እንደተገለጸዉ ያለቅድመዝግጅት ስለሚቀርብ ይህን የጥያቄ አይነት ለመጠቀም አይደፋፈርም:: ሆኖም ዋና ጥያቄ የሚመስል ሂደት በማካሄድ ነገሮችን እንዲደገሙ ከማድረግና በዚህም ችሎትን ከማሰላቸት ግፋ ሲልም የዐቃቤህግን ክስ የሚያፈርስ አጋጣሚ ከመፍጠር በዚያዉ በችሎት በተደረገች ዝግጅትም ቢሆን መሪ ጥያቄ በመጠየቅ ምስክሩን እንዳሻዉ እንዳይናገር መቆጣጠር ይመከራል:: በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ዋናዉ ግብ ምስክሩን መቆጣጠር የሚመሰክረዉን ነገር መወሰን በዚህም ለመዋሸት ያለዉን ዝንባሌ ወዘተ ማስቀረት ነዉ:: በዋና ጥያቄ ጊዜ ሊነሱ የሚገባቸዉ ዝግ ያልሆኑ ጥያቄዎችን በማንሳት ምስክሩ የሚናገረዉን ነገር ልቅ ማድረግ ሂደቱን ዐቃቤህጉ ሳይሆን ምስክሩ እንዲቆጣጠረዉ ማድረግ ይሆናል::
አጭርና ነጠላ ጥያቄ፡- የተከሳሽን ምስክር በመስቀለኛ ጥያቄ መቆጣጠር የሚቻልበት መንገድ ጥያቄዉን መሪ ጥያቄ በማድረግ ብቻ አይደለም:: ጥያቄዉን አጭር ማድረግም እንዲሁ በምስክሩ ላይ የበላይነትን ያስገኛል:: ጥያቄዉ ከአንድ በላይ ሃሳብ ከሌለዉ እና ርዝመቱም አጭር ከሆነ ምስክሩ ለዚሁ ብቻ መልስ እንዲሰጥ ሰለሚገደድ ብዙም መፈናፈኛ አይኖረዉም:: በተለይ ከአንድ በላይ ሃሳብ አለመያዙ ምስክሩ መርጦ የመመለስ ስራ እንዳይሰራ ያደርገዋል የመልሱ ወሰን የታጠረ ይሆናል::
ከዚህ በተያያዘ ከአንድ በላይ የሆኑ ጥያቄዎችን አነባብሮ በአንድ ጊዜ መጠየቅ የሚገኘዉን መልስ ግልጽ እንዳይሆን ያደርገዋል:: አንድ መልስ ቢሰጥ ለየትኛዉ ጥያቄ እንደተመለሰ ማወቅ አይቻልም:: ስለዚህ እንደዋና ጥያቄ ጊዜ በአንድ ጊዜ አንድ ጥያቄ ብቻ ማንሳት ተገቢ ይሆናል::

መልሱ የሚታወቅ (የሚረጋገጥ) ጥያቄ፡- የመስቀለኛ ጥያቄ መልሱ የሚታወቅ ወይም ማስረጃ ሊቀርብበት የሚችል መሆን ይኖርበታል:: ግን ቀደም ሲል እንደተገለጸዉ ትልቁ ችግር ስለመከላከያ ምስክርነትም ሆነ ስለምስክሩ አስቀድሞ የሚሰበሰብ ማስረጃ የለም:: ስለዚህ የዐቃቤህግ መስቀለኛ ጥያቄዎች በዕድል ባወጣ ያዉጣዉ ወዘተ ላይ ተመስርተዉ የሚጠየቁ ናቸዉ:: ሆኖም ማስረጃ በተሰበሰበባቸዉ አጋጣሚዎች ለምስክሩ የሚቀርብ መስቀለኛ ጥያቄ ሊመለስ የሚገባዉን መልስ የሚጠቁም ሊሆን ይገባል:: ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠዉ መልስ ምንም ይሁን ምን በቂ ስለሚሆን የሚገኘዉ መልስ ምንነት ስጋት አይፈጥርም:: የሚፈለገዉን መልስ ምስክሩ አመነም አላመነም ዉጤቱን አይቀይረዉም:: ምክንያቱም ቢያምን ዐቃቤህግ እንደሚፈልገዉ ሆነለት ማለት ሲሆን ከካደ ደግሞ ማስረጃ ስላለ ምስክርነቱን ማስተባበልና በዚህም ምስክሩ ተዓማኒነት የሌለዉ መሆኑን ማሳየት ይቻላል::
የመስቀለኛ ጥያቄዎች አደረጃጀት፡- ዉጤታማ መስቀለኛ ጥያቄ በጥያቄዎች አይነት ብቻ የሚወሰን አይደለም:: የጥያቄዎቹ ቅደም ተከተልም (ቅንብር) የራሱ አስተወጽዖ ይኖረዋል:: በተለይ በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ ምስክሩን በሚገባ መቆጣጠር እጅግ አስፈላጊ ከመሆኑ አኳያ የጥያቄዎቻችን አወቃቀር ይህን የመቆጣጠር ችሎታ የሚያሳጣ መሆን የለበትም:: ስለዚህ የተቃራኒ ወገንን ምስክር የምንጠይቅ እንደመሆኑ በቀላሉ የምንፈልገዉን ነገር ለማግኘት አስቸጋሪ ስለሚሆን የጥያቄዎቻችን አወቃቀር የምስክሩን ወዳጅነት የሚያስገኝ እንዲሆን የግድ ነዉ::
ዐቃቤህግ መስቀለኛ ጥያቄ ሊጠይቅ ከወሰነ በዚህ ጥያቄ ሊያሳካ የፈለገዉን ነገር በሂደቱ መጀመሪያ ላይ መግለጽ የለበትም:: ይህ ግብ በምስክሩ ከታወቀ የተቃራኒ ወገን ምስክር እንደመሆኑ የመስቀለኛ ጥያቄዉ ሂደት ወደዚህ ግብ እንዲደርስ መፍቀዱ አጠራጣሪ ነዉ:: ስለዚህ ይህን ግብ የሚደብቅ የጥያቄዎች ቅደምተከተል መኖር አለበት::
ከዚህ የተነሳ በመነሻዉ ላይ የሚጠየቁ ጥያቄዎች ከምስክሩ ጋር ፍጥጫን የማያስነሱ ምስክሩ በቀላሉ ሊያምናቸዉ ወይም ሊስማማባቸዉ የሚችሉ ፍሬነገሮችን የሚመለከቱ መሆን ይገባቸዋል:: ይህን ማድረግ በዐቃቤህጉና በተከሳሽ ምስክር መካከል ሰላማዊ ሁኔታ ይፈጥራል:: ስለዚህ ከምስክሩ የሚፈለገዉን ለማግኘት ቀላል ይሆናል ቢያንስ ምስክሩ መሰናክሎችን ከመፍጠር ይታቀባል::
ይህ ማለት ደግሞ ዐቃቤህግ ለክሱ እጅግ አስፈላጊ የሚላቸዉን ነጥቦች መጀመሪያ ላይ ማንሳት የለበትም ማለት ነዉ:: እነዚህን ጉዳዮች ከመነሻዉ ከገለጸ ምስክሩ የመስቀለኛ ጥያቄዉን ዓላማ በቀላሉ ማወቅ ስለሚችል እና ይህም ምስክሩ በዋና ጥያቄ ጊዜ ከተናገረዉ ሊቃረን ስለሚችል ምስክሩ ይህን የተፈለገ ነገር ለመስጠት አይፈቅድም:: በሚችለዉ መንገድ ራሱን ከመቃረን ለማዳን የማስተካከያ መረጃዎችን ከመግለጽ ያለፈ ነገር ለመፈጸም ፈቃደኛ እንዳይሆን ያደርገዋል:: ስለዚህ ዐቃቤህግ መነሻዉ ላይ ከዋና ጥያቄ ሂደት በተቃራኒ ዋና ነጥቦችን ሳይሆን ዝርዝር ጉዳዮችን (በተቻለ መጠን ምስክሩ የማይክዳቸዉን) እንዲያነሳ ይመከራል::
ከዚህ ሌላ ዐቃቤህግ የመስቀለኛ ጥያቄ ዓላማዉን ለመደበቅ በጥያቄና መልሱ ሂደት ጊዜ ከአንድ የጥያቄ ሃሳብ ወደሌላዉ በመዝለል ምስክሩ የነገሩን አቅጣጫ እንዳይገነዘብ ማድረግ ይችላል:: ለዚህም ጥያቄዎቹ በተለያየ ርዕስ ስር እንዲደራጁ ሊያደርግ ይገባል:: ከዚህ ጋር በተያያዘ የአካባቢ ማስረጃን አስመልክቶ ከዋና ጥያቄ ጋር በማያያዝ ያነሳነዉ ሃሳብ ለመስቀለኛ ጥያቄም አግባብነት ይኖረዋል:: በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ ዓላማዉ ምስክሩ የዐቃቤህግን የክርክር አቅጣጫ እንዳይገነዘብ ማደረግ በመሆኑ የአካባቢ ማስረጃን የሚመለከቱ ጥያቄዎች እነዚህን ማስረጃዎቸ በአንድ ላይ የማሰባሰብ ባህሪ እንዳይኖራቸዉ ማድረግ ያስፈልጋል:: ምክንያቱም ከተሰባሰቡ ትርጉማቸዉ ግልጽ ስለሚሆን ምስክሩ የክርክሩን አቅጣጫ በቀላሉ እንዲረዳዉ በማድረግ መሰናክል እንዲፈጥር ይገፋፋዋል:: ስለዚህ መስቀለኛ ጥያቄዎች የአካባቢ ማስረጃዎች እንዲበታተኑ የማድረግ ችሎታ ሊኖራቸዉ ይገባል:: ለዚህም ከላይ እንደተመከለተዉ የጥያቄዎችን ቅድም ተከተለ በማዘባረቅ ከርዕስ ወደርዕስ መዟዟር አስፈለጊ ነዉ::
ከጥያቄዎች ቅደም ተከተል ጋር በተያያዘ አዘዉትሮ የሚታይ ስህተት አለ:: በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ ምስክሩ ሊክዳቸዉ የማይችሉ ፍሬነገሮችን መሰረት በማድረግ ዐቃቤህግ ለሚያቀርባቸዉ ጥያቄዎች በሚገኙ መልሶች የሚገነባ ታሪክ ሊኖር ይችላል:: ከዚህ በኋላ የዚህን ሁሉ ጥያቄና መልስ እንድምታ (ድምዳሜ) ምስክሩ እንዲናገር ከተጠየቀ መልሱ የተከሳሹን ክርክር የሚጎዳ ከመሰለዉ ወይም ከሆነ ምስክሩ የጥያቄዉ አቅጣጫ ሰለሚገባዉ ቀደም ሲል የሰጣቸዉን መልሶች የሚያስተካክል መልስ ሊሰጥ ስለዚህ ለክሱ የሚረዳዉን ነገር የመደበቅ ተግባር ሊፈጽም ይችላል:: ይህም እንኳ ባይሆን ተከሳሹ ወይም ጠበቃዉ በክርክሩ ላይ በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ የደረሰዉን ጉዳት በድጋሚ ጥያቄ ጊዜ የማስተካከል ስራ እንዲሰራ የማባነን ዉጤት ይኖረዋል:: ይህም ካልሆነ ፍርድቤቱ ራሱ በማጣሪያ ጥያቄ ጊዜ ነገሩን እንዲያነሳ ምስክሩም በዚህ አጋጣሚ ነገሩን የሚያድበሰብስ ወይም የሚያርም ተግባር እንዲፈጽም የማስታወስ ዉጤት ይኖረዋል:: በተግባር ሲደረግ የሚስተዋለዉም እንዲህ ያለ ዉጤትን የሚያመጣ አጠያየቅ ነዉ::
ስለዚህ ይህን የነገሩን ማሰሪያ ጥያቄ ዐቃቤህግ መጠየቅ የለበትም:: ቀላልና ተራ በሚመስሉ ጥያቄዎች የተገነባዉ ታሪክ እንድምታ ለፍርድቤቱ የሚተዉ ነዉ:: ምናልባት ለፍርድቤቱ ግልጽ የማይሆን ቢሆን በመስቀለኛ ጥያቄ የተሰጡ መልሶች የሚጠቁሙት ድምዳሜ ምን እንደሆነ በክርክር ማቆሚያ ንግግር ጊዜ መግለጽ ይቻላል::
ነገር ግን አሁን ባለዉ አሰራር ይህ ከላይ የተመለከተዉ የአሰራር አቅጣጫ ምን ያህል ያስኬዳል? የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነዉ:: ምክንያቱም የክርክር መዝጊያ ንግግር ወይም በተለምዶ አጠራሩ የመፋረጃ ሃሳብ እንዲቀርብ የሚያደፋፍሩ ፍርድቤቶች ጥቂት ከመሆናቸዉም በላይ እንዲቀርብ የሚያደርጉትም ቢሆኑ በአብዛኛዉ በጽሁፍ እንዲቀርብ የሚያደርጉ ሰለሆነ እንዲሁም የቀረበዉን ሃሳብ የሚጠቀሙበት ማለትም በዉሳኔ ጊዜ ከግምት የሚያስገቡት ፍርድቤቶች በእጀጉ ጥቂት በመሆናቸዉ ዐቃቤህግ በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ ያስመሰከራቸዉ ፍሬነገሮች ድምር ዉጤት ምን እንደሆነ በክርክሩ ጊዜ (በመስቀለኛ ጥያቄ ማጠናቀቂያ ጊዜ) ካልጠቆመ እንዲህ የሚያደርግበት መድረክ አያገኝም:: ከዚህ የተነሳ ዐቃቤህግ ከተከሳሽ ምስክር ጋር በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ዉስጥ ወይም ማሳረጊያ ላይ የምስክርነቱን እንድምታ እመን አትመን እሰጥ አገባ ዉስጥ ሲገባ ይታያል:: ስለዚህ ፍርድቤቶች የክርክር ማቆሚያ ንግግርን አሰራር እንዲያከብሩ ዐቃቤህግ መወትወት ዳኞችም ይህን አሰራር ባህል እንዲያደርጉት የግድ ነዉ::
ከዚህ በላይ ያየናቸዉ የጥያቄ አደረጃጀት ስራዎች ብቸኛ አይደሉም:: በርከት ያሉ በተለያዩ በለሙያዎች የሚቀርቡ ዘዴዎች አሉ:: ሆኖም ከላይ ያነሳናቸዉ ዘዴዎች ከኛ የአሰራር ልምድ ጋር ቁርኝት ስላላቸዉ ሊጠቀሱ በቅተዋል::

5.3 ምትክ መጥሪያ
መጥሪያ ሰጪው ተገቢውን ጥረት አድርጎ መጥሪያን ለተከሳሽ በግል የመስጠት ወይም አማራጭ የመጥሪያ አሰጣጥ ዘዴን በመጠቀም ለማድረስ ያልተቻለ መሆኑን ወይም ተከሳሽ ወይም ወኪሉ ወይም ስለ እርሱ ሆነው መጥሪያውን መቀበል የሚገባው ማናቸውም ሰው መጥሪያ የደረሰው ስለመሆኑ ማረጋገጫ ለመፈረም እንቢተኛ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ በቃለ መሓላ አረጋግጦ መጥሪያውን ሲመልስ እንዲሁም ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ መጥሪያ እንዳይደርሰው ሆነ ብሎ የተሸሸገ ወይም መሰናከል ያደረገ መሆኑን ሲረዳ መጥሪያው በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ግልፅ በሆነ ስፍራ እና በተከሳሹ መደበኛ መኖሪያ ቤት ወይም በመጨረሻ ጊዜ ይኖርበት የነበረበት መኖሪያ ቤት ወይም የንግድ ወይም የስራ ቦታ እንዲለጠፍ በማድረግ ተከሳሹ መጠራቱን እንዲያውቀው ያደርጋል (በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 103 እና 105)፡፡
5.4 ፖስታ በመላክ ወይም በጋዜጣ ማስታወቂያ
የመጨረሻው የመጥሪያ ማድረስ አማራጭ ዘዴ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሹ በፖስታ ቤት አማካኝነት መጥሪያውን በመላክ ወይም በጋዜጣ ማስታወቂያ አማካኝነት ተከሳሹ መጠራቱን እንዲያውቀው ማድረግ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሹ በፖስታ ቤት አማካኝነት መጥሪያውን በመላክ ተከሳሹን ለማግኘት ሙከራ ይደረጋል፤ በዚህ ዘዴ ተከሳሽ መቅረብ ካልቻለ በመጨረሻው አማራጭ ፍርድ ቤቱ በጋዜጣ ማስታወቂያ አማካኝነት ተከሳሹ መጠራቱን እንዲያውቀው ያደርጋል፡፡
ፍርድ ቤቱ መጥሪያው በተከሳሹ ወይም በወኪሉ መደበኛ መኖሪያ ቤት ወይም በሚሰራበት የስራ አድራሻ በአደራ ፖስታ እንዲላክ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 106 (1) መሰረት ማዘዝ ይችላል፡፡ በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ስር በግልፅ እንደተደነገገው ፖስታ ቤቱ መጥሪያውን ያደረሰ መሆኑን ወይም ተከሳሹ ወይም ወኪሉ መጥሪያውን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በፅሁፍ ሲያሳውቅ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሹ መጥሪያ እንደደረሰ ሊቆጥር ይችላል፡፡
ተከሳሹ የሚኖረው የመጥሪያ ትእዛዙን ከሰጠው ፍርድ ቤት የስልጣን ክልል ውጪ የሆነ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በሚኖርበት ወይም በሚሰራበት ወይም በሚነግድበት ቦታ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት መጥሪያውን እንዲያደርስ ሊልክ እንደሚችል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 107 ላይ ተደንግጓል፡፡ መጥሪያው የተላከለት ፍርድ ቤት የወሰደውን እርምጃ በፅሁፍ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡ ከኢትዮጲያ ግዛት ውጭ ለሚኖር ተከሳሽ መጥሪያ የሚቀበል ወኪል የሌለው እንደሆነ በተከሳሹ ስምና አድራሻ ተጽፎ ለሚገኝበት ሀገር በፖስታ ይላካል፡፡ ከኢትዮጲያ ግዛት ውጭ የሚኖር ተከሳሽ አድራሻው የማይታወቅ ከሆነ ደግሞ ኢትዮጲያ ጋዜጣ ላይ የመጥሪያ ማስታወቂያ እንዲወጣ ፍርድ ቤቱ ለማዘዝ ይችላል (በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 108)፡፡
