አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
The 2025 National Moot Court Competition on International Humanitarian Law Kicks Off at University of Gondar
****
The 2025 International Humanitarian Law (IHL) National Moot Court Competition officially began today, the 27th of May 2025, in Gondar, Ethiopia, marking the 8th edition of this prestigious event. Jointly organized by the University of Gondar, School of Law and International Committee of the Red Cross (ICRC), this year’s competition focuses on the theme: “Protection of Health Care in Armed Conflict.”

Law students from Arbaminch University, Bahir Dar University, Haramaya University, Hawassa University, Jimma University, and the University of Gondar are participating in this important event.
በዓለምአቀፋዊ የሰብዓዊነት ህግጋት ላይ ትኩረት ያደረገው 8ኛው ሀገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር ፍጻሜውን አገኘ
****
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህግ ት/ቤት ከዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ጋር በመተባበር በዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊነት ህግጋት ላይ ትኩረት ያደረገው 8ኛው ሀገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር በጎንደር አስተናግዷል::

ግንቦት 21/2017 ዓ.ም ፍጻሜውን ባገኘው በዚህ ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምስለ ችሎት ውድድር በትናንትናው ዕለት የጅማ እና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተወዳዳሪ ተማሪዎች ለፍፃሜ ውድድር መድረሳቸው ይታወቃል። በመሆኑም ዛሬ በተደረገው የፍፃሜ ውድድር የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ባደረጉት ውድድር የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቀዋል፡፡ እንዲሁም የጅማ ዩኒቨርሲቲ እና የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በቅደም ተከተል የሁለተኛና የሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ያጠናቀቁ ሲሆን፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ጥሩ የክርክር ጽሁፍ አቅራቢ ዘርፍ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪ የሆነችው ተማሪ ንያማል ቲቢትሀ ጥሩ ተናጋሪ በሚል ዘርፍ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች፡፡ አሸናፊዎች በአፍሪካ ደረጃ ኬኒያ ናይሮቢ ላይ በሚካሄደው አህጉራዊ ፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ይሆናል፡፡
"የገቢ ግብር ቢቀንስ አሰሪዎችም በነጻነት ሰራተኛ እንዲቀጥሩ ያበረታታል ይህም የስራ እድል ፈጠራን ያሳድጋል" -አቶ መርዕድ ፍቅረዮሃንስ

በኢትዮጵያ ሰራተኞች በተደጋጋሚ የሚነሱት ጥያቄዎች ዋነኛው የገቢ ግብር ጉዳይ ነው። የገቢ ግብር በሰራተኛው ላይ ብቻ ሳይሆን በቀጣሪ ድርጅቶች ላይም ከፍተኛ ጫና የሚያደርስ እንደሆነ ባለሞያዎች ይናገራሉ።

መንግስት በአንፃሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና በሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ጭምር በተደጋጋሚ የተጠየቀው የተቀጣሪ ሰራተኛ ገቢ ግብር ቅነሳ ላይ ይኼ ነው የሚባል ምላሽ እስካሁን አልሰጠም።

በዚሁ ጉዳይ ሸገር ኤፍ ኤም የጠየቃቸው የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ መርዕድ ፍቅረዮሃንስ የገቢ ግብሩ እርከን ቢስተካከል የሰራተኛ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ባይችል እንኳን የተወሰነ አፎይታ እንደሚሰጥ ያነሳሉ።

ባለሞያው በዝርዝር ምን አሉ ?

"መንግስት ለመጠናቀቅ 38 ቀናት በቀረው በጀት ዓመት ወደ 900 ቢሊዮን ብር ከቀረጥ እና ቀጥታ ካልሆነ ታክስ እንዲሁም 50 ቢሊዮን ብር ከመንግስት እና ከግል ተቀጣሪ ሰራተኞች ለመሰብስብ አቅዶ እየሰራ ነው።

50  ቢሊዮን ብሩን መንግስት የሚሰበስበው ከግል እና ከመንግስት የጡረታ ፈንዶች ነው። በአገር አቀፍ በግል እና በመንግስት የተቀጠሩ 4.4 ሚሊየን ሰራተኞች አሉ። 50 ቢሊዮን ብር የሚሰበሰበውም በሀቅ ከሚከፍሉት ከእነዚሁ ሰራተኞች ነው።

የተቀጣሪ ሰራተኛ ገቢ ግብሩ ቢቀነስ ምን ለውጥ ይመጣል?

