አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ውድ የተከበራችሁ የዚህ ቻናል እና ግሩፕ ቤተሰቦች የትዊትተር አካውንት የሌላችሁ የትዊተር አካውንት እንድትከፍቱና እንድትዘጋጁ የትዊተር አካዉንት እንዲኖራችሁ ትጠየቃላችሁ።
ከከፈታችሁ በሗላ የትዊተር አካዉንታችሁ እዚሁ ላይ ሸር በማድረግ Follow, Like and Retweet እናደርግላችሗለን።
ምክንያቱም፤
እንደ አንድ ዜጋ እውነትን ይዘን ዝም በማለታችን ውሸት ሀገራችንን ሲያፈርስ እንዳናይ የሀገራችንን እውነት ለአለም የምናሰማበት የትዊተር ዘመቻ ያስፈልገናል።

በዚህ ዘመን በአለም መንግስታት ውሳኔ ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆነው ሶሻል ሚዲያ ዋናው እና አንዱ Tweeter ነው።🩸

ስለ አከፋፈቱ የምናግዛችሁ ይሆናል።

📌ትዊት በምናደርግበት ሰዓት የትዊተር አካውንቶቻችን እንዳይዘጋብን የሚረዱ ጥቆማዎች‼️‼️

1.የትዊተር አካውንት ስም(username )በተቻለ መጠን ትክክለኛ ስም ያድርጉ

2.የትዊተር አካውንት ስም(username ) ከአንድ በላይ ቁጥር አያስገቡ

3.የትዊተር አካውንቶ ላይ ስልክ ቁጥርዎን መጨመር አይዘንጉ

4.Follow የሚያደርጓቸውን አካውንቶች ቁጥር በአንድ ጊዜ አያብዙ

5.የትዊተር ፎሎወር እናበዛለን የሚሉ መተግበሪያዎችን (applications )ፈፅመው አይጠቀሙ

6.ትዊተር በሚጠቀሙበት በተለይም ዘመቻ በሚያደርጉበት ጊዜ Tweet /Quote Tweet ሲያደርጉ የተወሰነ ደቂቃ ልዮነት ይኑረው(time gap of at least 5-10 minutes)

7.ዘመቻ ሲያደርጉ የሚፈልጓቸውን መልዕክተኛ በመምረጥ Schedule Tweet(በመረጡት የጊዜና የጊዜ ገደብ ራሱ tweet የሚያደርግሎትን አማራጭ ይጠቀሙ

8.እንደ tweet ሁሉ retweet የሚያደርጉበትን ድግግምሽ ክፍተት ይስጡ

9.ከስልክ ቁጥርዎ በተጨማሪ የኢሜል አድራሻ Account ላይ ማከልን አይዘንጉ

10. ዘመቻ ከሚደረግባቸው ወቅቶች ውጪ የራስዎን መልዕክት Tweet ያድርጉ

11.ደህንነታቸው የተረጋገጠ (Secured )መተግበሪያዎች (Twitter for Android/IOS) እና ማሰሻዎች ብቻ(Firefox, Chrome,Opera,Safari ) ትዊተርን ይጠቀሙ

12.ማንነት & አድራሻ መሰወሪያ (VPN) መተግበሪያዎችን አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ከመጠቀም ይቆጠቡ

13.በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ትዊቶችን like,reply ,retweet & quote tweet ከማድረግ ይቆጠቡ

