#ብር_የመለወጡ_ቀጥተኛ_ጥቅም!
***
ብዙ ሰዎች በተደጋገሚ ብሩ በመለወጡ በቀጥታ ኢኮኖሚው ላይ የሚመጣውን ጥቅም ንገረን ብለው ጠይቀውኛል! ብር በመለወጡ የሚገኙት የአጭር ግዜ እና የረጅም ግዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች የሚከተሉት ናቸው!
የአጭር ግዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች፡- በሀገራችን ከ113ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ከፋይናንስ ገበያው ቁጥጥር ውጪ አለ! ስለዚህ የገንዘብ ለውጡ ይህንን ገንዘብ ወደ ብሄራዊ ባንክ የመለወጥ እድል ይፈጥራል!
#ለምሳሌ፡- ምንጩ ያልታወቀ በመሆኑ ወደ ባንክ ሳይመጣ ከሚበላሸው፤ ከሀገር ውጪ በጎረቤት ሀገር በመሸሹ ከማይመለሰው፤ የመቀየሪያ ወቅቱ ከሚያልፍበት፤ በጎርፍ፤ በቃጠሎ፤ ወዘተ ከወደመው ውጪ 100 ቢሊዮን ብር እንኳን ወደ ህጋዊ የባንክ ስርዓት ቢመጣ ከፍተኛ ገንዘብ ከገበያ የመሰብሰብ እድል ስለሚፈጠር የዋጋ ንረት በሚታይ መልኩ የመቀነስ አቅም ይኖረዋል!
ምንጩ ያልታወቀ፤ በሙስና የተገኘ፤ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ከፍተኛ ገንዘብ በገበያ በድርጅቶች እና በሰዎች እጅ እንደሚገኝ ይታወቃል! ስለዚህ የተቀመጠውን የጥሬ ገንዘብ ገደብ (1.5 ሚሊዮን ብር ለማለት ነው!) እና ከ5 ሺህ ብር በላይ በባለቤቶች እንዲቀመጥ የሚያዘውን መመሪያ ተከትሎ ህገወጦችን ለመለየት እድል ይፈጥራል፡፡
#ለምሳሌ፡- በህገወጥ መንገድ ሃብት ያከማቸ ሰው ወይም ድርጅት ህጋዊ ከሆኑት ሰዎች ተገቢ ያልሆነ Advantage እንደወሰደ ግልጽ ነው! ስለዚህ የብሩ መቀየር የተለየ እድል ያገኙ ሰዎችን በተወሰነ መልኩ ለመቆጣጠር ያሰችላል፡፡
የረጅም ግዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች፡- ኢትዮጲያ ውስጥ በባንክ ቤቶች ያለው የቁጠባ መጠን ማነስ እና ባንኮች ለባለሃብቶች የሚያቀርቡት የብድር መጠን ማነስ የታወቀ ጉዳይ ነው! ስለዚህ ለምሳሌ 100 ቢሊዮኑ ቢሰበሰብ እና የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ገደቡን ተከትሎ 80 ቢሊዮኑ በባንኮች ቢቀመጥ ተጨማሪ ቁጠባ እና ተጨማሪ የብድር አቅርቦት እንዲገኝ ያደርጋል፡፡
#ለምሳሌ፡- መንግስት ባወጣዊ አዲስ መመሪያ መሰረት የግል ባንኮች የመንግስትን የግምጃ ቤት ሰነድ የመግዛት እድል ተፈጥሮላቸዋል! ስለዚህ መንግስት ወደ ፊት ለሚያስበው የበጀት ጉድለትን በሀገር ውስጥ የመሙላት ፍላጎት ተጨማሪ የገንዘብ ምንጭ ሆኖ ሊያገለግለው ይችላል፡፡
ገንዘቦች በመሰብሰባቸው እና በግል ባንኮች ውስጥ በመቀመጣቸው የሚቀርበው ብድር የግል ሴክተሩን በማነቃቃት ተጨማሪ ምርት እንዲመረት፤ ተጨማሪ ሰራተኛ እንዲቀጠር፤ ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች አድገው የውጪ ምንዛሬ ግኝት እንዲያድግ፤ የሀገር ውስጥ አምራቾች ተበረታተው ከውጪ የሚገቡትን የመተካት አቅም የሚፈጥሩ ከሆነ የውጪ ምንዛሬ እንዲቆጠብ፤ ወዘተ የማድረግ አቅም ይኖረዋል፡፡
ነገር ግን ብር መለወጡ ብቻውን ስር ነቀል ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ያመጣል ማለት አይደለም! ምክንያቱም ዋጋ ንረት፤ ስራ አጥነት፤ የውጪ ምንዛሬ ክምችት ማነስ፤ የበጀት ጉድለት፤ ዝቅተኛ ምርት እና ምርታማነት መኖር፤ የንግድ ሚዛን መዛባት፤ ወዘተ በገንዘብ ምክንያት ብቻ የመጡም አይደሉም በገንዘብ ምክንያት ብቻም የሚፈቱ አይደሉም! ሌሎች ፖሊሲዎች እና ስራዎች በተጨማሪነት መሰራታቸው ግድ ነው!