የገቢ ግብሩ እርከን ቢስተካከል የ4.4 ሚሊዮን ሰራተኛ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ባይችል እንኳን የተወሰነ አፎይታ ይሰጣቸዋል።

በተጨማሪም አሰሪዎችም በነጻነት ሰራተኛ እንዲቀጥሩ ያበረታታል ይህም የስራ እድል ፈጠራን ያሳድጋል።

መንግስት ግብሩን ቢቀንስ ምንም አያጣም። ሰራተኛው በተዘዋዋሪ መልሶ በአንድም በሌላም መንገድ ለመንግስት ገቢ ማድረጉ አይቀርም።

የጎረቤት አገራትን ተሞክሮ በምሳሌነት ብናነሳ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ዝቅተኛ ክፍያ እየተከፈላቸው ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ናቸው።

ለማሳያም ኬንያ [እናንሳ] የሚቆርጡትን ግብር ከማየታችን በፊት የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ የኢትዮጵያና የኬኒያ የመገበያያ ገንዘብ ከዶላር አንፃር አቻ መሆናቸው ልብ ማለት ይገባል፡፡

ከግብር አንፃር ስናይ ኬንያ 800 ሺህ ብር ከሚያገኝ ተቀጣሪ ላይ 35 በመቶ ግብር ስትቆርጥ ኢትዮጵያ ከ10 ሺህ 900 ብር ጀምሮ ተመሳሳይ ግብር ትቆርጣለች።

በኢትዮጵያ 600 ብር ከሚያገኝ ጀምሮ የገቢ ግብር ሲቆርጥበት በኬኒያ ግብር የሚቆረጠው 4 ሺህ ብር ከሚያገኝ ደሞዝተኛ ነው።"
ሲሉ አስረድተዋል።

ከሰራተኛው ላይ የገቢ ግብር መቀነስ ለምን እንዳልተቻለ ባለፈው የምክርቤት አባላት የገቢዎች ሚኒስቴርን ጠይቆ ገቢዎች ሚኒስቴር በሰጠው ምላሽ የተሰጠውን ሃላፊነት ማስፈፀም እንጂ ይቀነስ፣ ይጨመር የሚልበት ስልጣን እንደሌለው አስረድቷል።

ሰራተኛው እያነሳ ያለው የገቢ ግብር ቅነሳ ጥያቄ ተገቢ ነው ያሉት አቶ መርዕድ ፍቅረዮሃንስ እንዴት ይቀነስ በሚለው ላይ ግን በስፋት መወያየት እና በጥንቃቄ ማየት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

Credit : Sheger FM 102.1

@TikvahethMagazine
አለሕግAleHig ️
የገቢ ግብር ቢቀንስ አሰሪዎችም በነጻነት ሰራተኛ እንዲቀጥሩ ያበረታታል ይህም የስራ እድል ፈጠራን ያሳድጋል" -አቶ መርዕድ ፍቅረዮሃንስ
የገንዘብ_ሚኒስቴር_መመሪያ_ቁጥር_1063_2017.pdf
5.8 MB
#ታክስ #ኦዲት

የገንዘብ ሚኒስቴር፥ የታክስ ኦዲት የሚከናወንበትን ሥርዓት እና የታክስ ስሌት ማስታወቂያ የሚወጣበትን አኳኋን ለመወሰን መመሪያ አውጥቷል።

መመሪያው ከትላንትና በስቲያ ጀምሮ ስራ ላይ ውሏል።

መመሪያው ስለ አጠቃላይ ኦዲት ምን ይላል ?

የታክስ ባለስልጣን አጠቃላይ ኦዲት የሚያከናውነው ፦

- በስጋት ግምገማ ወቅት ታክስ ከፋዩ በህግ በተደነገገው መሰረት የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ገቢውን የማስታወቅ እና ታክስ የመክፈል ግዴታውን ያልተወጣ መሆኑ ሲታወቅ እና ይህም ሁኔታ የተለያዩ ታክሶችን የሚመለከት ሲሆን፤

- ሌላ አይነት ኦዲት በመደረግ ላይ ባለበት ጊዜ የተገኙ ታክስ ከፋዩ የፈጸማቸው ተገቢ ያልሆኑ አድራጎቶች ኦዲቱ በማይሸፍናቸው በሌሎች ታክሶች ላይ ጭምር ውጤት ያላቸው መሆኑ ሲታወቅ፤