14. ብዛት ላላቸው ተጠቃሚዎች ቀጥተኛ መልዕክት ከመላክ(direct messaging ) ይቆጠቡ

15 .የትዊተር የይለፍ ቃልዎን (twitter password )በመደበኛነት ይቀያይሩ : ተመሳሳይ የይለፍ ቃል (password) ከመጠቀም ይቆጠቡ።
via #UnityForEthiopia
በተጨማሪ አለም አቀፍ ድርጅቶች ያለመከሰስ ከለላ እንዳላቸው ከተለያዩ አለም አቀፍ ስምምነቶች መረዳት ይቻላል፡፡ያለመከሰስ ከለላ ከሚሰጣቸው አለም አቀፍ ድርጅቶች መካከል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(የተ.መ.ድ) እና እንደ አለም አቀፍ የጤና ድርጅት ( World Health Organization)፣አለም አቀፍ የገንዘብ ፈንድ (International Monetary Fund)፣የአለም ባንክ (World Bank) የመሳሰሉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ ተወካዮች (UN specialized agencies) ተጠቃሽ ሲሆኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያለመከሰስ ከለላ በአባል ሀገራቱ ውስጥ ሊጠበቅለት እንደሚገባ በድርጀቱ ቻርተር አንቀፅ 105 ስር ሰፍሮ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በ1946 የተባበሩት መንግስታት ልዩ መብት እና ከለላ ኮንቬንሽን (Convention on the Privileges and Immunities of the United Nations 1946) ለድርጅቱ ከለላ እንደሚሰጠው ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ያለመከሰስ ከለላ ያላቸው አካላት እነ ማን ናቸው?
የውጪ ሀገር መንግስታት፣ተወካዮቻቸው ማለትም ዲፕሎማቶች፣ቆንስላዎች እና ልዩ መልክተኞች እንዲሁም አለም አቀፍ ድርጅቶች እና ሰራተኞቻቸው በተለያዩ አለም አቀፍ ህጎችን እና ስምምነቶች መሰረት ያለመከሰስ ከለላ መብት አላቸው፡፡
በቬና የዲፒሎማቲክ ግንኙነት ኮንቬንሽን (1961 Vienna convection on diplomatic relation) በሀገራት የጋራ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ስምምነት ላይ መሰረት በማድረግ ለዲፕሎማቲክ መልዕክተኞች እና ለቤተሰባቸው አባላት ያለመከሰስ ከለላን ይሰጣል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ልዩ መብት እና ከለላ ኮንቬንሽን (Convention on the Privileges and Immunities of the United Nations) እንደተደነገገው ለተቋሙ ስራ ወሳኝ ሚና ላላቸው ማለትም 1. የአባል ሀገራት ተወካዮች( representatives of Member States)በኮንቬንሽኑ አንቀፅ 3 ክፍል 11፣የተ.መ.ድ ሀላፊዎች( United Nations officials) በአንቀፅ 5 ክፍል 18 እና በተልዕኮ ላይ ላሉ የተ.መ.ድ ባለሞያዎች( experts on missions for the United Nations)በኮንቬንሽኑ አንቀፅ 6 ክፍል 22 መሰረት ከለላ እንደሚሰጥ ያስቀምጣል፡፡በተጨማሪ የተ.መ.ድ ዋና ፀሐፊ ከለላ የሚሰጣቸውን የተ.መ.