አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Statement of the Problem

በጥናት ስራ ወቅት #ትክክለኛውን (Significant Problem) በርዕሰ ሀሳቡ ውስጥ ማመልከት አስፈላጊም ፈታኝም ነው። ብዙ ተማሪዎች በጥናታቸው ማረጋገጥ የፈለጉትን ጭብጥ በግልጽ ለመዘርዘር ይቸገራሉ።


ለአብዛኞች የርዕስ ምንጭ ኢንተርኔት ነው! እኔ በግሌ ከመማሪያ መፅሃፎቻችሁ፤ ከስራ ልምዶቻችሁ፤ ከምትመለከቱት ሁኔታ፤ ከግል ፍላጎቶቻችሁ በመነሳት የምትችሉትን፤ ዳታ የሚገኝበትን እና የእናንተ የሆነ (Orginal)/በሌሎች የተሰራም የርዕስ ሃሳብ ከሆነ ከቀደሙ ስራዎች የተለየ አተያይ ያለው ጥናት ብትሰሩ ጥሩ ነው።


#ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ይደውል እና ርዕሴ "The #impact of unemployment on household welfare" ነው ይላል! ታዲያ በጥናት ማረጋገጥ የፈለከው ጉዳይ ምንድን ነው? ሲባል "ስራ አጥነት ለቤተሰብ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለሟሟላት ያለው ጫና" ይላል። ልብ በሉ Impact በአማርኛ ትርጓሜው #ጫና ነው እያለ ነው!


ከላይ ያለውን ምሳሌ ተከትሎ አጥኚው ስራ አጥ መሆን ያለውን #አሉታዊ_ጫና (Negative Impact) ሊፈልግ ነው ማለት ነው። ከዛ ስራ አጥ መሆን ገቢ እንዳይኖር ስለሚያደርግ ቤተሰቡ ድሃ ይሆናል/ይራባል (Research Hypothesis) የሚል አይነት ውጤት በመፈለግ ላይ ይሆናል ትኩረቱ (ሂደቱን ልብ ላይለው ይችላል)።


እዚህ ጋር ሁለት ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች አሉ፦

#አንደኛው፦ የጥናቱን ውጤት ዳታ ሰብስቦ ውጤት ከመተንተኑ በፊት ወደ እርግጠኝነት የቀረበ ግምት እያስቀመጠ ነው። ስለዚህ ምን አልባት ጥናቱ ሲጠናቀቅ የጥናቱ ውጤት ስራ አጥ መሆን መሰረታዊ (Significant) ችግር ቤተሰቦች ላይ አይፈጥርም! የሚል ከሆነ፡ እንዴት ብሎ? ለመቀበል በመቸገር ውጤት ወደ መለወጥ (Manipulation) ሊገባ ይችላል።


አስታውሱ ጥናት ማለት ከሚታወቅ መነሻ ወደ የማይታወቅ እውነት መሄድ ነው "Known To Unknown" ምን ማለት ነው? በላይኛው ምሳሌ አጥኝው ጥናት ከመጀመሩ በፊት ስራ አጥነት ተፅኖ እንዳለው ያውቃል። ነገር ግን #በዳታ እስካላረጋገጠ ድረስ ስራ አጥነት እንዴት (Negative/Positive? እና በምን ያህል ጥልቀት? (Significance Level) ተፅኖ እንዳለው ማወቅ አይችልም (መላምት ወይም Hypothesis ማስቀመጥ ግን ይችላል!)።


#ለምሳሌ፦ አንድ Independent Variable በጥናት ማረጋገጥ የተፈለገውን ውጤት (Dependent Variable) 89% ያህል ተፅኖ የመፍጠር አቅም ቢኖረው፡ እውነት ነው ተፅኖ አለው! ነገር ግን መሰረታዊ (Significant) የችግሩ መንስሄ አይደለም፡፡ ለዚህ ሲባል ነው በአብዛኛው በ90%, 95%, 99% አስተማማኝነት (Significance Level) ድረስ ብቻ የምትተነትኑት #ተፅኖ እና #መሰረታዊ_ተፅኖ የሚለውን ለመለየት ነው።


ማህበራዊ ሳይንስ ጥናት የምትሰሩ ተማሪዎች ዝቅተኛው 90% አስተማማኝነት (Significance Level) ቢፈቀድም የተፈጥሮ ሳይንስ ነክ ጥናት ለምትሰሩ ዝቅተኛው ከ95% አስተማማኝነት (Significance level) በታች እንዲሆን አትመከሩም።