- ታክስ ከፋዩ ኦዲት እንዲደርግ ሲጠየቅ እና በታክስ ባለስልጣኑ አጠቃላይ ኦዲት አስፈላጊ መሆኑ ሲታመንበት፤

- አግባብነት ባላቸው በሌሎች የታክስ ህጎች በተገለጹ ሌሎች ምክንያቶች፤

- ታክስ ከፋዩ በጭብጥ ኦዲት ተደርጎ አከራካሪ ከሆነ እና በቅሬታ ጽ/ቤት በኩል አጠቃላይ ኦዲት እንዲደረግ ትዕዛዝ ሲሰጥ፤ ... ነው ይላል።

የታክስ ባለስልጣን አጠቃላይ አዲት በሚያከናውንበት ጊዜ ፦
° ተገቢ ያልሆነ የሂሳብ ስሌት፣ ግድፈት፤
° ገቢን ማሳነስ፤
° ተገቢ ያልሆነ የታክስ አሰያየም
° በታክስ ማስታወቂያ ወይም ስሌት ረገድ የተፈጸመ ሌላ ማናቸውም ጥፋት ያለመኖሩን ለማረጋገጥ፤ ሁሉንም ወይም የተወሰኑትን የታክስ አይነቶች በሚመለከት ዝርዝር እና ጥልቀት ያለው ምርመራ ማድረግ እንዳለበት መመሪያው ላይ ሰፍሯል።

ይህ የማጣራት ተግባር አግባብነት እስካለው ድረስ የህግ ድንጋጌዎችን ተከትሎ መፈጸም እንዳለበትም ይገልጻል።

(ሙሉ መመሪያው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
ፕላስቲክ❗️ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2000 እስከ 5000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ፀደቀ!!

ለእንጀራ፣ ለዳቦ እና ለተለያዩ የሸቀጥ እቃዎች መጠቅለያነት የሚውለውን የአንድ ብሩን ፕላስቲክ ይዞ መገኘት ከ2000 እስከ 5000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ጸደቀ፡

ያመረተ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ለገበያ ያቀረበ ወይም የሸጠ፣ ለንግድ ዓላማ ያከማቸ ወይም ይዞ የተገኘ ከ50,000 ብር በማያንስና ከ200,000 ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት  እንዲቀጣ አዋጁ ያዝዛል፡፡

የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) የአዋጁን ይዘት በንባብ ባቀረቡበት ወቅት፤ የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) ህዝባችን በፕላስቲክ እቃ ይዞ ወደ ቤቱ ከገባ ይጣለው? ወይስ መልሶ ለአካባቢ ጥበቃ ያስረክበው? የሚል ጥያቄ ከጠየቁ ብኋላ የምናመርተው የፕላስቲክ ውጤት ዳግም እንድንጠቀምበት የሚያደርግ ቢሆን አይሻልም ወይ? ምክንያቱም 10 ጊዜ የምጠቀምበትን ፕላስቲክ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቀም ማለት ተገቢ አይደለም፣ አዋጁ ፕላስቲኩን ከተጠቀምኩበት ወዲያ የት ማስቀመጥ እንዳለበት አላስቀመጠም ብለዋል፡፡

አዋጁ ይዞ የተገኝ እንዲቀጣ ይደነግጋል ህዝባችን የዚህ ግንዛቤ ይኖረዋል ወይ? የትኛው ፕላስቲክ እንደሆነ የመለየት ግንዛቤስ አለው ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ሌላ አንድ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው ማንኛውም ሰው #ፕላስቲክ ይዞ ከተገኘ ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፤ ይህ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ ጋር  እንዴት ታየ? በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ሊጠቀመው ስለሚችል ጫና አይፈጥርም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ  አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ፌስታሎችን ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍልም ስለሚጠቀማቸው ቅጣቱ ያን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል፡፡

ለምሳሌ «አንዲት አሮጊት ወይም ሽማግሌ የሁለት ብር ዳቦ ወይም የአስር ብር ስኳር ገዝተው ሲሄዱ 5 ሺህ ብር ክፍሉ ቢባሉ ላይኖራቸው ስለሚችል ቅጣቱ ከ5 ሺህ ወደ 2 ሺህ ዝቅ እንዲል ተደርጓል ይህም የህብረተሰቡን የመክፈልም አቅም ከግንዛቤ ያስገባ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የፕላስቲክ ከረጢቶች ከቅጣቱ በላይ ሀገርን የሚጎዱ ናቸው እስከ መቶ ዓመት ድረስም አይበሰብሱም ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ ከዚህ አንጻር ቅጣቱ ሃያም ሰላሰም ሺህ ቢሆን ሀገርን ለማትረፍ ነው ብለዋል፡፡