ድ ሀላፊዎች ዝርዝር እና የይለፍ ወረቀት( laissez-passer) የሚሰጣቸውን ሀላፊዎች ለአባል ሀገራቱ እንደሚያሳውቅ ኮንቬንሽኑ ያስቀምጣል፡፡እንዲሁም ዋና ፀሐፊው እና ረዳት ፀሐፊው ሙሉ ያከመከሰስ ከለላ ያላቸው ሲሆን ከለላ የተሰጣቸውን አካላት ያለመከሰስ ከለላ ማንሳት( waive the immunity )ለዋና ፀሐፊው የተሰጠ ስልጣን ነው(አንቀፅ 6 ክፍል 23) ፡፡ የ1948ቱ የልዩ ኤጀንሲዎች ልዩ መብት እና ከለላ ኮንቬንሽን (Convention on the Privileges and Immunities of the Specialized Agencies ) ተመሳሳይ ድንጋጌዎችን አካቶ ይገኛል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ የህግ ማዕቀፍ ስንመለስ የፌደራል ፍርድ ቤቶችን ስልጣን በሚወስነው አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀፅ 4/6/ እና 5/1/ሠ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ሕጎችና ልምዶች እንዲሁም ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እንደተጠበቁ ሆነው፤ የውጭ ሀገር አምባሳደሮች፣ቆንስላዎች፣የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣የውጭ መንግሥታት ወኪሎች ተጠያቂ በሆኑባቸው ወይም/እና ልዩ መብትና ጥበቃ ያላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ሰዎች ተከራካሪ በሆኑበት ጉዳዮች የፌደራል ፍርድ ቤቶች የወንጀል እና የፍትሀ ብሄር የዳኝነት ስልጣን እንዳላቸው ይደነግጋል፡፡በልላ በኩል የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 39/4 በአለም ዓቀፍ ህግ ዲፕሎማቲክ ከለላን መሰረት ተከሳሹ የማይከሰስ እንደሆነ ወይም በህግ መብቱ የተሰጠው እንደሆነ የፖሊስ የምርመራ መዘገብን ለመዝጋት አንድ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 9/4 መሰረት ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ህግ አካል ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ የ1946 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ መብት እና ከለላ ኮንቬንሽንን(Convention on the Privileges and Immunities of the United Nations) በ1947 እና የቬና ዲፕሎማቲክ ግንኙነት ኮንቬንሽን ( 1961 Vienna convection on diplomatic relation) በ1974 ተቀብላ ያፀደቀች በመሆኑ እንዲሁም የተ.መ.ድ አባል ሀገር በመሆኗ የውጪ ሀገር መንግስታት ወኪል ዲፕሎማቶች እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የተወሰኑ ሀላፊዎቸን መከሰስ ከለላ ለማክበር ግዴታ ገብታለች፡፡በመሆኑም የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የፍርድ ስልጣን ከእነዚህ አለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር በተጣጣመ መልኩ መሆን ያለበት እና ያለመከሰስ ከለላን ያከበረ መሆን ይኖርበታል ማለት ነው፡፡
ያለመከሰስ ከለላ ያላቸው አካላት ያለባቸው ግዴታ
ያለመከሰስ ከለላ ያላቸው አካላት ከሚሰጣቸው ልዩ መብት እና ጥበቃ ጎን ለጎን የተቀባይ ሀገርን ህግ እና ደንቦች የማክበር ግዴታ እንዳለባቸው በአለም አቀፍ ህጎች ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ በ1961 የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ኮንቬንሽን አንቀፅ 41 ላይ እንደ ተደነገገው ልዩ መብት እና ጥበቃ ያላቸው ሰዎች የተቀባይን ሀገር ህግ የማክበር እንዲሁም በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት ግዴታ እንዳለባቸው ያስቀምጣል፡፡

እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአለምን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ አላማውን ለማሳካት በሚሰራው ስራም ሆነ የእርዳታ ተግባር በማንኛውም ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ የቻርተሩ አንቀፅ 2/7(United Nations not to intervene in matters which are essentially within the domestic jurisdiction of any state) ይገልፃል፡፡ ይህም ድርጅቱ የሀገራትን ሉዓላዊነት የማክበር ግዴታ እንዳለበት ያሳያል፡፡

ያለመከሰስ ከለላ ያላቸው አካላት ላይ ሊወሰድ የሚችል እርምጃ
የውጪ ሀገር መንግስታት እና የአለም ዓቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ያለመከሰስ ከለላን ያለግባብ በመጠቀም የሀገሪቱን ህግ ቢጥሱ እንዲሁም በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ቢገቡ ሀገሪቱ ልትወስድ የምትችለው እርምጃ በአለም አቀፍ ስምምነቶች እንዲሁም ልማዳዊ ህጎች ተካቶ ይገኛል፡፡

የውጪ መንግስታትን በተመለከተ በሀገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት የዲፕሎማቲክ ግንኙነት እስከ ማቋረጥ የሚደርስ እርምጃ ሊያስወስድ የሚችል ሲሆን የሀገር እና የድርጅት ተወካዮች ላይ ደግሞ ሁለት አይነት እርምጃዎች ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡የመጀመሪያው የህግ መተላለፉን የፈፀመው አካል ያለመከሰስ ከለላ እንዲነሳ(waiver of immunity) እና በህግ ተጠያቂ እንዲሆን ላኪ ሀገርን መጠየቅ ሲሆን ሁለተኛ እርምጃ ደግሞ ተወካዩን የማይፈለግ ሰው( persona non grata) በማለት ከሀገር ማስወጣት ናቸው፡፡ ተቀባይ ሀገር ተወካዩን በማንኛውም ሰዓት ውሳኔዋን ሳታብራራ ከሀገር እንዲወጣ ማድረግ ትችላለች/The receiving State may at any time and without having to explain its decision, notify the sending State that the head of the mission or any
ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀት፣ መገልገል እና የወንጀል ተጠያቂነት
1. ሀሰተኛ ሰነድ እና አይነቱ
ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀትና መገልገል የሀገርን ኢኮኖሚ እንዲሁም የዜጎችን መብትና ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ የወንጀል ተግባር ነው፡፡ ሀሰተኛ ሰነዶች ዝግጅት በረቀቀና እውነተኛውን በሚመስል መንገድ የሚፈፀም በመሆኑ ይህን ከባድ ወንጀል ለመከላከልና አጥፊዎችን ለመቅጣት ብሎም ህብረተሰቡ ከዚህ ወንጀል እራሱን እንዲጠብቅ ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀቱ በመንግስታዊና ህዝባዊ ድርጅቶች ሰነዶች ላይ የሚፈፀም ከሆነ በሙስና ወንጀል የሚያስጠይቅ ነው፡፡ መንግስታዊ ሰነድ ሲባል የሚኒስቴር መስሪያ ቤት ወይም የክልል ቢሮዎችና በየደረጃው ያሉ አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የወጡ በማስመሰል የሚዘጋጅ ሲሆን ለምሳሌ የንግድ ወይም ኢንቨስትመንት ፈቃድ ወረቀቶች፣ የይለፍ ወረቀቶች፣ የብቃት ማረጋገጫዎች፣ የስራ ፈቃድ ወረቀቶች፣ የስራ ልምድ፣ የክፍያ ማዘዣዎች፣ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ወይም ሊብሬዎች፣ ወዘተ የሚያካትት ነው፡፡ የህዝባዊ ድርጅቶች ሰነድ ደግሞ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ወይም ተቋማት ሰነዶች ለምሳሌ የመጋዘን ደረሰኝ፣ የእቃ ማውጫ ፈቃድ፣ የትምህርት ማስረጃ፣ የባንክ ክፍያ ሰነዶች እና መሰል በእነዚህ ተቋማት የሚሰጡ ሰነዶችን የሚመለከት ነው፡፡ እነዚህን ሰነዶች ማዘጋጀትና መገልገል የሚያስከትለውን የወንጀል ተጠያቂነት ከዚህ እንደሚከተለው በዝርዝር ይቀርባል፡፡

2. ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀት፣ መገልገል እና የሚያስከትለው የወንጀል ተጠያቂነት
ማንኛውም ሰው የሌላውን ሰው መብት ወይም ጥቅም ለመጉዳት ወይም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ተገቢ ያልሆነ ማናቸውም መብት ወይም ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ አንድ ፅሁፍ፣ መዝገብ ወይም ማንኛውም ሰነድ የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት በማስመሰል ያዘጋጀ ወይም የፈጠረ፤ በመንግስት ወይም በህዝባዊ ድርጅት መዝገብ፣ ፅሁፍ ወይም ሰነድ የሰፈረን እውነተኛውን ፅሁፍ በመለወጥ ወይም በመደለዝ፣ በሀሰተኛ ፊርማ፣ በእጅ በተደረገ ምልክት ወይም በጣት ፊርማ፣ በማህተም ወይም የሌለውን ስልጣን ወይም ችሎታ እንዳለው አስመስሎ በመፈረም ሀሰተኛ ሰነድ የፈጠረ እንደሆነ፤ አንድን የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሰነድ በተለይ የፈራሚውን ስም ወይም ፊርማ ወይም የሰነዱን ይዘት፣ አሃዝ፣ ፍሬ ነገር ወይም ዝርዝር መግለጫ በሙሉ ወይም በከፊል በመለወጥ፣ በማሻሻል፣ በመቀነስ ወይም በመጨመር ወይም በማጥፋት ወደ ሀሰተኛነት የለወጠ ወይም ማናቸውንም ሀሰተኛ ፍሬ ነገር ያስገባ ወይም እንዲገባ ያደረገ እንደሆነ በሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 23 መሰረት ከሶስት አመት እስከ አስር አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ያስቀጣል፡፡
በተጨማሪም የዚህ ወንጀል አፈፃፀም በሚከተለው ሁኔታ ሊከብድ የሚችል ሲሆን ይኽውም ሰነዶቹን እንዲያዘጋጅ፣ እንዲመዘግብ እንዲጠብቅ ወይም ከነዚሁ ውስጥ ቅጂዎችን እንዲሰጥ ሀላፊነት በተሰጠው የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሰራተኛ እንደሆነ ወይም ሰነዱን በመገልገል የተገኘው ጥቅም ከፍተኛነት ወይም በግለሰብ፣ በመንግስት ወይም በህዝባ ድርጅት ወይም በህዝብ ጥቅም ላይ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ ቅጣቱ ከአምስት አመት እስከ ሀያ አምስት አመት የሚደርስ እስራት ያስቀጣል፡፡