ከላይ የተገለጹትን የመጥሪያ አሰጣጥ ዘዴዎች በመጠቀም ማድረስ ያልተቻለ እንደሆነ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 105-109 በተደነገገዉ መሰረት መጥሪያ በፖስታ የማድረስ ዘዴና ምትክ መጥሪያ አሰጣጥ ዘዴንም መጠቀም ይቻላል፡፡ ከዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባዉ ጉዳይ እነዚህ የመጥሪያ አሰጣጥ ዘዴዎች ሥራ ላይ መዋል ያለባቸዉ መጥሪያን ለተከሳሽ በግል የመስጠት ዘዴን በመጠቀም ለማድረስ ያልተቻለ ወይም የማይቻል መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነዉ፡፡
6. የመጥሪያ አደራረስ ዉጤቶች
ከመጥሪያ አደራረስ ጋር ተያይዞ ሁለት ዓይነት ዉጤቶች ያሉ፡፡ እነሱም
• መጥሪያን በአግባቡ አለማድረስ ስለሚያስከትለዉ ዉጤት
• መጥሪያ በአግባቡ ደርሶት ያለመቅረብ ዉጤት
6.1 መጥሪያን በአግባቡ አለማድረስ ስለሚያስከትለዉ ዉጤት
የተለያዩ የመጥሪያ አሰጣጥ ዘዴዎችን በመጠቀም ተከሳሽ ስለተከሰሰበት ጉዳይ አዉቆ እራሱን እንዲከላከል ለመጥራት የሚቻል ሲሆን የመጥሪያ አደራረስ ዘዴዎቹን በቅደም ተከተል ጥቅም ላይ መዋል ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ መሰረት ከላይ የተጠቀዉን የመጥሪያ ማድረስ ቅደም ተከተል ደረጃ በደረጃ በማከናወን መጥሪያዉ ለተከሳሽ እንዲደርስ ካላደረገ በበቂ ሁኔታ መጥሪያዉ ለተከሳሽ ሊደርሰዉ አልቻለም ተብሎ ይገመታል፡፡ በመሆኑም አግባብነት የሌለዉ የመጥሪያ አደራረስ ዘዴ በመጠቀም ተከሳሹ ስለተከሰሰበት ጉዳይም ሆነ ፍርድ ቤት ስላለበት ቀጠሮ እንዳያዉቅ በመከልከል ራሱን የመከላከል ዕድል መንፈግ ተገቢዉን የሕግ ሥርዓት የተከተለ አሠራር አይደለም፡፡ ስለሆነም በዚህ ዓይነት አድራጎት በተከሳሽ መብትና ጥቅም ላይ ሊደርስ የሚችለዉን አዳጋ ለመከላከል ሲባል ፍርድ ቤቶች መጥሪያዉ በአግባቡ ባልደረሰ ጊዜ የተለያዩ እርምጃዎችን ለመዉሰድ እንደሚችሉ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70(ሀ) (ለ) እና 78(2) ይደነግጋሉ፡፡ ይኸዉም፡- ክርክሩ እንዲሰማ በተወሰነዉ ቀነ ቀጠሮ ከሳሽ ቀርቦ ተከሳሽ ያልቀረበ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሹ የተላከለት መጥሪያ የደረሰዉ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ መጥሪያዉ በትክክል መድረሱ ያልተረጋገጠ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ሁለተኛ መጥሪያ እንዲላክ ትዕዛዝ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ፍርድ ቤቱ ይህን ሳያደረግ በማለፍ ጉዳዩ ተከሳሽ በሌለበት አይቶ እንዲወሰን ትዕዛዝ ቢሰጥና በዚህ መሠረት ክርክሩ ተከሳሽ በሌለበት አይቶ በተከሳሽ ላይ ቢወሰንበት ተከሳሽ መጥሪያዉ በሚገባ ያልደረሰዉ መሆኑን ገልፆ ዉሳኔዉ ወይም ትዕዛዙ መሰጠቱን በተረዳ ጊዜ ዉስጥ ቀርቦ ትዕዛዙ ወይም ዉሳኔዉ እንዲነሳለት ማመልከት ይችላል፡፡ ይህም ሲሆን ፍርድ ቤቱ መጥሪያዉ ለተከሳሹ በአግባቡ ያልደረሰዉ መሆኑን ከተረዳ የተከሳሽ አቤቱታ ለከሳሽ እንዲደርስ ካደረገ በኋላ ብይኑን ወይም ትዕዛዙን በማንሳት ክርክሩን እንደገና ሰምቶ መወሰን እንዳለበት የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 78(2) ይደነግጋል፡፡ ስለሆነም መጥሪያን በተገቢዉ መንገድ ለተከሳሽ አለማድረስ የክርክሩን ዕድሜ ያለአግባብ ከሚያራዝምና ተከራካሪ ወገኖችን የሥራ ጊዜ ያለ አግባብ ከሚሻማ በቀር ብዙም ፋይዳ ያለዉ አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡
6.2 መጥሪያ በአግባቡ ደርሶት ያለመቅረብ ዉጤት
ፍርድ ቤት አንድ ጉዳይ ለማየት እና ውሳኔ ለማስተላለፍ የተለያዩ ቀጠሮዎች እንደሚሰጥ የታወቀ ነው፡፡ የመጀመሪያ ተከሳሽ መከሰሱን አውቆ ለቀረበበት ክስ መከላከያ የሚሆኑ ማስረጃዎችን በፅሁፍ የሚያቀርብበት ነው፡፡ ፍርድ ቤት ተከሳሽ መጥሪያው በአግባቡ ደርሶት መልሱን ይዞ ከቀረበ ፍርድ ቤቱ በሥነ ሥርዓት ህጉ 241 እና ተከታዮቹ መሰረት ክሱን ለመስማት ይቀጥራል፡፡
ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ ሊሰማ በተወሰነበት ቀነ ቀጠሮ ከሳሽ ቀርቦ ተከሳሽ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ የፍርድ ቤቱ ቀዳሚ ስራ መጥሪያው ለተከሳሹ መድረሱን ማረጋገጥ ነው (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 70)፡፡ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሽ የላከው መጥሪያ የደረሰው መሆኑን ካረጋገጠ በሌለበት ጉዳዩን መስማት ይቀጥላል፡፡ መጥሪያው ለተከሳሽ በአግባቡ ያልደሰረው መሆኑን ካረጋገጠ ወይም አጠራጣሪ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ሁለተኛ መጥሪያ እንዲላክ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ አንድ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ተከሳሾች የተላከው መጥሪያ ለአንዱ ወይም ለአንዳንዶች ሳይደርስ የቀረው በከሳሽ ቸልተኘነት ወይም ጉደለት ከሆነ ፍርድ ቤቱ ከሳሽ መጥሪያ ባልደሰው ወይም ባልደረሳቸው ተከሳሾች ላይ ያቀረበውን ክስ ሊዘጋ ወይም ቀነ ቀጠሮ ሊቀይር ይችላል፡፡

Forwarded from Entrust Consult 📗ኢንትረስት
የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
INSA
1. የይለፍ-ቃልዎን ደህንነት ማረጋገጥ
#_የፌስቡክ አካውንቶን ለሌላ ማንኛውም የኦንላይን አገልግሎት ላይ አይጠቀሙ፤
#_ የይለፍ-ቃልዎን በፍፁም ለሌላ ሰው አያጋሩ፤
#_የሚጠቀሙበት የይለፍ-ቃል ለመገመት አዳጋች የሆነ፣ በፍጹም የእርሶን ስም እና የተለመዱ ቃላትን ያልያዘ ሊሆን ይገባል፤
#_የይለፍ-ቃልዎ ፣ኢ-ሜይልዎን፣ የስልክ ቁጥሮን ወይም የልደት ቀንዎን በፍፁም የሚጠቀም መሆን የለበትም፤
2. የሚያስሱትን ድረ-ገጽ መረጃ በፍጹም አያጋሩ
#_አጥቂዎች ፌስቡክ የሚመስል የሐሰት ገጽ ፈጥረው በኢ-ሜይል አድራሻዎና በይለፍ ቃልዎ እንዲገቡ ሊጠይቁዎ ይችላሉ፤
#_ሁልጊዜም መረጃ የሚያስሱበትን ድረ-ገጽ URL ትክክለኝነት ያረጋግጡ፤
አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ www.facebook.com በማፈላለጊያው ላይ በመጻፍ ወደ ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ለመመለስ ይሞክሩ፤
#_ ከሜታ /Meta/ ወይም ፌስቡክ የሚላክሎትን ኢ-ሜይል በፍጹም ለሌላ ሰው አያጋሩ፣ በተለይም ስለ አካውንቶ ምስጢራዊ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ፤
#_ስለፊሺንግ ጥቃት እና ጠንካራ የይለፍ-ቃል አጠባበቅ ላይ ያለዎትን እውቀትና ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤
3. ኮምፒውተርዎን ለሌላ ሰው የሚያጋሩ ከሆነ የፌስቡክ አካውንቶን ዘግተው መውጣትዎን /Log Out/ ማድረግዎን አይዘንጉ፤
#_ኮምፒውተርዎን ዘግተው ሳይወጡ ወይም መሣሪያዎን ያዋሱ ከሆነም ከርቀት እንዴት መውጣት /Log Out Remotely/ እንደሚችሉ ይወቁ፤
#_ከርቀት ሆነው ለሌላ አካል ካዋሱት ኮምፒውተር ላይ ለመውጣት(log out) ለማድረግ ወደ ፌስቡክ "Security and Login Setting" ሲገቡ ከዚህ በፊት ይገቡባቸው የነበሩ መሣሪያዎችን ዝርዝር የሚያቀርብልዎ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሚፈልጉት መሣሪያ ላይ "Logout" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን መውጣት ይችላሉ፤
4. ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄ ሲላክልዎ አይቀበሉ
#_ጠላፊዎች ሰዎችን ለማጥመድ ሲፈልጉ ሀሰተኛ አካውንት ሊፈጥሩ ይችላሉ፤
#_የጠላፊዎች ጓደኛ መሆን ምን አልባት የእርሶን የፌስቡክ የፊት ገጽን /Timeline/ ሊበክሉ፣ የተለያዩ ጉዳዮችን በገጾ ላይ ሊያጋሩ ወይም በካይ መልዕክቶችን በመልዕክት መቀበያዎ ሊልኩብዎ ይችላሉ፤
5. ከበካይ ሶፍትዌሮች እራሶን ይጠብቁ
#_አጥፊ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተሮች፣ ሰርቨሮች /Server/ ወይም የኮምፒውተር ኔትወርክ ላይ ጉዳት ሊጥሉ ይችላሉ፤
#_የተበከለ ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ምን ዓይነት ባህሪያት እንደሚያሳዩ እና እነዚህን በካይ ሶፍትዌሮችን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ በሚመለከት ያለዎትን እውቀት ያዳብሩ፤
#_ማፈላለጊያዎትን በየጊዜው ያዘምኑ፣ አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን እና የማፈላለጊያ ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ፤
6. አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን /Links/ ከሚያውቁት ጓደኛ ወይም ድርጅት እንኳ ቢላክልዎ ከመክፈት ይቆጠቡ
#_እነዚህ በፌስቡክ ወይም በኢ-ሜይል የሚላኩ ማስፈንጠሪያዎች /Links/ ሊሆኑ ይችላሉ፤
#_ፌስቡክ ወይም Meta የይለፍ-ቃሎን በኢ-ሜይል እንዲያስገቡ በፍጹም እንደማይጠይቅዎ ይወቁ፤
#_አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያ ሲያጋጥሞ ለፌስቡክ ሪፖርት /report it/ ያድረጉ፤
7. ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ መንገዶችን ይተግብሩ
#_ከማይታወቁ አድራሻዎችና መሣሪያዎች ወደ አካውንትዎ የመግባት ሙከራ ሲደረግ የጥቆማ መረጃ እንዲደርሶ /get alerts about unrecognized logins/ ያድረጉ፤
#_ባለሁለት ደረጃ የማንነት ማረጋገጫ ዘዴ /Set up two-factor authentication/ ይጠቀሙ፤
#_ሌሎች የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የፌስቡክ Help & Support ላይ በመግባት ያለዎትን ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤
https://t.me/GudayAsfetsami
#Share
Muktarovich O.

#
Muktarovich O.
በወንጀል ምርመራ ሂደት የዐቃቤ ሕግ ሚና
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን ተከታታዮች፤ እንዴት ናችሁ ለዛሬ በወንጀል ምርመራ ሂደት የዐቃቤ ሕግ ሚና ምን ይመስላል በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ በፍትህ ሚኒስቴር በህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ውስጥ ዐቃቤ ሕግ ከሆኑት ከአይናለም ኃይለማሪያም ጋር ቆይታ አድርገን ተከታዩን ማብራሪያ ሰጠውናል እንደሚከተለው ይቀርባል፡-
በመጀመሪያ ዐቃቤ ህጓ ከኛ ጋር ለሚያደርጉት ቆይታ ምስጋናችን አቅርበን በወንጀል ምርመራ ሂደት የዐቃቤ ሕግ ሚና ምን ይመስላል? የሚለውን ጥያቂያችን አስከተልንላቸው
እሳቸውም የቃለ-መጠይቅ ክፍሉ ለዚህ ቃለ-መጠይቅ ስለጋበዛቸው ምስጋናቸውን አቅርበው ዐቃቤ ህግ በወንጀል ምርመራ ሂደት ውስጥ ብዙ ሚና ያለው ሲሆን በመጀመሪያ የምናየው ብለው ተከታዩን ርዕሰ-ጉዳይ በማስቀደም ማብራሪያቸውን ይጀምራሉ
አቤቱታ እና ጥቆማ በመቀበል ሂደት ውስጥ የዐቃቤ ህግ ሚና
በወንጀል ጉዳይ የዐቃቤ ህግ ሚና የሚጀምረው የወንጀል ጥቆማ ለፖሊስ ወይም ለዐቃቤ ህግ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን አንስተው በሌሎች ህጎች ለፖሊስ የተሰጠው ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ዐቃቤ ህግ በፌዴራል ፍርድ ቤት ስልጣን ስር የሚወድቅ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር ከማድረግ በተጨማሪ ክትትልና ድጋፍም ያደርጋል ብለዋል፣ በፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ዘርፍ የሚከናወኑ የምርመራ ሥራዎችንም ይመራል፣ ይከታተላል፣ ያስተባብራል፣ ሪፖርት እንዲቀርብለት ያደርጋል፤ ብለው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 40 ዋቢ አድርገው ያነሳሉ፡ ከተል አድርገውም ዐቃቤ ሕግ በሁሉም የፌዴራል ፖሊስ ጣቢያዎች እንዲሁም የፌዴራል ጉዳዮች በሚታዩባቸው የክልል ፖሊስ ጣቢያዎች ተገኝቶ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ጥቆማዎችን በህግ አግባብ በማስተናገድ ከፖሊስ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የደረሰውን የወንጀል አቤቱታ ወይም ጥቆማ በመቀበል የመጣውን ባለጉዳይ በሚገባ በማስተናገድ፤ የቀረበው አቤቱታ ወይንም ጥቆማ፤
በወንጀል ሊያስጠይቅ የሚችል መሆን አለመሆኑን በመለየት
ወንጀል ስለመፈጸሙ የሚጠቁም መረጃ ስለመኖሩ፣
