የወንጀል ምርመራ ትርጉምና ጠቀሜታ
====================
መንግሥት ወንጀል ምርመራና የወንጀል ክስ የማቅረብ ተግባር ሙሉ በሙሉ በውክልና ለግለሰብ ወይም የህግ ሰውነት ላለው ድርጅት አሳልፎ ለመስጠት የማይችልበትና በርካታ ምክንያቶች እንዳሉ ግልፅ በመሆኑ ምክንያቶቹን መዘርዘር አያስፈልግም፡፡
በመሆኑም መንግሥት በአንድ አካባቢ ወንጀል የተፈፀመ ስለመሆኑ አጠርጣሪ ሁኔታዎች ሲኖሩ ጉዳዩን የማጣራት ወንጀል የተፈፀመ ስለመሆኑ መረጃ ሲደርሰው መረጃና ማስረጃ የማሰባሰብና የወንጀል ምርመራ የማከናወን ግዴታና ሀላፊነት አለበት፡፡ ስለሆነም በአንድ አካባቢ ወንጀል ስለመፈፀሙ አጠራጣሪ ሁኔታ ወይም ወንጀል ስለመፈፀሙ መረጃ ሲደርሰው መረጃውን የሚቀበል እና የወንጀል ምርመራ ማከናወን የመጀመሪያው ተግባር ነው፡፡ ይኸም መንግሥት የሚያከናውነው የወንጀል ምርመራ የራሱ የሆነ ግብና ዓላማ አለው፡፡ ስለሆነም ስለ ወንጀል ምርመራ መሠረታዊ ግብና ዓላማ ለመረዳት በመጀመሪያ የወንጀል ምርመራ ትርጓሜና ጠቀሜታ ምንድን ነው? የሚለውን ነጥብ አንስቶ መወያየቱ የጎላ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
“የወንጀል ምርመራ” መሠረታዊ ትርጉም ስንመለከት የአማርኛ ቋንቋ መዝገበ ቃላቶች የወንጀል ምርመራ ለሚለው ፅንሰ ሃሣብ የተሟላ ትርጉም ሰጥተው እናገኝም፡፡ ይህንንም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት ኢንስቲቲዩት በ1993 ዓ.ም ባሣተመው መዝገበ ቃላት ለመረዳት ይቻላል፡፡ መዝገበ ቃላቱ “የወንጀል ምርመራ ማለት ሕገ ወጥ የሆኑ ተግባራትን እንደ ሌብነት ግድያና የመሳሰለው ጥፋት በደልና ስህተቶችን የምርመራ ሥራ ማከናወን” ማለት ነው በሚል ቁንፅል ትርጓሜ ሰጥቶት እናገኛለን፡፡ በአንፃሩ በእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላቶች ውስጥ የወንጀል ምርመራ /Criminal Investigation/ የሚለውን ፅንሰ ሃሣብ መሠረታዊ ምንነት ልዩ ባህሪያትና ዓላማ የሚያቅፋቸውን ተግባራት ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ የሚገልፅ ትርጓሜ ተሰጥቶት እናገኛለን፡፡
የወንጀል ምርመራ /Criminal Investigation/ የሚለው ፅንሰ ሃሣብ በእንግሊዝኛ የህግ ማዝገበ ቃላት የሰጠውን ትርጓሜ ስንመለከት “Criminal Investigation is a process of establishing that the crime is committed, identifying and apprehending the suspect, recovering the stoen property if any, and assisting in the prosecution of a person charged with crime’ የሚል ትርጓሜ ሰጥቶት እናገኛለን፡፡ ይህንን ትርጓሜ በትኩረት ስንመረምረው የሚከተሉትን መሠረታዊ ነጥቦች ያካተተ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
1. #የወንጀል ምርመራ በራሱ ግብ ሣይሆን የግብ ማሣካት ሂደት መሆኑ
