አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ከክስ በፊት እግድ ትዕዛዝ እንዲሰጥልን በሚል የሚቀርብ አቤቱታ ተከሳሽ የሆነ ወገን ላይ ያልተገባ የመብት ገደብ እንዳይደረግበት ጊዚያዊ እግድ የሚጠይቀው ወገን ክስ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ እንደሆነና ለክስ ዝግጅቱም ተጨማሪ ጊዜ የሚያስፈልግበትን ምክንያት ማስረዳት የሚጠበቅበት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ክሱ እስኪቀርብ ድረስ የዕግድ ትዕዛዙ ባይሰጥ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ማሳየትና ማረጋገጥ የሚጠበቅበት ሲሆን ፍርድ ቤቱም ክሱን ለማቅረብ የሚያስፈልገውን ምክንያታዊ ጊዜ ብቻ በመወሰን የእግድ ትዕዛዝ ሊሰጥ የሚገባ ስለመሆኑ በሰ/መ/ቁ.191402 ቅፅ 25 ላይ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።
💎💎💎💎💎💎✏️✏️✏️

አመልካች በሠበር አቤቱታው ለግልግል ጉባዔ የሚገቡንን ክፍያዎች በተመለከተ ክስ እስከምናቀርብ ድረስ ዋስትናዎች እንዳይከፈሉ ታግዶ እንዲቆይ ሊደረግ ይገባል ያለ በመሆኑ ለክርክሩ አወሳሰን ዋናው ጭብጥ ክስ ባልቀረበበት ሁኔታ የእግድ ጥያቄ ሊቀርብ ይችላልን? ዋስትናዎቹ ያለቅድመ ሁኔታ የሚከፈሉ መሆናቸው ሲታይ እግድ ሊሰጥባቸው ይችላል ወይስ አይችልም? የሚለውን መመርመር ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ 1ኛ ተጠሪ የሚከራከረው የእግድ ጥያቄ የሚቀርበው ዋና ክርክር ወይም ክስ ኖሮ ክርክሩ በፍርድ ቤት እስኪወሰን ድረስ ለጊዜው የሚሰጥ ትዕዛዝ ነው፡፡ ዋና ክርክር በሌለበት ገና ለገና ጉዳዩ በግልግል እስኪታይ ድረስ እግድ ይሰጥልኝ ብሎ ዳኝነት መጠየቅ በሕግ ያልተፈቀደ ነው በማለት ነው፡፡


እግድ በሠው የንብረት መብት አጠቃቀም ላይ ገደብ የሚፈጥር ነው፡፡ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 40(1) ላይ ጥበቃ የተደረገለት ንብረት መብት ላይ ገደብ ለማድረግ ደግሞ በሕግ በግልጽ በተመለከተ፣ ውስን ጉዳይና አፈጻጸሙም መብቱን መልሶ የመውሰድ ያህል ውጤት በማይፈጥር ሁኔታ ውስጥ ብቻ ሊሆን ይገባል የሚለው ስለሠብዓዊ መብት ጥበቃ የተደረጉ የሥምምነት ድንጋጌዎች ሆነ በሕገ-መንግሥቱ ውስጥ የተቀረጸ የሕግ መርሕ ነው፡፡ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 151 መሠረት ከፍርድ በፊት ንብረት ተከብሮ እንዲቆይ (attachment) የሚደረግበትን ሥርዓትና ሁኔታ የሚመለከተው ሆነ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 154 መሠረት ነገሩ በፍርድ እስኪወሰን ወይም ሌላ ትዕዛዝ እስኪሰጥ ድረስ ንብረቱ እንዳለ እንዲቆይ፣ ከመጥፋት እንዲድን ወይም እንዳይበላሽ፣ ለሌላ ሰዉ ተላልፎ እንዳይሰጥ፣ ወደ ሌላ ስፍራ እንዳይዛወር ወይም እንዳይባክን የእግድ ትዕዛዝ የተጠየቀው ለጥያቄው መሠረት የሆነው ክስ ቀርቦ ከሆነ እግድ መሰጠቱ የተከሳሹ ወገን የንብረት መበት አጠቃቀም ላይ የሚያስከትለውን ውጤት በመረዳት በጥንቃቄ መታየት ያለበት ነው፡፡


የእግድ ትዕዛዝ በመርሕ ደረጃ የቀረበ ክስን መሠረት ያደረገ እና በሥነ-ሥርዓት ሕጉ አግባብ በተመለከቱት መስፈርቶች የሚሰጥ ነው፡፡ ዓላማው ደግሞ ክሱ ያለ ውጤት እንዳይቀርና ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜም የሚፈጸምበት ንብረት እንዲኖርና ዜጎች መብታቸውን ማስከበር የሚችሉበትን ዕድል የሚፈጥርና በሂደቱም ፍርድ ቤቶች ላይ ያላቸውን እምነት የሚጨምር ነው፡፡ በመሆኑም ሠዎች ክስ ከማቅረባቸው በፊት ነገር ግን በክስ ዝግጅት ላይ እያሉ ተከሳሽ የሚሆነው ወገን ጉዳዩን በመረዳት ክስ ሲቀርብ ክሱ ውጤት እንዳይኖረው በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 154(ለ) እንደተመለከተው ተግባሮችን እየፈጸመ ከሆነ፤ ተግባሩን አለመከላከል ሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተቀረጸበትን ዓላማ እንዳይሳካ ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን እግዱ እንዲሰጥ የተጠየቀው ክስ ሳይቀርብ ከሆነ ተከሳሽ የሚሆነው ወገን ላይ ያልተገባ የመብት ገደብ እንዳይደረግበት፤ ጊዜያዊ እግድ የሚጠይቀው ወገን ክስ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ እንዳለ፣ የክስ ዝግጅቱ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈለገበትን ምክንያት፣ ክሱ እስኪቀርብ ድረስ የእግድ ትዕዛዙ ባይሰጥ የሚያስከትለው ጉዳት ማሳየት ያለበት ሲሆን ፍርድ ቤቱም ክሱን ለማቅረብ የሚያስፈልገውን ምክንያታዊ ጊዜ ድረስ ብቻ በጊዜ ገደብ የተገደበ የእግድ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡
በሰ/መ/ቁ.191402 ቅፅ 25 ላይ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።

Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
https://t.me/AleHig
#የሕግ_እውቀት alehig.com
#አለሕግ #ህግ #ሰበርመዝገብ #ቁጥር #191402 #የሕግ_መረጃ #እግድ
👍188
#የፍርድ_ቤቱን_ውሳኔ_አጥብቄ_የምቃወም_ቢሆንም_እቀበላለሁ ፣ የዚህን ውጤት የመጨረሻነት ተቀብያለሁ ፤ እንደ ህዝብ ለአንድነታችን እና ለዲሞክራሲያችን ጥንካሬ ስል እሺ እላለሁ።"
ይህን ታሪካዊ ንግግር ያደረገው ለ43ኛ የአሜሪካን ሀገር ፕሬዚዳንትነት ከ ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ ጋር የተወዳደረው እና በጠቅላይ ፍርድ ቤት ብይን 5 -4 በሆነ ድምጽ የተወሰነበት #አል_ጎር ነበር!

ጉዳዩን እንበልጥጠው!