ከለየ በኋላ ከፖሊስ ጋር በመሆን የምርመራ ዘዴዎችን በመወሰን ምርመራን ያስጀምራል ሲሉ የመጀመሪያውን የዐቃቤ ህግ ሚና ይናገራሉ፡፡
ምርመራን መምራት የዐቃቤ ህግ ድርብ ሚና መሆኑን ያነሱት ዐቃቤ ሕጓ
ምርመራው ከተጀመረ በኋላ፤
ቀድሞ ተጠርጣሪ ሊከሰስበት የሚችልበትን ወንጀል በመለየት፤ ከክስ ባሻገር ሌሎች አማራጭ መንገዶችን ይለያል፡፡
ውጤታማ በሆነ መንገድ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤት ለማቅረብ ይቻል ዘንድ ማስረጃዎች እንዴት መሰብሰብ እንዳለባቸዉ በመለየት መመሪያ ይሰጣል፡፡
ምርመራዉ የሞያ ምስክርነትን የሚፈልግ መሆኑን በመለየት ባለሞያዉ የምስክርነት ቃሉን እንዲሰጥ መመሪያ ይሰጣል፡፡
በተለያዩ የመንግስትና የግል ድርጅቶች የሚገኝ ማስረጃ እንዴት መሰብሰብ እንዳለበት በማሳየት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስለማስፈለጉ በመለየት ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡
ስለ ተጠርጣሪው መያዝ ውሳኔ በመስጠት በተያዘ ጊዜ ሊኖር ስለሚገባ የመብት ጥበቃ ወይም በማንኛውም ግለሰብ ላይ ከወንጀል ምርመራ ጋር በተያያዘ የተፈጸመ የመብት ወይም የህግ ጥሰት በሚኖርበት ወቅት ተገቢውን ማጣሪያ አድርጎ ውሳኔ ያሰጣል ሲሉ ዐቃቤ ህግ ምርመራን በመምራት ወቅት ያለውን ሚና ዘርዘር አድርገው ይናጋራሉ፤ ቀጥለውም በዚህም ወቅት
በቃል አቀባበል ጊዜ ተጠርጣሪው ያለው መብት ተነግሮት ሳይገደድ በፈቃደኝነት ቃል መስጠት እንዳለበት
ከማንኛውም አካላዊም ሆነ ስነ-ልቦናዊ ጫና የመጠበቅ መብት እንዳለው እንዲነገረው በማድረግ
በተመሳሳይ ጉዳይ በድጋሚ ያለመከሰስ መብት ያለው መሆኑ እንዲነገረው በማድረግ
እንደነገሩ ክብደት እና ሁኔታ በፍርድ ቤት በመቅረብ ስለተጠረጠረው ሰው የመያዣ ትዕዛዝን፣ ብርበራን፣ የዋስ መብትን እና ሌሎች የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሚያስፈልግባቸው ጉዳዮች ላይ ቀርቦ ጥያቄ ያቀርባል ክርክር ያደርጋል ብለዋል ፡፡
ብርበራ እና መያዝን በተመለከተ የዐቃቤህግ ሚናስ? ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ
ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ ጋር በመሆን በወንጀል ምርመራ የሚደረግን ማንኛውንም ብርበራ ለጉዳዩ አስፈላጊ መሆኑንና ተገቢዉን ማስረጃ ለማግኘት ብቻ የሚደረግ ወይም የተደረገ ስለመሆኑ በማረጋገጥ ለዚህም፡ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 32 መሰረት ወንጀል የተፈጸመበት ወይም በማስረጃነት የሚፈለግ ወይም የሚወረስ ዕቃ ብርበራዉ ሊደረግ በታሰበበት ቦታ ዉስጥ የተቀመጠ መሆኑን የሚያሳይ በቂ መረጃ ወይም ጥርጣሬ መኖሩን፤ ከሚመለከተዉ ፍርድ ቤት ብርበራዉ እንዲደረግ ትዕዛዝ ስለመሰጠቱ የሚያረጋግጥ የብርበራ ፍቃድ መኖሩን፤ እንዲሁም ያለብርበራ ትዕዛዝ የሚደረግ ከሆነም የብርበራ ትዕዛዝ ከፍርድ ቤት እስኪወጣ ዕቃዉ ይጠፋል ወይም አደጋ ይከሰታል ተብሎ በበቂ ሁኔታ ግምት የሚያስወስዱ ምክንያቶች ስለመኖራቸዉ፤ ብርበራዉ ከታሰበለት ዓላማ ዉጭ የተጠርጣሪዉን ወይም የሌላ ሰውን መብት ያልጣሰ መሆኑን ያረጋግጣል ሲሉ ብርበራ እና መያዝን በተመለከተ የዐቃቤ ህግ ምን እንደሚመስል ያብራራሉ፡፡
የኤግዚቢት አያያዝንና አቆያየትን በተመለከተ የዐቃቤ ህግ ሚና
ከፖሊስ ጋር በመሆን አንድ ንብረት በማስረጃነት ከመያዙ በፊት ንብረቱ ለወንጀል ምርመራው ወይም ለክሱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አስተዋፆ ያለዉ መሆኑን በማረጋገጥ፤ የማንኛውንም ኤግዚቢት ይዘት ወይም ባህሪ ለማወቅ በጣም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከተያዘዉ ንብረት ናሙና በመውሰድ በሚመለከተው አካል እንዲመረመር መመሪያ ዐቃቤ ሕጉ እንደሚሰጥ የገለጹት ዐቃቤ ሕጓ፤ የተያዘዉ ኤግዚቢት ከወንጀል ተግባሩ ጋር ተያያዥነት የሌለዉ ሆኖ ከተገኘ ንብረቱ ለባለንብረቱ እንዲመለስ መመሪያ በመስጠት የህጉን ተፈጻሚነት ያረጋግጣልም ብለዋል፡፡
ከዋስትና ጋር በተያያዘ የዐቃቤ ህግ ሚና
ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ ጋር በመሆን ተጠርጣሪ የተጠረጠረበት ወንጀል በወንጀል ሥነ-ሥርዐት ህጉ መሰረት ዋስትና የማያስከለክለው ከሆነ በዋስ እንዲለቀቅ በማድረግ፤ ዋስትና የሚያስከለክለው ከሆነ መርማሪ ፖሊስ በፍርድ ቤት ተገቢዉን ክርክር እንዲያደርግ ሊያሳዉቀዉ ወይም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፍርድ ቤት በመሄድ ተገቢውን ክርክር ሊያደርግ ይችላል ይላሉ፡፡ ዋስትና ማቅረብ ባልቻሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ህግ ምርመራው ተጠናቆ የምርመራ መዝገቡ በአስቸኳይ ውሳኔ እንዲያገኝ ጥረት ያደርጋል ያሉ ሲሆን ፖሊስ ከህግ ዉጭ በሆነ መንገድ ለተጠርጣሪ ዋስትና ከፈቀደ ወይም የዋስትና መብትን ከከለከለ ዐቃቤ ሕግ ድርጊቱ ስልጣንን አላግባብ መጠቀም በመሆኑ ለሚመለከተዉ አካል ምርመራ እንዲያጣራ በማሳወቅ አስፈላጊው እርምጃ እነዲወሰድ ያደርጋል ይላሉ፡፡
የምስክሮችን ቃል በመመርመርና በመመዘን ሂደት ውስጥ የዐቃቤ ህግ ሚና አጠራጣሪ፣
አሻሚና የሚጋጩ ማስረጃዎች ሲኖሩ ማስረጃዎቹን በድጋሚ አስቀርቦ የማጣራትና እንደ አስፈላጊነቱም ምስክሮች ተጨማሪ ቃል እንዲሰጡ በማድረግ ተጠርጣሪው እጅ ከፍንጅ ሳይሆን ከረጅም ጊዜ በኋላ በክትትል የተያዘ ከሆነ ተበዳይና ምስክሮች ተጠርጣሪውን ከሌሎች ሰዎች መሃል በአግባቡ የመረጡት ስለመሆኑና ተጨማሪ ቃላቸውን ስለመስጠታቸው ያረጋግጣል ሲሉ ዐቃቤ ህግ የምስክሮችን ቃል በመመርመርና በመመዘን ሂደት ያለውን ሚና ያብራራሉ ፡፡

========================
ዐቃቤህግ በመደበኛ የወንጀል ክስ ለመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ሲቀርብ ስለጉዳዩ በተለይም ስለምስክርነቱ አስቀድሞ ሳይዘጋጅ ማለትም ዕዉቀት ሳይኖረዉ ነዉ:: መስቀለኛ ጥያቄ ሂደት እንኳንስ ያለቅድመዝግጅት ዝግጅትም ተደርጎ አስቸጋሪ ሥራ ነዉ::
የመከላከያ ምስክሮች ከመዋሸት እስከ ሆን ብሎ አለማስታወስ ድረስ መሰናክል ሊፈጥሩ ይችላሉ:: በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደቱ ለዐቃቤህግ ተባባሪ ላይሆኑ ይችላሉ::
ስለዚህ ዐቃቤህግ በዚህ ሂደት ለማግኘት የሚፈልገዉን ምናልባትም ሊያገኝ የሚገባዉን ያለማግኘት ችግር ሊያጋጥመዉ ይችላል:: እንዲያዉም የራሱን ክስ ሊጎዳ የሚችል አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል::
ስለዚህ መስቀለኛ ጥያቄን ለማካሄድ ወይም ላለማካሄድ በከፍተኛ ጥንቃቄ መምረጥ አና ማካሄድ የግድ ነዉ:: ለዚህ ደግሞ አንዳንድ መርሆችንና ቴክኒኮችን ማወቅ ተገቢ ነዉ:: እነዚህ መርሆችና ቴክኒኮች በአሰራር ልማድ የምንፈጥራቸዉን ችግሮች ለማረም እገዛ ሊያደርጉ የሚችሉ ናቸዉ:: እነዚህን ቆየት ብለን የምናያቸዉ ሆኖ ከዚያ በፊት ስለመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ወሰን እና መጠን አንዳንድ ነገሮች እንይ::
በቅድሚያ ከላይ እንደተገለጸዉ መስቀለኛ ጥያቄ አስቸጋሪ ሂደት ነዉ:: አደጋዎቸ አሉት:: ስለዚህ መስቀለኛ ጥያቄ ማከሄድ ተመራጭ ላይሆን ይችላል:: መስቀለኛ ጥያቄ አለማካሄድ ምን ዉጤት አለዉ? በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 140 እንደተመለከተዉ መስቀለኛ ጥያቄ አለመጠየቅ በሌላዉ ወገን የተነገረዉን እንደማመን አያስቆጥርም:: ስለዚህ መስቀለኛ ጥያቄ ብዙም ባይደፈር ይመረጣል:: በተለይም የመስቀለኛ ጥያቄ ግብ ከሆኑት (የተቃራኒን ምስክርነት የማይታመን መሆኑን ማሳየት በክሱ ላይ የደረሰዉን ጉዳት ማስተካከል ወዘተ) አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ለማሳካት የምንችል ወይም ተገቢ ካልሆነ በቀር ወይም ምስክሩ ለጉዳያችን የምንፈልገዉ መረጃ ብቸኛ ምንጭ ካልሆነ በቀር መስቀለኛ ጥያቄ ማካሄድ የሚመከር አይደለም::
ሆኖም ዘወትር እንደሚስተዋለዉ አንዳንድ ምስክሮች ባህሪያቸዉ ምንም ሳይጠየቁ መሄድ የለባቸዉም የሚያስብል ይሆናል:: በዚህ ጊዜ መስቀለኛ ጥያቄ ማንሳት የግድ ከሆነ ከላይ ሲባል እንደነበረዉ አደጋዉ የበዛ በመሆኑ መጠኑን ማሳነስ ይመከራል::
በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 137(3) ስር መስቀለኛ ጥያቄ በዋና ጥያቄ ጊዜ በተመለሱ ነገሮች ዉስጥ ያለዉን ስህተት አጠራጣሪ ወይም የማይታመን ቃል ለፍርድ ቤቱ ለመግለጽ ወይም ለማስተባበል የሚደረግ መሆኑ ተደንግጓል:: ስለዚህ ከዚህ የወጣ ጥያቄ ሲነሳ ተቃዉሞ ሊገጥም ይችላል:: ሆኖም በዋና ጥያቄ ከተፈጠረዉ ድንበር ወጥቶ መጠየቅ የሚቻልባቸዉ የተለዩ አጋጣሚዎች ይኖራሉ:: ለምሳሌ የምስክሩን ተዓማኒነት የሚመለከቱ ጥያቄዎች በዋና ጥያቄ ጊዜ ባይነሱም በጠቅላላዉ ምስክሩ የተናገረዉን ነገር ተዓማኒነት የሚመለከት ስለሚሆን ተቀባይነት ያለዉ አካሄድ ነዉ:: ለምሳሌ የተለመደዉ የተከሳሽ መከላከያ ክርክር (በወንጀሉ ጊዜ በወንጀሉ ቦታ አልነበርኩም) ሲቀርብ የሚነገረዉ ታሪክ የተፈጸመበትን ጊዜ ከወንጀሉ ጊዜ ጋር እንዲገጥም የማድረግ ነገር ስለሚኖር ምስክሩ ጊዜን በመለየት ረገድ ስላለዉ ችሎታ ለማረጋገጥ በዚህ ዙሪያ ጥያቄ ቢነሳ ሊከለከል አይገባም:: ምስክሩ ተዓማኒነቱ ምን ያህል እንደሆነ ለማሳየት የሚረዳ በመሆኑ ተገቢ ነዉ::
ከተዓማኒነት ጋር በተያያዘ ምስክሩ በነገሩ ዉስጥ ያለዉ ጥቅም ወይም ፍላጎት ሊታለፍ የማይገባዉ ነጥብ ነዉ:: ምስክሩ የሚሰጠዉ ምስክርነት ከነገሩ ዉስጥ ካለዉ ጥቅም ወይም ፍላጎት የተነሳ ከዕዉነት የራቀ ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ በነገሩ ዉስጥ ጥቅም እንዳለዉ ማሳየት በሰጠዉ ምስክርነት ላይ ዕምነት እንዲታጣ ሊያደርግ ስለሚችል በዋና ጥያቄ አልተነሳም ተብሎ ቀሪ ሊደረግ አይገባም::
አንዳንዴ ምስክሩ ራሱ ለመስቀለኛ ጥያቄ በሚመልስበት ጊዜ በዋና ጥያቄ ጊዜ ላልተነሱ ሀሳቦች መንገድ ሊከፍት ይችላል:: በዚህ ጊዜ ምስክሩ ራሱ ባነሳዉ ነገር ላይ ሌላ መስቀለኛ ጥያቄ የማይጠየቅበት ምክንያት አይኖርም:: ስለዚህ ዐቃቤህግ እነዚህን አጋጣሚዎች በንቃት መጠባበቅ ይገባዋል፣ ለዚህም ምስክርነቱን በሚገባ ማዳመጥ ይኖርበታል፡፡
ከጭብጥ ከመዉጣት ሌላ በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት የማይፈቀድ ነገር ምስክርን ማስፈራራት እና ማንጓጠጥ ነዉ:: ምስክሩ ዐቃቤህግ የሚፈልገዉን እንዲል መገደድ የለበትም:: ይህን ማድረግ የሚቻለዉ ክህሎት በተሞላዉ የአጠያየቅ ዘዴ መሆን አለበት:: አዘዉትሮ በፍርድቤቶች በሚደረግ ክርክር ጊዜ የሚስተዋል በህግ ባለሙያዎች (ዐቃብያነህግ ጠበቆች ዳኞች) የሚባል አንድ ነገር አለ:: ምስክሩ እነዚህ ባለሙያዎች እንደፈለጉት ወይም ዕዉነት ነዉ ብለዉ እንደሚያስቡት ሳይናገር በቀረ ጊዜ በሃሰት መመስከር በወንጀል እንደሚያስቀጣ ይነግሩታል:: ይህ ነገር ማስፈራራት ከመሆኑ በተረፈ ነገሩ ተሰምቶ ሳያልቅ እና ምስክሩ የተናገረዉ ሃሰት ይሁን ዕዉነት ሳይረጋገጥ በጉዳዩም ላይ በምስክሩም ላይ ፍርድ የመስጠት ያህል ይሆናል:: ከዐቃቤህግ የህግ ጠባቂነት ሚና አኳያም የሰዉን መብት የሚደነግጉ ህጎችን የመጣስ ዉጤት ይኖረዋል::
የመስቀለኛ ጥያቄዎች ባህሪያት (መሪ ጥያቄ)፡-- ይህ የጥያቄ አይነት በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ዉስጥ በህግ የተፈቀደ ቢሆንም ዐቃቤህግ (ሌሎች ባለሙያዎችም) ሲጠቀሙበት አይስተዋልም:: በርግጥ ይህ የጥያቄ አይነት ስለሚያስከትለዉ መልስ ማወቅን ስለሚጠይቅና ዐቃቤህግ ደግሞ ከላይ እንደተገለጸዉ ያለቅድመዝግጅት ስለሚቀርብ ይህን የጥያቄ አይነት ለመጠቀም አይደፋፈርም:: ሆኖም ዋና ጥያቄ የሚመስል ሂደት በማካሄድ ነገሮችን እንዲደገሙ ከማድረግና በዚህም ችሎትን ከማሰላቸት ግፋ ሲልም የዐቃቤህግን ክስ የሚያፈርስ አጋጣሚ ከመፍጠር በዚያዉ በችሎት በተደረገች ዝግጅትም ቢሆን መሪ ጥያቄ በመጠየቅ ምስክሩን እንዳሻዉ እንዳይናገር መቆጣጠር ይመከራል:: በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ዋናዉ ግብ ምስክሩን መቆጣጠር የሚመሰክረዉን ነገር መወሰን በዚህም ለመዋሸት ያለዉን ዝንባሌ ወዘተ ማስቀረት ነዉ:: በዋና ጥያቄ ጊዜ ሊነሱ የሚገባቸዉ ዝግ ያልሆኑ ጥያቄዎችን በማንሳት ምስክሩ የሚናገረዉን ነገር ልቅ ማድረግ ሂደቱን ዐቃቤህጉ ሳይሆን ምስክሩ እንዲቆጣጠረዉ ማድረግ ይሆናል::
አጭርና ነጠላ ጥያቄ፡- የተከሳሽን ምስክር በመስቀለኛ ጥያቄ መቆጣጠር የሚቻልበት መንገድ ጥያቄዉን መሪ ጥያቄ በማድረግ ብቻ አይደለም:: ጥያቄዉን አጭር ማድረግም እንዲሁ በምስክሩ ላይ የበላይነትን ያስገኛል:: ጥያቄዉ ከአንድ በላይ ሃሳብ ከሌለዉ እና ርዝመቱም አጭር ከሆነ ምስክሩ ለዚሁ ብቻ መልስ እንዲሰጥ ሰለሚገደድ ብዙም መፈናፈኛ አይኖረዉም:: በተለይ ከአንድ በላይ ሃሳብ አለመያዙ ምስክሩ መርጦ የመመለስ ስራ እንዳይሰራ ያደርገዋል የመልሱ ወሰን የታጠረ ይሆናል::