በማህበራዊ ሳይንስ እስከ 90% Significance level ለምን ተፈቀደ? ካላችሁ በአብዛኛው በማህበራዊ ሳይንስ #ባህሪያዊ ጥናት (Quasi-Experimental) ስለሚከናወን ውጪያዊ ተፅኖዎችን ለመቆጣጠር ስለሚያስቸግር ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ Variable በአብዛኛው ከተፅኖ ነፃ ስለሚሆኑ ወደ ትክክለኛነት የቀረቡ የመሆን እድል ይጠበቅባቸዋል (#ለምሳሌ፦ መድሃኒት የማዳን አቅሙ በጥናት ከ95% በላይ የተረጋገጠ መሆኑን ማሳየት ይገባል እንደማለት ነው)። #ለምሳሌ፦ በማህበራዊ ሳይንስ ጥናት ድሃ የመሆንን 90% ምክንያት ለመግለጽ እንኳን ፈታኝ ነው።


#ሁለተኛው፦ Impact, Effect, Determinant.....ብሎ የጀመረ ርዕሰ አሉታዊ (Negative) ችግር እየለየ ነው ብሎ ማለት አይደለም። የአንድ ጉዳይ ተፅኖ/Impact እያጠናቹ ነው ማለት መልካምም መጥፎም ተፅኖ ነው እያረጋገጣችሁ ያላችሁት። ምክንያቱም የውጤት ዝርዝራችሁ ላይ ቤታ ወይም ኮፊሸንት ሲነበብ Negative ወይም Positive እና የሚያወጣው ተፅዕኖው አሉታዊም አዎንታዊም ነው እያላችሁ ነው።


#ለምሳሌ፦ አንድ ሰው በንግግሩ "ስራ ማጣቴ በህይወቴ Impact ፈጥሮብኛል" ቢል! ወዲያው ማመን የምትጀምሩት #ጉዳት ፈጥሮብኛል (ተርቢያለሁ፤ ተስፋ አስቆርጦኛል፤ ወዘተ) ማለቱን ነው እንጂ "ስራ አጥ መሆኔ የተሻለ የህይወት አረዳድ ሰጥቶኛል ወይም የፈጠራ ሃሳብ እንዳመነጭ አግዞኛል" እያላቹ እንደሆነ አትገምቱም። ነገር ግን ጥናት ስትሰሩ የተፅኖ ትርጉም እናንተ ሳትሆኑ ዳታው ነው አዎንታዊ/አሉታዊ ወይም Negative/Positive ማለት ያለበት።


በተመሳሳይ የጥናት ሀተታ ወይም Statement of the Problem ስታስቀምጡ ስለምታጠኑት ጉዳይ ችግር እየዘረዘራችሁ ሳይሆን የጥናታችሁን የቀደመ አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅኖ እያሳያችሁ ነው።
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
👍101
ከውል ውጪ ስለሚደርስ ጉዳት ካሳ ማወቅ ያለብዎት ነገር
ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች
ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል።

እነዚህ ጉዳቶች ከወንጀል ድርጊት፣ ከውል ጥሰት ወይም ከውል ውጪ ከሚመጣ ኃላፊነት ሊነሱ ይችላሉ። የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ የህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ደመቀ ይብሬ እንደሚሉት፣ ከውል ውጪ በሚደርስ ጉዳት ህግ ዋነኛ ዓላማ ጉዳት ያደረሰውን አካል በመለየት ተጎጂው ተገቢውን ካሳ እንዲያገኝ ማስቻልና ሌሎችም ከዚህ እንዲማሩ ማድረግ ነው።

#ጉዳት ምንድን ነው?
የፍትሐ ብሔር ህጉ ለ"ጉዳት" የሚለው ቃል ቀጥተኛ ትርጉም ባይሰጥም፣ ከህጉ አጠቃላይ ይዘት በመነሳት በሰው ጥቅም፣ አካል ወይም ህይወት ላይ የሚደርስ ጉድለት መሆኑን መረዳት ይቻላል።