የወንጀል ምርመራ ጎን በጎን የሚፈፀሙ የተለያዩ ተግባሮችን የያዘ የሥራ ሂደት /Process/ መሆኑ ነው፡፡ የወንጀል ምርመራ ማከናወን በራሱ መሠረታዊ ግብ አይደለም፡፡ የወንጀል ምርመራ የተለያዩ ዓላማዎችን ለማሣካት የሚከናወን የሥራ ሂደት ነው፡፡ ለዚህም ነው የወ.መ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ 12 የወንጀል ምርመራ የሚጀመረው ወንጀል ስለመፈፀሙ ምክንያታዊ ጥርጣሬ ሲኖር መሆኑን የሚደነግገው በእኛ አገር የወንጀል ምርመራ መጀመር በራሱ እንደ አንድ ግብ የሚታይበትና በተለይም
የወንጀል ባህሪ በሌላቸው የፍታብሔር ጉዳዮች መነሻ በማድረግ ተጀምረው ጊዜና ጉልበት ከባከነባቸው በኋላ የሚመክኑ የምርመራ ሥራዎች መኖራቸው
ያለበቂ ምክንያት ሰውን በቁጥጥር ሥር ለማዋልና አስሮ ለማቆየት ሲባል ዓርብ ተጀምረው ሰኞ የሚቋረጡ ምርመራዎች
ወንጀል ከተፈፀመ በኋላ ተጠርጣሪውን ፍርድ ቤት በዋስ እስኪለቀው ድረስ የተወሰነ ደረጃ ከተራመደ በኋላ ከዚያ በኋላ የሚዘነጉና ተቋርጠው የሚቀሩ ምርመራዎች መኖራቸው ሲታይ የወንጀል ምርመራ መጀመርን በራሱ መሠረታዊ ግብ አድርጎ የመውሰድ የተዛባ አመለካከት እንዳለ ለመገንዘብ እንችላለን፡፡
2. #የወንጀል ምርመራ የሚከናወነው በመጀመሪያ ወንጀል የተፈፀመ መሆኑን ለማጣራት ነው፡፡ የወንጀል ምርመራ ከወንጀል ምርመራ የሚጠበቀው ወንጀል ለመፈፀሙ በተለያየ መንገድ መረጃ ሲደርስ በእርግጥ ወንጀሉ የተፈፀመ መሆኑ ወይም መረጃው በሀሰት ተቀነባብሮ የቀረበ የተባለው ወንጀልም ያልተፈፀመ መሆኑን ማረጋገጥ ነው፡፡ በእኛ አገር ምርመራ የማከናወን ስልጣን ያለው አካል /ፖሊስ/ ወንጀል ሰለመፈፀሙ ጥቆማ ሲደርሰው የምርመራ ሥራውን በእርግጥ የተባለው ወንጀል ተፈፅሟል ወይስ አልተፈፀመም የሚለውን ነጥብ በማጣራት አይጀምርም፡፡ ይልቁንም ወንጀሉ ስለመፈፀሙ እርግጠኛ ሣይሆንና ማስረጃ ሣያሰባስብ ወንጀሉን ፈፀሙ የተባሉትን ሰዎች በመያዝ ጥቆማ አቅራቢው ስለጉዳዩ ያውቃሉ ያላቸውን ምስክሮች ቃል በመቀበል ምርመራውን ጀምሮ የሚያጠናቅቅበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡
በዚህ ምክንያት ወንጀል ፈፅመዋል የተባሉት ሰዎች አላግባብ ተከስሰው ብዙ ጊዜ ከታሰሩ በኋላ ተፈፀመ የተባለው ወንጀል በሀሰት ተቀነባብሮ የቀረበ መሆኑን የተረጋገጠበት ሁኔታ በአማራ ክልል በተለያዩ ደረጃ ያሉ ፍርድ ቤቶች ከሰጧቸው ውሣኔዎች ለመረዳት ይቻላል፡፡
በአጠቃላይ አንድ መረጃና ጥቆማ የደረሰው ፖሊስ የቀረበለትን መረጃ በደፈናው ማመን የለበትም፡፡ በመረጃው የተገለፀው ወንጀል ተፈፅሟል ከሚል መደምደሚያ ላይም ስለጉዳዩ ማስረጃ ከማሰባሰቡና ከማጣራቱ በፊት መድረስ የለበትም፡፡ ስለሆነም መርማሪው ነፃና ገለልተኛ ሆኖ በመጀመሪያ በእርግጥ ወንጀሉ በትክክል ተፈፅሟልን? የሚለውን ነጥብ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ታዓማኒነት ያላቸውን መረጃዎች በማሰባሰብ ዕውነታውን መፈለግ ይገባዋል፡፡