ከዚህ በተያያዘ ከአንድ በላይ የሆኑ ጥያቄዎችን አነባብሮ በአንድ ጊዜ መጠየቅ የሚገኘዉን መልስ ግልጽ እንዳይሆን ያደርገዋል:: አንድ መልስ ቢሰጥ ለየትኛዉ ጥያቄ እንደተመለሰ ማወቅ አይቻልም:: ስለዚህ እንደዋና ጥያቄ ጊዜ በአንድ ጊዜ አንድ ጥያቄ ብቻ ማንሳት ተገቢ ይሆናል::
========================
ዐቃቤህግ በመደበኛ የወንጀል ክስ ለመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ሲቀርብ ስለጉዳዩ በተለይም ስለምስክርነቱ አስቀድሞ ሳይዘጋጅ ማለትም ዕዉቀት ሳይኖረዉ ነዉ:: መስቀለኛ ጥያቄ ሂደት እንኳንስ ያለቅድመዝግጅት ዝግጅትም ተደርጎ አስቸጋሪ ሥራ ነዉ::
የመከላከያ ምስክሮች ከመዋሸት እስከ ሆን ብሎ አለማስታወስ ድረስ መሰናክል ሊፈጥሩ ይችላሉ:: በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደቱ ለዐቃቤህግ ተባባሪ ላይሆኑ ይችላሉ::
ስለዚህ ዐቃቤህግ በዚህ ሂደት ለማግኘት የሚፈልገዉን ምናልባትም ሊያገኝ የሚገባዉን ያለማግኘት ችግር ሊያጋጥመዉ ይችላል:: እንዲያዉም የራሱን ክስ ሊጎዳ የሚችል አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል::
ስለዚህ መስቀለኛ ጥያቄን ለማካሄድ ወይም ላለማካሄድ በከፍተኛ ጥንቃቄ መምረጥ አና ማካሄድ የግድ ነዉ:: ለዚህ ደግሞ አንዳንድ መርሆችንና ቴክኒኮችን ማወቅ ተገቢ ነዉ:: እነዚህ መርሆችና ቴክኒኮች በአሰራር ልማድ የምንፈጥራቸዉን ችግሮች ለማረም እገዛ ሊያደርጉ የሚችሉ ናቸዉ:: እነዚህን ቆየት ብለን የምናያቸዉ ሆኖ ከዚያ በፊት ስለመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ወሰን እና መጠን አንዳንድ ነገሮች እንይ::
በቅድሚያ ከላይ እንደተገለጸዉ መስቀለኛ ጥያቄ አስቸጋሪ ሂደት ነዉ:: አደጋዎቸ አሉት:: ስለዚህ መስቀለኛ ጥያቄ ማከሄድ ተመራጭ ላይሆን ይችላል:: መስቀለኛ ጥያቄ አለማካሄድ ምን ዉጤት አለዉ? በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 140 እንደተመለከተዉ መስቀለኛ ጥያቄ አለመጠየቅ በሌላዉ ወገን የተነገረዉን እንደማመን አያስቆጥርም:: ስለዚህ መስቀለኛ ጥያቄ ብዙም ባይደፈር ይመረጣል:: በተለይም የመስቀለኛ ጥያቄ ግብ ከሆኑት (የተቃራኒን ምስክርነት የማይታመን መሆኑን ማሳየት በክሱ ላይ የደረሰዉን ጉዳት ማስተካከል ወዘተ) አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ለማሳካት የምንችል ወይም ተገቢ ካልሆነ በቀር ወይም ምስክሩ ለጉዳያችን የምንፈልገዉ መረጃ ብቸኛ ምንጭ ካልሆነ በቀር መስቀለኛ ጥያቄ ማካሄድ የሚመከር አይደለም::
ሆኖም ዘወትር እንደሚስተዋለዉ አንዳንድ ምስክሮች ባህሪያቸዉ ምንም ሳይጠየቁ መሄድ የለባቸዉም የሚያስብል ይሆናል:: በዚህ ጊዜ መስቀለኛ ጥያቄ ማንሳት የግድ ከሆነ ከላይ ሲባል እንደነበረዉ አደጋዉ የበዛ በመሆኑ መጠኑን ማሳነስ ይመከራል::
በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 137(3) ስር መስቀለኛ ጥያቄ በዋና ጥያቄ ጊዜ በተመለሱ ነገሮች ዉስጥ ያለዉን ስህተት አጠራጣሪ ወይም የማይታመን ቃል ለፍርድ ቤቱ ለመግለጽ ወይም ለማስተባበል የሚደረግ መሆኑ ተደንግጓል:: ስለዚህ ከዚህ የወጣ ጥያቄ ሲነሳ ተቃዉሞ ሊገጥም ይችላል:: ሆኖም በዋና ጥያቄ ከተፈጠረዉ ድንበር ወጥቶ መጠየቅ የሚቻልባቸዉ የተለዩ አጋጣሚዎች ይኖራሉ:: ለምሳሌ የምስክሩን ተዓማኒነት የሚመለከቱ ጥያቄዎች በዋና ጥያቄ ጊዜ ባይነሱም በጠቅላላዉ ምስክሩ የተናገረዉን ነገር ተዓማኒነት የሚመለከት ስለሚሆን ተቀባይነት ያለዉ አካሄድ ነዉ:: ለምሳሌ የተለመደዉ የተከሳሽ መከላከያ ክርክር (በወንጀሉ ጊዜ በወንጀሉ ቦታ አልነበርኩም) ሲቀርብ የሚነገረዉ ታሪክ የተፈጸመበትን ጊዜ ከወንጀሉ ጊዜ ጋር እንዲገጥም የማድረግ ነገር ስለሚኖር ምስክሩ ጊዜን በመለየት ረገድ ስላለዉ ችሎታ ለማረጋገጥ በዚህ ዙሪያ ጥያቄ ቢነሳ ሊከለከል አይገባም:: ምስክሩ ተዓማኒነቱ ምን ያህል እንደሆነ ለማሳየት የሚረዳ በመሆኑ ተገቢ ነዉ::
ከተዓማኒነት ጋር በተያያዘ ምስክሩ በነገሩ ዉስጥ ያለዉ ጥቅም ወይም ፍላጎት ሊታለፍ የማይገባዉ ነጥብ ነዉ:: ምስክሩ የሚሰጠዉ ምስክርነት ከነገሩ ዉስጥ ካለዉ ጥቅም ወይም ፍላጎት የተነሳ ከዕዉነት የራቀ ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ በነገሩ ዉስጥ ጥቅም እንዳለዉ ማሳየት በሰጠዉ ምስክርነት ላይ ዕምነት እንዲታጣ ሊያደርግ ስለሚችል በዋና ጥያቄ አልተነሳም ተብሎ ቀሪ ሊደረግ አይገባም::
አንዳንዴ ምስክሩ ራሱ ለመስቀለኛ ጥያቄ በሚመልስበት ጊዜ በዋና ጥያቄ ጊዜ ላልተነሱ ሀሳቦች መንገድ ሊከፍት ይችላል:: በዚህ ጊዜ ምስክሩ ራሱ ባነሳዉ ነገር ላይ ሌላ መስቀለኛ ጥያቄ የማይጠየቅበት ምክንያት አይኖርም:: ስለዚህ ዐቃቤህግ እነዚህን አጋጣሚዎች በንቃት መጠባበቅ ይገባዋል፣ ለዚህም ምስክርነቱን በሚገባ ማዳመጥ ይኖርበታል፡፡
ከጭብጥ ከመዉጣት ሌላ በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት የማይፈቀድ ነገር ምስክርን ማስፈራራት እና ማንጓጠጥ ነዉ:: ምስክሩ ዐቃቤህግ የሚፈልገዉን እንዲል መገደድ የለበትም:: ይህን ማድረግ የሚቻለዉ ክህሎት በተሞላዉ የአጠያየቅ ዘዴ መሆን አለበት:: አዘዉትሮ በፍርድቤቶች በሚደረግ ክርክር ጊዜ የሚስተዋል በህግ ባለሙያዎች (ዐቃብያነህግ ጠበቆች ዳኞች) የሚባል አንድ ነገር አለ:: ምስክሩ እነዚህ ባለሙያዎች እንደፈለጉት ወይም ዕዉነት ነዉ ብለዉ እንደሚያስቡት ሳይናገር በቀረ ጊዜ በሃሰት መመስከር በወንጀል እንደሚያስቀጣ ይነግሩታል:: ይህ ነገር ማስፈራራት ከመሆኑ በተረፈ ነገሩ ተሰምቶ ሳያልቅ እና ምስክሩ የተናገረዉ ሃሰት ይሁን ዕዉነት ሳይረጋገጥ በጉዳዩም ላይ በምስክሩም ላይ ፍርድ የመስጠት ያህል ይሆናል:: ከዐቃቤህግ የህግ ጠባቂነት ሚና አኳያም የሰዉን መብት የሚደነግጉ ህጎችን የመጣስ ዉጤት ይኖረዋል::
የመስቀለኛ ጥያቄዎች ባህሪያት (መሪ ጥያቄ)፡-- ይህ የጥያቄ አይነት በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ዉስጥ በህግ የተፈቀደ ቢሆንም ዐቃቤህግ (ሌሎች ባለሙያዎችም) ሲጠቀሙበት አይስተዋልም:: በርግጥ ይህ የጥያቄ አይነት ስለሚያስከትለዉ መልስ ማወቅን ስለሚጠይቅና ዐቃቤህግ ደግሞ ከላይ እንደተገለጸዉ ያለቅድመዝግጅት ስለሚቀርብ ይህን የጥያቄ አይነት ለመጠቀም አይደፋፈርም:: ሆኖም ዋና ጥያቄ የሚመስል ሂደት በማካሄድ ነገሮችን እንዲደገሙ ከማድረግና በዚህም ችሎትን ከማሰላቸት ግፋ ሲልም የዐቃቤህግን ክስ የሚያፈርስ አጋጣሚ ከመፍጠር በዚያዉ በችሎት በተደረገች ዝግጅትም ቢሆን መሪ ጥያቄ በመጠየቅ ምስክሩን እንዳሻዉ እንዳይናገር መቆጣጠር ይመከራል:: በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ዋናዉ ግብ ምስክሩን መቆጣጠር የሚመሰክረዉን ነገር መወሰን በዚህም ለመዋሸት ያለዉን ዝንባሌ ወዘተ ማስቀረት ነዉ:: በዋና ጥያቄ ጊዜ ሊነሱ የሚገባቸዉ ዝግ ያልሆኑ ጥያቄዎችን በማንሳት ምስክሩ የሚናገረዉን ነገር ልቅ ማድረግ ሂደቱን ዐቃቤህጉ ሳይሆን ምስክሩ እንዲቆጣጠረዉ ማድረግ ይሆናል::
አጭርና ነጠላ ጥያቄ፡- የተከሳሽን ምስክር በመስቀለኛ ጥያቄ መቆጣጠር የሚቻልበት መንገድ ጥያቄዉን መሪ ጥያቄ በማድረግ ብቻ አይደለም:: ጥያቄዉን አጭር ማድረግም እንዲሁ በምስክሩ ላይ የበላይነትን ያስገኛል:: ጥያቄዉ ከአንድ በላይ ሃሳብ ከሌለዉ እና ርዝመቱም አጭር ከሆነ ምስክሩ ለዚሁ ብቻ መልስ እንዲሰጥ ሰለሚገደድ ብዙም መፈናፈኛ አይኖረዉም:: በተለይ ከአንድ በላይ ሃሳብ አለመያዙ ምስክሩ መርጦ የመመለስ ስራ እንዳይሰራ ያደርገዋል የመልሱ ወሰን የታጠረ ይሆናል::
ከዚህ በተያያዘ ከአንድ በላይ የሆኑ ጥያቄዎችን አነባብሮ በአንድ ጊዜ መጠየቅ የሚገኘዉን መልስ ግልጽ እንዳይሆን ያደርገዋል:: አንድ መልስ ቢሰጥ ለየትኛዉ ጥያቄ እንደተመለሰ ማወቅ አይቻልም:: ስለዚህ እንደዋና ጥያቄ ጊዜ በአንድ ጊዜ አንድ ጥያቄ ብቻ ማንሳት ተገቢ ይሆናል::
መልሱ የሚታወቅ (የሚረጋገጥ) ጥያቄ፡- የመስቀለኛ ጥያቄ መልሱ የሚታወቅ ወይም ማስረጃ ሊቀርብበት የሚችል መሆን ይኖርበታል:: ግን ቀደም ሲል እንደተገለጸዉ ትልቁ ችግር ስለመከላከያ ምስክርነትም ሆነ ስለምስክሩ አስቀድሞ የሚሰበሰብ ማስረጃ የለም:: ስለዚህ የዐቃቤህግ መስቀለኛ ጥያቄዎች በዕድል ባወጣ ያዉጣዉ ወዘተ ላይ ተመስርተዉ የሚጠየቁ ናቸዉ:: ሆኖም ማስረጃ በተሰበሰበባቸዉ አጋጣሚዎች ለምስክሩ የሚቀርብ መስቀለኛ ጥያቄ ሊመለስ የሚገባዉን መልስ የሚጠቁም ሊሆን ይገባል:: ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠዉ መልስ ምንም ይሁን ምን በቂ ስለሚሆን የሚገኘዉ መልስ ምንነት ስጋት አይፈጥርም:: የሚፈለገዉን መልስ ምስክሩ አመነም አላመነም ዉጤቱን አይቀይረዉም:: ምክንያቱም ቢያምን ዐቃቤህግ እንደሚፈልገዉ ሆነለት ማለት ሲሆን ከካደ ደግሞ ማስረጃ ስላለ ምስክርነቱን ማስተባበልና በዚህም ምስክሩ ተዓማኒነት የሌለዉ መሆኑን ማሳየት ይቻላል::
የመስቀለኛ ጥያቄዎች አደረጃጀት፡- ዉጤታማ መስቀለኛ ጥያቄ በጥያቄዎች አይነት ብቻ የሚወሰን አይደለም:: የጥያቄዎቹ ቅደም ተከተልም (ቅንብር) የራሱ አስተወጽዖ ይኖረዋል:: በተለይ በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ ምስክሩን በሚገባ መቆጣጠር እጅግ አስፈላጊ ከመሆኑ አኳያ የጥያቄዎቻችን አወቃቀር ይህን የመቆጣጠር ችሎታ የሚያሳጣ መሆን የለበትም:: ስለዚህ የተቃራኒ ወገንን ምስክር የምንጠይቅ እንደመሆኑ በቀላሉ የምንፈልገዉን ነገር ለማግኘት አስቸጋሪ ስለሚሆን የጥያቄዎቻችን አወቃቀር የምስክሩን ወዳጅነት የሚያስገኝ እንዲሆን የግድ ነዉ::
ዐቃቤህግ መስቀለኛ ጥያቄ ሊጠይቅ ከወሰነ በዚህ ጥያቄ ሊያሳካ የፈለገዉን ነገር በሂደቱ መጀመሪያ ላይ መግለጽ የለበትም:: ይህ ግብ በምስክሩ ከታወቀ የተቃራኒ ወገን ምስክር እንደመሆኑ የመስቀለኛ ጥያቄዉ ሂደት ወደዚህ ግብ እንዲደርስ መፍቀዱ አጠራጣሪ ነዉ:: ስለዚህ ይህን ግብ የሚደብቅ የጥያቄዎች ቅደምተከተል መኖር አለበት::
ከዚህ የተነሳ በመነሻዉ ላይ የሚጠየቁ ጥያቄዎች ከምስክሩ ጋር ፍጥጫን የማያስነሱ ምስክሩ በቀላሉ ሊያምናቸዉ ወይም ሊስማማባቸዉ የሚችሉ ፍሬነገሮችን የሚመለከቱ መሆን ይገባቸዋል:: ይህን ማድረግ በዐቃቤህጉና በተከሳሽ ምስክር መካከል ሰላማዊ ሁኔታ ይፈጥራል:: ስለዚህ ከምስክሩ የሚፈለገዉን ለማግኘት ቀላል ይሆናል ቢያንስ ምስክሩ መሰናክሎችን ከመፍጠር ይታቀባል::
ይህ ማለት ደግሞ ዐቃቤህግ ለክሱ እጅግ አስፈላጊ የሚላቸዉን ነጥቦች መጀመሪያ ላይ ማንሳት የለበትም ማለት ነዉ:: እነዚህን ጉዳዮች ከመነሻዉ ከገለጸ ምስክሩ የመስቀለኛ ጥያቄዉን ዓላማ በቀላሉ ማወቅ ስለሚችል እና ይህም ምስክሩ በዋና ጥያቄ ጊዜ ከተናገረዉ ሊቃረን ስለሚችል ምስክሩ ይህን የተፈለገ ነገር ለመስጠት አይፈቅድም:: በሚችለዉ መንገድ ራሱን ከመቃረን ለማዳን የማስተካከያ መረጃዎችን ከመግለጽ ያለፈ ነገር ለመፈጸም ፈቃደኛ እንዳይሆን ያደርገዋል:: ስለዚህ ዐቃቤህግ መነሻዉ ላይ ከዋና ጥያቄ ሂደት በተቃራኒ ዋና ነጥቦችን ሳይሆን ዝርዝር ጉዳዮችን (በተቻለ መጠን ምስክሩ የማይክዳቸዉን) እንዲያነሳ ይመከራል::
ከዚህ ሌላ ዐቃቤህግ የመስቀለኛ ጥያቄ ዓላማዉን ለመደበቅ በጥያቄና መልሱ ሂደት ጊዜ ከአንድ የጥያቄ ሃሳብ ወደሌላዉ በመዝለል ምስክሩ የነገሩን አቅጣጫ እንዳይገነዘብ ማድረግ ይችላል:: ለዚህም ጥያቄዎቹ በተለያየ ርዕስ ስር እንዲደራጁ ሊያደርግ ይገባል:: ከዚህ ጋር በተያያዘ የአካባቢ ማስረጃን አስመልክቶ ከዋና ጥያቄ ጋር በማያያዝ ያነሳነዉ ሃሳብ ለመስቀለኛ ጥያቄም አግባብነት ይኖረዋል:: በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ ዓላማዉ ምስክሩ የዐቃቤህግን የክርክር አቅጣጫ እንዳይገነዘብ ማደረግ በመሆኑ የአካባቢ ማስረጃን የሚመለከቱ ጥያቄዎች እነዚህን ማስረጃዎቸ በአንድ ላይ የማሰባሰብ ባህሪ እንዳይኖራቸዉ ማድረግ ያስፈልጋል:: ምክንያቱም ከተሰባሰቡ ትርጉማቸዉ ግልጽ ስለሚሆን ምስክሩ የክርክሩን አቅጣጫ በቀላሉ እንዲረዳዉ በማድረግ መሰናክል እንዲፈጥር ይገፋፋዋል:: ስለዚህ መስቀለኛ ጥያቄዎች የአካባቢ ማስረጃዎች እንዲበታተኑ የማድረግ ችሎታ ሊኖራቸዉ ይገባል:: ለዚህም ከላይ እንደተመከለተዉ የጥያቄዎችን ቅድም ተከተለ በማዘባረቅ ከርዕስ ወደርዕስ መዟዟር አስፈለጊ ነዉ::
ከጥያቄዎች ቅደም ተከተል ጋር በተያያዘ አዘዉትሮ የሚታይ ስህተት አለ:: በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ ምስክሩ ሊክዳቸዉ የማይችሉ ፍሬነገሮችን መሰረት በማድረግ ዐቃቤህግ ለሚያቀርባቸዉ ጥያቄዎች በሚገኙ መልሶች የሚገነባ ታሪክ ሊኖር ይችላል:: ከዚህ በኋላ የዚህን ሁሉ ጥያቄና መልስ እንድምታ (ድምዳሜ) ምስክሩ እንዲናገር ከተጠየቀ መልሱ የተከሳሹን ክርክር የሚጎዳ ከመሰለዉ ወይም ከሆነ ምስክሩ የጥያቄዉ አቅጣጫ ሰለሚገባዉ ቀደም ሲል የሰጣቸዉን መልሶች የሚያስተካክል መልስ ሊሰጥ ስለዚህ ለክሱ የሚረዳዉን ነገር የመደበቅ ተግባር ሊፈጽም ይችላል:: ይህም እንኳ ባይሆን ተከሳሹ ወይም ጠበቃዉ በክርክሩ ላይ በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ የደረሰዉን ጉዳት በድጋሚ ጥያቄ ጊዜ የማስተካከል ስራ እንዲሰራ የማባነን ዉጤት ይኖረዋል:: ይህም ካልሆነ ፍርድቤቱ ራሱ በማጣሪያ ጥያቄ ጊዜ ነገሩን እንዲያነሳ ምስክሩም በዚህ አጋጣሚ ነገሩን የሚያድበሰብስ ወይም የሚያርም ተግባር እንዲፈጽም የማስታወስ ዉጤት ይኖረዋል:: በተግባር ሲደረግ የሚስተዋለዉም እንዲህ ያለ ዉጤትን የሚያመጣ አጠያየቅ ነዉ::