via the Ethiopian economist view
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

መንግስት ሰራተኛው የግብር እፎይታ ቢደረግለትስ?
መንግስት ላለፉት ሁለት ዓመታት የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነትን ጫናን ለመቀነስ ከፊስካል ፖሊሲ አማራጮች መካከል ከፍተኛ የሆነ የቀረጥ እና የግብር እፎይታ እንዲሁም የሸቀጥ እና የአገልግሎት ዋጋ ድጎማዎችን እያደረገ ነው።
የቀረጥ እና የግብር እፎይታ እንዲሁም የሸቀጥ እና የአገልግሎት ዋጋ ድጎማዎች ከፍተኛ ቢሊዮኖችን ያሳጣም እንዲሁም ከካዝና ያስወጣ ቢሆንም ዝቅተኛ የገቢ ባለቤት የሆነው የህብረተሰብ ክፍል የኑሮ ውድነት ፈተናው ቋሚ መስሏል።
በቅርቡ የህብረተሰብ ውይይቶች ላይ የኑሮ ውድነት ጫና እና የመንግስት ሰራተኞች ሁኔታዎችን ለመቋቋም እጅጉን እየተፈተኑ እንደሆነ የተለያዩ ቦታዎች ግን ተመሳሳይ እይታዎች ነበሩ።
ድጎማ እና የቀረጥ እፎይታ ጊዚያዊ አሰራር መሆኑ ከታመነበት የመንግስት ሰራተኛው በጊዚያዊነት የግብር ማሻሻያ አልያም የግብር እፎይታ ቢደረግለት ጊዚያዊ ችግሮችን ለማለፍ ሊያግዘው ይችላል።
የመንግስት ሰራተኛው በቁጥር ብዙ አይደለም! በተለምዶ የመንግስት ሰራተኛው ላይ የሚደረግ የፊሲካል ፖሊሲ ማሻሻያዎች ገበያውን እና ማክሮ ኢኮኖሚውን እንደሚያናጋው የሚቀርበው መከራከሪያ ሙሉ ለመሉ አሳማኝ አይደለም።
የመንግስት የተረጋጋ እና የማይቆራረጥ የገቢ ምንጮቹ መካከል ከመንግስት ሰራተኛው የሚሰበሰበው ግብር አንዱ እንደሆነ ቢታወቅም መሰረታዊ የገቢ አሰባሰቡ ከተፈተሸ በገበያው ብዙ ወደ ግብር ስርዓት ያልገባውን ክፍል በመቃኘት የዘርፉን አቅም ማሳደግ ይቻላል።
የግል እና የአክሲዮን ድርጅቶች ለሰራተኞቻቸው የኑሮ ውድነትን መሰረት በማድረግ የክፍያ ማካካሻ አካሄድ የሚከተሉ አሉ! ነገር ግን የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝም (Salary) ሆነ ደሞዝ የሚገዛው (Wages) ላይ መሻሻያ አይታይም።
#ለምሳሌ፦ ኮቪድ የገባ ሰሞን ድርጅቶች የግብር እፎይታ (ከ70 ቢሊየን ብር በላይ አቻ ያለው) እና የቫት ወጪ አጠቃቀም ላይ ማበረታቻ ቀርቦላቸው ነበር።
ለውይይት ያህል ነው! የመንግስት ሰራተኛው በጊዚያዊነት የግብር ማሻሻያ አልያም የግብር እፎይታ ቢደረግለት ስለሚኖረው አዎንታዊ አልያም አሉታዊ ጉዳይ እናውራበት።
በዋሲሁን በላይ
#አለ_ልዩልዩ
#አለ_ህግ #አለ_ልዩልዩ #አለ_ችሎት #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share

አንድ ሰው "መንግስት በጣም አዋጪ ለሆኑ ፕሮጀክቶቹ ገንዘብ በብዛት አትሞ በፍጥነት ቢሰራበት ችግሩ ምንድን ነው?"