3. #የወንጀል ምርመራ የሚከናወነው ተጠርጣሪውን ለመለየትና በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው፡፡ ስለሆነም የወንጀል ምርመራ የሚያከናውነው አካል ወንጀል መፈፀሙ ካረጋገጠ በኋላ ተጠርጣሪዎቹን ለመለየትና ለመያዝ የሚከናወን የሥራ ሂደት ነው፡፡ የአንድ ምርመራ እና የወንጀል የፍትህ ሥርዓት ውጤታማነት ተጠርጣሪዎቹን ለመለየትና ተጠርጣሪዎቹን በመያዝ አቅም ነው፡፡ በዚህ በኩልም ቀላል የማይባሉ ችግሮች መኖራቸውን የሚያመላክቱ መረጃዎች ስላሉ ትኩረት ሰጥተን ልንሠራ ይገባናል፡፡
4. #የወንጀል ምርመራ ሌላው ትኩረት በወንጅሉ የተወሰዱ ንብረቶች በአስቸኳይ ተከታትሎ መያዝና ማስመለስ ጭምር ነው፡፡ በመሆኑም ከላይ ከተገለፁት ተግባራት ጎን በጎን በወንጀሉ የተወሰደ ንብረት ለማስመለስ በትጋት መሥራትን ይጠይቃል፡፡ ይህንን በአግባቡ ማከናወን ሲቻል ብቻ ነው፡፡ “ማንም ሰው በወንጀል ሥራ ፍሬ ተጠቃሚ ሊሆን አይገባውም” የሚለውን መሠረታዊ መርህ ተግባራዊ ለማድረግ የሚቻለው፡፡
5. #የወንጀል ምርመራ አጥፊውን ለፍርድ ለማቅረብና የሚችል ማስረጃ ለማሰባሰብና በወንጀል ክስ፣ የሙግትና የፍርድ ሂደት አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ ነው፡፡ እዚህ ላይ አንድ አንድ መርማሪዎች ምርመራው ከተጠናቀቀ ዐቃቤ ሕግ ክስ ካቀረበ በኋላ የወንጀል ምርመራ መሠረታዊ ግብ እንደተሳካ አድርገው በተከሣሽ አቀራረብም ሆነ በምስክሮች አቀራረብ እኛን የሚመለከት አይደለም የሚል ክርክር ያቀርባሉ፡፡ አንድ ምርመራ ተከናውኖ ተከሣሹና ማስረጃዎች ፍርድ ቤት ቀርበው ተጠያቂ የማይሆን ከሆነ የወንጀል ምርመራ መሠረታዊ ግቡን አያሣካም፡፡ ሌሎች አገሮች ተከሣሽን በመክሰስና ጥፋተኛ ለማሰኘት የሚደረገው ዕገዛ የወንጀል ምርመራ አንደኛው ሂደት እንደሆነ “ Criminal Investigation is the process of assisting prosection of

the person charged with crime.” በማለት ይገልፃሉ፡፡ በመሆኑም የወንጀል ምርመራ የወንጀል የምርመራ መዝገቡን እስከ ማጠናቀቅ ድረስ ያለውን ሂደት ብቻ የሚመለከት አድርገው የሚያስቡና ተከሣሹንና በምርመራ ሂደት የተሰበሰቡትን ማስረጃዎች ለፍርድ ቤት በማቅረቡ ሂደት ምንም አይነት እገዛ ማድረግ እንደሌለባቸው የሚያስቡ መርማሪ ፖሊሶች “ የወንጀል ምርመራን እንደ መሠረታዊ ግብ ማሣኪያ ሂደት ሣይሆን ምርመራ ማጣራቱ በራሱ ግብ አድርገው የሚመለከቱ በመሆናቸው የአመለካከት ለውጥ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. #የወንጀል ምርመራ ልዩ ባህሪ ያላቸውና የወንጃል ሰለባ የሆኑ ሰዎች በመያዣነት የታገቱባቸው ወንጀሎች ተፈፅመው በሆነ ጊዜ ከላይ ከተገለፁት ተግባራት በተጨማሪ የወንጀል ሰለባ የሆኑትን ሰዎች ከተጋረጠባቸው አደጋ ለመታደግና አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያገኙ የሚከናወነውን ተግባር ያጠቃልላል፡፡ የተፈፀመው ወንጀል ሰውን አስገድዶ መሰወር፣ ጠልፉ፣ ንፁሐን ዜጎችን ማገትና መደራደሪያ ማድረግ የመሳሰሉት በሆነ ጊዜ ከላይ ከተገለፁት በተጨማሪ የወንጀሉን ሰለባ ለማስለቀቅ የሚከናወኑ ተግባራትን ያጠቃልላል፡፡