ስለዚህ ይህን የነገሩን ማሰሪያ ጥያቄ ዐቃቤህግ መጠየቅ የለበትም:: ቀላልና ተራ በሚመስሉ ጥያቄዎች የተገነባዉ ታሪክ እንድምታ ለፍርድቤቱ የሚተዉ ነዉ:: ምናልባት ለፍርድቤቱ ግልጽ የማይሆን ቢሆን በመስቀለኛ ጥያቄ የተሰጡ መልሶች የሚጠቁሙት ድምዳሜ ምን እንደሆነ በክርክር ማቆሚያ ንግግር ጊዜ መግለጽ ይቻላል::
ነገር ግን አሁን ባለዉ አሰራር ይህ ከላይ የተመለከተዉ የአሰራር አቅጣጫ ምን ያህል ያስኬዳል? የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነዉ:: ምክንያቱም የክርክር መዝጊያ ንግግር ወይም በተለምዶ አጠራሩ የመፋረጃ ሃሳብ እንዲቀርብ የሚያደፋፍሩ ፍርድቤቶች ጥቂት ከመሆናቸዉም በላይ እንዲቀርብ የሚያደርጉትም ቢሆኑ በአብዛኛዉ በጽሁፍ እንዲቀርብ የሚያደርጉ ሰለሆነ እንዲሁም የቀረበዉን ሃሳብ የሚጠቀሙበት ማለትም በዉሳኔ ጊዜ ከግምት የሚያስገቡት ፍርድቤቶች በእጀጉ ጥቂት በመሆናቸዉ ዐቃቤህግ በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ ያስመሰከራቸዉ ፍሬነገሮች ድምር ዉጤት ምን እንደሆነ በክርክሩ ጊዜ (በመስቀለኛ ጥያቄ ማጠናቀቂያ ጊዜ) ካልጠቆመ እንዲህ የሚያደርግበት መድረክ አያገኝም:: ከዚህ የተነሳ ዐቃቤህግ ከተከሳሽ ምስክር ጋር በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ዉስጥ ወይም ማሳረጊያ ላይ የምስክርነቱን እንድምታ እመን አትመን እሰጥ አገባ ዉስጥ ሲገባ ይታያል:: ስለዚህ ፍርድቤቶች የክርክር ማቆሚያ ንግግርን አሰራር እንዲያከብሩ ዐቃቤህግ መወትወት ዳኞችም ይህን አሰራር ባህል እንዲያደርጉት የግድ ነዉ::
ከዚህ በላይ ያየናቸዉ የጥያቄ አደረጃጀት ስራዎች ብቸኛ አይደሉም:: በርከት ያሉ በተለያዩ በለሙያዎች የሚቀርቡ ዘዴዎች አሉ:: ሆኖም ከላይ ያነሳናቸዉ ዘዴዎች ከኛ የአሰራር ልምድ ጋር ቁርኝት ስላላቸዉ ሊጠቀሱ በቅተዋል::
የመስቀለኛ ጥያቄዎች አደረጃጀት፡- ዉጤታማ መስቀለኛ ጥያቄ በጥያቄዎች አይነት ብቻ የሚወሰን አይደለም:: የጥያቄዎቹ ቅደም ተከተልም (ቅንብር) የራሱ አስተወጽዖ ይኖረዋል:: በተለይ በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ ምስክሩን በሚገባ መቆጣጠር እጅግ አስፈላጊ ከመሆኑ አኳያ የጥያቄዎቻችን አወቃቀር ይህን የመቆጣጠር ችሎታ የሚያሳጣ መሆን የለበትም:: ስለዚህ የተቃራኒ ወገንን ምስክር የምንጠይቅ እንደመሆኑ በቀላሉ የምንፈልገዉን ነገር ለማግኘት አስቸጋሪ ስለሚሆን የጥያቄዎቻችን አወቃቀር የምስክሩን ወዳጅነት የሚያስገኝ እንዲሆን የግድ ነዉ::
ዐቃቤህግ መስቀለኛ ጥያቄ ሊጠይቅ ከወሰነ በዚህ ጥያቄ ሊያሳካ የፈለገዉን ነገር በሂደቱ መጀመሪያ ላይ መግለጽ የለበትም:: ይህ ግብ በምስክሩ ከታወቀ የተቃራኒ ወገን ምስክር እንደመሆኑ የመስቀለኛ ጥያቄዉ ሂደት ወደዚህ ግብ እንዲደርስ መፍቀዱ አጠራጣሪ ነዉ:: ስለዚህ ይህን ግብ የሚደብቅ የጥያቄዎች ቅደምተከተል መኖር አለበት::
ከዚህ የተነሳ በመነሻዉ ላይ የሚጠየቁ ጥያቄዎች ከምስክሩ ጋር ፍጥጫን የማያስነሱ ምስክሩ በቀላሉ ሊያምናቸዉ ወይም ሊስማማባቸዉ የሚችሉ ፍሬነገሮችን የሚመለከቱ መሆን ይገባቸዋል:: ይህን ማድረግ በዐቃቤህጉና በተከሳሽ ምስክር መካከል ሰላማዊ ሁኔታ ይፈጥራል:: ስለዚህ ከምስክሩ የሚፈለገዉን ለማግኘት ቀላል ይሆናል ቢያንስ ምስክሩ መሰናክሎችን ከመፍጠር ይታቀባል::
ይህ ማለት ደግሞ ዐቃቤህግ ለክሱ እጅግ አስፈላጊ የሚላቸዉን ነጥቦች መጀመሪያ ላይ ማንሳት የለበትም ማለት ነዉ:: እነዚህን ጉዳዮች ከመነሻዉ ከገለጸ ምስክሩ የመስቀለኛ ጥያቄዉን ዓላማ በቀላሉ ማወቅ ስለሚችል እና ይህም ምስክሩ በዋና ጥያቄ ጊዜ ከተናገረዉ ሊቃረን ስለሚችል ምስክሩ ይህን የተፈለገ ነገር ለመስጠት አይፈቅድም:: በሚችለዉ መንገድ ራሱን ከመቃረን ለማዳን የማስተካከያ መረጃዎችን ከመግለጽ ያለፈ ነገር ለመፈጸም ፈቃደኛ እንዳይሆን ያደርገዋል:: ስለዚህ ዐቃቤህግ መነሻዉ ላይ ከዋና ጥያቄ ሂደት በተቃራኒ ዋና ነጥቦችን ሳይሆን ዝርዝር ጉዳዮችን (በተቻለ መጠን ምስክሩ የማይክዳቸዉን) እንዲያነሳ ይመከራል::
ከዚህ ሌላ ዐቃቤህግ የመስቀለኛ ጥያቄ ዓላማዉን ለመደበቅ በጥያቄና መልሱ ሂደት ጊዜ ከአንድ የጥያቄ ሃሳብ ወደሌላዉ በመዝለል ምስክሩ የነገሩን አቅጣጫ እንዳይገነዘብ ማድረግ ይችላል:: ለዚህም ጥያቄዎቹ በተለያየ ርዕስ ስር እንዲደራጁ ሊያደርግ ይገባል:: ከዚህ ጋር በተያያዘ የአካባቢ ማስረጃን አስመልክቶ ከዋና ጥያቄ ጋር በማያያዝ ያነሳነዉ ሃሳብ ለመስቀለኛ ጥያቄም አግባብነት ይኖረዋል:: በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ ዓላማዉ ምስክሩ የዐቃቤህግን የክርክር አቅጣጫ እንዳይገነዘብ ማደረግ በመሆኑ የአካባቢ ማስረጃን የሚመለከቱ ጥያቄዎች እነዚህን ማስረጃዎቸ በአንድ ላይ የማሰባሰብ ባህሪ እንዳይኖራቸዉ ማድረግ ያስፈልጋል:: ምክንያቱም ከተሰባሰቡ ትርጉማቸዉ ግልጽ ስለሚሆን ምስክሩ የክርክሩን አቅጣጫ በቀላሉ እንዲረዳዉ በማድረግ መሰናክል እንዲፈጥር ይገፋፋዋል:: ስለዚህ መስቀለኛ ጥያቄዎች የአካባቢ ማስረጃዎች እንዲበታተኑ የማድረግ ችሎታ ሊኖራቸዉ ይገባል:: ለዚህም ከላይ እንደተመከለተዉ የጥያቄዎችን ቅድም ተከተለ በማዘባረቅ ከርዕስ ወደርዕስ መዟዟር አስፈለጊ ነዉ::
ከጥያቄዎች ቅደም ተከተል ጋር በተያያዘ አዘዉትሮ የሚታይ ስህተት አለ:: በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ ምስክሩ ሊክዳቸዉ የማይችሉ ፍሬነገሮችን መሰረት በማድረግ ዐቃቤህግ ለሚያቀርባቸዉ ጥያቄዎች በሚገኙ መልሶች የሚገነባ ታሪክ ሊኖር ይችላል:: ከዚህ በኋላ የዚህን ሁሉ ጥያቄና መልስ እንድምታ (ድምዳሜ) ምስክሩ እንዲናገር ከተጠየቀ መልሱ የተከሳሹን ክርክር የሚጎዳ ከመሰለዉ ወይም ከሆነ ምስክሩ የጥያቄዉ አቅጣጫ ሰለሚገባዉ ቀደም ሲል የሰጣቸዉን መልሶች የሚያስተካክል መልስ ሊሰጥ ስለዚህ ለክሱ የሚረዳዉን ነገር የመደበቅ ተግባር ሊፈጽም ይችላል:: ይህም እንኳ ባይሆን ተከሳሹ ወይም ጠበቃዉ በክርክሩ ላይ በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ የደረሰዉን ጉዳት በድጋሚ ጥያቄ ጊዜ የማስተካከል ስራ እንዲሰራ የማባነን ዉጤት ይኖረዋል:: ይህም ካልሆነ ፍርድቤቱ ራሱ በማጣሪያ ጥያቄ ጊዜ ነገሩን እንዲያነሳ ምስክሩም በዚህ አጋጣሚ ነገሩን የሚያድበሰብስ ወይም የሚያርም ተግባር እንዲፈጽም የማስታወስ ዉጤት ይኖረዋል:: በተግባር ሲደረግ የሚስተዋለዉም እንዲህ ያለ ዉጤትን የሚያመጣ አጠያየቅ ነዉ::
ስለዚህ ይህን የነገሩን ማሰሪያ ጥያቄ ዐቃቤህግ መጠየቅ የለበትም:: ቀላልና ተራ በሚመስሉ ጥያቄዎች የተገነባዉ ታሪክ እንድምታ ለፍርድቤቱ የሚተዉ ነዉ:: ምናልባት ለፍርድቤቱ ግልጽ የማይሆን ቢሆን በመስቀለኛ ጥያቄ የተሰጡ መልሶች የሚጠቁሙት ድምዳሜ ምን እንደሆነ በክርክር ማቆሚያ ንግግር ጊዜ መግለጽ ይቻላል::
ነገር ግን አሁን ባለዉ አሰራር ይህ ከላይ የተመለከተዉ የአሰራር አቅጣጫ ምን ያህል ያስኬዳል? የሚል ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነዉ:: ምክንያቱም የክርክር መዝጊያ ንግግር ወይም በተለምዶ አጠራሩ የመፋረጃ ሃሳብ እንዲቀርብ የሚያደፋፍሩ ፍርድቤቶች ጥቂት ከመሆናቸዉም በላይ እንዲቀርብ የሚያደርጉትም ቢሆኑ በአብዛኛዉ በጽሁፍ እንዲቀርብ የሚያደርጉ ሰለሆነ እንዲሁም የቀረበዉን ሃሳብ የሚጠቀሙበት ማለትም በዉሳኔ ጊዜ ከግምት የሚያስገቡት ፍርድቤቶች በእጀጉ ጥቂት በመሆናቸዉ ዐቃቤህግ በመስቀለኛ ጥያቄ ጊዜ ያስመሰከራቸዉ ፍሬነገሮች ድምር ዉጤት ምን እንደሆነ በክርክሩ ጊዜ (በመስቀለኛ ጥያቄ ማጠናቀቂያ ጊዜ) ካልጠቆመ እንዲህ የሚያደርግበት መድረክ አያገኝም:: ከዚህ የተነሳ ዐቃቤህግ ከተከሳሽ ምስክር ጋር በመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት ዉስጥ ወይም ማሳረጊያ ላይ የምስክርነቱን እንድምታ እመን አትመን እሰጥ አገባ ዉስጥ ሲገባ ይታያል:: ስለዚህ ፍርድቤቶች የክርክር ማቆሚያ ንግግርን አሰራር እንዲያከብሩ ዐቃቤህግ መወትወት ዳኞችም ይህን አሰራር ባህል እንዲያደርጉት የግድ ነዉ::
ከዚህ በላይ ያየናቸዉ የጥያቄ አደረጃጀት ስራዎች ብቸኛ አይደሉም:: በርከት ያሉ በተለያዩ በለሙያዎች የሚቀርቡ ዘዴዎች አሉ:: ሆኖም ከላይ ያነሳናቸዉ ዘዴዎች ከኛ የአሰራር ልምድ ጋር ቁርኝት ስላላቸዉ ሊጠቀሱ በቅተዋል::
አሳሳቢው ወንጀል እና የአዲስ አበባ የራይድ ሹፌሮች
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በራይድ ታክሲ የትራንስፓርት አገልግሎት በሚሰጡ ሹፌሮች ላይ የሚፈፀም ግድያንና የከባድ ውንብድና ወንጀልን በተመለከተ የተጣሩ የምርመራ መዛግብትን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ
በራይድና በሌሎች የትራንስፓርት አገልግሎት ድርጅቶች አማካኝነት የሚሰጡ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ለከተማው ማህበረሰብ ቀልጣፋ የሆነ ትራንስፖርት በመስጠት የከተማውን ማህበረሰብ ችግር በመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል፡፡
አገልግሎቱ በትራንስፓርት ዘርፉ ከሚሰጠው ጥቅም ባሻገር ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት በዚህ ዘርፍ ተሰማርተው ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን በሚደግፉ አሽከርካሪዎች ላይ በተለያየ ጊዜ አሰቃቂ #ወንጀሎች ተፈጽመዋል፡፡
ወንጀሎቹ ከተፈፀሙበት ጊዜ ጀምሮ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ከተሰጠው ስልጣንና ተግባር አኳያ፤ በተቋሙ የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ በርካታ የወንጀል ምርመራዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በቅርቡም ከነሀሴ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከዐቃቤ ህግና ከመርማሪ ፖሊሶች የተውጣጣ የጋራ ቡድን በማዋቀር 9 የምርመራ መዝገቦችን በማደራጀት ጥልቅ የሆነ ምርመራ ሲደረግ ቆይቷል፡፡
በምርመራ ግኝቱ ማረጋገጥ እንደተቻለውም በራይድ የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ሹፌሮች ላይ የወንጀል ተግባሩን የሚፈፅሙት የውንብድና ቡድኑ አባላት አብዛኛውን ጊዜ ወንጀሉን ከመፈፀማቸው በፊት የትራንስፖርት አገልግሎት ፈላጊ በመምሰል፣ መልካም ግንኙነት በመፍጠር ተበዳይ በሆኑት ሹፌሮች ላይ እምነት እንዲያድርባቸው ካደረጉ በኋላ አብዛኛውን ጊዜ ከአዲስ አበባ ወደ ዝዋይ መስመር በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ ከተሞች የትራንስፓርት አገልግሎት እንዲሰጣቸው ያደርጋሉ፤ በኋላም አገልግሎቱን ወደ ሚያገኙበት አካባቢ ሹፌሮቹን በመውሰድ እና በአንዳንድ ሁኔታዎችም አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ ራቅ ወዳሉና ሰዎች ወደማይበዙባቸው ቦታዎች በምሽት በመውሰድ ሹፌሮቹን ለሽንት አቁምልን በማለት ካስቆሙ በኋላ ወንጀሉን የሚፈጽሙ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡
የምርመራ ግኝቱ እንደሚያመላክተው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡትን አሽከርካሪዎች በጋራ በመሆን በስለት በመውጋት፣ በገመድ አንገታቸውን በማነቅና በሽጉጥ ተኩሰው #በመግደል #አስክሬናቸውን በመጣል ተሽከርካሪዎቹንና ሌሎች ንብረቶችን እንደሚወስዱ ተረጋግጧል፡፡
በቡድን የተደራጁ የወንበዴ ቡድኖች በሹፌሮቹ ላይ ጥቃት በመሰንዘር የሚያሽከረክሩትን ተሽከርካሪና ሌሎች ንብረቶች ከወሰዱ በኋላ የወሰዱትን ተሽከርካሪ በዝቅተኛ ዋጋ ያለምንም ህጋዊ ሰነድ በመግዛት አይነታቸውን በመቀየር፣ ታርጋ በመለጠፍ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሌላ የተደራጀ ቡድን መኖሩም በምርመራ ተረጋግጧል፡፡ የምርመራ ቡድኑ በዚህ የውንብድና ቡድን ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹን ወንጀል ፈፃሚዎንና በውንብድና ተግባር የተወሰዱ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