ሌላው መገንዘብ የሚገባን ጉዳይ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 23 (4) መሰረት በወንጀል የሚያስጠይቀው ሀሰተኛ ሰነዶችን ማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን ይዞ መገኘትና መገልገል ጭምር ሲሆን በዚህም መሰረት ወደ ሀሰት የተለወጠ ወይም በሀሰት የተዘጋጀ ሰነድ በቤቱ፣ በተሽከርካሪው፣ በኪሱ ወይም በማንኛውም አግባብ በቁጥጥሩ ስር የተገኘ እንደሆነ ከላይ በተጠቀሰው ቅጣት ጋር ተመሳሳይ በሆነ ይቀጣል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም ሰው ወደ ሀሰት በተለወጠ ወይም በሀሰት በተዘጋጀ ሰነድ እያወቀ የተገለገለበት እንደሆነ በተመሳሳይ ይቀጣል፡፡

በሉላ በኩል ከግብር አከፋፈል ጋር በተያያዘ ማንኛውም ሰው ሆን ብሎ ወይም በከባድ ቸልተኝነት ለገቢዎች ሚኒስቴር የተጭበረበሩ ሰነዶችን ያቀረበ በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 አንቀፅ 118 መሰረት ከሶስት እስከ አስራ አምስት አመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል፡፡ በአንቀፅ 119 መሰረት ደግሞ እነዚህን የተጭበረበሩ ደረሰኞችን ያዘጋጀ፣ ያተመ፣ የሸጠ ወይም ያሰራጨ ወይም የተጠቀመ ከሰባት አመት እስከ አስር አመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል፡፡ የዚህን ወንጀል አፈፃፀም ለመከላከል ሲባል የተደነገገ ሌላ ጥፋት ሀሰተኛ ደረሰኞችን ለመስራት፣ ለማዘጋጀት ወይም ለማተም የሚያገለግል ማሽን፣ መሳሪያ ወይም ሶፍትዌር የያዘ፣ የሸጠ፣ ያከራየ ወይም በሌላ መንገድ ያቀረበ ማንኛውም ሰው ከአስር እስከ አስራ አምስት አመት እስራት እንደሚቀጣ በህጉ መደንገጉ ነው፡፡ በተመሳሳይ እነዚህን ሀሰተኛ ደረሰኞችን የያዘ፣ ያስቀመጠ፣ ለሽያጭ ያመቻቸ ወይ ሀሰተኛ ደረሰኞችን ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደረገ ከሶስት እስከ አምስት አመት እስራት ይቀጣል፡፡

ከጉምሩክ መንግስታዊ ስራዎች ጋር በተያያዘ ማንኛውም ሰው በጉምሩክ ኮሚሽን ላይ ጉዳት ለማድረስ ወይም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ኮሚሽኑ የሚጠቀምበትን ቅፅ፣ ማህተም፣ መታወቂያ፣ አርማ፣ የጉምሩክ ማሸጊያ ወይም ማናቸውም ሰነድ ወይም ምልክት ወደ ሀሰተኛነት የለወጠ ወይም አስመስሎ የሰራ ወይም ይህንኑ ያከፋፈለ፣ የተጠቀመ ወይም ለመጠቀም የሞከረ ወይም ለጉምሩክ ስነ ስርአት የሚቀርቡ ሰነዶችን የሰረዘ፣ የደለዘ፣ የፋቀ ወይም አስመስሎ የሰራ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀፅ 167 እና በጉምሩክ አዋጅ ማሻሻያ አዋጅ 1160/2011 አንቀፅ 169(4) መሰረት ከአምስት እስከ አስር አመት እስራት ይቀጣል፡፡

ከላይ ከተመለከቱት መንግስታዊና ህዝባዊ ሰነዶችን ማዘጋጀትና መገልገል ወንጀል በተጨማሪ በእለት ተእለት የኑሮ እንቅስቃሴ የምንጠቀምባቸውን ግላዊ ሰነዶችን በሀሰተኛ መንገድ ማዘጋጀትና መገልገል ከለይ ከተመለከተው ከባደ ሁኔታ ዝቅ ባለ በመለስተኛ ደረጃ በወንጀል የሚያስጠይቅ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ጥቅም ወይም መሻሻልን ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ ተገቢ መብት ለማስገኘት የሚችሉ ፅሁፎችን፣ ግላዊ ሁኔታን የሚገልፁ ማስረጃዎችን ወይም ምስክርነትን ማስረጃዎችን ወይም ማናቸውንም አይነት ጉዳይ የሚመለከቱ የምስክርነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ወደ ሀሰተኛነት የለወጠ ወይም አስመስሎ የሰራ ወይም እያወቀ ይህን የመሰለውን ሰነድ እንዲገለገልበት ለሌላ ሰው መስጠት በ1996 ዓ/ም የወንጀል ህግ አንቀፅ 385 መሰረት በቀላል እስራት ወይም መቀጮ ያስቀጣል፡፡ ይህ ሰነድ የግል ጉዳይን የያዘ እንደሆነ ከአንድ አመት ባልበለጠ እስራት፣ ወይም ሰነዱ ህዝባዊ ባህሪ ያለው ሆኖ እንደመታወቂያ ወረቀት ወይም የልደት ምስክር ወረቀት ወይም የችግርተኛነት፣ የመልካም ጠባይ፣ የብቁነት ወይም ብቁ አለመሆን ማረጋገጫ ምስክርነት ወይም የህዝብ መዝገብ ወይም መቆጣጠሪያ ቅጂ እንደሆነ ከሶስት ወር በማያንስ እስራት ያስቀጣል፡፡

በሌለ በኩል ወንጀሉን የፈፀመው እነዚህን ሰነዶች እንዲያዘጋጅ፣ እንዲያስቀምጥ፣ እንዲጠብቅ ወይም እንዲሰጥ ሀላፊነት በተሰጠው የመንግስት ሰራተኛ እንደሆነ እና ይህን ወንጀል ያደረገው በሌላ ሰው መብት ላይ ጉዳት ለማድረስ ሳያስብ እንደሆነ ከስድስት ወር እስከ አምስት አመት በሚደርስ እስራት ወይም በመቀጮ ወይም በሁለቱም ያስቀጣል፡፡
የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
INSA

1. የይለፍ-ቃልዎን ደህንነት ማረጋገጥ

#_የፌስቡክ አካውንቶን ለሌላ ማንኛውም የኦንላይን አገልግሎት ላይ አይጠቀሙ፤

#_ የይለፍ-ቃልዎን በፍፁም ለሌላ ሰው አያጋሩ፤

#_የሚጠቀሙበት የይለፍ-ቃል ለመገመት አዳጋች የሆነ፣ በፍጹም የእርሶን ስም እና የተለመዱ ቃላትን ያልያዘ ሊሆን ይገባል፤

#_የይለፍ-ቃልዎ ፣ኢ-ሜይልዎን፣ የስልክ ቁጥሮን ወይም የልደት ቀንዎን በፍፁም የሚጠቀም መሆን የለበትም፤

2. የሚያስሱትን ድረ-ገጽ መረጃ በፍጹም አያጋሩ

#_አጥቂዎች ፌስቡክ የሚመስል የሐሰት ገጽ ፈጥረው በኢ-ሜይል አድራሻዎና በይለፍ ቃልዎ እንዲገቡ ሊጠይቁዎ ይችላሉ፤

#_ሁልጊዜም መረጃ የሚያስሱበትን ድረ-ገጽ URL ትክክለኝነት ያረጋግጡ፤
አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ www.facebook.com በማፈላለጊያው ላይ በመጻፍ ወደ ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ለመመለስ ይሞክሩ፤