ለጠየቀው ጥያቄ፣ ከኢኮኖሚ #ህግ አንፃር የተሰጠ ማብራሪያ፡፡
ገንዘብ #እንደፈለጉ በማተም የሚያስፈልጉ ወጪዎችን መሸፈን ይቻላል!
ነገር ግን አዲስ የሚታተመው ገንዘብ ኢኮኖሚው ከሚሸከመው የገንዘብ መጠን በላይ ከሆነ (መታተም ካለበት ዝቅተኛ መጠን ከበለጠ) እና ገንዘቡ ታትሞ የሚያርፍበት ሴክተር እና የአዲሱ ገንዘብ የስርጭት ሂደት ያልተጠና ሲሆን ነው አዲስ የሚታተመው ገንዘብ ችግር መሆን የሚጀምረው፡፡
.........................
በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ገንዘብ በዘፈቀደ ሊታተም እና ሊሰራጭ አይችልም (በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ አስተዳደር ደካማነት ብዙ ገንዘብ ማተም የፈለገ ሀገር መብቱ ነው! ነገር ግን በዋጋ ንረት ዋጋ የሚከፍለው ኢኮኖሚው ነው)፡፡ ገንዘብ ለአንድ ኢኮኖሚ አስፈላጊም አደጋም ነው! ለዚህም ሲባል የገንዘብ ፖሊሲ (Monetary policy) በጠንካራ ተቋማት (በዋናነት በብሄራዊ ባንክ) በከፍተኛ ክትትል እንቅስቃሴው እንዲመራ ይደረጋል፡፡
በኢኮኖሚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት የተቀበለው ድንቁ ኢኮኖሚስት Milton Friedman በአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ የገንዘብ አቅርቦት ማደግ ያለበት በየዓመቱ ከጠቅላላው ምርት GDP ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መጠን ወይም ፐርሰንት ነው (ስርዓቱ K-Percent Rule ይባላል) ስለዚህ የገንዘብ ኖት መጠን የሚወሰነው ጠቅላላ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከሚኖረው እድገት እና እንቅስቃሴ አንጻር ከ3 ከመቶ ያልበለጠ ህትመት እንዲሆን ይመክራል፡፡
ጥያቄውን ያነሳልኝ ልጅ ኢኮኖሚክስን የተማረ ስላልነበር ለጠየቀው ጥያቄ መልስ መስጠት አለብኝ (እንዲሁም ኢኮኖሚክስን ላልተማራችሁ ሰዎች የሚረዳ ከሆነ) ጥያቄውን ለመመለስ ያህል…….....
የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ በገበያው ያለው የቁሳቁስ እና የአገልግሎት አቅርቦት ከሰዎች የመግዛት ፍላጎት እና አቅም ጋር እየመዘነ ኢኮኖሚው በፈጠረው ሃብት አንጻር ተጨማሪ ገንዘብ ወደ ገበያው በተለያየ መንገድ መልቀቅ አለበት፡፡
ነገር ግን በተለይ የዋጋ ንረት ላለበት ኢኮኖሚ (ነባሩ የዋጋ ንረት ከገንዘብ ፈሰስ አንጻር የተባባሰ ከሆነ) ተጨማሪ ገንዘብ ተጨማሪ የሸማች አቅም በመጨመር ምርት በሚፈለገው ፍጥነት ወደ ገበያ ሳይመጣ ፉክክር እና ፍላጎትን በመፍጠር ያለው ምርት ላይ ዋጋ እንዲጨመር ሊያደርግ ይችላል (የዚህ አይነቱ አጋጣሚ በአንደኛው እና በሁለተኛው ጦርነት ወቅት በተወሰኑ የአውሮፓ ሀገራት፤ አፍሪካ ውስጥም በዝምባብዌ፤ በላይቤሪያ፤ ወዘተ ሆኖ ያውቃል)፡፡
#ለምሳሌ፡- መንግስት ግዙፍ የመስኖ ግድብን በመስራት 200ሺ ሄክታር የስንዴ ማሳን እስከማልማት የሚደርስን የፕሮጀክቱን ወጪ 20ቢሊየን ብር አትሞ ቢያዘጋጅ ብለን እናስብ፡፡ ቀጥታ ለመስኖ ግንባታ (ሲሚንቶ (የተወሰነ ግብዓት)፤ ብረት (የተወሰነ ግብዓት)፤ የግንባታ ማሽነሪ፤ ወዘተ) እና ለሰብል ዝግጅት (ምርጥ ዘር፤ የአፈር ማዳበሪያ፤ ለማጓጓዣ ነዳጅ፤ ጸረ-ሰብል መድሃኒት፤ ወዘተ) ኢኮኖሚው በብር ገዝቶ ማቅረብ ይችላል?
ስለዚህ ብር የሚያገለግለው ለሀገር ውስጥ ግብዓት (የውጪ ምንዛሬ ለማይጠይቁ ግብዓት ፍጆታ ካላቸው) እና የባለሙያ ክፍያ/የአገልግሎት ክፍያ ለመፈጸም ነው፡፡ ምክንያቱም የውጪ ምንዛሬ ለሚጠይቁ የፕሮጀክት ወጪዎች ብርን በቀጥታ መጠቀም ስለማይቻል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት በቂ የውጪ ምንዛሬ በሌለበት ብርን በማተም ብቻ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ በማድረግ ለማጠናቀቅ ከባድ ነው፡፡
ፕሮጀክቶች ለመጠናቀቅ ረጅም ጊዜ የመውሰድ ልምድ ስላላቸው እና አሁን በሀገራችን የሰዎች ቀጥተኛ ተሳትፎ በማሽኖች ስላልተተካ በየፕሮጀክቶቹ እና ለፕሮጀክቱ ግብዓት የሚያቀርቡ ተቋማት ከፍተኛ የሰው ሃይል ስለሆነ የሚጠቀሙት ከፍተኛ ክፍያ (በደሞዝ እና በስራ ማስኬጃ) በጠቅላላ ሂደቱ በሙሉ ይወጣል፡፡
ስለዚህ ለረጅም ጊዜ ለስራ ማስኬጃ የሚወጣው ወጪ ገበያ ውስጥ ለሸመታ በሚል ስለሚወጣ አቅርቦት እስካልተሻሻለ ያለው አነስተኛ አቅርቦት ላይ ገንዘብ ያላቸው ሸማቾች ሲጨመሩ ፉክክሩ እቃዎችን ከእጥረት የተነሳ ውድ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
#ለምሳሌ፡- ይህ ፕሮጀክት እስኪጠናቀቅ ድረስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ 10ሺ በቤታቸው/በቤተሰቦቻቸው ድጋፍ በቤት ያለስራ ተቀምጠው የነበሩ ወጣቶችን በወር የ5ሺ ብር ደሞዝተኛ ቢያድርግ፡ እነዚህ ሰዎች በየወሩ የ5ሺ ብር የአገልግሎትም ሆነ የቁሳቁስ ሸመታ ላይ ሊሳተፉ ይችላሉ! ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ምርት ወደ ገበያ ከማምጣቱ በፊት ወጣቶቹ ወደ ሸመታ በመግባታቸው ፉክክሩን በመጨመር ዋጋዎችን ከፍላጎት በተነሳ ምክንያት (Demand Pull Inflation) ውድ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