ምርመራቸው በተጠናቀቁና ክስ በተመሰረተባቸው መዝገቦች ላይ እንደታየው ቡድኑ ሶስት የሚሆኑ ሰዎችን በመግደል ሟቾች ሲያሽከረክሩት የነበሩትን ተሽከርካሪና ሌሎች ንብረቶችን የወሰዱ ሲሆን በዚህም ሂደት ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ህይወት ጠፍቷል፡፡ በተመሳሳይም በሌሎች ምርመራቸው በሂደት ላይ ባሉ መዝገቦችም ንብረት ከመዘረፉ ባለፈ የሰው ህይወት መጥፋቱ ተረጋግጧል፡፡
የምርመራ ቡድኑ ባደረገው እልህ አስጨራሽና ጠንካራ ምርመራ በዚህ የወንበዴ ቡድን ውስጥ ሆነው ወንጀሉን በተደራጀ ሁኔታ ሲፈፅሙ የነበሩ ሰዎችን በመያዝ ከተደራጀው 9 የምርመራ መዝገቦች ውስጥ 6 መዝገቦችን በማጠናቀቅ በ12 ተከሳሾች ላይ እስከ ሞት ፍርድ ድረስ በሚያስቀጣ በከባድ የውንብድና ወንጀልና በህገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል ክስ የተመሰረተ ሲሆን በቀጣይም ምርመራቸው እየተከናወኑ በሚገኙ መዝገቦች ላይ ጥልቅ ምርመራ በማድረግ አጥፊዎችን በህግ የማስጠየቅ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በራይድና በሌሎች ድርጅቶች አማካኝነት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሹፌሮች በቡድን በመሆን አገልግሎት በሚጠይቁ ሰዎች ላይ #ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡
አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜም ስለደንበኛው ሙሉ መረጃ መጠየቅና መያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ ውጭ ወይም አዲስ አበባ ውስጥም ሆኖ ጭር ወዳለ ቦታ አገልግሎት በሚጠይቁ ሰዎች ላይ አጠራጣሪ ሁኔታ ካዩባቸው ለጥንቃቄ የሚረዱ ተግባራትን በመፈፀም፣ በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላቶች መረጃዎችን በመስጠት፤ በተደጋጋሚ እንደሚታየውም አገልግሎት በመስጠት ሂደት የተለየ ግንኙነት የሚፈጥሩ ደንበኞች ላይ ትውውቅ አለን በሚል መዘናጋት መፈጠር የሌለበት መሆኑን እና መሰል ክስተቶችም ሲያጋጥሙ ማህበረሰቡ አገልግሎቱን ለሚሰጡ ሹፌሮች ድጋፍ እንዲያደርግና ለፀጥታ አካላት መረጃ በመስጠት የዘውትር ትብብር እንዲያደርግ ስንል እንጠይቃለን፡፡
የፕሬስ መግለጫ
ከፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ
https://t.me/lawsocieties
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Please #Share በማድረግ ሂይወትን እንታደግ 🙏
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👉

የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር
ዜጎች ሠላምና ደህንነታቸው ተጠብቆ መብትና ነጻነታቸው ተከብሮ የመኖር መብት አላቸው፡፡ የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ማስጠበቅ እንዲሁም የዜጎችን መብትና ደህንነት ማስከበር የመንግስት ዋነኛ ሃላፊነት ነው፡፡ ከሰላምና ደህንነት ጋር በተያያዘ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም የሚነሳ እንደመሆኑ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን የሚመለከቱ የህግ ማዕቀፎች መኖር አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ በሀገራችን የጦር መሳሪያ አያያዝ የሚመራበትን የህግ አግባብ እንዲሁም በአጥፊዎች ላይ ያለውን የህግ ተጠያቂነት እንዳስሳለን፡፡
የጦር መሳሪያ ምንነት
የጦር መሳሪያ ማለት በአስነሺ ኃይል የሚፈነዳ ወይም በፍንዳታ ኃይል ጥይትን፣ አረርን፣ ቦምብን፣ ፈንጂን፣ ሚሳይልን፣ ሮኬትን እና ማናቸውም ተተኳሽ ነገር በማስፈንጠር በሕይወት፣ በአካል ወይም በንብረት ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል መሳሪያ ሲሆን ጥይትን እና ተያያዥነት ያላቸውን አባሪዎችን የሚጨመር መሆኑን አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አንቀጽ 2(2) ሥር ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡ አባሪዎችን የተባሉት የመሳሪያ መያዣን፣ ማንገቻን፣ መለዋወጫ፣ ማፅጃ፣ መጠገኛ እንዲሁም የጥይት መያዣ መጋዘን ወዘተ የሚጨምር ነው፡፡ በሌላ በኩል አዋጁ በአንቀፅ 2(13) ስር ከጦር መሳሪያ ውጪ ላሉ ጉዳት አድራሽ ዕቃዎች ትርጓሜ የሰጠ ሲሆን ይህም በስለታማነታቸው ምክንያት ወይም የኤሌክትሪክ ሀይል በመጠቀም ወይም መርዛማ በመሆናቸው በሰው አካልና ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ እንደ ሳንጃ፣ ገጀራ፣ሜንጫ፣ ጦር፣ ቀስት ጎራዴ፣ ሴንጢ እና መሰል መሳሪያዎችን የሚያጠቃልል እንደሆነ ከአዋጁ መረዳት ይቻላል፡፡
የጦር መሳሪያ የሚሰጥበት አግባብና ይዘቱ
👆👆👆
በግለሰብ ደረጃ የሚያዙ የጦር መሳሪያዎች ለመያዘ የፀና ፍቃድ ያስፈልጋል፡፡ ዜጎች የጦር መሳሪያ ፍቃድ ከማግኘታቸዉ በፊት የተለያዩ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለዉ ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ የመኖር ፍቃድ ያለው መሆን፣ የአደገኛ ዕፅ ወይም የመጠጥ ሱስ የሌለበት መሆን፣ በፍርድ ቤት ውሳኔ ወይም በህግ ችሎታውን ያላጣ ሰው መሆን፣ የተስተካከለ አእምሮ ያለው ወይም የሐይል አጠቃቀም ባህሪ የሌለው መሆኑ በተቆጣጣሪ ተቋም የታመነበት መሆን፣ የመሳሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ ስልጠና እንዲወስድ ሲጠየቅ ፍቃደኛ መሆን፣ ለጦር መሳሪያ ፍቃድና እድሳት አስፈላጊውን ክፍያ መክፈል፣ መልካም ሥነ ምግባር ያለው ለመሆኑ ከሚኖርበት አካባቢ አስተዳደር የትብብር ደብዳቤ ማቅረብ መቻል ወዘተ በአዋጁ የተጠቀሱ መስፈርቶች ናቸው፡፡
የተጠቀሱትን መስፈርቶች ለሚያሟላ ሰው የሚሰጠው የጦር መሳሪያ ፍቃድ የባለፈቃዱን ሰው ሙሉ ስም፣ ፎቶ፣ የትውልድ ቀን፣ አሻራ፣ አድራሻ፣ የጦር መሳሪያውን አይነት፣ የውግ ቁጥር፣ የጥይት ብዛት፣ ተዛማጅ እቃ፣ ፍቃዱን የሰጠው ባለስልጣን ስም፣ ፊርማ፣ ማህተም፣ ፍቃደ የተሰጠበት ቀን እና ፍቃድ የሚያበቃበት ቀን እንዲሁም ሌሎች ተቆጣጣሪው ተቋም በመመሪያ የሚያወጣቸውን መስፈርቶችን የሚያካትት መሆን አለበት፡፡ ይህም ያስፈለገበት መሰረታዊ ዓላማ በፍቃድ ተቀባዩም ሆነ ሰጪዉ ላይ የህግ ተጣያቂነት ለማስፈን እንዲሁም የተደራጀ መረጃ መያዝ ወንጀልን በመከላልም ረገድ ጠቃሚ በመሆኑ ነው፡፡
የጦር መሳሪያ አጠቃቀምንና አያያዝን አስመልክቶ የተከለከሉ ተግባራት
ማንኛውም ሰው የፀና ፍቃድ ሳይኖረው የጦር መሳሪያ፣ አባሪ እቃዎችን እና ለልማት ሥራ የሚውሉትን ሳይጨምር የጉዳት አድራሽ እቃዎችን ወደ ሀገር ማስገባት፣ ከሀገር ማስወጣት፣ መያዝ፣ ማስቀመጥ፣ ማከማቸት፣ መገልገል፣ ማሳየት፣ መደለል፣ መሸጥ፣ መግዛት፣ ማስተላለፍ፣ ማዘዋወር፣ ማጓጓዝና ማምረት የተከለከሉ ተግባራት ናቸው፡፡ በተጨማሪም በአምራቹ ወይም በተቆጣጣሪ ተቋም የተሰጠ የጦር መሳሪያ የውግ ቁጥርን በሙሉ ወይም በከፊል መቀየር፣ ማጥፋት ወይም በማናቸውም አይነት ሁኔታ ተለይተው እንዳይታወቁ ማድረግ እንዲሁም የጦር መሳሪያን ወይም የጦር መሳሪያን የተመለከተ አገልግሎት ማስተዋወቅ የተከለከለ ነው፡፡
በሌላ በኩል አያያዝን በተመለከተ ሰላማዊ ሰልፍ ወይም አድማ በሚደረግባቸው ስፍራዎች፣ የምርጫ ሥራዎች የሚከናወኑበት ቦታዎች፣ በሆቴሎች፣ በሲኒማና ትያትር ቤቶች፣ በሙዚየሞችና ተመሳሳይ በሆኑ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች፣ በትምህርት፣ በሀይማኖትና እምነት ተቋማት ግቢ ውስጥ፣ በሆስፒታሎችና ክልኒኮች፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የህዝብ አገልግልት በሚሰጥባቸው ስፍራዎች፣ ፓርኮች ወይም በዱር እንስሳት መጠለያዎች ወዘተ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ተግባር ነው፡፡
በተያያዘም የጦር መሳሪያ ፍቃድ የተሰጠው ሰዉ ፈቃድ ከተሰጠው ክልል ውጪ ባሉ የክልልና ትላልቅ ከተሞች ለሕዝብ በሚታይ መልኩ ታጥቆ መንቀሳቀስ አይችልም፡፡ ሆኖም በሥራ ላይ ላሉ የህግ አስከባሪዎች ለስራቸዉ አላማ የጦር መሳሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ የተፈቀደ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፈቃድ ተሰጠው ሰው በአዋጁ አንቀፅ 18 ሥር የተመለከቱት ግዴታዎች ያሉበት ሲሆን ለአብነትም የጦር መሳሪያውን ይዞ የሚንቀሳቀስ ሰው የፍቃድ ወረቀቱን አብሮ መያዝ የሚጠበቅበት ከመሆኑም በተጨማሪ መሳሪያው ሲበላሽ፣ ሲጠፋ፣ ሲሰረቅ፣ ሲቀማ ወይም በማንኛውም ምክንያት ከቁጥጥሩ ውጪ ሲሆን በ15 ቀናት ውስጥ ለተቆጣጣሪው ተቋም ማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡
የጦር መሳሪያ ፍቃድ ስለሚታደስበት፣ ስለሚታገድበት፣ ስለሚሰረዝበት እና ስለሚወረስበት አግባብ
በአዋጅ አንቀጽ 13፣ 14 እና 15 መሰረት የጦር መሳሪያ ፍቃድ የተሰጠው ማንኛውም ሰው የፍቃድ አገልግሎት ጊዜው ከማብቃቱ ከ60 ቀናት በፊት የእድሳት ጥያቄውን ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወይም ውክልና ለተሰሠጠው የክልል ፖሊስ ኮሚሸን ተቋም ማቅረብ አለበት፡፡ ነገር ግን ጥያቄው ቀርቦ ተቆጣጣሪው ተቋም የእድሳት ጥያቄው ላይ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የቀድሞው ፍቃድ እንደፀና ይቆያል፡፡ ፍቃድ የተሰጠው ሰው ያቀረባቸው ማስረጃዎች አጠራጣሪ ሆነው ሲገኙና ጉዳዩን ማጣራት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ ከተሰጠው ፍቃድ ውጭ መሳሪያውን ለሌላ ተግባር ያዋለው ስለመሆኑ በቂ ጥርጣሬ ሲኖር እንዲሁም የአገልግሎት ጊዜው ያበቃና ያልታደሰ ከሆነ ፈቃዱ ይታገዳል፡፡ ነገር ግን ባለፈቃዱ በ60 ቀናት ውስጥ በቂ ምክንያት አቅርቦ ማስታካከል ከቻለ እግዱ ይነሳለታል፡፡ ነገር ግን ማስታካከል ካልቻለ የጦር መሳሪያው በተቆጣጣሪ ተቋሙ ይወረሳል፡፡
በተጨማሪም መሣሪያው ወንጀል የተፈጸመበት ስለመሆኑ በፍርድ ቤት ሲረጋገጥ፣ ባለፍቃዱ ሲሞት፣ ያለበት አድራሻ ሳይታወቅ ሲቀር ወይም በፍርድ ወይም በህግ ችልታውን ሲያጣ፣ ፈቃድ የተሰጠው ድርጅት ከሆነ ድርጅቱ ከፈረሰ ወይም ከተዘጋ፣ በራሱ ፍላጎት ፍቃዱን ሲመለስ፣ ፍቃዱን ለማግኘት ከሚያስፈለጉ መስፈርቶች አንዱ የተጓደለ ከሆነ፣ ሀሰተኛ ማስረጃ ያቀረበ መሆኑ ሲታወቅ እንዲሁም መሳሪያ ከተበላሸና ሊጠገን የማይቻል ከሆነ ፈቃዱ ተሰርዞ ይወረሳል፡፡
የወንጀል ተጠያቂነት
በጦር መሳሪያ መነገድ ወንጀል በሚመለከት የወንጀል ህግ አንቀፅ 481 ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ ከላይ የተመለከተውን ክልከላ እና ግዴታ በመተላለፍ የፀና ፈቃድ ሳይኖረው የጦር መሳሪያ ወደ ሀገር ካስገባ፣ ከሀገር ካስወጣ፣ ካስቀመጠ፣ ከተገለገለ፣ ከደለለ፣ ከገዛ፣ ከሸጠ፣ ካጓጓዘ፣ ካመረተ…ወዘተ ከ1 እስከ 3 አመት በሚደርስ ቀላል እስራት እና ከ5,000 እስከ 10,000 በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡

በፍትሐብሔር ክርክር የፍርድ ቤት መጥሪያ ደርሶት በቀነ ቀጠሮ ተከራካሪ ወገኖች አለመቅረብ ህጋዊ አንድምታው ምን ይመስላል?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ፍርድ ቤት አንድ ጉዳይ ማየት እና ውሳኔ ለማስተላለፍ የተለያዩ ቀጠሮዎች እንደሚሰጥ የታወቀ ነው፡፡ የመጀመሪያ ተከሳሽ መከሰሱን አውቆ ለቀረበበት ክስ መከላከያ የሚሆኑ ማስረጃዎችን በፅሁፍ የሚያቀርብበት ነው፡፡ ፍርድ ቤት ተከሳሽ መጥሪያው በአግባቡ ደርሶት መልሱን ይዞ ከቀረበ ፍርድ ቤቱ በስነ-ስርዓት ህጉ 241 እና ተከታዮቹ መሰረት ክሱን ለመስማት ይቀጥራል፡፡
ክስ ለመስማት ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ቀጠሮ ሁለተኛ ቀጠሮ ነው፡፡ በስነ-ስርዓት ህጉ 241 እና ተከታዮቹ መሰረት ክስ መስማት ሁለት ሂደቶችን የያዘ ነው፤ የመጀመሪያው ስለ መጀመሪያ ክስ መስማት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ስለዋናው ክስ መስማት ነው፡፡ የመጀመሪያው ክስ መስማት ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለዋና ክስ መስማት የሚያዘጋጅበት ሂደት ሲሆን፤ ፍርድ ቤት የቀረበውን ክስን እና የተከሳሽን መልስ የሚያነብበት፣ የግራ ቀኙን አቋም የሚሰማበት፣ ተቀዳሚ መቃወሚያ ላይ ብይን የሚሰጥበትና ጭብጥ የሚመሠርትበት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ዋና ክስ መስማት ሂደት ማለትም የተከራካሪ ወገኖችን ክርክር መስማት፣ ምስክሮችን መስማት እና ማስረጃዎችን መርመር እንዲሁም የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥበት ሂደት ነው፡፡.