ለህዝቡ ግንዛቤ ለመስጠትም ከመጪው ሃሙስ ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ይካሄዳል ሲሉ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡አዋጁ የፕላስቲክ ጫማዎችን፣ የውሃ ኮዳዎችን እና ወፍራም የፕላስቲክ ውጤቶችን አይጨምርም መባሉን ሰምተናል፡፡

አዋጁ ማንኛውም ሰው ከመኖሪያ ቤቱ ድንበር አንስቶ ከሃያ ሜትር በላይ አካባቢውን የማጽዳት ግዴታን ያስቀምጣል፡፡አዋጁም በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ምንጭ ፣ ሸገር ኤፍ ኤም
#ኢትዮጵያ

ለእንጀራ፣ ለዳቦ እና ለተለያዩ የሸቀጥ እቃዎች መጠቅለያነት የሚውለውን የአንድ ብሩን ፕላስቲክ ይዞ መገኘት ከ2,000 እስከ 5,000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ጸደቀ፡

ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ፤ " ዜጎችን በማያውቁት ጉዳይ ለቅጣት የሚዳርግ ነው " የሚል ትችት ከምክር ቤት አባላት ቀርቦበታል፡፡

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ የጸደቀው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ፤ ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኝ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፡፡

ያመረተ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ለገበያ ያቀረበ ወይም የሸጠ፣ ለንግድ ዓላማ ያከማቸ ወይም ይዞ የተገኘ ከ50,000 ብር በማያንስና ከ200,000 ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከ5 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት  እንዲቀጣ አዋጁ ያዝዛል፡፡

የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) የአዋጁን ይዘት በንባብ ከቀረቡ በኃላ የም/ቤት አባላት ጥያቄ አቅርበዋል።

የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) ህዝባችን በፕላስቲክ እቃ ይዞ ወደ ቤቱ ከገባ ይጣለው ? ወይስ መልሶ ለአካባቢ ጥበቃ ያስረክበው ? የሚል ጥያቄ ጠይቀዋል።

አክለው የምናመርተው የፕላስቲክ ውጤት ዳግም እንድንጠቀምበት የሚያደርግ ቢሆን አይሻልም ወይ ? ምክንያቱም 10 ጊዜ የምጠቀምበትን ፕላስቲክ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቀም ማለት ተገቢ አይደለም፣ አዋጁ ፕላስቲኩን ከተጠቀምኩበት ወዲያ የት ማስቀመጥ እንዳለበት አላስቀመጠም ብለዋል፡፡

አዋጁ ይዞ የተገኝ እንዲቀጣ ይደነግጋል ህዝባችን የዚህ ግንዛቤ ይኖረዋል ወይ ? የትኛው ፕላስቲክ እንደሆነ የመለየት ግንዛቤስ አለው ወይ ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ሌላ አንድ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው ማንኛውም ሰው ፕላስቲክ ይዞ ከተገኘ ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፤ ይህ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ ጋር  እንዴት ታየ ? በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ሊጠቀመው ስለሚችል ጫና አይፈጥርም ወይ ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ  አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ፌስታሎችን ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍልም ስለሚጠቀማቸው ቅጣቱ ያን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል፡፡

" ለምሳሌ አንዲት አሮጊት ወይም ሽማግሌ የሁለት ብር ዳቦ ወይም የአስር ብር ስኳር ገዝተው ሲሄዱ 5 ሺህ ብር ክፍሉ ቢባሉ ላይኖራቸው ስለሚችል ቅጣቱ ከ5 ሺህ ወደ 2 ሺህ ዝቅ እንዲል ተደርጓል ይህም የህብረተሰቡን የመክፈልም አቅም ከግንዛቤ ያስገባ ነው " ሲሉ አስረድተዋል፡፡

" የፕላስቲክ ከረጢቶች ከቅጣቱ በላይ ሀገርን የሚጎዱ ናቸው እስከ መቶ ዓመት ድረስም አይበሰብሱም " ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ " ከዚህ አንጻር ቅጣቱ ሃያም ሰላሰም ሺህ ቢሆን ሀገርን ለማትረፍ ነው " ብለዋል፡፡