በሌላ ጎን እነዚህ የ5ሺ ብር አዳዲስ ደሞዝተኞች የባንክ ደብተር አውጥተው በወር አንድ አንድ ሺ ብር ማስቀመጥ ቢጀምሩ ባንኮች የተቀበሉትን ቁጠባ በኢንቨስትመንት መልኩ ቢያበድሩት ድጋሚ ገንዘብ ወደ ገበያው ፈሰስ ሆኖ ተመሳሳይ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡ በተለይ ገንዘብን በጥሬ ገንዘብነት መያዝ ለለመደ ማህበረሰብ ከባንኩ ቁጥጥር ውጪ የሚውለውን ገንዘብ መጠን ስለሚጨምረው የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መዛባቱ ሲባባስ በተለያዩ የMonetary ዘዴዎች ገንዘቡን ወደ ማዕከላዊ ባንኩ ለመሰብሰብ አስቸጋሪ ነው፡፡
አስተውሉ የታተመው ገንዘቡ ወደ ገበያ ሳይሰራጭ ለፕሮጀክት ብቻ ማዋል የሚባል አመክንዬ ሊኖር አይችልም! እንዲሁም የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳይ ሲወራ ስለጥቂት ሰዎች ሳይሆን ስለድምር ተጽዕኖው ነው የሚወራው፡፡ ምን ማለቴ ነው ? በቀላሉ ከላይኛው ምሳሌ በመነሳት ፕሮጀክቱ ሊኖር የሚችለው አንድ ቦታ ላይ ነው፡ ሰዎቹም 10ሺ ናቸው የሚል ክርክር ቢነሳ ጠንካራ አይደለም! ምክንያቱም የማክሮ ኢኮኖሚውም ሆነ የዋጋ ንረት የሚሰላው የየአካባቢዎቹን አማካይ ጥቅል ውጤት ተወስዶ ነው፡፡
#WaseAlpha
by Wase Belay

የቢዝነስ ፕላን (Business Plan) እና የቢዝነስ አዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ማካከል ያለው ልዩነት!
አዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ማካሄድ ማለት ለማከናወን ያሰቡትን የቢዝነስ አይነት (በተለይ አዲስ ቢዝነስ) ጠቅላላ ሁኔታ መዳሰስ ሲሆን ለሚሰራው ቢዝነስ በዛ ያሉ አማራጮች ስለመኖራቸው ማሳየት እና የሚታሰበው ፕሮጀክት ከማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች አንጻር ምን ያህል ተቀባይነት እንዳለው የሚያጣራ ይሆናል፡፡
#ለምሳሌ፡- ከብት ማደለብ የሚባል ቢዝንስ ስለማዋጣቱ ቢጠና እስካልተተገበረ ድረስ ሃሳባዊ ነው፡፡ ነገር ግን በአዋጪነት ጥናት ከዳታ በመነሳት፤ የቀደሙ አቅርቦት እና ፍላጎትን በመለካት፤ የፖሊሲ አማራጮች መኖራቸውን ማጣራት፤ በመጪው ጊዜ አቅርቦት፤ ፍላጎት እና ዋጋ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ትንበያ መስራት፤ ቢዝነሱ ሊገጥሙት የሚችሉትን ስጋቶች መለየት፤ የሚጠበቁ መፍትሄዎችን ማሳየት፤ የፕሮጀክቱን ማህበራዊ ቅቡልነት ማረጋገጥ፤ ቢዝነሱ በገበያ ያለውን ተፎካካሪነት መለካት፤ ወዘተ ነው፡፡
