አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው ውሳኔ የተሰጠበትን ድንጋጌ አርሞ አፀደቀ
-------------------
(ዜና ፓርላማ) ሰኔ 30 ፣ 2017 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 3ኛ ልዩ ስብሰባው፤ በምክር ቤቱ የአሠራር እና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 49 (2)ሀ መሠረት ውሳኔ የተሰጠበት ድንጋጌ እንዲታረም በሚል ከሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አፅድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው፤ ከአሁን በፊት ውሳኔ የተሰጠበት ድንጋጌ እንዲታረም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ አርሞ አፅድቋል፡፡

የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ኢሳ ቦሩ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 37ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅ፤ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1387/2017 አድርጎ ማፅደቁ አስታውሰዋል፡፡

ከአሁን በፊት የነበረው የረቂቅ አዋጅ ድንጋጌ እንዲታረም መደረጉ አተገባበሩ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሊያስከትል ስለሚችል ረቂቅ አዋጁን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የተከበሩ አቶ ኢሳ ቦሩ አስረድተዋል፡፡

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 780/2005ን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1387/2017 ላይ ከነባሩ አዋጅ አንቀፅ 26 ንዑስ አንቀፅ (3) ቀጥሎ አዲስ ንዑስ አንቀፅ (4) ማሻሻያ የተደረገበት መሆኑን የተከበሩ አቶ ኢሳ ቦሩ አብራርተዋል፡፡

የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፤ ረቂቅ አዋጁ ለሰብአዊ መብት ጥሰት በር የሚከፍት በመሆኑ ድንጋጌውን መሻሻሉ ተገቢነት ያለው መሆኑን ገልጸዋል
፡፡

በፍትህ ተቋማት በምርመራ ሂዴት ላይ በዜጎች አላስፈላጊ ድርጊት እንዳይፈፅሙ ክፍተት እንዳይሰጥ ለማስቻል የድንጋጌውን እርምት በጥሩ ጎን እንደሚረዱት የምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡

አዋጁም ለሕትመት ሳይበቃ ቀድሞ እንዲታረምና እንዲስተካከል መደረጉ የሚበረታታ ተግባር መሆኑን የምክር ቤት አባላት ገልጸዋል፡፡

በምክር ቤቱ የአሠራር እና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 49 (2)ሀ መሠረት ድንጋጌው መሻሻያ ተደርጎበት፤ የውሳኔ ሃሳብ፤ ውሳኔ ቁጥር 11/2017 ሆኖ  በአንድ ተአቅቦ፤ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡

#HPR