ከሳሽ ወይም ተከሳሽ በየትኛው ቀነ ቀጠሮ መቅረባቸው እጅግ አስፈላጊ ነው? በሁሉም ቀጠሮዎች ወይስ መከላከያ ማስረጃ በሚቀርበበት ወይስ ክስ በሚሰማበት? ወደሚሉት ነጥቦች ስንገባ በእርግጥ ተከራካሪ ወገኖች እራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው ፍርድ ቤት በሚወስነው በማንኛውም ቀጠሮ ቀን ፍርድ ቤት መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በቀጠሮዎች አለመገኘት የክስ መዝገብ መዘጋት፣ የመከለከያ ማስረጃ የማቀረብና የመከላከል መብትን ማጣት እና ሌሎች ተከራካሪ ወገኖች ቢቀርቡ ሊቀሩ የሚችሉ ትዕዛዞች እንዲሰጡ ይሆናል፡፡
በፍትሐብሔር የሥነ-ሥርዓት ሕጉ እንዲሁም ሰበር በተለያዩ መዝገቦች የሰጣቸውን ውሳኔዎች (ለምሳሌ በመዝገብ ቁጥር 14184፣ 15835፣ 36412፣ 36390፣ 58487 እና 95638) ስንመለከት ለመልስ በተቀጠረበት ቀጠሮ የከሳሽም ሆነ የተከሳሽ አለመገኘት መዝገብ እንዲዘጋ ወይም ክርክሩ ተከሳሽ በሌለበት እንዲታይም የማድረግ ውጤት አይኖረውም፡፡ ከሳሹ ወይም መጥሪያ እንዲያደርስ ታዞ የነበረው አካል ማድረሱን ወይም አለማድረሱን እንዲያረጋግጥ መጥሪያ በመላክ ወይም በሌላ ማንኛውም ዘዴ ማረጋገጥ አለበት፡፡ ተከሳሹ የደረሰው መሆኑን ካረጋገጠ የመጀመሪያ ክስ ለመስማት ቀጠሮ መስጠት የሚችል ሲሆን ተከሳሹ ካልደረሰው ደግሞ ድጋሚ መጥሪያ ለተከሳሹ መላክ ይኖርበታል፡፡
በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ህጉ አንቀጽ 69 መሰረት ፍርድ ቤቱ ቃል/ጉዳዩ ሊሰማ (hearing of suit) በወስነው ቀነ ቀጠሮ ከሳሽ (ክስ ያቀረበው) እና ተከሳሽ ራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው መቅረብ አለባቸው (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 69) ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ ሊሰማ በተወሰነበት ቀነ ቀጠሮ አለመቅረብ የሚያስከትለው ውጤት እንደ ቀሪው ተከራካሪ ወገን ይወሰናል፡፡ ሁለቱም ተከራካሪዎች ሳይቀርቡ ሲቀር፣ ከሳሽ ሲቀር እና ተከሳሽ ሲቀር ተፈጻሚ የሚሆነው ሥርዓት የተለያየ ነው፡፡
ሁለቱም ወገኖች ሳይቀርቡ የቀሩ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ይዘጋዋል፡፡ ከሳሽ በቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ ተከሳሽ ቀርቦ የቀረበበትን ክስ የካደ ከሆነ መዝገቡን በመዝጋት ተከሳሽን ያሰናብተዋል (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 73)፤ ሆኖም ግን ከሳሽ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በቀዳሚ ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረበትን በቂ ምክንያት ገልጾ መዝገቡ እንዲታይ አቤቱታ ካቀረበ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሽ የከሳሽ አቤቱታ እንዲደርሰው በማድረግ መዝገቡን እንደገና ከፍቶ ነገሩ እንዲቀጥል ትዕዛዝ በመስጠት ጉዳዩ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ይወስናል፡፡
ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ ሊሰማ በተወሰነበት ቀነ ቀጠሮ ከሳሽ ቀርቦ ተከሳሽ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ የፍርድ ቤቱ ቀዳሚ ስራ መጥሪያው ለተከሳሹ መድረሱን ማረጋገጥ ነው (ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 70)፡፡ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሽ የላከው መጥሪያ የደረሰው መሆኑን ካረጋገጠ በሌለበት ጉዳዩን መስማት ይቀጥላል፡፡ መጥሪያው ለተከሳሽ በአግባቡ ያልደሰረው መሆኑን ካረጋገጠ ወይም አጠራጣሪ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ሁለተኛ መጥሪያ እንዲላክ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ተከሳሽ መጥሪያው የደረሰው መሆኑ ቢረጋገጥ እንኳን ለተከሳሹ የተሰጠበት ቀን ለክሱ መልስ ለማዘጋጀት በቂ ሆኖ በማይገመት አጭር ጊዜ መሆኑን ፍርድ ቤቱ የተረዳው ከሆነ ፍርድ ቤቱ የክርክሩን መሰማት ለሌላ ቀነ ቀጠሮ ያስተላልፈዋል፡፡ አንድ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ተከሳሾች የተላከው መጥሪያ ለአንዱ ወይም ለአንዳንዶች ሳይደርስ የቀረው በከሳሽ ቸልተኘነት ወይም ጉደለት ከሆነ ፍርድ ቤቱ ከሳሽ መጥሪያ ባልደረሰው ወይም ባልደረሳቸው ተከሳሾች ላይ የቀረበውን ክስ ሊዘጋ ወይም ቀነ ቀጠሮ ሊቀይር ይችላል፡፡
ክርክሩ በሌለበት እንዲቀጥል የተወሰነበት ተከሳሽ በቀጣይ ቀነ ቀጠሮ ቀርቦ በቂ በሆነ ምክንያት በመጀመሪው ቀነ ቀጠሮ ያለመቅረቡን ካስረዳ መከላከያውን አቅርቦ የመከራከር መብት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 72 ይደነግጋል፡፡ እንዲሁም ክርክሩ ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን ቀርቦ መልስ ሳይሰጥ ወይም መከራከሪያውን ሳያሰማ በሌለበት ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ መሰጠቱን ካወቀ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተከሳሽ መጥሪያው በሚገባ ያልደረሰው መሆኑን ወይም በቂ ምክንያት በማቅረብ ትዕዛዙ ወይም ውሳኔው እንዲነሳለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 78 መሰረት መጠየቅ ይችላል፡፡ በዚሁ ድንጋጌ መሰረትም ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ያቀረበውን አቤቱታ አግባብ መሆኑን ከተረዳ ለከሳሽ አቤቱታው እንዲደርሰው በማድረግ ትዕዛዙን ወይም ውሳኔውን በማንሳት ክርክሩን እንደገና ስምቶ ይወስናል፡፡
ሆኖም በቂ ምክንያት ምንድን ነው? የሚለው ነጥብ አከራካሪ ሊሆን ይችላል፡፡ የቀረበው ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑ እንደ ጉዳዩ ዓይነት የሚታይ በመሆኑ አንድ ዓይነት ትርጉም መስጠት አይቻልም፡፡ ነገር ግን የተከራካሪ ወገኖች በእኩል የመዳኘት መብት እንዲሁም ተከሳሽ ለቀረበበት ክስ የበኩሉን መልስ የመስጠት መብቱ፤ የመሰማት መሠረታዊ መብት (The right to be heard) ይበልጥ ሊያስከብር በሚችል ሁኔታ መተርጎም አለበት፡፡ እንዲሁም የስነ ስርዓት ህጉ ዓላማን ፍትሐዊ በሆነ ስርዓት በአጭር ጊዜ፣ በአነስተኛ ውጪ እና ድግግሞሽን ባስቀረ ሁኔታ የተከራካሪ ወገኖችን ጉዳይ መቋጨትን በሚያሳካ መልኩ መተርጓም አለበት፡፡
ሳሙኤል ግርማ
ሕግ ባለሙያ እና ጠበቃ

#Update
በፎፌክስ ትሬዲንግ ስም የሚያታልሉ ግለሰቦችንና ቡድኖችን በህግ ተጠያቂ ማድረግ እንደሚቻል ተገለፀ።
በፎሬክስ ትሬዲንግ የኦንላይን ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን" የሚል የፌስቡክና የቴሌግራም ማስታወቂያ በሚያስነግሩ የተደራጁ ቡድኖች የተጭበረበሩ ሰዎችን አስመልክቶ ቲክቫህ ተከታታይ ዘገባ መስራቱ ይታወሳል።
ጉዳዩን አስመልክቶ የሚመለከተውን አካል ያነጋገርን ሲሆን ፥ በዚህ ጉዳይ ወንጀል ተፈፅሞብኛል የሚሉ ግለሰቦች የሚያቀርቡትን ጥቆማና መረጃ ተከትሎ ከህግ አካላት እና ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ጉዳዩን እንደሚያጣሩ የኢትዮጵያ ፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የህዝብ ግንኙነትና የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለ አሰፋ ለቲክቫህ ገልፀዋል።
አቶ እንዳለ በፎሬክስ ትሬዲንግ የማጭበርበር ድርጊት ጉዳይ እስካሁን ጥቆማ ለመስሪያ ቤቱ እንዳልደረሰ የገለፁ ሲሆን "ወንጀል ተፈፅሞብኛል" የሚሉ ሰዎች በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ምርመራ ክፍል ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው በማሳሰብ ፥ በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤት በኩል የሚፈለገው እገዛ ለፖሊስ እንደሚሰጥ አስረድተዋል።
ይህን መሰል የማታለል ድርጊት በህግ እንዴት ይታያል?
ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ያናገርናቸው ጠበቃ እና የህግ አማካሪ እንዲሁም በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት አቶ እሱባለው አማረ የወንጀል ድርጊቱ ፈርጀ ብዙ የህግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ገልፀዋል።
ጠበቃ እና የህግ አማካሪው አቶ እሱባለው ድርጊቱ በንብረት መብት (property right) ላይ ከሚፈፀም ወንጀል ጋር እንደሚያዝ ያስረዱ ሲሆን በዋናነት በንብረት ላይ ሊፈፀም ከሚችሉ ወንጀሎች ተብለው በወንጀል ህጋችን ከተጠቀሱት መሃከል በ"አታላይነት" ወንጀል እንደሚያስጠይቅ ለቲክቫህ ገልፀዋል።
"አታላይነት" በወንጀል ህጉ ከአንቀፅ 692 ጀምሮ ሽፋን እንደተሰጠው የገለፁት የህግ መምህሩ ፥ "ማታለልን ያካተቱ ወንጀሎች" በሚል ንዑስ ስር ያለ የዚህ ድንጋጌ ንዑስ አንቀፅ 1 "ማንም ሰው የማይገባ ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ አሳሳች የሆኑ ነገሮችን በመናገር፣ የራሱን ማንነት ወይም ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለጽ የሚገባውን ነገር በመደበቅ ወይም የሌላውን ሰው የተሳሳተ እምነት ወይም ግምት በመጠቀም፣ በማድረግም ሆነ ባለማድረግ ሌላውን ሰው አታልሎ የራሱን ወይም የሶስተኛ ወገንን የንብረት ጥቅም የሚጎዳ አድራጎት እንዲፈፀም ያደረገ እንደሆነ የአታላይነት ወንጀል እንደተፈፀመ ያስቀምጣል" ሲሉ አስረድተዋል።
ይህ የወንጀል ድርጊት በቀላል እስራት ወይም
እንደነገሩ ከባድነት ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት እና የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለ አሰፋ በፎሬክስ ስም የማታለል ወንጀል ተፈፅሞብኛል የሚሉ ሰዎች ወይም በጉዳዩ ላይ አጠራጣሪ ነገሮችን የተመለከቱ ግለሰቦች ፖሊስ ጋር ከመሄድ ባሻገር ለተቋሙ በስልክ ቁጥር +251-11-812-8261 ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉ በማስረዳት ፥ ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር ክትትል እንደሚደረግ ገልፀዋል።
በኦላይን የሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመጠቆም @tikvahmagbot ይጠቀሙ።
በጉዳዩ ላይ ለመወያየት https://t.me/tikvahforum/22079 ላይ ሀሳቦትን ያካፍሉን።
👋 @TikvahethMagazine

Forwarded from ሕግ ቤት
ከህግ ትምህርት ቤት መሠረታዊ ትሩፋቶች ጥቂቶቹ
*****
ምንጭ ወ/ሮ ትብለጥ ቡሽራ Tiblet Bushra
**
የህግ ትምህርት ቤት በአንድ ወገን ብቻ የተነገረ ታሪክ ወይም ፍሬ ነገር ሁሌም ጎዶሎ እንደሆነ ያስተምርሀል፡፡ በምንም ጉዳይ አቋም ከመውሰድህ፣ ከመፍረድህ፣ አስተያየት ከመስጠትህ በፊት ሙሉ ታሪኩን ማወቅ በመርህ ደረጃ እንደቅድመ ሁኔታ ያስቀምጥብሀል ”There is always the other side of a story” ብለህ እንድታስብ ያስገድድሀል፡፡ ከዛ ውጪ የሚደረስ ድምዳሜ ትክክለኛ ያልሆነ ወይም የተዛባ፣ ያዳለ፣ ፍትሀዊነት የጎደለው ነው፡፡ ይህ አይነት አስተሳሰብ እንዲኖርህ የሚጠበቀው ደግሞ እጅህ ላይ በመጡ የህግ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆን በአገራዊ ጉዳዮች፣ በግለሰቦች ጉዳዮች በምትሰማቸው ከአንድ ወገን የሚነገሩ ታሪኮች፣ ውሳኔዎችም ጭምር ነው፡፡
የህግ ትምህርት ቤት ለሀሳቦች ክፍት መሆንን (Open mindedness) ያስተምርሀል፡፡ እውነት ወይም ሀሰት ፈተና ቀርቦልህ ለአንድ ጥያቄ እውነትም ብለህ 10/10 ሀሰትም ብለህ 10/10 ልታገኝ ትችላለህ ልታጣም ትችላለህ፡፡ ለመልስህ እንዳቀረብከው የክርክር ነጥብ ጥንካሬ እና ምክኒያታዊነት፡፡ በዚህ አንተ ከያዝከው ሀሳብ የተለየ ሀሳብ ይዞ አሳማኝ ምክኒያት ለሚያቀርብልህ እጅ መስጠት እና የራስን ሀሳብ በምክኒያት መተው ሽንፈት እንዳልሆነ ያስተምርሀል፡፡
የህግ ትምህርት ቤት የሀሳብ ነጻነት ጠቀሜታን፣ የሀሳብ ነጻነት ማክበርን ወይም ለሌሎች እይታ ዋጋ መስጠትን ያስተምርሀል፡፡ በአንድ አከራካሪ ጉዳይ ላይ አስተማሪህ የያዘውን አቋም እያወክ ይህን ጉዳይ በፈተና መልክ ሲያመጣው ካስተማሪው የተለየው የራስህን አቋም በምክኒያት አስደግፈህ ካቀረብክ ከኔ አቋም ውጪ አቋም ኖረው ብሎ ዜሮ አይሰጥህም፡፡ ካንተ ጋር ባይስማማም እንደ መከራከሪያ ነጥቦችህ ጥንካሬ እና ምኪኒያታዊነት ከፍ ያለ ማርክ ሊሰጥህም ይችላል፡፡ ይህን ሲያረግ ከኔ ብትለይም ያንተን ሀሳብ አከብራለሁ፣ ዋጋ እሰጠዋለሁ፣ አቋሜን እያወክ የራስህን አቋም ማስቀመጥህን እንደንቀት አላየውም እንደጥንካሬ፣ እንደ እሴት ጭማሪ አየዋለሁ እንጂ የሚል ትምህርት ያስተምርሀል፡፡
የህግ ትምህርት ቤት ስለ “ጥርጣሬ ተጠቃሚ” “benefit of doubt” ጽንሰ ሀሳብ ሲያስተምርህ ይህን ጽንሰ ሀሳብ ከወንጀል ጉዳዮች በዘለለ በሌሎች ጉዳዮችም እንድትተገብረው ጥበብን (wisdom) ያስተምርሀል፡፡ ስለሆነ ሰው ወይም ጉዳይ የማትገምተው አይነት ነገር ስትሰማ “እውነት ላይሆን ይችላል” “ከሚመስለው ውጪ ሊሆን ይችላል እውነቱ” “ምናልባት ይሄን እንዲያደርግ ያስቻለው አስገዳጅ ሁኔታ ሊኖር እኮ ይችላል” እና የመሳሰሉ ሌላ ከሚኖሩ አጠራጣሪ ነገሮች ለመጠቀም የሚያስችለው ሁኔታዎችን ከግምት ማስገባትን ሊጨምር ይችላል፡፡
የህግ ትምህርት ቤት በመርህ ደረጃ በጭፍን መታዘዝ (blind obedience) ልክ አለመሆኑን ያስተምራል፡፡ ለአለቃ መታዘዝ አንደኛው የስነ-ምግባር ግዴታ ቢሆንም ህገ-ወጥ የሆነ ትእዛዝን አለመቀበል መብትህ ሳይሆን ግዴታህ አርጎ ያስተምርሀል፡፡ ይህ ትምህርት እና አመክኒዮው ደሞ ለሌሎች ጉዳዮችም እንድትጠቀመው ትምህርት ይሆንሀል፡፡
የህግ ትምህርት ቤት ስለሰው ልጆች ክቡርነት፣ እኩልነት፣ ነጻነት… እያስተማረህ ትህትናን/ humility፣ በምንም ሁኔታ ላይ ብትሆን አንተ ከማንም እንደማታንስ ከማንም እንደማትበልጥም ያስተምርሀል ወይ ደግሞ ያስታውስሀል።
የህግ ትምህርት ቤት ባህል፣ ወግ፣ ሀይማኖት፣ ማንነት በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ወይም በግለሰቦች ውስጥ ያለውን ቦታ ያንን ችላ ያለ ምንም ነገር ዘለቄታ እንደማይኖረው ያስተምራል፡፡ በዛው ልክ ጎጂ የሆኑ ባህላዊ ድርጊቶችን ለመቀየር ወይም አዲስ ባህልን ለመፍጠር (to set Norm or standards) ሕግ ያለውን ኃይል ያሳይሀል
የህግ ትምህርት ቤት የህግ የበላይነትን መጠበቅ ወይም ማስጠበቅ ለሁላችንም የጋራ ሰላም፣ ደህንነት እና ጥቅም፣ ዋስትና መሆኑን ፈትፍቶ ያስተምርሀል፡፡
Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ሊፈጠር የሚችለውን ቅሬታ ስለማንሳት/ ይፋ ስለማድረግ፡ የውጭ አገር ዜጎችን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት እና ባለይዞታ ሊያደርግ ይችላል በተባለው ረቂቅ አዋጅ ላይ ጥቂት እይታዎች
1. አሁን ያለው የሕግ ሥርዓት (የቀድሞው ሕግ - የፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጾች 390-393)
አጠቃላይ መርህ፡ ገደብ ከሌለ በቀር የውጭ ዜጎች በፍትሃ ብሔር መብቶቸ፣ የመስራትና የመጠቀም መብቶችን በሚመለከት ረገድ እንደ ኢትዮጵያውያን የሚቆጠሩ መሆኑን ተድንግጎ ይገኛል፡፡ (አንቀጽ 389(1)) ።
መሰረታዊ ገደቦች፡- በ‹ንጉሰ ነገስቱ ትእዛዝ› በግልፅ ካልተፈቀደ በስተቀር የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብት ሊሆን እንደማይችል በአንቀጽ 390 ስር የተቀመጠውን ድንጋግይ በግልፅ ይከለክላል (ይህም ከንጉሠ ነገሥቱ በኋላ በነበረው ዘመን ከመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን ይሁንታ ወይም ድንጋጌ ጋር ይዛመዳል) ።
ማስፈጸሚያ፡- የውጭ አገር ዜጎች ሰዎች ንብረቱን ያለፍቃድ ካገኙ በኋላ በስድስት ወራት ውስጥ ለኢትዮጵያዊው መሸጥ ይጠበቅባቸው ነበር፣ ምንም እንኳን በቅን ልቦና ቢያደርጉም፣ ለምሳሌ በውርስ (አንቀጽ 391) ። ይህን ያለማድረግ ንብረቱ በመንግስት ባለስልጣኖች ጠያቂነት ተይዞ በግዳጅ ሽያጭ ለኢትዮጵያዊ እንዲተላለፍ የሚደረግ መሆኑ ይህ ተግባር ላስከተለው ወጪና ደንብ መተላለፍ ደግሞ የሽያጩ 20% የገንዘብ ቅጣት የሚጣል ስለመሆኑ ተደንግጎ ይገኛል፡፡(አንቀጽ 392(1) እና (2))።
የተፈፃሚነት ወሰን፡- ከሙሉ የባለቤትነት መብት በተጨማሪ እነዚህ ገደቦች ከባለቤትነት ጋር በተያያዙ መብቶች ላይም ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ ለምሳሌ የአላባ ጥቅም (ከሌላ ሰው ንብረት የመጠቀም እና ትርፍ የማግኘት መብት) ወይም ምናልባትም የባለቤትነት መብትን በሚመስሉ የረጅም ጊዜ የሊዝ ውል (አንቀጽ 393)።
አመክንዮ (ከህጉ በውስጠ ታዋቃኒት ሊወሰድ የሚችለው ግምት)፡- የዚህ ማዕቀፍ ታሪካዊ ዳራ ሲቃኝ የጠባቂነት አካሄድን(Protectionist stance) የሚያንፀባርቅ ሲሆን ምናልባትም መሬት በዋነኛነት ለኢትዮጵያውያን እንዲቆይ፣ አስፈላጊ በሆነው አገራዊ ሃብት (መሬት) ላይ የውጭ ቁጥጥርን ለመከላከል እና ምናልባትም ከኢኮኖሚ ብዝበዛ ወይም ከልክ ያለፈ የውጭ ተጽእኖ ለመከላከል ታስቦ የተቀረፀ እንደነበር ደርሳናት ይጠቁማሉ።
2. አዲሱ ረቂቅ ህግ፡ ጠቃሚ ነጥቦች እና ግምገማ
ረቂቅ ህጉ ዜና ከ65 አመታት በላይ የቆየውን ገደብ የሚያነሳ በመሆኑ ጠቃሚም አከራካሪም የህግ፣ ህገመንግስታዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አሉት፡፡
ሀ. ሕገ መንግሥታዊነት እና ሕጋዊነት፡-
ሕገ መንግሥታዊ መሰናክል (የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 40(3)) ፡ ትልቁ የሕግ እንቅፋት ይህ ነው። “መሬት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት በመሆኑ ለሽያጭም ሆነ ለሌላ መገበያያ መንገዶች ሊተላለፍ አይችልም” በማለት አንቀጽ 40(3) በማያሻማ ሁኔታ ይናገራል። እንዲሁም መሬት የመንግስት ወይም የህዝብ ንብረት እንደሆነ እና ዜጎች በትክክል መሬቱን የያዙ እንዳልሆኑ ይልቁንም የመጠቀም መብት እንዳላቸው (በአብዛኛው በመንግስት ሊዝ) መሆኑን በግልፅ አስቀምጧል። በግንባታ እና በመሬት ባለቤትነት መካከል ያለው ዋናው የክርክር ነጥብ ማንም ኢትዮጵያዊ እንኳን ሳይቀር ከስር ያለውን መሬት በግሉ መያዝ ካልቻለ የውጭ ዜጋ እንዴት የማይንቀሳቀስ ንብረት ሊኖረው ይችላል? አብዛኛውን ጊዜ መሬቱም ሆነ በላዩ ላይ ያሉት ሕንፃዎች እንደማይንቀሳቀስ ንብረት የሚቆጠሩ መሆኑ ይታመናል፡፡
ተገቢነት ያለው ወይም እምቅ ትርጓሜ/ሰርከምቬንሽን፡- ወደፊት ተገቢውን ሂደት ጨርሶ ተግባር ላይ እንዲውል የታቀደው ህግ የመሬቱን እና የህንፃውን ባለቤትነት (ለምሳሌ የፋብሪካ መዋቅር ወይም በጋራ መኖሪያ ቤት ውስጥ ያለ አፓርትመንት) መካከል ያለውን ልዩነት ለመለየት ሊሞክር ይችላል። ምናልባት ልክ እንደ ኢትዮጵያውያን ዜጎች፣ በመንግስት የተሰጠ የመሬት ሊዝ ውል እያለ የውጭ አገር ዜጎች የሕንፃው ባለቤት ሊሆኑ እንደሚችሉ ሊጠቁም ይችል ይሆናል፡፡
የሕገ መንግሥት ጥናት፡- ይህ አተረጓጎም እንኳን በጥንቃቄ ሊጤን ይገባዋል። በመዋቅሮች ላይ የባለቤትነት እና የሊዝ መብት ለውጭ ዜጎች መስጠት የአንቀጽ 40(3)ን ይዘትና እና መንፈስ ያከብራልን? ዜጎች በሊዝ የመሸጥ መብት ቢኖራቸውም ሕገ መንግሥቱ “ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች” የመጨረሻውን የመሬት ባለቤትነት የተጎናፀፉ መሆናቸውን በግልፅ አስቀምጧል። ለውጭ አገር ዜጎች የባለቤትነት መሰል መብቶችን መስጠት - ሕንፃዎችን እና የሊዝ ኮንትራቶችን ብቻ ያካተተ ቢሆንም - ይህንን አስፈላጊ ሀሳብ ያጠፋል ተብሎ ክርክር ሊቀርብበት ይችላል፡፡ በዚህ ሁኔታ "ባለቤትነት" የሚለው ቃል እራሱ እጅግ በጣም ረቂቅ ነው፡፡
የይዞታ መብት፡- ምንም እንኳን ለውጭ አገር ዜጎች የተሻሻሉ የይዞታ መብቶችን መስጠት (እንደ ረጅም ጊዜ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የሊዝ ውል) “የባለቤትነት መብት” የመስጠት ያህል ሕገ መንግሥታዊ ባይሆንም እነዚህ መብቶች በረቂቅ ሕጉ እንዴት እንደሚገለጹ ልብ ማለት ያስፈልጋል።
ህጋዊነት ማጠቃለያ፡- ረቂቅ ህጉ “ባለቤትነት” የሕንፃ ባለቤትነት ብቻ እንደሆነ በጥንቃቄ እስካልተደነገገ ድረስ፣ ለዜጎች ካለው የመሬት ሊዝ ሥርዓት ጋር ተዳምሮ፣ የመሬት ባለቤትነትን ከማስተላለፍ ጋር የተያያዘ ማንኛውንም አንድምታ እስካልቀረበ ድረስ፣ ተከራካሪ ከሆነ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ከፍተኛ አደጋ አለው። ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን ስንመለከት ያለዚህ ዓይነት ጥንቃቄ የተሞላበት መመዘኛ “ባለቤትነት” የሚለውን ቃል መጠቀም በሕግ አነጋገር እጅግ በጣም አጠራጣሪ መሆኑ አይቀሬ ነው።
ለ. ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፡ መፈናቀል እና የመሬት ዘረፋ/ ነጠቃ፡
ይህ በተለይ እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትላልቅ የአገሪቱ ከተሞች ውስጥ ትልቅ የህዝብ ጉዳይ ነው።
ወቅታዊ ጫና፡- ለረዥም ጊዜ ነዋሪዎች ቀደም ሲል በፈጣን የከተሞች መስፋፋት እና የልማት ፕሮጀክቶች (እንደ "ኮሪደር ልማት" ያሉ) ፣ በተደጋጋሚ በቂ የካሳ ክፍያ ላለመከፈልና ለማህበራዊ ትሥስር መበጠስ ተዳርገናል የሚል ስሞታዎችን አልፎ አልፎ በማሰማት ላይ እንደሚገኙም ይሰማል፡፡
የአለምአቀፍ ፍላጎት ተጽእኖ፡- የውጭ ባለቤትነትን መፍቀድ—ምናልባትም በሀብታሞች ወይም በቢዝነስ ሰዎች—በሚፈለጉ ሰፈሮች የሪል እስቴትን ዋጋ በሚያስደንቅ ሁኔታ ሊጨምር ይችላል። በዝቅተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ቤት መግዛት ወይም የቀደመ ትሥ ስራቸውን በከተማ ማዕከላዊ ቦታዎች ላይ ማቆየት የማይቻልበት ሁኔታ በዚህ ምክንያት ፍጥነቱን ሊጨምር የሚችልበት አጋጣሚ ሰፊ ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላ አገላለፅ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ የከተማ ቦታዎች/አከባቢዎች በአገር ውስጥ ባለሃብቶች እና የውጭ ዜጎች እጅ ሊያከማቹ የሚችሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል።
የመኖሪያ ቤት የማቅረብ አቅም፡- በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የከተማ አካባቢዎች የመኖሪያ ቤት እጥረት ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡ አሁን ለሚታየው ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት እጥረት ለነዋሪዎች አቅርቦትን ለማሳደግ የተሰሩ በርካታ ስራዎች ቢኖሩም ችግሩ በተለያዩ ምክን ያቶች እየጨመረ ከመሔዱ ወጪ ስለመቀነሱ ይፋዊ ሪፖርት ወይም ሳይንሳዊ ጥናት የለም፡፡ ስለሆነም ለዚህ ግዙፍ ችግር ትርጉም ያለውን እርምጃ ሳይወስዱ የውጭ ፍላጎትን ማምጣት ችግሩን የባሰ ሊያባብስ ይችላል፡፡ ይህም የመኖሪያ ቤት ዋጋን

ለብዙ ሰዎች የበለጠ ተደራሽ እንዳይሆን፣ እንዳይቀመስ ያደርጋል።
ግምት፡- የውጭ የገንዘብ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ በማድረግ የሪል እስቴት ገበያ ኢንቨስትመንትን ያበረታታል ተብሎ ቢገመትም ቀጣይነት ያለውን እድገትን ከማረጋግጥ አንፃር አሉታዊ ተፅኖዎች ይኖሩታል፡፡
የምግብ ዋስትና/የገጠር መሬት፡- ረቂቅ ህጉ በዋናነት በከተማ ላይ ያተኮረ ቢመስልም በገጠርም ሆነ በእርሻ መሬት ላይ ተፈጻሚነት ያለው ስለመሆኑ እስካሁን በዜና በግልፅ የተነገረ ነገር የለም። የውጭ አገር ዜጎች የገጠር መሬት ባለቤትነት ከተፈቀደ ስለ የምግብ ዋስትና፣ ሉዓላዊነት እና የገበሬው ማህበረሰቦች መነቀል አሳሳቢ ጉዳዮች ሁነው ይከሰታሉ።
) - መንግስት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ፣የውጭ ምንዛሪ ለመፍጠር፣የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን እና የከተማ አካባቢን ለማሻሻል እንደ አንድ ቁልፍ ዘዴ ሊመለከተው ይችላል፤ ተገቢም ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎች መሰል ዋናዎቹ አደጋዎች ከእነዚህ ሊሆኑ ከሚችሉ ጥቅሞች ጋር ሚዛናዊ መሆን አለባቸው።
ሐ. የቁጥጥር እና የአተገባበር ስጋቶች፡-
ግልጽነት እና የተፈፃሚነት ወሰን፡- ረቂቅ ሕጉ ግልጽ የሆኑ ትርጓሜዎችን ይፈልጋል። የውጭ ዜጎች ምን ዓይነት ሪል እስቴት ማለትም የመኖሪያ፣ የንግድ እና የኢንዱስትሪ—መያዝ ይችላሉ? እንደ ዋና ከተሞች ወይም ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ያሉ የጂኦግራፊያዊ ገደቦች ሊኖሩት ይገባልን? በንብረቶች ብዛት ወይም መጠን ላይ ገደቦች ያስፈልጉ ይሆን?
ስልቶች፡- ለውጭ አገር ዜጎች የታሰበ የተለየ የረጅም ጊዜ የሊዝ ውል ነው ወይስ የባለቤትነት መብት? ?
የጥንቃቄ እርምጃዎች፡- ዜጎችን ከአከባቢያቸው እንዳይፈናቀሉ ለመጠበቅ ምን መከላከያዎች ተግባራዊ ሊሆኑ ይገባል? አሉታዊ ተጽእኖዎችን ለመቀነስ የውጭ ባለቤትነት ልዩ ታክሶች ወይም ደንቦች (እንደ ከፍተኛ የንብረት ታክስ ወይም ግምታዊ ግብሮች) የህጉ ርዕሰ ጉዳይ ይሆናሉን? ያልተፈቀዱ የመሬት ግዢዎችን ለማስቆም የአሰራር ሂደቱን ህጉ እንዴት ሊቆጣጠር ይገባል?
ግልጽነት እና መመካከር፡- ይህ ረቂቅ ህግ አሁን ባለበት ደረጃ ከህዝብ ጋር ያልተማከረበት ሁኔታ በመፈጠሩ(አገሪቱ ውስጥ ካለው የህግ ሪቂቅ የማምንጨት ስርዓት ሊሆን ይችላል) ጥርጣሬና ተቃውሞ ከወዲሁ እያስነሳ ይገኛል፡፡ አንዳንዶች ዝርዝር ይዘቱን ሳይመለከቱና ሳያነቡ ገና በፅንስ ላይ ባለ ረቂቅ ላይ የሰላ የሚመስል ትችት ሲሰነዝሩ እየተሰማ ነው፡፡ ሆኖም ከወዲሁ ጥርጣሬና ተቃውሞ መነሳቱ ህጉ ወደፊት በሚኖሩት ሂደቶች በጥንቃቄና በጥልቀት እንዲታይ ሊያደርግ የሚችል እድል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ የሆኖ ሁኖ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መፅደቁን የተሰማው ረቂቅ ህግ በርካታ አንድምታዎች ያሉትና የረዥም አመታት ታሪክን የሚያስቀር በመሆኑ የዚህ አይነት ለውጥ የባለድርሻ አካላትን ሰፊ ተሳትፎ እና ውይይትን ይጠይቃል።
3. ማጠቃለያ
የውጭ አገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትንና ባለይዞታነት መብትን በሚመለከት ኢትዮጵያ ለረጅም፤ ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ ስታራምደው የነበረውን ፖሊሲ በተመለከተ አሁን የቀረበው ረቂቅ ህግ በእጅጉ የሚቀይረው መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይኸው አዲስ የፖሊሲ ለውጥ እንደ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ባሉ የፋይናንስ ግቦች ተገቢ መሆኑ ሊደገፍ የሚችል ቢሆንም ብዙ መሰናክሎችም ሊያጋጥሙት እንደሚችሉ ግን ሊታወቅ የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
ሕገ መንግሥታዊ ፈተና፡- ‹‹ባለቤትነት›› በትክክል እንዴት እንደሚገለፅና የሕዝብ/የመንግሥት የመሬት ባለቤትነትን ሐሳብ እንደሚያፀና ከኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 40(3) ጋር መጣጣሙ በጣም አጠራጣሪ ነው።
ከፍተኛ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ስጋቶች፡- የመሬት ወረራ፣ መፈናቀል (በተለይ በትልልቅ ከተሞች) ፣ የመኖሪያ ቤት እጦት እና የእኩልነት መጓደል የመባባስ እድሉ ሰፊ ሲሆን ይህም ከወዲሁ እየተነሳ ካለው ከህዝቡ ስጋት ጋር የሚስማማ ነው።
የጠንካራ ደንብ አስፈላጊ ነው፡- ህጉ ከወጣ እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ መቅረጽ፣ ትክክለኛ ትርጓሜዎች/ ፍቺዎች እንዲኖሩት ማድረግ፣ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ እና ለዜጎች ጠንካራ ጥበቃ ማድረግ ያስፈልጋል። ሆኖም እነዚህን መስፈርቶች ማሟላት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።
ይህ ረቂቅ ህግ ግልፅ ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎችን እና መሬት በኢትዮጵያ የህግ እና ማህበራዊ መዋቅር ውስጥ የሚጫወተውን መሰረታዊ ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት በጥልቀት መመርመር አለበት። እንዲህ ዓይነት ሕግ ከመውጣቱ በፊት፣ ሕገ መንግሥታዊነትን እና እንደ መሬት ወረራና መፈናቀል ያሉ ጎጂ ማኅበራዊ ጉዳዮችን በሚመለከት ትክክለኛ ሥጋቶችን ለመፍታት በቁም ነገርና በቁርጠኝነት አርቆ ማሰብና ሰፊ ምሁራዊና ሕዝባዊ ውይይት ማድረን ያስፈልጋል። መንግስት ለምን እንደዚህ አይነት ጉልህ ለውጥ እንደሚያስፈልግ በግልፅ በማስረዳት ህገ መንግስቱን እንዴት እንደሚያከብር እና የኢትዮጵያውያንን ጥቅም አጉልቶ እንደሚያስከብር ለዜጎች የማስረዳትና የማሳየት ህገ መንግስታዊ ግዴታ ያለበት መሆኑን ጭምር ለአፍታም ያክል ሊዘነጋው የማይገባ ጉዳይ ነው።
በውጭ ኢንቨስትመንት ዓላማዎች እና በማህበራዊ ፍትህ እና በሕገ-መንግሥታዊ መርሆዎች መካከል ሚዛን ስለመፍጠር ምን ያስባሉ? እባኮትን ከዚህ በታች ባለው የአስተያየቶች መስጫ ሳጥን ውስጥ ሀሳብዎን ያካፍሉ!
የኢትዮጵያ ህግ፣ የንብረት ባለቤትነት መብት፣ የውጭ ኢንቨስትመንት፣ ህገ-መንግስታዊ ህግ፣ የህዝብ ፖሊሲ እና የኢኮኖሚ ልማት!
#አልማው_ወሌ ጠበቃና የህግ አማካሪ እንደጻፈው