ነገር ግን ፕሮጀክቶች (Business Plan) ገንዘቡ ከየት ተገኝቶ፤ ምን ያህል ሰዎች ተቀጥሮ፤ የት አካባቢ አምርቶ፤ ምን አምርቶ፤ እንዴት ሸጦ፤ እንዴት ማስታወቂያ አሰርቶ፤ እንዴት ምርቱን አከፋፍሎ፤ ስንት ሸጦ፤ በስንት ሸጦ፤ ወዘተ የሚሉ የታክቲክ እና የስትራቴጂ ስልቶችን በመንደፍ ከኢኮኖሚ አንጻር አትራፊ/አዋጪ ማድረግ እንደሚቻል የሚሰራ ሰነድ ነው፡፡
ከብት ማድለብ አዋጪ መሆኑ ሳይጣራ ከብት ለማድለቢያ መኖ የሚገዛበት ቦታ ሊመረጥ አይችልም፡፡ ስለዚህ የቢዝነስ ፕላን (Business Plan) የሚሰራው የቢዝነሱ አዋጪነት (Feasibility Study) ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡
#ለምሳሌ፡- ኢንቨስትመንት ፍቃድ፤ የቦታ ጥያቄ ወይም ብድር ለመጠየቅ የሚሰራው ጥናት የአዋጪነት ጥናት (Feasibility Study) ነው፡፡ ምክንያቱም የሚሰራው ፕሮጀክት ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ተቀባይነት ያለው መሆኑን እንዲሁም በፖሊሲ የሚደገፍ መሆኑን በማጣራት ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ቢዝነስ ፕላን ቢዝነሱን ላሰበው ሰው ብቻ ከማስፈለጉ በተጨማሪ ዋና አላማው ኢኮኖሚያዊ አዋጪ (ትርፋማ) መሆኑ ብቻ ነው፡፡
The Ethiopian economist views

#የቀብድ ግብይት አዋጪ ነው! በዋጋ ንረት ወቅት ያለወለድ አበዳሪ አካል ተጎጂ ነው።
ለወዳጃችሁ የዛሬ ዓመት ያበደራችሁትን ገንዘብ ዘንድሮ ሲከፍል ያንኑ ነው። በማህበራዊ ምክንያት የገንዘቡ የመግዛት አቅም ስለተዳከመ ወዳጅ ወለድ አስቦ አይሰጥም! አበዳሪ ለማካካሻ ወለድ አይጠይቅም።
በተመሳሳይ ቀብድ ቀድሞ ተቀባይ በማህበራዊ ተፅዕኖ የዋጋ ለውጥ ላለመፍጠር ይገደዳል። በተቃራኒው ቀብድ ቀድሞ በመክፈል የተፃፈም ሆነ ያልተፃፈ ስምምነት ውስጥ የወደቀ ሸማች ነባር ዋጋ ለመክፈል እድል ያገኛል።
#ለምሳሌ፦ ዛሬ 3ሺ ብር ለተባላችሁት እቃ ከወር በኋላ 3ሺ ብር ይዛችሁ ብትመጡ 4ሺ ብር ቢገባ ዋስትና የላችሁም! ነገር ግን በማህበራዊ ዋስትና ዘዴ ባንዱ #ቀብድ ከወር በፊት 1ሺ ብር ከፍላችሁ ቢሆን ከወር በኋላ 4ሺ ብር ዋጋ ላይ ላትወድቁ ትችላላችሁ።
ሻጮች የእጅ በእጅ ክፍያ እና የቀብድ ክፍያ መካከል ረጅም የጊዜ ልዩነት እና የዋጋ ልዩነት ላይፈጥሩ ይችላሉ የሚለው ታሳቢ ተደርጎ #እድሉ_ያላችሁ ሰዎች ለመሸመት ለወሰናችሁት ቁስ ፈጣን ውሳኔ ከሌላችሁ የዋጋ ንረት ተገማች ስላልሆነ በቀብድ መገበያየት መጥፎ አይደለም።
የዋጋ ንረት የመቀነስ ባህሪ ባለው ገበያ ላይ የቀብድ ተጠቃሚ ሻጭ ነው። በቀብድ 4ሺ ብር ያሰረው ዋጋ በገበያ ተመን 3ሺ ብር ቢወርድ ዋጋ ለመቀነስ ላይገደድ ይችላል።
የዋጋ ንረት እና የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከሙ ካልቀረ ለመሸመት ያሰቡትን በፍጥነት መሸመት ወይም እድሉ ካለ በቀብድ የጊዜ የዋጋ ለውጥን መቀነስ ይቻላል።