ፍሎሪዳ በአሜሪካ ካሉ ግዛቶች ውሰጥ የምትገኝ እና በፕሬዝዳንትነት ምርጫ ላይ ሁነኛ ሚና ከሚጫወቱ እና ወሳኝ ከሚባሉ ግዛቶች አንዷ ናት ።
ግዛቷ ውስጥ አንድ ሕግ አለ በከባድ ወንጀል የተፈረደበት እና መሰየም ያልተደረገለት ሰው የመምረጥ መብት ይነፈጋል ።

በምርጫው ጊዜ ከዚህ በፊት ወንጀል ሰርተዋል ተብሎ በ Database ተመዝግቦ የሚገኙ ሰዎች ስም ከሌሎች ወንጀል ካልሰሩ ሰዎች ፤ እንዲሁም ወንጀል ቢሰሩም የመምረጥ መብትን ከማያስከለክሉ ቀላል የወንጀል ዓይነት ከሰሩ ሰዎች ጋር የስም መመሳሰል በመፈጠሩ በግዛቲቱ ወደ 91,000 ሰዎች እንዳይመርጡ ተደርገዋል ።

እነዚህ የስም መመሳሰሎች ደግሞ ጥቁር አሜሪካዊያን እና አል ጎርን ይመርጣሉ ተብሎ የሚጠበቁ ሰዎች እንደሆኑም ይገለጻል ፤ ይህ ውጤት አጠቃላይ የምርጫ ውጤትም ላይ ጥላ አጥልቶ ነበር ፤ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ በኋላ በመካከላቸው የነበረውን ልዩነት እንመልከት

ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ 2,912,790
አል ጎር 2,912,253
ልዩነት 537 ድምጽ ብቻ
91,000 ሰው በስም መመሳሰል ባይወገድ እና አል ጎርን ቢመርጥ ወይም አብዛኛው አል ጎርን ቢመርጥ በአሜሪካን ታሪክ አል ጎር 43ኛ ፕሬዚዳንት ይሆን ነበር ።

የስም መመሳሰልን ጉዳይ እናፍታታው ።

በፍሎሪዳ ግዛት ውስጥ ወንጀል ከሰራህ ስምህ ዳታቤዝ ላይ ይመዘገባል ፤ በተለይም ከባድ የሚባሉ ወንጀሎቹን ከሰራህ የመምረጥ መብትህ ይነፈጋል ዳታ ቤዝ ላይ Flagged 🛑 ይደረጋል ።

ለምሳሌ 1.Alex L.Smith (ከባድ ወንጀል የሰራ)
2.Allex A.Smith (ወንጀል ያልሰራ) ግን በስም መመሳሰል ከምርጫ የተወገደ

እንግዲህ በዚህ መልክ ሀቁን ያጣው አል ጎር ፤ ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ "ምንም ጥርጥር አይኑር፣ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አጥብቄ ባልስማማም እቀበላለሁ" በማለቱ ይህ ንግግሩ ለፍርድ ቤቱ የሰጠው ቦታን በማመልከት ታሪካዊ ንግግር ሊባል ችሏል ፤ ከግል ምኞቱ በላይ የሀገሪቱን መረጋጋት በማስቀደም ሕገ መንግሥታዊ ቀውስ እንዳይፈጠር ረድቷል ተብሎም ተንቆለጳጵሷል ።

#ወደ_መልዕክቴ_ልምጣ👇

የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 79 ንዑስ አንቀጽ 2 እና 3 እንደሚከተለው ይነበባል ።

2. በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግሥት አካል፣ከማንኛውም ባለሥልጣን ሆነ ከማንኛውም ሌላ ተጽዕኖ ነጻ ነው፡፡
3. ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነጻነት ያከናውናሉ፡፡ ከሕግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም፡፡

ፍርድ ቤቶቻችን ላይ ችግር የለውም ካላችሁ 10 ገጽ የሚሆኑ ችግሮችን ልጽፍላችሁ እችላለሁ የ አስፈጻሚው አካል ጣልቃ ገበነት ፣ ሙስና ፣ የዳኞች ብቃት ማነስ ፣ የዳኞች ክፍያ ማነስ ለስራው ተነሳሽነት እንዲያጡ ማድረግ ፤ በቴክኖሎጂዎች አለመታገዝ..........

ግን ከእነዚህ ሁሉ ችግሮችም ጋር በቻልነው አቅም የፍርድ ቤቱን ገለልተኝነት እናክብር ፤ ፍርድ ቤቶችን ከአስፈጻሚው አካል ከጫና ነጻ እንዲሆኑ እንስራ ፤ በሕግ እና በሕግ ብቻ እንዲመሩ እናበረታታ ፤ ስነ ምግባር የጎደላቸውን ዳኞችን በሕጉ መሰረት እንቅጣ ፤ ፍርድ ቤት የሕዝብ አመኔታ የሚጣልበት ተቋም ስህተት ቢሰራም እንኳን ሕጉ ባስቀመጠው በራሱ ሰንሰለት የሚስተካከልበት ተቋም እንጂ የሕዝብ የጩኸት ምንጭ እንዳይሆን እንተባበር እንጂ የማንም አካል ጣልቃ ገብነትን አንሻት አንመኝ! ምክንያቱም ውጤቱ ከዚህም እጅግ የከፋ ነውና! አበቃሁ!
#ሰላም ✌️
Abebayehu Geta Enaro
መምህር ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
Alternative legal enlightenment & Service
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
https://t.me/AleHig
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_እውቀት alehig.com
#አለሕግ #ህግ #ሰበርመዝገብ #ሕግ_መረጃ #እግድ
22👍2
1. በቂ የወንጀል ጥርጣሬ መኖሩ ተጣርቶ በፓሊስ የወንጀል ምርመራ ይጀመርበታል ፣
2. የምርመራ መዝገቡ ለአቃቤሕግ ከተላከ በሁላ ፣ ለመክሰስ የሚያስችል ማስረጃና የሕግ መሰረት መኖሩ ሲረጋግጥ ክስ የመስረትበታል ፣ ካልሆነ መዝገቡ ይዘጋል ፣
3. ፍ/ቤት ክሱ እንዲደረሰው ትእዛዝ ከስጠ በሁላ ይሄው ደርሶት እራሱን ለመከላከል እድል ይስጠዋል
4. አቃቤሕግ መጀመሪያ ማስረጃውን ያሰማል ፣
5. ፍ/ቤቱ የአቃቤ ሕግን ማስረጃ ከሰማ በሁዋላ ፣ ተከላከል ይለዋል ፣ ወይም መከላከል ሳያስፈልገው በነጻ ያሰናብተዋል ፣
6. ተከላከል ከተባለ ፣ አለኝ የሚለውን መከላከያ አቅርቦ ያሰማል ፣ ይከራከራል ። መከላከል መስረታዊ መብት ነው ፣
7. ተከላከል ከተባለ በሁዋላ ፍ/ቤቱ ጥፋተኛ ሊለው ወይም በነጻ ሊያሰናብተው ይችላል ፣

አንድ ሰው ወንጀል ፈጽሞ ጥፋተኛ ተባለ የሚባለው በዚህ ሂደት ውስጥ አልፎ ነው ። ክስ ከተመሰረተበት በሁዋላ እንኩዋን በሁለት የስነ ስርአት ደረጃዎች ነጻ የመባል እድል አለው ። ማንኛችንም ነገ በሆነ አጋጣሚ በሰውየው ቦታ ልንሆን እንችላለን ። ሕግ የስጠውን መብት እናክብርለት ፣ ቀድሞ ፈራጅ አንሁን ፣ ውጤቱን እንጠብቅ ።

፣ ከማስታወሻዬ ፣ በአንድ ወቅት ...