#ለካሳ ክፍያ መሟላት ያለባቸው ነገሮች
ከውል ውጪ ባለው የኃላፊነት ህግ መሰረት ካሳ ለማስከፈል፣ ተጎጂው ጉዳት እንደደረሰበት እና ጉዳቱም የደረሰው ኃላፊነት አለበት በተባለው ሰው ድርጊት ወይም እሱ ኃላፊነት በሚወስድባቸው ድርጊቶች መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።
የኃላፊነት ምንጮች
ከፍተኛ የህግ ባለሙያው አቶ ደመቀ እንደሚጠቅሱት፣ ከውል ውጪ የሚደርስ ኃላፊነት ህግ መሰረት (የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2027) ሶስት አይነት የኃላፊነት ምንጮች አሉ፦
#በጥፋት ላይ የተመሰረተ ኃላፊነት
#ጥፋት ሳይኖር የሚመጣ ኃላፊነት
#ሌላ ሰው ለሚያደርሰው ጉዳት የሚኖር ኃላፊነት
የጉዳት ዓይነቶች
የህግ ባለሙያው እንዳብራሩት፣ የተለያዩ የጉዳት ዓይነቶች አሉ።
1. ግልጽ የሆኑ ጉዳቶች
እነዚህ ጉዳቶች የተጎጂውን ንብረት ወይም ገንዘብ ነክ ጥቅም በቀጥታ የሚነኩ ናቸው። ይህ የጉዳት አይነት ቀጥታ ንብረት ላይ የሚደርስ ጉዳትን ወይም በአካልና በህይወት ላይ የሚደርስ ጉዳትን ያጠቃልላል።
ግልጽ የሆኑ ጉዳቶች አሁን የደረሱ ወይም ወደፊት የሚደርሱ ሊሆኑ ይችላሉ።

#አሁን የደረሱ ጉዳቶች: የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2090 እንደሚያመለክተው፣ እነዚህ በአሁኑ ጊዜ በእርግጠኝነት የደረሱና በግልጽ የሚታወቁ ጉዳቶች ሲሆኑ፣ ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ የጉዳትና የካሳ መጠኑ በፍርድ ቤት እስከሚወሰንበት ጊዜ ድረስ ያለውን ይመለከታል።