በቅርቡ አንዲት ልጅ ፈርኒቸር ቤት ትከራከራለች። "የዛሬ ወር ጫማ መደርደሪያ 2,800ብር እንዲሰራልሽ 500ብር ቀብድ ስጪ ሲለኝ ስላልወሰንኩ ዛሬ ላይ ያንኑ ምርት 4,000ብር ገብቷል አለኝ" ትላለች ሻጭ "ያንቺ ጥፋት ነው! ያኔ ወስነሽ ቢሆን በቅናሹ ይሰራልሽ ነበር! አሁንም ካልወሰንሽ በቀጣይ የሚደርስበትን የግብዓት ዋጋ አላውቅም" ይላል። Via #WaseAlpha

Statement of the Problem
በጥናት ስራ ወቅት #ትክክለኛውን (Significant Problem) በርዕሰ ሀሳቡ ውስጥ ማመልከት አስፈላጊም ፈታኝም ነው። ብዙ ተማሪዎች በጥናታቸው ማረጋገጥ የፈለጉትን ጭብጥ በግልጽ ለመዘርዘር ይቸገራሉ።
ለአብዛኞች የርዕስ ምንጭ ኢንተርኔት ነው! እኔ በግሌ ከመማሪያ መፅሃፎቻችሁ፤ ከስራ ልምዶቻችሁ፤ ከምትመለከቱት ሁኔታ፤ ከግል ፍላጎቶቻችሁ በመነሳት የምትችሉትን፤ ዳታ የሚገኝበትን እና የእናንተ የሆነ (Orginal)/በሌሎች የተሰራም የርዕስ ሃሳብ ከሆነ ከቀደሙ ስራዎች የተለየ አተያይ ያለው ጥናት ብትሰሩ ጥሩ ነው።
#ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ይደውል እና ርዕሴ "The #impact of unemployment on household welfare" ነው ይላል! ታዲያ በጥናት ማረጋገጥ የፈለከው ጉዳይ ምንድን ነው? ሲባል "ስራ አጥነት ለቤተሰብ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለሟሟላት ያለው ጫና" ይላል። ልብ በሉ Impact በአማርኛ ትርጓሜው #ጫና ነው እያለ ነው!
ከላይ ያለውን ምሳሌ ተከትሎ አጥኚው ስራ አጥ መሆን ያለውን #አሉታዊ_ጫና (Negative Impact) ሊፈልግ ነው ማለት ነው። ከዛ ስራ አጥ መሆን ገቢ እንዳይኖር ስለሚያደርግ ቤተሰቡ ድሃ ይሆናል/ይራባል (Research Hypothesis) የሚል አይነት ውጤት በመፈለግ ላይ ይሆናል ትኩረቱ (ሂደቱን ልብ ላይለው ይችላል)።
እዚህ ጋር ሁለት ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች አሉ፦
#አንደኛው፦ የጥናቱን ውጤት ዳታ ሰብስቦ ውጤት ከመተንተኑ በፊት ወደ እርግጠኝነት የቀረበ ግምት እያስቀመጠ ነው። ስለዚህ ምን አልባት ጥናቱ ሲጠናቀቅ የጥናቱ ውጤት ስራ አጥ መሆን መሰረታዊ (Significant) ችግር ቤተሰቦች ላይ አይፈጥርም! የሚል ከሆነ፡ እንዴት ብሎ? ለመቀበል በመቸገር ውጤት ወደ መለወጥ (Manipulation) ሊገባ ይችላል።
አስታውሱ ጥናት ማለት ከሚታወቅ መነሻ ወደ የማይታወቅ እውነት መሄድ ነው "Known To Unknown" ምን ማለት ነው? በላይኛው ምሳሌ አጥኝው ጥናት ከመጀመሩ በፊት ስራ አጥነት ተፅኖ እንዳለው ያውቃል። ነገር ግን #በዳታ እስካላረጋገጠ ድረስ ስራ አጥነት እንዴት (Negative/Positive? እና በምን ያህል ጥልቀት? (Significance Level) ተፅኖ እንዳለው ማወቅ አይችልም (መላምት ወይም Hypothesis ማስቀመጥ ግን ይችላል!)።