ከፀጋዬ ደመቀ ገፅ
#join #join #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

#የወንጀል #ምስክሮችና ጠቋሚዎች #ጥበቃ
........
የወንጀል ድርጊትን ለመቆጣጥር እና ለመከላከል እንዲሁም ወንጀለኞች የወንጀል ድርጊት ከፈፀሙ በኋላ ተደብቀው እንዳይቀሩና ህግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ የወንጀል ምስክሮች እና ጠቋሚዎች የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ይህን ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ በምስክርነታቸው ወይም በጠቋሚነታቸው ምክንያት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ከሚደርስባቸው አደጋና ጥቃት መከላከል አስፈላጊ ነው፡፡ ሀገራችንም ይህንኑ በመረዳት የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ ህግ አውጥታ ሥራ ላይ ውሏል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ የምስክር እና የጠቋሚዎች ምንነት፣ በአዋጁ የተካተቱ የጥበቃ እርምጃ ዓይነቶችን እና የጥበቃ ስምምነት እንዳስሳለን፡፡
የምስክር እና ጠቋሚዎች ምንነት
ጠቋሚ ወይም ምስክር ማለት በወንጀል ምርመራ፣ በወንጀል ክስ ወይም በወንጀል ማጣራት ሒደት መረጃ ወይም ምስክርነት የሰጠ ወይም ለመስጠት የተስማማ ሰው እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀፅ 2(1) ላይ ትርጓሜ ተሰጥቶታል፡፡
የጥበቃ ተጠቃሚነት እና ተፈፃሚነቱ
በአዋጁ አንቀፅ 2(2) የጥበቃ ተጠቃሚ ማለት ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር የጥበቃ ስምምነት የተፈራረመ ምስክር፣ ጠቋሚ ወይም የምስክር ወይም የጠቋሚ ቤተሰብ አባል ነው፡፡ በዚህ መልኩ ስምምነት የገባ ምስክር ወይም ጠቋሚ በአዋጅ ላይ የተቀመጡት የጥበቃ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች ይደረጉለታል፡፡ ሆኖም እነዚህ የጥበቃ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች ከፍተኛ የሰለጠነ የሰው ሀይል፣ ጊዜ፣ ገንዘብ እና ወጪን የሚጠይቁ በመሆኑ ከአገራችን እድገት እና የኢኮኖሚ አቅም አኳያ ለሁሉም ምስክሮች እና የወንጀል ጠቋሚዎች ከለላ እና ጥበቃ ማድረግ አይቻልም፡፡ በመሆኑም የጥበቃ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች ማግኘት የሚቻለው በአዋጁ ላይ የተቀመጡት መስፈርቶች ተሟልተው ሲገኙ እንደሆነ በአዋጁ አንቀፅ 3 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህ አዋጅ መሠረት የሚደረጉ የጥበቃ እና ጥንቃቄ እርምጃዎች ተፈፃሚ የሚሆኑት፡-
በሕግ የተደነገገው የፅኑ እስራት መነሻ ከግምት ሳይገባ አስር ዓመትና ከዚያ በላይ በሆነ ፅኑ እስራት ወይም በሞት ሊያስቀጣ በሚችል የወንጀል ድርጊት ተጠርጣሪ ላይ የሚሰጥ ምስክርነትን ወይም ጥቆማን ወይም የሚካሄድ ምርመራን በሚመለከት ሆኖ:-
የወንጀል ድርጊቱ ያለምስክሩ ወይም ያለጠቋሚው ምስክርነት ወይም ጥቆማ በሌላ ማናቸውም መንገድ ሊረጋገጥ ወይም ሊደረስበት የማይችል ሲሆን እና
በምስክሩ፣ በጠቋሚው ወይም በምስክሩ ወይም በጠቋሚው ቤተሰብ ህይወት፣ አካላዊ ደህንነት፣ ነጻነት ወይም ንብረት ላይ ከባድ አደጋ ይደርሳል ተብሎ ሲታመን ነው፡፡
ነገር ግን አዋጁ ይህንን መስፈርት ቢያስቀምጥም ፍትህ ሚኒስቴር እና የፌዴራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጥበቃ ተጠቃሚ ላልሆኑ ምስክሮችና ጠቋሚዎችም በአዋጁ አንቀፅ 4 ስር የተቀመጡ አንዳንድ ጥበቃዎችን እንደአስፈላጊነቱ ሊያደርግ እንደሚችል ይገልፃል፡፡
ይህም በሚስጥር መያዝ ያለበት ካልሆነ በስተቀር ለጠቋሚ ጥቆማ ባቀረበበት ጉዳይ ላይ ወቅታዊ መረጃና ምክር መስጠት እንዲመሰክር ለተጠራ ምስክር የጉዞና የውሎ አበል መስጠት
በበቀል የተወሰደ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲታገድ ወይም እንዲሻር ማድረግ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ የማካካሻ እርምጃ መውሰድ በበቀል እርምጃ ለደረሰ ጉዳት የህክምና አገልግሎት በመንግሥት ሆስፒታል በነፃ መስጠት ለምስክሩ ወይም ለጠቋሚው የምክር አገልግሎት መስጠት ወይም እንዲያገኝ ማድረግን የሚያካትት ነው፡፡
የጥበቃ እርምጃ ዓይነቶች
ለወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች የሚደረጉ የጥበቃ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች በአዋጁ አንቀፅ 4 ስር ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡ የጥበቃ እና የጥንቃቄ እርምጃዎች እንደ ሁኔታው በተናጠል ወይም በጣምራ ለጥበቃ ተጠቃሚ ተፈጻሚ የሚደረጉ ሲሆን ይህም ፡-
የአካልና ንብረት ደህንነት ጥበቃ
የመኖሪያ ስፍራ መቀየርን ጨምሮ ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ ቦታ መስጠት
ማንነትንና ባለንብረትነትን መደበቅ
ማንነትን መቀየር
ለራስ መጠበቂያ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ መስጠት
መረጃ በተሰጠበት የወንጀል ድርጊት ያለመከሰስ
መረጃ በሚሰጥበት የወንጀል ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊትም ሆነ በኋላ ተከሳሽ በጥበቃ ተጠቃሚው መኖሪያ ወይም የሥራ ቦታ ወይም ትምህርት ቤት አካባቢ እንዳይደርስ ማገድ
የፍርድ ሂደት ተጀምሮ ምስክርነት እስከሚሰጥ ድረስ የምስክር ማንነት እንዳይገለጽ ማድረግ
ምስክርነት በዝግ ችሎት እንዲሰጥ ማድረግ
ምስክርነት በአካል ሳይታይ ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ ወይም ማንነትን በመሸፈን እንዲሰጥ ማድረግ
ማስረጃ በኤሌክትሮኒክስ ወይም በሌላ የተለየ ዘዴ እንዲቀርብ ማድረግ
በሚስጥር መያዝ ያለበት ካልሆነ በስተቀር ለጠቋሚ ጥቆማ ባቀረበበት ጉዳይ ላይ ወቅታዊ መረጃና ምክር መስጠት
እንዲመሰክር ለተጠራ ምስክር የጉዞና የውሎ አበል መስጠት
የጥበቃ እርምጃው የመኖሪያ ስፍራን ለውጥ ካስከተለ የጓዝ ማንሻ ወጪን መሸፈን
በበቀል የተወሰደ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲታገድ ወይም እንዲሻር ማድረግ ወይም
ተመጣጣኝ የሆነ የማካካሻ እርምጃ መውሰድ
በበቀል እርምጃ ለደረሰ ጉዳት የህክምና አገልግሎት በመንግሥት ሆስፒታል በነጻ መስጠት
በጥበቃ እርምጃው ምክንያት ለደረሰ የገቢ ማጣት ወይም በበቀል እርምጃ ለደረሰ የመሥራት ችሎታ ማጣት የመሠረታዊ ፍላጎት ማሟያ ወጪን መሸፈን
በጥበቃ ሥር እያለ ለደረሰ ሞት የቀብር ማስፈጸሚያ ወጪ መሸፈንና ለቤተሰብ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ
የጥበቃ ተጠቃሚው የሥራና የትምህርት ዕድል እንዲያገኝ መርዳት
ለምስክሩ ወይም ለጠቋሚው የምክር አገልግሎት መስጠት ወይም እንዲያገኝ ማድረግን እንደሚያካትት በአዋጁ ላይ ተዘርዝሮ ይገኛል፡፡
የጥበቃ ስምምነት
በአዋጁ አንቀፅ 2(2) መሰረት የጥበቃ ተጠቃሚ ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር የጥበቃ ስምምነት የተፈራረመ ምስክር፣ ጠቋሚ ወይም የምስክር ወይም የጠቋሚ ቤተሰብ አባል ሲሆን በአዋጁ አንቀፅ 8 መሰረት የአካልና ንብረት ደህንነት ጥበቃ፣ የመኖሪያ ስፍራ መቀየርን ጨምሮ ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ ቦታ መስጠት፣ ማንነትንና ባለንብረትነትን መደበቅ እና ማንነትን መቀየር ከተመለከቱት የጥበቃ ዓይነቶች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ ተግባራዊ ለማድረግ በሚኒስቴሩ እና በጥበቃ ተጠቃሚው መካከል የጥበቃ ስምምነት መፈረም አለበት፡፡ የጥበቃ ተጠቃሚው አካለ መጠን ያላደረሰ ወይም በፍርድ የተከለከለ ሰው ከሆነ የጥበቃ ስምምነቱ ከወላጆቹ ወይም ከአሳዳሪው ጋር የሚፈረም ሲሆን ጥበቃው የጥበቃ ተጠቃሚው አካለ መጠን ከደረሰ ወይም የህግ ችሎታውን መልሶ ካገኘ በኋላ የሚቀጥል ከሆነ ስምምነቱን የጥበቃ ተጠቃሚው ራሱ መፈረም እንዳለበት በህጉ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
የጥበቃ ተጠቃሚ የሆነው አካለ መጠን ያላደረሰ ልጅ መረጃ ወይም ምስክርነት የሚሰጠው በወላጁ ወይም በአሳዳሪው ላይ ሲሆን፣ ወላጅ ወይም አሳዳሪ የሌለው ሲሆን፣ አስፈላጊው ጥረት ተደርጎ ወላጁን ወይም አሳዳሪውን ማግኘት ያልተቻለ እንደሆነ፣ ወላጁ ወይም አሳዳሪው በቂ ባልሆነ ምክንያት ፈቃዱን ሳይሰጥ ሲቀር ወይም በማናቸውም ምክንያት ፈቃዱን መስጠት ሳይችል ሲቀር ሚኒስቴሩ በአንቀፅ 9 መሰረት ከልጁ ጋር ልዩ የጥበቃ ስምምነት ሊፈራረም ይችላል፡፡.....................