#_ ከሜታ /Meta/ ወይም ፌስቡክ የሚላክሎትን ኢ-ሜይል በፍጹም ለሌላ ሰው አያጋሩ፣ በተለይም ስለ አካውንቶ ምስጢራዊ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ፤

#_ስለፊሺንግ ጥቃት እና ጠንካራ የይለፍ-ቃል አጠባበቅ ላይ ያለዎትን እውቀትና ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

3. ኮምፒውተርዎን ለሌላ ሰው የሚያጋሩ ከሆነ የፌስቡክ አካውንቶን ዘግተው መውጣትዎን /Log Out/ ማድረግዎን አይዘንጉ፤

#_ኮምፒውተርዎን ዘግተው ሳይወጡ ወይም መሣሪያዎን ያዋሱ ከሆነም ከርቀት እንዴት መውጣት /Log Out Remotely/ እንደሚችሉ ይወቁ፤

#_ከርቀት ሆነው ለሌላ አካል ካዋሱት ኮምፒውተር ላይ ለመውጣት(log out) ለማድረግ ወደ ፌስቡክ "Security and Login Setting" ሲገቡ ከዚህ በፊት ይገቡባቸው የነበሩ መሣሪያዎችን ዝርዝር የሚያቀርብልዎ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሚፈልጉት መሣሪያ ላይ "Logout" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን መውጣት ይችላሉ፤

4. ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄ ሲላክልዎ አይቀበሉ

#_ጠላፊዎች ሰዎችን ለማጥመድ ሲፈልጉ ሀሰተኛ አካውንት ሊፈጥሩ ይችላሉ፤

#_የጠላፊዎች ጓደኛ መሆን ምን አልባት የእርሶን የፌስቡክ የፊት ገጽን /Timeline/ ሊበክሉ፣ የተለያዩ ጉዳዮችን በገጾ ላይ ሊያጋሩ ወይም በካይ መልዕክቶችን በመልዕክት መቀበያዎ ሊልኩብዎ ይችላሉ፤

5. ከበካይ ሶፍትዌሮች እራሶን ይጠብቁ

#_አጥፊ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተሮች፣ ሰርቨሮች /Server/ ወይም የኮምፒውተር ኔትወርክ ላይ ጉዳት ሊጥሉ ይችላሉ፤

#_የተበከለ ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ምን ዓይነት ባህሪያት እንደሚያሳዩ እና እነዚህን በካይ ሶፍትዌሮችን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ በሚመለከት ያለዎትን እውቀት ያዳብሩ፤

#_ማፈላለጊያዎትን በየጊዜው ያዘምኑ፣ አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን እና የማፈላለጊያ ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ፤

6. አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን /Links/ ከሚያውቁት ጓደኛ ወይም ድርጅት እንኳ ቢላክልዎ ከመክፈት ይቆጠቡ

#_እነዚህ በፌስቡክ ወይም በኢ-ሜይል የሚላኩ ማስፈንጠሪያዎች /Links/ ሊሆኑ ይችላሉ፤

#_ፌስቡክ ወይም Meta የይለፍ-ቃሎን በኢ-ሜይል እንዲያስገቡ በፍጹም እንደማይጠይቅዎ ይወቁ፤

#_አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያ ሲያጋጥሞ ለፌስቡክ ሪፖርት /report it/ ያድረጉ፤

7. ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ መንገዶችን ይተግብሩ

#_ከማይታወቁ አድራሻዎችና መሣሪያዎች ወደ አካውንትዎ የመግባት ሙከራ ሲደረግ የጥቆማ መረጃ እንዲደርሶ /get alerts about unrecognized logins/ ያድረጉ፤

#_ባለሁለት ደረጃ የማንነት ማረጋገጫ ዘዴ /Set up two-factor authentication/ ይጠቀሙ፤

#_ሌሎች የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የፌስቡክ Help & Support ላይ በመግባት ያለዎትን ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

https://t.me/GudayAsfetsami
#Share
Muktarovich O.
በተንቀሳቃሽ ስልኮቻችን አማካኝነት የሚፈጸሙ የማጭበርበር ተግባሮች

በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት የሚፈጸሙ የማጭበርበ ተግባራት በስልኮቻችን አማካኝነት በተጠቃሚዉ ላይ የሚቃጣ የጥቃት አይነት ነው፡፡

የጥቃቱ መነሻም የምንጠቀምባቸዉ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ከሲም ካርድ ጋር ግንኙነት በሚፈጥርበት ጊዜ እንዲሁም ከበይነመረብ ጋር በሚገናኝበት ወቅት የሚፈጸሙ የማጭበርበር አይነቶች ናቸዉ።

በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ከሚፈጸሙ የማጭበርበሪያ መንገዶች መካከል የሚከተሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ ፦

👉 በስልኮቻችን ላይ ያልተሳኩ ጥሪዎችን በማድረግ( (Missed call) የሚፈጸም ማጭበርበር

ይህ አይነት የማጭበርበር ወንጀል መልሰዉ የይደዉሉልኝ ጥሪ በማስመሰል እና ተጠቃሚዎች መልሰው እንዲደዉሉላቸው በማድረግ ያላቸዉን ሂሳብ በሰከንድ የመዉሰድ ስልት ነዉ።

👉 በአላስፈላጊ መልክቶችን በማጥለቅለቅ የሚፈጸም ማጭበርበር ፦ ይህ ደግም በጣም ብዙ መልክቶችን በመላክ የሚመጣ የማጭበርበር ስልት ሲሆን ከመልክቶችም መካከል እንደ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፣ ሎተሪ ደርሷችኋል፣ ስኮላርሽፕ እና የመሳሰሉትን መልክቶች በመላክ ደንበኞች መልሰው እንዲልኩ፣ እንዲደዉሉ በማድረግ ሚስጥራዊ መረጃን መመንተፍ፣ ሂሳብን መዉሰድ እና ሌሎችን ድርጊቶች በማድረግ የሚፈጸም የማጭበርበር ወንጀል ነዉ።

👉 በቀጥታ በመደወል / direct call /፦ በቀጥታ በመደወል ከትክክለኛ ሰዉ ወይም ከትክክለኛ ድርጅት እንደተደወለ በማስመሰል የተለያዩ መረጃዎችን/ፋይሎችን/ዶክመንቶችን መስረቅ፣ማንነታችን የማጣራት፣ የተለያዩ ሚስጢራዊ ኮዶችን፣ አካዉንቶችን፣ የይለፍ ቃሎችን የመመንተፍ እንዲሁም በዚህ አካዉንት ብር መላክ አለብዎ ምክንያቱም ስኮላር ደርሶዎታል ፣ ሎተሪ ደርሶዎታል እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች በመጠቀም የሚፈጸም የማጭበርበር ስልት ነው፡፡
Source: INSA
#Share ላልሰማ ያሰሙ #ሼር
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
በሲም ካርዳችን ወንጀል ከሚሰሩና ከሚዘርፉ አጭበርባሪዎች ራሳችን እንዴት እንጠብቅ?

የሰዎችን የስልክ ቁጥር የራስ በማስመሰል የሚሰሩ የማጭበርበር ወንጀሎች መበራከታቸው ተነግሯል።

ይህን ስራ የሚሰሩት አጭበርባሪዎች ወደ ቴሌኮም ኩባንያ በመደወል ስልካቸው እንደተሰረቀ ወይም እንደተበላሸ በመንገር የሰዎችን ስልክ ቁጥርን ወደራሳቸው በማዞር ነው ገንዘብ እና ግላዊ ሚስጥሮችን የሚመነትፉት።

የስልክ ቁጥሩ ባለቤት ስልኩ እጁ ላይ እያለ የሚደወሉ ስልኮች እና መልዕክቶች በአጭበርባሪዎቹ እጅ የሚገባ ሲሆን ቀጥሎም የባንክ እና ዲጂታል መገበያያ መተግበርያ የይለፍ ቃሎችን በመቀየር አጭበርባሪዎቹ ያሻቸውን ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ለዚህ ጥቃት የሚያጋልጡ ምክንያቶችን እና የጥንቃቄ እርምጃዎችን በዝርዝር ያንብቡ፦ https://bit.ly/4bDdidL