እነ እገሌ ፣ በቢሊዮን ብር ዘረፉ ተባለ ። ተራገበ ፣ ተጋነነ ፣ ብዙ ተጮህ ። ተጠርጣሪዋቹ ፣ ቤተሰብ ፣ ወዳጅ ዘመዳቸው አፈረ ፣ አንገቱን ደፋ ። ብዙ ሰው በየቤቱ ሰምቶ አዘነባቸው ፣ እነዚህን መግደል እንጂ የምን ክስ ምናምን ነው ተባለ ፣ እኛ ጠበቆቹም ተሰደብን ፣ ሞራል የሌላችው ፣ እንዴት ለነዚህ ይቆማሉ ተባልን ።

ክስ ተመሰረተ ፣ ወሬውና ክሱ አይገናኝም ፣ ክሱና እውነታው አይገናኝም ። እናም ፣ ቆይቶ ፣ ሰዎቹ እንዲከሱ ይፈለግበት የነበረው ፓለቲካ ሲለወጥ ፣ ክሳቸው ተነሳ ።

ዝርዝሩን ሳናውቅ ለመፍረድ አንቸኩል ። ብዙ በተዋራባቸው የወንጀል ጉዳዮች ላይ በጠበቃነት ተሳትፌአለሁ ። በአብዛኛው ግነቱና እውነቱ አይገናኝም ። ሰከን ማለት ፣ ግራ ቀኙን መስማት ፣ ማገናዘብ ፣ ከስሜታዊ ፈራጅነት መቆጠብ ጥሩ ነው ... የወንጀል ምርመራውን ለፓሊስ ፣ የክሱን ጉዳይ ለአቃቤሕግ ፣ ዳኝነቱን ለፍ/ቤት እንተወው ....

መልካም ቀን ። በአበበ አስማረ
Alternative legal enlightenment & Service
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
https://t.me/AleHig
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_እውቀት alehig.com
#አለሕግ #ህግ #ሰበርመዝገብ  #ሕግ_መረጃ #እግድ
👍106🙏1
ህግ ትምህርት ቤት እያለሁ ስለ መሰማት መብት "right to be heard" ስንማር መምህሬ የነገረን ሁሌም የማስታውሳት አንድ እውነታን ደጋግሞ ይነግረን ነበር።
ሁሉን አዋቂው(Omniscience ) የሆነው እግዚአብሄርም አዳም ፍሬውን እንደበላ እያወቀ እንኳ "...ፍሬውን በላህ ወይ..."በማለት ጠይቆ የአዳምን የመሰማት መብቱን አክብሮለት ነበር ይለናል። እውነት ነው። አምላክ የመሰማትን መብት አልነፈገም። በፍጥረት ጅማሬ ያከበረው መብትም ይሄን መብት ይመስለኛል።ብሄራዊ ጀግናችን ገለቴ ቡርቃ በህይወቷ ስለሆነው ነገር ባዝንም በዛኛው ወገን ያለው ሳልሰማ አስተያየት መስጠት አልፈልግም። ሁሉም ወገን ይሰማ ከማለት ውጪ።ከሁለት ወገን ሳይሰሙ ከውሳኔ መድረስ የደቦ ፍርድ ነው።

- ብስራት መለሰ (ጋዜጠኛ)
Alternative legal enlightenment & Service
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
https://t.me/AleHig
https://linktr.ee/alehig
alehig.com
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_እውቀት #አለሕግ #ህግ #ሰበርመዝገብ #ሕግ_መረጃ #እግድ
37👍19🥰4👏1
በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ላይ የተደቀኑ ስጋቶች፣

ዓለም አቀፍና የሕገ-መንግስት ብርሃን ውስጥ ሲፈተሽ በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ሥራ ላይ የዋለው በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ ማስመሰልን እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከል የወጣው አዋጅ፣ ከአገራዊ የሕገ-መንግስት ድንጋጌዎችና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕጎች አኳያ ሲታይ በርካታ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ሆኖ አግኝተነዋል። በተለይም "በሽፋን ስር ምርመራ የሚያደርጉ መርማሪዎች ከግድያ ውጪ በሆነ በማንኛውም ወንጀል ተጠያቂ እንደማይሆኑ" የሚያዘው ድንጋጌ፣ የሕግ የበላይነትን እና የሰብዓዊ መብቶችን መርሆዎች አደጋ ላይ የሚጥል ነው የሚሉ አስተያየቶች በስፋት እየተሰሙ ነው።

#የኢትዮጵያ_ሕገ-መንግስት እና #የአዋጁ_ተግዳሮቶች
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት፣ በመሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ዙሪያ ሰፊ ድንጋጌዎችን አስቀምጧል። በተለይም አንቀጽ 13 የመንግስት አካላት ሁሉ በሕገ-መንግስቱ የተደነገጉትን የሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች የማክበርና የማስከበር ግዴታ እንዳለባቸው ይደነግጋል። አንቀጽ 14 የሰብዓዊ ክብርን፣ አንቀጽ 15 የሕይወት መብትን፣ አንቀጽ 16 የአካል ደህንነት መብትን፣ አንቀጽ 17 የነጻነት መብትን፣ አንቀጽ 18 ደግሞ ጭካኔ የተሞላበት፣ ኢ-ሰብዓዊ ወይም አዋራጅ ቅጣት ወይም አያያዝን ይከለክላል።
አዲሱ አዋጅ "መርማሪዎች ከግድያ ውጪ በማንኛውም ወንጀል አይጠየቁም" በሚለው ድንጋጌው፣ እነዚህን የሕገ-መንግስት መርሆዎች የሚጻረር ነው የሚል ጠንካራ መከራከሪያ ይቀርባል። አንድ መርማሪ ገንዘብ በመቀበል፣ ንጹሃንን በማሰቃየት ወይም ሌላ የመብት ጥሰት በመፈጸም ተጠያቂነትን የሚያመልጥ ከሆነ፣ የሕገ-መንግስቱ የመብቶች ጥበቃ ዋጋ የለውም የሚል ስጋት ይፈጠራል። ይህ ድንጋጌ ለሙስና፣ ለሥልጣን አላግባብ መጠቀም እና ለሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ክፍት በር ሊከፍት ይችላል።

#ዓለም_አቀፍ_ሕጎችና_ስምምነቶች
ኢትዮጵያ በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶችንና ኮንቬንሽኖችን አጽድቃለች።

ከእነዚህም መካከል፡-
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር (UN Charter): ይህ ቻርተር የሰብዓዊ መብቶችን ማክበር እና ማስከበር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መሰረታዊ ዓላማዎች አንዱ እንደሆነ ይገልጻል።

ዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን (International Covenant on Civil and Political Rights - ICCPR): ኢትዮጵያ ይህን ቃል ኪዳን አጽድቃለች። ቃል ኪዳኑ በግልጽ የሕይወትን፣ የነጻነትን፣ ከማሰቃየት የመጠበቅን እና የሕግ ፊት እኩልነትን መብቶች ያስቀምጣል። የትኛውም አገር ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል ሰበብ እነዚህን መሰረታዊ መብቶች መርገጥ እንደሌለበት ዓለም አቀፍ ሕግ ያዛል።

የማሰቃየትን እና ሌሎች ጭካኔ የተሞላባቸው፣ ኢ-ሰብዓዊ ወይም አዋራጅ ቅጣቶችን ወይም አያያዞችን የሚከለክል ኮንቬንሽን (Convention Against Torture and Other Cruel, Inhuman or Degrading Treatment or Punishment - CAT): ኢትዮጵያ የዚህ ኮንቬንሽን አባል ስትሆን፣ ማሰቃየትን በማንኛውም ሁኔታ ለመከልከል እና ወንጀለኞችን ተጠያቂ ለማድረግ ግዴታ አለባት። አዲሱ አዋጅ "መርማሪው ማሰቃየት ቢፈጽም አይጠየቅም ማለት ነው?" የሚለው ስጋት፣ የዚህን ኮንቬንሽን መርሆዎች የሚጻረር ነው።
በተጨማሪም፣ ገንዘብ ሕገወጥ የማድረግ (Money Laundering) እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት (Terrorist Financing) ወንጀሎችን ለመዋጋት የወጡ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ቢኖሩም፣ እነዚህ ስምምነቶች ወንጀልን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ አበክረው ያሳስባሉ። የፋይናንስ ተግባር ግብረ ኃይል (Financial Action Task Force - FATF) ያሉ ድርጅቶችም ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመዋጋት የሚረዱ ደረጃዎችን ሲያወጡ፣ የሕግ የበላይነትን እና የመብቶችን ጥበቃ ግምት ውስጥ ያስገባሉ።

#የሞራል_ሕግ_እና_የሕግ_የበላይነት
ከሕግ በላይ የሆነ የሞራል ሕግ አለ የሚለው መርህ በበርካታ ፍልስፍናዎች እና የሕግ አስተምህሮዎች ዘንድ ተቀባይነት አለው። ይህ ማለት አንድ ሕግ በጽሑፍ ቢቀመጥም፣ ዓለም አቀፍ የሞራል እና የፍትህ መርሆዎችን የሚጻረር ከሆነ ተቀባይነት የለውም። "ከግድያ ውጪ በሌላ ወንጀል አይጠየቅም" የሚለው ድንጋጌ፣ የሕግ የበላይነትን እና የፍትህን መሰረታዊ መርሆዎች የሚዳፈር በመሆኑ፣ በብዙዎች ዘንድ የሞራል ብቁነት የለውም የሚል ትችት ይቀርብበታል። የሕግ የበላይነት ሁሉም ሰው ከሕግ በታች እኩል ነው የሚለውን መርህ ያመለክታል፤ የመርማሪዎችን ተጠያቂነት ማስቀረት ይህን መርህ ይጥሳል።

#የመናገር_እና_የመሰብሰብ_ነጻነት
አዋጁ በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በጋዜጠኞች እና በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ ጫና ይፈጥራል የሚለው ስጋትም ትልቅ ቦታ አለው። የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 29 የመናገር እና የመግለጽ ነጻነትን፣ አንቀጽ 30 የመሰብሰብ፣ የመመደብ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትን ያረጋግጣል። አዋጁ ከእነዚህ መብቶች ጋር እንዴት እንደሚጣጣም ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ያስፈልገዋል። የመንግስት ተቃዋሚዎችን ወይም ሕጋዊ በሆነ መንገድ የፖሊሲ ትችት የሚያቀርቡ አካላትን "ሽብርተኝነትን መርዳት" በሚል ሰበብ ኢላማ ለማድረግ የሚያስችል ክፍተት እንዳለው የሚሰጋ ከሆነ፣ ለዴሞክራሲያዊ ምህዳር መስፋፋት እንቅፋት ይሆናል።
መደምደሚያ
ሽብርተኝነትን እና ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን መዋጋት የማንኛውም ሉዓላዊ መንግስት ሕጋዊ ግዴታ እና የዜጎች ደህንነት ጉዳይ ነው። ይሁን እንጂ፣ ይህ ትግል የዜጎችን መሰረታዊ መብቶች እና የሕግ የበላይነት መርሆዎችን ሳያጓድል መከናወን ይኖርበታል። አዲሱ አዋጅ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕጎችን እና የኢትዮጵያን ሕገ-መንግስት መሰረታዊ ድንጋጌዎችን የሚያከብር መሆኑን ለማረጋገጥ፣ ሰፊ ውይይት እና ምናልባትም ክለሳ ሊደረግበት ይገባል። አለበለዚያ፣ ሕግን ለማስከበር በሚል የሚወጡ ሕጎች ራሳቸው ለሕገ-ወጥነት በር ከፍተው የሞራል እና የሕግ ቀውስ ሊፈጥሩ ይችላሉ።

እናንተስ፣ አዲሱ አዋጅ የሀገራችንን ሕገ-መንግስት እና ዓለም አቀፍ ሕጎችን ያከብራል ብላችሁ ታስባላችሁ?

የህዝብ ጤና የሀገር ጤና ነው!

በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
ሚኪያስ መላክ ተዘጋጅቶ በአለሕግ አማራጭ የሕግ እውቀት እና አገልግሎት ቀረበ ነው።
Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_መረጃ https://t.me/AleHig
#የሕግ_እውቀት alehig.com
#AleHig #አለሕግ #አለሕግ #ህግ
10
#የአዋጁ_አስፈላጊነትና_የሕግ_ከለላ_ስጋቶች
የፍትህ ሚኒስቴር የአዋጅ ቁጥር 1387/2017ን በተመለከተ ማብራሪያ ቢሰጥም፣ የሕጉ አተገባበር በዜጎች መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች እና የሕግ የበላይነት ላይ ሊያስከትል የሚችለው ተጽእኖ አሁንም አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል። "አላምንም" የሚለው ምላሽዎም፣ በዚህ አዋጅ ዙሪያ ያለውን ሰፊ አለመተማመን የሚያንፀባርቅ ነው።

#እስቲ_ይህንን_ስጋት በዝርዝር እንመልከት።

#የአዋጁ_አስፈላጊነትና_የሕግ_ከለላ_ስጋቶች
አዋጅ ቁጥር 1387/2017 የወንጀል ድርጊት ማትረፍ እንደማይቻል ለማረጋገጥ፣ የገንዘብ ሕገወጥነትንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከል ያለመ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር ያብራራል። አዋጁ ከቀድሞው አዋጅ ቁጥር 780/2005 በተሻለ መልኩ 21 አመንጪ ወንጀሎችን በዝርዝር ማካተቱ፣ ጠንካራ የአሰራር ስርዓት ማበጀቱ እና የዋና ተጠቃሚዎችን ማንነት የመለየት ሥርዓት መዘርጋቱ፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል ከዓለም አቀፍ መስፈርቶች ጋር ለመጣጣም ጠቃሚ እርምጃዎች ናቸው።
ሆኖም፣ የአዋጁ ዋነኛ አወዛጋቢ ነጥብ "በሽፋን ስር ምርመራ" ለሚያካሂዱ መርማሪዎች የሚሰጠው የሕግ ከለላ (Immunity) ነው። ሚኒስቴሩ ይህ ከለላ የሚሰጠው መርማሪው "በራሱ ፈቃድ አስቦና ፈቅዶ ሳይሆን ያለፈቃዱ፣ ተገዶ፣ በተጽእኖ፣ ወይም ከአቅሙ በላይ በሆነ ማንኛውንም ምክንያት ሌላ ከባድ ጉዳትን ለማስቀረት ወይም የተሰጠውን ሕጋዊ ተልእኮ ለማሳካት ሲል" ለሚፈጽመው ወንጀል መሆኑን ቢያብራራም፣ ይህ ትርጓሜ በተግባር አደገኛ ስጋቶችን ይዞ ይመጣል።

#የግዳጅ" ትርጓሜ ብዥታ እና የተጠያቂነት ክፍተቶች
የ"ግዳጅ" የሚለው ቃል አተረጓጎም እና አተገባበር አሁንም ግልጽ አይደለም። መርማሪው በእርግጥ ተገዶ ነው ወይስ በፈቃደኝነት ወንጀል የፈጸመው? ይህንን ለመወሰን የሚያስችል ግልጽ፣ ተጨባጭ እና ገለልተኛ የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓት ከሌለ፣ የሕግ ከለላው ለሥልጣን አላግባብ መጠቀም ምቹ ሽፋን ሊሆን ይችላል። ሕግን አስከባሪ አካላት ራሳቸው ለሕግ ተገዢ መሆናቸውን ማረጋገጥ እጅግ አስፈላጊ ነው።

በተጨማሪም፣ አዋጁ "ከግድያ ውጪ" የሚል ገደብ ቢያስቀምጥም፣ እንደ ማሰቃየት፣ ሕገወጥ እስር፣ ከሕግ ውጪ የሆነ የገንዘብ ዝውውር እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመርማሪዎች ቢፈጸሙ፣ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥበት መንገድ ምን ያህል ጠንካራ ነው የሚለው ጥያቄ መልስ አላገኘም። የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት (አንቀጽ 18) ከጭካኔ የተሞላበት፣ ኢ-ሰብዓዊ ወይም አዋራጅ ቅጣት የመጠበቅ መብትን ይደነግጋል። ኢትዮጵያ የፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕጎች፣ በተለይም የማሰቃየትን የሚከለክል ኮንቬንሽን (CAT)፣ ማሰቃየትን ጨምሮ ማንኛውንም ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ይከለክላሉ።
"በግዳጅ ተደረገ" በሚል ሽፋን እነዚህ ወንጀሎች ያለ ቅጣት እንዲያልፉ ከተደረገ፣ የአገር ውስጥም ሆነ ዓለም አቀፍ የሕግ ግዴታዎች ይጣሳሉ። ይህ ደግሞ እርስዎ የገለጹትን "ሕጋዊ ህገወጥ" ተግባራት መራባት ያስከትላል።

#ዲሞክራሲያዊ ምህዳር እና #የሕግ_የበላይነት_ስጋት
አዋጁ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ያለመ ቢሆንም፣ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ኢላማ ለማድረግ የሚያስችል ክፍተት እንዳለው የሚሰነዘረው ስጋት ተገቢ ነው። የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት (አንቀጽ 29 እና 30) የመናገር፣ የመሰብሰብና የመደራጀት መብቶችን በግልጽ ያረጋግጣል። ማንኛውም ሕግ እነዚህን መብቶች ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ብቻ ሊገድብ ይገባል እንጂ ሊያጠፋ አይገባም። የመንግስት ተቃዋሚዎችን ወይም ሕጋዊ በሆነ መንገድ የፖሊሲ ትችት የሚያቀርቡ አካላትን "ሽብርተኝነትን መርዳት" በሚል ሰበብ ኢላማ ለማድረግ የሚያስችል ክፍተት እንዳለው የሚሰጋ ከሆነ፣ የሀገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በእጅጉ ይጎዳል።

#የሕግ_የበላይነት ማለት ሁሉም ሰው፣ መንግስትንና ባለሥልጣናትን ጨምሮ፣ ለሕግ ተገዢ ነው ማለት ነው።

አዋጁ ለመርማሪዎች የሚሰጠው ልዩ የሕግ ከለላ፣ ይህንን መርህ የሚሸረሽር እና ከመደበኛ የፍትህ ሥርዓት በላይ የሆነ "ልዩ ሥርዓት" የሚፈጥር ሆኖ ከታየ፣ አለመተማመን መፈጠሩ አይቀሬ ነው። ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የመብቶች ጥሰት እና ተጠያቂነት አለመኖር ሲነሱ የቆዩ ስጋቶች እንደነበሩ ግምት ውስጥ ሲገባ፣ አዲሱ አዋጅ እነዚህን ስጋቶች ይበልጥ የሚያባብስ ነው የሚል ስሜት መፍጠሩ ተፈጥሯዊ ነው።

#የሕግ_ማዕቀፎች የሀገርን ደህንነት ማስጠበቅ ሲገባቸው፣ በተመሳሳይ መልኩ የዜጎችን መብት ዋስትና መስጠት እና የሕግ የበላይነትን ማክበር አለባቸው። አንዱን ለማስጠበቅ ሌላውን መስዋዕት ማድረግ ዘላቂ ሰላምንና መረጋጋትን አያመጣም። የአዋጅ ቁጥር 1387/2017 ተግባራዊነት፣ የመሠረታዊ መብቶችን እና የሕግ የበላይነትን ዋጋ እንዳይቀንስ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ቁርጠኝነት ይጠይቃል። ያለበለዚያ፣ አደገኛ ሁኔታዎችን በመፍጠር ወደ #"ሕጋዊ_ህገወጥ" ድርጊቶች ሊያመራ የሚችልበት ስጋት #አለ
በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
ሚኪያስ መላክ ተዘጋጅቶ በአለሕግ አማራጭ የሕግ እውቀት እና አገልግሎት ቀረበ ነው።
Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_መረጃ https://t.me/AleHig
#የሕግ_እውቀት alehig.com
#AleHig #አለሕግ #አለሕግ #ህግ
13🔥1
በድብቅ የሚደረግ ምርመራ በአዲሱ አዋጅ መሰረት
የፍትሕ ሚኒስቴር በቅርቡ የጸደቀው፣ የወንጀል ንብረትን ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ፣ ከፍርድ ቤት ፈቃድ ውጪ የሚደረግ ምርመራን እንደማይፈቅድ አስታውቋል።
ይህ ማብራሪያ አዋጁን በተመለከተ በሕዝብ ዘንድ ያለውን የተሳሳተ ግንዛቤ ለመፍታት ያለመ ነው።
የፍትሕ ሚኒስቴር ማብራሪያ፦
ሚኒስቴሩ አዲሱ አዋጅ ከመደበኛው የወንጀል ምርመራ ሂደት የተለየ መንገድ እንደሚከተል አጽንኦት ሰጥቷል። እንዲህም ሲል አብራርቷል፦

ከተለመደው ምርመራ የተለየ ነው፡ እንደ ተለመደው ምርመራ፣ ተጠርጣሪዎችን በፍርድ ቤት ትእዛዝ መያዝ፣ ሰነዶችን መሰብሰብ እና ምስክሮችን መስማት የመሳሰሉትን ሂደቶች አይከተልም።

ውስብስብ ወንጀሎች ላይ ያተኩራል፡ አዋጁ ውስብስብ ወንጀሎችን ከመሰረቱ ለመለየት የሚያስችል የምርመራ ሂደትን የሚከተል ነው። ለምሳሌ፣ መርማሪ አካል፡-

እንደ ወንጀለኛ መስሎ ከወንጀለኞች ጋር ሊቀላቀል ወይም አብሮ ሊሰራ ይችላል።

እንደ ተባባሪ መስሎ አብሮ ውሎ ሊያድር ይችላል።

ወንጀለኞች ሲሸጡ ገዢ መስሎ፣ ሲገዙ ደግሞ ሻጭ መስሎ ሊሆን ይችላል።
የፍርድ ቤት ትእዛዝ ሚና፦
የፍርድ ቤት ትእዛዝ ግዴታ ነው፡ መርማሪው አካል ምርመራ ማድረግ የሚችለው የፍርድ ቤት ትእዛዝ ሲያገኝ ብቻ ነው።

የፍርድ ቤት ግልጽ መመሪያዎች፡ ፍርድ ቤት በአሳማኝ ምክንያት በሽፋን የሚደረግ ምርመራ እንዲደረግ ሲፈቅድ፣ አዋጁ በትእዛዙ ላይ የሚከተሉትን በግልጽ ማስቀመጥ እንዳለበት ደንግጓል፦
የምርመራው ዘዴ።
የአተገባበር ሁኔታ።
ምርመራው የሚከናወንበት ጊዜ።
የተሳሳቱ ግንዛቤዎች ማስተባበያ፦
ሚኒስቴሩ ስለ አዲሱ አዋጅ ያሉትን በርካታ የተሳሳቱ ግንዛቤዎችን አስተባብሏል፦

ማሰቃየት ወይም ማስገደድ የለም፡ አዋጁ ተጠርጣሪን አስሮ በማሰቃየት እንዲመረመር አይፈቅድም፣ እንዲሁም ማስረጃዎችን በማስገደድ እንዲሰበሰቡ አያደርግም።
ይህ ፈጽሞ ስህተት ነው።

ለወንጀል ድርጊት ተጠያቂነት፡ አዋጁ ወንጀል ለፈጸሙ መርማሪዎች ያለመከሰስ መብት አይሰጥም። ፍርድ ቤት በአሳማኝ ምክንያት በሽፋን ስር የሚደረግ ልዩ የምርመራ ዘዴ እንዲተገበር ሲፈቅድ፣ መርማሪው በተጠርጣሪዎች ወይም በሌላ ሦስተኛ ወገኖች ላይ ወንጀል ቢፈጽም፣ በወንጀል ይጠየቃል።
መርማሪ ከክስ ነጻ የሚሆንባቸው ሁኔታዎች፦
ሚኒስቴሩ፣ መርማሪ ከወንጀል ክስ ነጻ የሚሆንበትን ልዩ ድንጋጌ አስረድቷል፤ ይህ ግን ወንጀል ለመፈጸም አጠቃላይ ያለመከሰስ መብት አይደለም፦

ይህ ነጻ መሆን የሚመለከተው መርማሪው ከተጠርጣሪዎች ጋር የወንጀል ተካፋይ ወይም ግብረ-አበር ሲሆን፣ ይህን ያደረገው በራሱ ፈቃድ አስቦና ፈቅዶ ሳይሆን፦
ያለፈቃዱ፣
ተገዶ፣
በተጽእኖ፣
በተጠርጣሪዎች ሕገ ወጥ ትዕዛዝ፣ ወይም

ከአቅሙ በላይ በሆነ በማንኛውም ምክንያት ሌላ ከባድ ጉዳትን ለማስቀረት ወይም የተሰጠውን ሕጋዊ ተልእኮ ለማሳካት ሲል ወንጀል የሚፈጽምበት ሁኔታ ሲኖር ነው።
ይህ ድንጋጌ የሚያሳየው መርማሪ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት (ከግድያ ውጪ) ማንኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ከወንጀል ክስ ነጻ የሚደረግበትን ሁኔታ ለማመላከት የተደነገገ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
የሕዝብ ስጋቶች፦
ይህ አዋጅ፣ መርማሪዎችን በአቅማቸው በላይ በሆነ ምክንያት (ከግድያ በስተቀር) ማንኛውንም ወንጀል ቢፈጽሙ ተጠያቂ የማያደርግ መሆኑ፣ ከምክር ቤት ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል። ተቺዎች ይህ ድንጋጌ መርማሪዎችን ወንጀል እንዲፈጽሙ በር ይከፍታል የሚል ስጋት አላቸው።
ይህ የፍትሕ ሚኒስቴር ማብራሪያ፣ በድብቅ የሚደረጉ ምርመራዎች የሚከናወኑበትን ሁኔታዎች እና ገደቦች ግልጽ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፣ የፍርድ ቤት ቁጥጥር ወሳኝ መሆኑን በማጉላት፣ ሊኖር በሚችል አላግባብ አጠቃቀም ዙሪያ የሚነሱ ስጋቶችን ለመፍታት ይሞክራል።
ፍትሕ ሚኒስቴር
በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_መረጃ https://t.me/AleHig
#የሕግ_እውቀት alehig.com
#AleHig #አለሕግ #አለሕግ #ህግ
12👏5
ሕግ ለሰው ልጅ ቀንበር ወይስ አጋዥ?
ሰው ለሕግ ሳይሆን ሕግ ነው ለሰው የተሰጠው፣

ሕግ የተሰራው ለሰው ልጅ ጥቅም እንጂ፣ ሰው ለሕግ ተገዢ እንዲሆን ብቻ አይደለም። ሕግ የሰው ልጅ ሰላማዊና ፍትሃዊ ኑሮ እንዲመራ የሚያግዝ መሳሪያ ነው። በመሆኑም፣ ሕግጋት ሲተገበሩ የሰው ልጅ ክብርና መብት ማስከበር ላይ ማተኮር አለባቸው። ሕጎች የብዙሃንን መብትና ጥቅም የሚያስጠብቁ ሲሆኑ፣ ሕዝቡ ለሕግ የሚኖረው ክብር ይጨምራል።
👍75
ሕግ ማለት ሰውን የሚያንጽ፣ የተሻለ ዜጋ የሚያደርግ፣ የሚያበለጽግ እና ወደተሻለ የኢኮኖሚ ደረጃ ለመድረስ በር የሚከፍት ሥርዓት የሚዘረጋ መሆን አለበት። ሕግ ሰዎች የሚገደቡበት፣ የሚያስጨንቅ፣ የሚያደኸይ፣ የሚጎዳና የሚያንገበግብ መሆን የለበትም። በተሻለ ነፃነት የሚያኖር እና ሕጉን ለሚያከብሩ የሚያበረታታ ሲሆን፣ ለማያከብሩት ግን ደግሞ በተቃራኒው በዋናነት የሚያስተምር ሲሆን ነገር ግን መተላለፉ ሲደጋገም የሚቀጣ መሆን አለበት።
#Mikias_Melak
በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_መረጃ https://t.me/AleHig
#የሕግ_እውቀት alehig.com
#AleHig #አለሕግ #አለሕግ #ህግ
14👍5🤔1
👉👉👉ነገረ ግራ ቀኝ👈👈👈
🔼✔️🔥📣💥

በወንጀል ችሎት:-
✔️ቀኝ:- ዐቃቤ ሕግ (መርማሪ ፖሊስ)
✔️ግራ:- ተጠርጣሪ/ተከሳሽና ጠበቃው

በፍ/ብሔር ችሎት:-
✔️ቀኝ:- ከሳሽ (አመልካች)
✔️ግራ:- ተከሳሽ (መልስ ሰጭ)

ግራ ቀኙ የሚወሰነው ከችሎቱ አኳያ ነው::
(ከችሎቱ በስተቀኝ በስተ ግራ)

ይህ ከችሎት ሥርዓት ድንጋጌዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ባለጉዳዮች ፍ/ቤት ሲቀርቡ ይህን አውቀው መቀመጥና መቆም አለባቸው::
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
11👍6
የንግድ ሥራ ፍቃድ ሳይኖራቸው በሞያ ፍቃድ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ ጠበቆች ፣የኢንሹራንስ ወኪሎች ፣ኢንሹራንስ ጉዳት ገማች ግለሰቦች በሚመለከት:-

➡️ ከግብር አመቱ አጠቃላይ እንደ ገቢ 35 በመቶ እንደ ወጪ 65 በመቶ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ሆኖ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብሩን በማስላት ተወስኖ ገቢው እንዲሰበሰብ።

➡️ የንግድ ሥራ ያልሆነ ገቢ ያላቸው የመኖሪያ ቤት አከራዮች ከግብር አመቱ አጠቃላይ ገቢ 35 በመቶ እንደ ወጪ 65 በመቶ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ሆኖ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብሩን በማስላት ተወስኖ ገቢው እንዲሰበሰብ።

➡️ በግል ኮድ 02 እና በንግድ ኮድ 03 ተሸከርካሪ የኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ አጠቃላይ የኪራይ ገቢ ላይ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት በመረጃ የሚወሰን በመሆኑ ግብሩን በማስላት ተወስኖ ገቢው እንዲሰበሰብ።

➡️ በህግ ደረሰኝ የመጠቀም ግዴታ ተፈጻሚ የማይደረግባቸው የከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች /በቴክኖሎጂ ስምሪት የሚሰጣቸውን የሜትር ታከሲዎች ጨምሮ/ የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 ሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብሩን በማስላት ተወስኖ ገቢው እንዲሰበሰብ መወሰኑን ይገልጻል።

(ተጨማሪውን ከተያያዘው ደብዳቤ ይመልከቱ)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia
Mikias_Melak
በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_መረጃ https://t.me/AleHig
#የሕግ_እውቀት alehig.com
#AleHig #አለሕግ #አለሕግ #ህግ
8👍1
ከውርስ መንቀል (Dishersion)
ከውርስ መንቀል ማለት አንድ ተናዛዥ የውርስ ሕግ በሚደነግገው መሠረት ባደረገው ኑዛዜ ውስጥ፣ ምክንያቱን በግልጽ በመግለጽ ወይም በዝምታ፣ ከወራሾቹ አንዱን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑትን ወራሾች በውርሱ እንዳይካፈሉ ያደረገበት ሥርዓት ነው። ይህ በውርስ ሕግ እውቅና እና ውጤት የሚሰጠው የሕግ ሂደት ነው።
* ከወራሽነት ሙሉ በሙሉ ማውጣት: ከውርስ መንቀል ማለት ከውርስ ሀብቱ ምንም ዓይነት ድርሻ አለማግኘት እንጂ አነስተኛ ድርሻ ማግኘት አይደለም።
* የሕግ ድንጋጌዎች:
* የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 937/1/ ተናዛዡ ከወራሾቹ አንዱን ከወራሽነት የመንቀል መብት እንዳለው ይደነግጋል።
* የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 938/1/ ደግሞ፣ ተናዛዡ ልጅን ወይም ወደታች የሚቆጠረውን ወራሽ ለመንቀል የደረሰበትን ምክንያት በኑዛዜው ውስጥ ካልገለፀ በቀር፣ ያደረገው ኑዛዜ እንደማይፀና ያስቀምጣል። ይህ የሚያሳየው ህጉ የቅርብ ወራሾችን ከውርስ የመንቀል ጉዳይ ላይ ጥብቅ መስፈርቶችን እንዳስቀመጠ ነው።
* ተፈጻሚነት: ይህ እርምጃ ሊወሰድ የሚችለው ሕጉ ወራሾች በሚያደርጋቸው ግለሰቦች ላይ ብቻ ነው። አንድ ግለሰብ የሚወረሰው በ3ኛ ወይም 4ኛ ደረጃ ወራሾች በሚሆኑ ዘመዶቹ ከሆነ፣ ለሌላ ሰው ሲናዘዝ እነዚህን ዘመዶቹን በዝምታ ከውርሱ መንቀል ይችላል።
* አላማ: ከውርስ መንቀል ወራሾችን ከውርስ ሀብት የሚያስወግድ ጠንካራ ውሳኔ ነው። ይህ ውሳኔ በሰከነ አእምሮ እና በቂ ምክንያት መወሰድ እንዳለበት ታሳቢ መሆን አለበት። ያለ በቂ ምክንያት እና በእልህ ወይም በቁጣ ተነሳስቶ የሚደረግ ውሳኔ በዘላቂነት በሰዎች መካከል የስሜት መሻከርን ሊያስከትል ይችላል።

በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ ተዘጋጅቶ በአለሕግ አማራጭ የሕግ እውቀት እና አገልግሎት የቀረበ ነው።
Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_መረጃ https://t.me/AleHig
#የሕግ_እውቀት alehig.com
#AleHig #አለሕግ #አለሕግ #ህግ
12
ከውል ውጪ ስለሚደርስ ጉዳት ካሳ ማወቅ ያለብዎት ነገር
ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል።

እነዚህ ጉዳቶች ከወንጀል ድርጊት፣ ከውል ጥሰት ወይም ከውል ውጪ ከሚመጣ ኃላፊነት ሊነሱ ይችላሉ። የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ የህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ደመቀ ይብሬ እንደሚሉት፣ ከውል ውጪ በሚደርስ ጉዳት ህግ ዋነኛ ዓላማ ጉዳት ያደረሰውን አካል በመለየት ተጎጂው ተገቢውን ካሳ እንዲያገኝ ማስቻልና ሌሎችም ከዚህ እንዲማሩ ማድረግ ነው።

#ጉዳት ምንድን ነው?
የፍትሐ ብሔር ህጉ ለ"ጉዳት" የሚለው ቃል ቀጥተኛ ትርጉም ባይሰጥም፣ ከህጉ አጠቃላይ ይዘት በመነሳት በሰው ጥቅም፣ አካል ወይም ህይወት ላይ የሚደርስ ጉድለት መሆኑን መረዳት ይቻላል።

#ለካሳ ክፍያ መሟላት ያለባቸው ነገሮች
ከውል ውጪ ባለው የኃላፊነት ህግ መሰረት ካሳ ለማስከፈል፣ ተጎጂው ጉዳት እንደደረሰበት እና ጉዳቱም የደረሰው ኃላፊነት አለበት በተባለው ሰው ድርጊት ወይም እሱ ኃላፊነት በሚወስድባቸው ድርጊቶች መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።
የኃላፊነት ምንጮች
ከፍተኛ የህግ ባለሙያው አቶ ደመቀ እንደሚጠቅሱት፣ ከውል ውጪ የሚደርስ ኃላፊነት ህግ መሰረት (የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2027) ሶስት አይነት የኃላፊነት ምንጮች አሉ፦
#በጥፋት ላይ የተመሰረተ ኃላፊነት
#ጥፋት ሳይኖር የሚመጣ ኃላፊነት
#ሌላ ሰው ለሚያደርሰው ጉዳት የሚኖር ኃላፊነት
የጉዳት ዓይነቶች
የህግ ባለሙያው እንዳብራሩት፣ የተለያዩ የጉዳት ዓይነቶች አሉ።
1. ግልጽ የሆኑ ጉዳቶች
እነዚህ ጉዳቶች የተጎጂውን ንብረት ወይም ገንዘብ ነክ ጥቅም በቀጥታ የሚነኩ ናቸው። ይህ የጉዳት አይነት ቀጥታ ንብረት ላይ የሚደርስ ጉዳትን ወይም በአካልና በህይወት ላይ የሚደርስ ጉዳትን ያጠቃልላል።
ግልጽ የሆኑ ጉዳቶች አሁን የደረሱ ወይም ወደፊት የሚደርሱ ሊሆኑ ይችላሉ።

#አሁን የደረሱ ጉዳቶች: የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2090 እንደሚያመለክተው፣ እነዚህ በአሁኑ ጊዜ በእርግጠኝነት የደረሱና በግልጽ የሚታወቁ ጉዳቶች ሲሆኑ፣ ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ የጉዳትና የካሳ መጠኑ በፍርድ ቤት እስከሚወሰንበት ጊዜ ድረስ ያለውን ይመለከታል።

#ወደፊት የሚደርሱ ጉዳቶች: የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2092 እንደሚያስረዳው፣ በደረሰው ጉዳትና በካሳ ተመኑ ላይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ የማይቆሙና የሚቀጥሉ የጉዳት ዓይነቶች ናቸው።
2. የህሊና ጉዳት
ይህ የጉዳት አይነት የተጎጂውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የማይጎዳ ሆኖም በስሜት፣ በሀዘን ወይም በሀፍረት መልክ የሚገለጽ ሞራላዊ ጉዳት ነው።
የጉዳት ካሳ ስሌት
ጉዳትን ተከትሎ የሚመጣው ካሳ፣ ለጉዳት ለደረሰበት ሰው የጉዳት መጠኑ ተሰልቶ በዛ ልክ የሚሰጠው ጥቅም ነው። የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2090(1) እና 2091 ይህንን ያብራራል።
ለተጎጂው የሚገባውን ካሳ ለማስላት፣ የተጎጂውን የስራ ሁኔታ ማወቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው። ጉዳት የደረሰበት ሰው ተቀጥሮ የሚሰራ፣ የራሱን ስራ እየሰራ የሚኖር ወይም ስራ በመስራት ላይ ያልነበረ ሊሆን ይችላል።
1. ተቀጥሮ ለሚሰራ ሰው የሚሰጥ ካሳ
ጉዳቱ ከስራው ጋር የተገናኘ ከሆነ፣ የክርክሩ ሂደትና የካሳ አሰላል ስርዓቱ በአሰሪና ሰራተኛ ህግ (ቁጥር 1064/2010 እና 1156/2011) መሰረት ይመራል። ከስራው ጋር የማይገናኝ ከሆነ ግን በከውል ውጪ ኃላፊነት የህግ ድንጋጌዎች ይመራል።
#ጊዜያዊ ጉዳት: ጉዳቱ ጊዜያዊ ከሆነ፣ ስራ እስከሚጀምር ድረስ ሊያገኝ ይችል የነበረውን ያክል ካሳ ያገኛል።
#ከፊል ቋሚ ጉዳት: መስራት ባላስቻለው መጠን ልክ ይሰላል።
#ቋሚ ጉዳት: እስከ ጡረታ ጊዜው ድረስ ተሰልቶ ይሰጠዋል።
የአካል ጉዳት ሲደርስ፣ የወደፊት ጉዳት ካሳ ስሌት ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን፣ የሰራተኛውን የገቢ መጠን እና ተጎጂው ጡረታ ለመውጣት የቀረውን ጊዜ በደንብ ማጤን ያስፈልጋል።
2. የራሱን ስራ ለሚሰራ ሰው የሚሰጥ ካሳ
የራሱን ስራ እየሰራ ለሚተዳደር ሰው ካሳውን ለማስላት ገቢውን ለማወቅ አስቸጋሪ ሊሆን ቢችልም፣ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ወርሃዊ ወይም አመታዊ አማካይ ገቢውን በመመልከት ያጣውን ወይም ሊያጣ የሚችለውን ጥቅም በማስላት ካሳውን መተመን ይቻላል።
3. ስራ አጥ ለነበረ ሰው የሚሰጥ ካሳ
በህመም፣ ለመስራት ባለመፈለግ፣ የሚመጥነውን ስራ በማጣት ወይም በጠቅላላው ስራ አጥ በመሆን ስራ እየሰሩ ያልነበሩ ሰዎች ላይ ጉዳት ቢደርስባቸው የገቢውን መጠን ማወቅ ስለሚያስቸግር ካሳውን ማስላት ይከብዳል። በዚህ ጊዜ ዳኞች በፍትሃዊነት (በርትዕ) ካሳውን ለማስላት ይገደዳሉ።
4. በሞት ምክንያት የሚሰጥ ካሳ
በአደጋ ምክንያት ሞት ሲያጋጥም፣ ካሳ የመጠየቅ መብት ያለው ማነው የሚለው ወሳኝ ነው። የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2095 መሰረት የሟች ባል/ሚስት፣ ወላጆች እና ተወላጆች ካሳ መጠየቅ ይችላሉ። ለእነዚህ ሰዎች የሚከፈለው ካሳ ቀለብ ስለሆነ፣ በቤተሰብ ህጉ መሰረት ቀለብ ጠያቂ ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶችን ማሟላትና ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል።
5. ለህሊና ጉዳት የሚሰጥ ካሳ
የህሊና ጉዳት የሰው ልጅ የውስጥ ስሜት ጉዳት በመሆኑ ካሳውን በገንዘብ መለካት አስቸጋሪ ነው። ሆኖም የህሊና ጉዳት ሲያጋጥም የገንዘብ ካሳ እንደሚከፈል በፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2105(1) ተቀምጧል።
የህሊና ጉዳት ካሳ የሚከፈለው በልዩ ሁኔታ በህግ ለተመለከቱ ጉዳቶች ብቻ እንጂ ሁልጊዜም ካሳ እንደማያስከፍል የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2105(2) ይደነግጋል። የህሊና ጉዳት ካሳ የሚወሰነው ርትዕን መሰረት አድርጎ ሲሆን፣ የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2106-2115 ይህንን ያብራራል። የህሊና ጉዳት ካሳ 1,000 ብር መብለጥ እንደሌለበት የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2116(3) ያስቀምጣል።
የካሳ አከፋፈል ስርዓት
ጉዳት መድረሱ፣ ለጉዳቱ ማን ኃላፊነት እንደሚወስድና የካሳ ክፍያው መጠን ከተለየ በኋላ መወሰን ያለበት ሌላ ወሳኝ ጉዳይ የካሳ አከፋፈል ስርዓቱ ነው። የህግ ባለሙያው እንዳሉት፣ ሁለት አይነት የካሳ አከፋፈል ስርዓቶች አሉ፦
1. የቁርጥ ክፍያ
ይህ የካሳ ክፍያ የተወሰነበትን መጠን በአንድ ጊዜ ለባለመብቱ በመክፈል የሚፈጸም ነው። ይህ ዘዴ በብዙ ሀገራት የሚተገበርና መርህም ነው።
2. በየጊዜው የሚደረግ ክፍያ
መርሁ የጉዳት ካሳን በቁርጥ መክፈል ቢሆንም፣ በልዩ ሁኔታ ግን በየጊዜው እንዲከፈል ተደርጎ መወሰን እንደሚቻል በህጉ ተቀምጧል። ካሳን በየጊዜው እንዲከፈል ለመወሰን፣ የካሳው ባህሪ፣ የአካባቢ ሁኔታዎች እና የካሳ ከፋዩ ማረጋገጫ መስጠት ያለባቸው ነጥቦች ናቸው።
#Mikias_Melak
በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_መረጃ https://t.me/AleHig
#የሕግ_እውቀት alehig.com
#AleHig #አለሕግ #አለሕግ #ህግ
4