#ወደፊት የሚደርሱ ጉዳቶች: የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2092 እንደሚያስረዳው፣ በደረሰው ጉዳትና በካሳ ተመኑ ላይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ የማይቆሙና የሚቀጥሉ የጉዳት ዓይነቶች ናቸው።
2. የህሊና ጉዳት
ይህ የጉዳት አይነት የተጎጂውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የማይጎዳ ሆኖም በስሜት፣ በሀዘን ወይም በሀፍረት መልክ የሚገለጽ ሞራላዊ ጉዳት ነው።
የጉዳት ካሳ ስሌት
ጉዳትን ተከትሎ የሚመጣው ካሳ፣ ለጉዳት ለደረሰበት ሰው የጉዳት መጠኑ ተሰልቶ በዛ ልክ የሚሰጠው ጥቅም ነው። የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2090(1) እና 2091 ይህንን ያብራራል።
ለተጎጂው የሚገባውን ካሳ ለማስላት፣ የተጎጂውን የስራ ሁኔታ ማወቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው። ጉዳት የደረሰበት ሰው ተቀጥሮ የሚሰራ፣ የራሱን ስራ እየሰራ የሚኖር ወይም ስራ በመስራት ላይ ያልነበረ ሊሆን ይችላል።
1. ተቀጥሮ ለሚሰራ ሰው የሚሰጥ ካሳ
ጉዳቱ ከስራው ጋር የተገናኘ ከሆነ፣ የክርክሩ ሂደትና የካሳ አሰላል ስርዓቱ በአሰሪና ሰራተኛ ህግ (ቁጥር 1064/2010 እና 1156/2011) መሰረት ይመራል። ከስራው ጋር የማይገናኝ ከሆነ ግን በከውል ውጪ ኃላፊነት የህግ ድንጋጌዎች ይመራል።
#ጊዜያዊ ጉዳት: ጉዳቱ ጊዜያዊ ከሆነ፣ ስራ እስከሚጀምር ድረስ ሊያገኝ ይችል የነበረውን ያክል ካሳ ያገኛል።
#ከፊል ቋሚ ጉዳት: መስራት ባላስቻለው መጠን ልክ ይሰላል።
#ቋሚ ጉዳት: እስከ ጡረታ ጊዜው ድረስ ተሰልቶ ይሰጠዋል።
የአካል ጉዳት ሲደርስ፣ የወደፊት ጉዳት ካሳ ስሌት ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን፣ የሰራተኛውን የገቢ መጠን እና ተጎጂው ጡረታ ለመውጣት የቀረውን ጊዜ በደንብ ማጤን ያስፈልጋል።
2. የራሱን ስራ ለሚሰራ ሰው የሚሰጥ ካሳ
የራሱን ስራ እየሰራ ለሚተዳደር ሰው ካሳውን ለማስላት ገቢውን ለማወቅ አስቸጋሪ ሊሆን ቢችልም፣ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ወርሃዊ ወይም አመታዊ አማካይ ገቢውን በመመልከት ያጣውን ወይም ሊያጣ የሚችለውን ጥቅም በማስላት ካሳውን መተመን ይቻላል።
3. ስራ አጥ ለነበረ ሰው የሚሰጥ ካሳ
በህመም፣ ለመስራት ባለመፈለግ፣ የሚመጥነውን ስራ በማጣት ወይም በጠቅላላው ስራ አጥ በመሆን ስራ እየሰሩ ያልነበሩ ሰዎች ላይ ጉዳት ቢደርስባቸው የገቢውን መጠን ማወቅ ስለሚያስቸግር ካሳውን ማስላት ይከብዳል። በዚህ ጊዜ ዳኞች በፍትሃዊነት (በርትዕ) ካሳውን ለማስላት ይገደዳሉ።
4. በሞት ምክንያት የሚሰጥ ካሳ
በአደጋ ምክንያት ሞት ሲያጋጥም፣ ካሳ የመጠየቅ መብት ያለው ማነው የሚለው ወሳኝ ነው። የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2095 መሰረት የሟች ባል/ሚስት፣ ወላጆች እና ተወላጆች ካሳ መጠየቅ ይችላሉ። ለእነዚህ ሰዎች የሚከፈለው ካሳ ቀለብ ስለሆነ፣ በቤተሰብ ህጉ መሰረት ቀለብ ጠያቂ ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶችን ማሟላትና ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል።
5. ለህሊና ጉዳት የሚሰጥ ካሳ
የህሊና ጉዳት የሰው ልጅ የውስጥ ስሜት ጉዳት በመሆኑ ካሳውን በገንዘብ መለካት አስቸጋሪ ነው። ሆኖም የህሊና ጉዳት ሲያጋጥም የገንዘብ ካሳ እንደሚከፈል በፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2105(1) ተቀምጧል።
የህሊና ጉዳት ካሳ የሚከፈለው በልዩ ሁኔታ በህግ ለተመለከቱ ጉዳቶች ብቻ እንጂ ሁልጊዜም ካሳ እንደማያስከፍል የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2105(2) ይደነግጋል። የህሊና ጉዳት ካሳ የሚወሰነው ርትዕን መሰረት አድርጎ ሲሆን፣ የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2106-2115 ይህንን ያብራራል። የህሊና ጉዳት ካሳ 1,000 ብር መብለጥ እንደሌለበት የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2116(3) ያስቀምጣል።
የካሳ አከፋፈል ስርዓት
ጉዳት መድረሱ፣ ለጉዳቱ ማን ኃላፊነት እንደሚወስድና የካሳ ክፍያው መጠን ከተለየ በኋላ መወሰን ያለበት ሌላ ወሳኝ ጉዳይ የካሳ አከፋፈል ስርዓቱ ነው። የህግ ባለሙያው እንዳሉት፣ ሁለት አይነት የካሳ አከፋፈል ስርዓቶች አሉ፦
1. የቁርጥ ክፍያ
ይህ የካሳ ክፍያ የተወሰነበትን መጠን በአንድ ጊዜ ለባለመብቱ በመክፈል የሚፈጸም ነው። ይህ ዘዴ በብዙ ሀገራት የሚተገበርና መርህም ነው።
2. በየጊዜው የሚደረግ ክፍያ
መርሁ የጉዳት ካሳን በቁርጥ መክፈል ቢሆንም፣ በልዩ ሁኔታ ግን በየጊዜው እንዲከፈል ተደርጎ መወሰን እንደሚቻል በህጉ ተቀምጧል። ካሳን በየጊዜው እንዲከፈል ለመወሰን፣ የካሳው ባህሪ፣ የአካባቢ ሁኔታዎች እና የካሳ ከፋዩ ማረጋገጫ መስጠት ያለባቸው ነጥቦች ናቸው።
#Mikias_Melak
በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
Alternative legal enlightenment & Service
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_መረጃ https://t.me/AleHig
#የሕግ_እውቀት alehig.com
#AleHig #አለሕግ #አለሕግ #ህግ
9