ለህዝቡ ግንዛቤ ለመስጠትም ከመጪው ሃሙስ ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ይካሄዳል ሲሉ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

አዋጁ የፕላስቲክ ጫማዎችን፣ የውሃ ኮዳዎችን እና ወፍራም የፕላስቲክ ውጤቶችን አይጨምርም ተብሏል።

አዋጁ ማንኛውም ሰው ከመኖሪያ ቤቱ ድንበር አንስቶ ከሃያ ሜትር በላይ አካባቢውን የማጽዳት ግዴታንም ያስቀምጣል፡፡

አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

#ShegerFM101.2

@tikvahethiopia
" የተርሚናል አገልግሎት ክፍያው የሚፈጸመው ማህበራቱ በስኬት ባንክ በከፈቷቸው አካውንቶች በቴሌብር አማካኝነት ነው " - ማህበራቱ

ነባር ተራ እስከባሪዎችን በመተካት የተርሚናል አስተዳደር እና ቁጥጥር ስልጠና የወሰዱ ከ 80 በላይ በሚሆኑ ማህበራት(ኢንተርፕራይዝ) የተደራጁ ተራ አስከባሪ ወጣቶች ዛሬ ከሰአት ስራ ጀምረዋል።

ዛሬ ጠዋት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ እና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ፣የአዲስ አበባ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ያብባል አዲስ በተገኙበት የተመረቁት 996 የታክሲ ተራ አስከባሪ ወጣቶች ከሰአት በኋላ ስራ መጀመራቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

ነባሮቹን ተራ አስከባሪ ወጣቶች በመተካት ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ የገቡት ወጣቶች በየወረዳው የተደራጁ ሲሆን በከተማዋ በሚገኙ 87 ተርሚናሎች ወደ ስራ ገብተዋል።

የተርሚናል አገልግሎት ክፍያው የሚፈጸመው ማህበራቱ በስኬት ባንክ በከፈቷቸው አካውንቶች በቴሌብር አማካኝነት መሆኑን ቲክቫህ ያነጋገራቸው የማህበራቱ አባላት ገልጸዋል።

ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ በሚል ከትላንት ጀምሮ የተበተነው እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው በራሪ ወረቀት የተቀመጠው የአገልግሎት ክፍያ በየትኛውም መነሻ እና መድረሻ ላይ 10 ብር መሆኑን በመግለጽ ክፍያውንም በዲጂታል መንገድ ብቻ እንዲፈጸም ይጠይቃል።

በተጨማሪም ከተቀመጠው የአገልግሎት ክፍያ በላይ የከፈለ አሽከርካሪም ሆነ ረዳት 4000 ብር እንደሚቀጡ ይገልጻል።

ነባር ተራ አስከባሪዎች በመረጡት የስራ ዘርፍ እንዲሰማሩ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረግላቸዋል ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
income_tax_amendment_proclamation-_amharic-_05282025.pdf
864.3 KB
#ለመረጃ፡ የገንዘብ ሚኒስቴር የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ የመጀመሪያ ረቂቅ አዘጋጅቷል! የረቂቁን የአማርኛ ቅጂ ማንበብ ለምትፈልጉ....
ከሰራተኛው ደሞዝ የሚነጥቀው አዋጅ ድንጋጌ ተሰረዘ!
በዚህ ጉዳይ ላይ ቀደም ሲል ረቂቅ አዋጁ ላይ ከሰራተኛ ደሞዝ መቀነስ ተገቢ እንዳሎነ እና ሰራተኛው ላይ ሌላ የመከራ ቀንበር መጫን እንደሆነ አንስቼ ይህ ድንጋጌ ከረቂቅ አዋጁ ላይ መውጣት እንዳለበት ከብዙወቻቹ ጋር መወያየታችን ይታወቃል፡፡ ምናልባትም ፓርላማው ከተሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ውድቅ ያደረገው ድንጋጌ ይመስለኛል፡፡ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ አሁንም ግን ኢትዮጵያ እያጸደቀቻቸው ያሉ ችኩልና ህዝብን ለበለጠ መከራ ሚዳርጉ አዋጆች በድጋሚ ሊጤኑ ይገባል።
በፊቃዱ ደሪባ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446 ኛው አመተ ሒጅራ የኢድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
EID MUBAREK🙏