#ለምሳሌ፦ አንድ Independent Variable በጥናት ማረጋገጥ የተፈለገውን ውጤት (Dependent Variable) 89% ያህል ተፅኖ የመፍጠር አቅም ቢኖረው፡ እውነት ነው ተፅኖ አለው! ነገር ግን መሰረታዊ (Significant) የችግሩ መንስሄ አይደለም፡፡ ለዚህ ሲባል ነው በአብዛኛው በ90%, 95%, 99% አስተማማኝነት (Significance Level) ድረስ ብቻ የምትተነትኑት #ተፅኖ እና #መሰረታዊ_ተፅኖ የሚለውን ለመለየት ነው።
ማህበራዊ ሳይንስ ጥናት የምትሰሩ ተማሪዎች ዝቅተኛው 90% አስተማማኝነት (Significance Level) ቢፈቀድም የተፈጥሮ ሳይንስ ነክ ጥናት ለምትሰሩ ዝቅተኛው ከ95% አስተማማኝነት (Significance level) በታች እንዲሆን አትመከሩም።
በማህበራዊ ሳይንስ እስከ 90% Significance level ለምን ተፈቀደ? ካላችሁ በአብዛኛው በማህበራዊ ሳይንስ #ባህሪያዊ ጥናት (Quasi-Experimental) ስለሚከናወን ውጪያዊ ተፅኖዎችን ለመቆጣጠር ስለሚያስቸግር ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ Variable በአብዛኛው ከተፅኖ ነፃ ስለሚሆኑ ወደ ትክክለኛነት የቀረቡ የመሆን እድል ይጠበቅባቸዋል (#ለምሳሌ፦ መድሃኒት የማዳን አቅሙ በጥናት ከ95% በላይ የተረጋገጠ መሆኑን ማሳየት ይገባል እንደማለት ነው)። #ለምሳሌ፦ በማህበራዊ ሳይንስ ጥናት ድሃ የመሆንን 90% ምክንያት ለመግለጽ እንኳን ፈታኝ ነው።
#ሁለተኛው፦ Impact, Effect, Determinant.....ብሎ የጀመረ ርዕሰ አሉታዊ (Negative) ችግር እየለየ ነው ብሎ ማለት አይደለም። የአንድ ጉዳይ ተፅኖ/Impact እያጠናቹ ነው ማለት መልካምም መጥፎም ተፅኖ ነው እያረጋገጣችሁ ያላችሁት። ምክንያቱም የውጤት ዝርዝራችሁ ላይ ቤታ ወይም ኮፊሸንት ሲነበብ Negative ወይም Positive እና የሚያወጣው ተፅዕኖው አሉታዊም አዎንታዊም ነው እያላችሁ ነው።
#ለምሳሌ፦ አንድ ሰው በንግግሩ "ስራ ማጣቴ በህይወቴ Impact ፈጥሮብኛል" ቢል! ወዲያው ማመን የምትጀምሩት #ጉዳት ፈጥሮብኛል (ተርቢያለሁ፤ ተስፋ አስቆርጦኛል፤ ወዘተ) ማለቱን ነው እንጂ "ስራ አጥ መሆኔ የተሻለ የህይወት አረዳድ ሰጥቶኛል ወይም የፈጠራ ሃሳብ እንዳመነጭ አግዞኛል" እያላቹ እንደሆነ አትገምቱም። ነገር ግን ጥናት ስትሰሩ የተፅኖ ትርጉም እናንተ ሳትሆኑ ዳታው ነው አዎንታዊ/አሉታዊ ወይም Negative/Positive ማለት ያለበት።
በተመሳሳይ የጥናት ሀተታ ወይም Statement of the Problem ስታስቀምጡ ስለምታጠኑት ጉዳይ ችግር እየዘረዘራችሁ ሳይሆን የጥናታችሁን የቀደመ አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅኖ እያሳያችሁ ነው።
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig