አንድ ሰው "መንግስት በጣም አዋጪ ለሆኑ ፕሮጀክቶቹ ገንዘብ በብዛት አትሞ በፍጥነት ቢሰራበት ችግሩ ምንድን ነው?"
ለጠየቀው ጥያቄ፣ ከኢኮኖሚ #ህግ አንፃር የተሰጠ ማብራሪያ፡፡
ገንዘብ #እንደፈለጉ በማተም የሚያስፈልጉ ወጪዎችን መሸፈን ይቻላል!
ነገር ግን አዲስ የሚታተመው ገንዘብ ኢኮኖሚው ከሚሸከመው የገንዘብ መጠን በላይ ከሆነ (መታተም ካለበት ዝቅተኛ መጠን ከበለጠ) እና ገንዘቡ ታትሞ የሚያርፍበት ሴክተር እና የአዲሱ ገንዘብ የስርጭት ሂደት ያልተጠና ሲሆን ነው አዲስ የሚታተመው ገንዘብ ችግር መሆን የሚጀምረው፡፡
.........................
በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ገንዘብ በዘፈቀደ ሊታተም እና ሊሰራጭ አይችልም (በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ አስተዳደር ደካማነት ብዙ ገንዘብ ማተም የፈለገ ሀገር መብቱ ነው! ነገር ግን በዋጋ ንረት ዋጋ የሚከፍለው ኢኮኖሚው ነው)፡፡ ገንዘብ ለአንድ ኢኮኖሚ አስፈላጊም አደጋም ነው! ለዚህም ሲባል የገንዘብ ፖሊሲ (Monetary policy) በጠንካራ ተቋማት (በዋናነት በብሄራዊ ባንክ) በከፍተኛ ክትትል እንቅስቃሴው እንዲመራ ይደረጋል፡፡
በኢኮኖሚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት የተቀበለው ድንቁ ኢኮኖሚስት Milton Friedman በአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ የገንዘብ አቅርቦት ማደግ ያለበት በየዓመቱ ከጠቅላላው ምርት GDP ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መጠን ወይም ፐርሰንት ነው (ስርዓቱ K-Percent Rule ይባላል) ስለዚህ የገንዘብ ኖት መጠን የሚወሰነው ጠቅላላ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከሚኖረው እድገት እና እንቅስቃሴ አንጻር ከ3 ከመቶ ያልበለጠ ህትመት እንዲሆን ይመክራል፡፡
ጥያቄውን ያነሳልኝ ልጅ ኢኮኖሚክስን የተማረ ስላልነበር ለጠየቀው ጥያቄ መልስ መስጠት አለብኝ (እንዲሁም ኢኮኖሚክስን ላልተማራችሁ ሰዎች የሚረዳ ከሆነ) ጥያቄውን ለመመለስ ያህል…….....
የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ በገበያው ያለው የቁሳቁስ እና የአገልግሎት አቅርቦት ከሰዎች የመግዛት ፍላጎት እና አቅም ጋር እየመዘነ ኢኮኖሚው በፈጠረው ሃብት አንጻር ተጨማሪ ገንዘብ ወደ ገበያው በተለያየ መንገድ መልቀቅ አለበት፡፡
ነገር ግን በተለይ የዋጋ ንረት ላለበት ኢኮኖሚ (ነባሩ የዋጋ ንረት ከገንዘብ ፈሰስ አንጻር የተባባሰ ከሆነ) ተጨማሪ ገንዘብ ተጨማሪ የሸማች አቅም በመጨመር ምርት በሚፈለገው ፍጥነት ወደ ገበያ ሳይመጣ ፉክክር እና ፍላጎትን በመፍጠር ያለው ምርት ላይ ዋጋ እንዲጨመር ሊያደርግ ይችላል (የዚህ አይነቱ አጋጣሚ በአንደኛው እና በሁለተኛው ጦርነት ወቅት በተወሰኑ የአውሮፓ ሀገራት፤ አፍሪካ ውስጥም በዝምባብዌ፤ በላይቤሪያ፤ ወዘተ ሆኖ ያውቃል)፡፡
#ለምሳሌ፡- መንግስት ግዙፍ የመስኖ ግድብን በመስራት 200ሺ ሄክታር የስንዴ ማሳን እስከማልማት የሚደርስን የፕሮጀክቱን ወጪ 20ቢሊየን ብር አትሞ ቢያዘጋጅ ብለን እናስብ፡፡ ቀጥታ ለመስኖ ግንባታ (ሲሚንቶ (የተወሰነ ግብዓት)፤ ብረት (የተወሰነ ግብዓት)፤ የግንባታ ማሽነሪ፤ ወዘተ) እና ለሰብል ዝግጅት (ምርጥ ዘር፤ የአፈር ማዳበሪያ፤ ለማጓጓዣ ነዳጅ፤ ጸረ-ሰብል መድሃኒት፤ ወዘተ) ኢኮኖሚው በብር ገዝቶ ማቅረብ ይችላል?
ስለዚህ ብር የሚያገለግለው ለሀገር ውስጥ ግብዓት (የውጪ ምንዛሬ ለማይጠይቁ ግብዓት ፍጆታ ካላቸው) እና የባለሙያ ክፍያ/የአገልግሎት ክፍያ ለመፈጸም ነው፡፡ ምክንያቱም የውጪ ምንዛሬ ለሚጠይቁ የፕሮጀክት ወጪዎች ብርን በቀጥታ መጠቀም ስለማይቻል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት በቂ የውጪ ምንዛሬ በሌለበት ብርን በማተም ብቻ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ በማድረግ ለማጠናቀቅ ከባድ ነው፡፡
ፕሮጀክቶች ለመጠናቀቅ ረጅም ጊዜ የመውሰድ ልምድ ስላላቸው እና አሁን በሀገራችን የሰዎች ቀጥተኛ ተሳትፎ በማሽኖች ስላልተተካ በየፕሮጀክቶቹ እና ለፕሮጀክቱ ግብዓት የሚያቀርቡ ተቋማት ከፍተኛ የሰው ሃይል ስለሆነ የሚጠቀሙት ከፍተኛ ክፍያ (በደሞዝ እና በስራ ማስኬጃ) በጠቅላላ ሂደቱ በሙሉ ይወጣል፡፡
ስለዚህ ለረጅም ጊዜ ለስራ ማስኬጃ የሚወጣው ወጪ ገበያ ውስጥ ለሸመታ በሚል ስለሚወጣ አቅርቦት እስካልተሻሻለ ያለው አነስተኛ አቅርቦት ላይ ገንዘብ ያላቸው ሸማቾች ሲጨመሩ ፉክክሩ እቃዎችን ከእጥረት የተነሳ ውድ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
#ለምሳሌ፡- ይህ ፕሮጀክት እስኪጠናቀቅ ድረስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ 10ሺ በቤታቸው/በቤተሰቦቻቸው ድጋፍ በቤት ያለስራ ተቀምጠው የነበሩ ወጣቶችን በወር የ5ሺ ብር ደሞዝተኛ ቢያድርግ፡ እነዚህ ሰዎች በየወሩ የ5ሺ ብር የአገልግሎትም ሆነ የቁሳቁስ ሸመታ ላይ ሊሳተፉ ይችላሉ! ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ምርት ወደ ገበያ ከማምጣቱ በፊት ወጣቶቹ ወደ ሸመታ በመግባታቸው ፉክክሩን በመጨመር ዋጋዎችን ከፍላጎት በተነሳ ምክንያት (Demand Pull Inflation) ውድ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
በሌላ ጎን እነዚህ የ5ሺ ብር አዳዲስ ደሞዝተኞች የባንክ ደብተር አውጥተው በወር አንድ አንድ ሺ ብር ማስቀመጥ ቢጀምሩ ባንኮች የተቀበሉትን ቁጠባ በኢንቨስትመንት መልኩ ቢያበድሩት ድጋሚ ገንዘብ ወደ ገበያው ፈሰስ ሆኖ ተመሳሳይ ችግር ሊፈጥር ይችላል፡፡ በተለይ ገንዘብን በጥሬ ገንዘብነት መያዝ ለለመደ ማህበረሰብ ከባንኩ ቁጥጥር ውጪ የሚውለውን ገንዘብ መጠን ስለሚጨምረው የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መዛባቱ ሲባባስ በተለያዩ የMonetary ዘዴዎች ገንዘቡን ወደ ማዕከላዊ ባንኩ ለመሰብሰብ አስቸጋሪ ነው፡፡
አስተውሉ የታተመው ገንዘቡ ወደ ገበያ ሳይሰራጭ ለፕሮጀክት ብቻ ማዋል የሚባል አመክንዬ ሊኖር አይችልም! እንዲሁም የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳይ ሲወራ ስለጥቂት ሰዎች ሳይሆን ስለድምር ተጽዕኖው ነው የሚወራው፡፡ ምን ማለቴ ነው ? በቀላሉ ከላይኛው ምሳሌ በመነሳት ፕሮጀክቱ ሊኖር የሚችለው አንድ ቦታ ላይ ነው፡ ሰዎቹም 10ሺ ናቸው የሚል ክርክር ቢነሳ ጠንካራ አይደለም! ምክንያቱም የማክሮ ኢኮኖሚውም ሆነ የዋጋ ንረት የሚሰላው የየአካባቢዎቹን አማካይ ጥቅል ውጤት ተወስዶ ነው፡፡
#WaseAlpha
by Wase Belay
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

#የቀብድ ግብይት አዋጪ ነው! በዋጋ ንረት ወቅት ያለወለድ አበዳሪ አካል ተጎጂ ነው።
ለወዳጃችሁ የዛሬ ዓመት ያበደራችሁትን ገንዘብ ዘንድሮ ሲከፍል ያንኑ ነው። በማህበራዊ ምክንያት የገንዘቡ የመግዛት አቅም ስለተዳከመ ወዳጅ ወለድ አስቦ አይሰጥም! አበዳሪ ለማካካሻ ወለድ አይጠይቅም።
በተመሳሳይ ቀብድ ቀድሞ ተቀባይ በማህበራዊ ተፅዕኖ የዋጋ ለውጥ ላለመፍጠር ይገደዳል። በተቃራኒው ቀብድ ቀድሞ በመክፈል የተፃፈም ሆነ ያልተፃፈ ስምምነት ውስጥ የወደቀ ሸማች ነባር ዋጋ ለመክፈል እድል ያገኛል።
#ለምሳሌ፦ ዛሬ 3ሺ ብር ለተባላችሁት እቃ ከወር በኋላ 3ሺ ብር ይዛችሁ ብትመጡ 4ሺ ብር ቢገባ ዋስትና የላችሁም! ነገር ግን በማህበራዊ ዋስትና ዘዴ ባንዱ #ቀብድ ከወር በፊት 1ሺ ብር ከፍላችሁ ቢሆን ከወር በኋላ 4ሺ ብር ዋጋ ላይ ላትወድቁ ትችላላችሁ።
ሻጮች የእጅ በእጅ ክፍያ እና የቀብድ ክፍያ መካከል ረጅም የጊዜ ልዩነት እና የዋጋ ልዩነት ላይፈጥሩ ይችላሉ የሚለው ታሳቢ ተደርጎ #እድሉ_ያላችሁ ሰዎች ለመሸመት ለወሰናችሁት ቁስ ፈጣን ውሳኔ ከሌላችሁ የዋጋ ንረት ተገማች ስላልሆነ በቀብድ መገበያየት መጥፎ አይደለም።
የዋጋ ንረት የመቀነስ ባህሪ ባለው ገበያ ላይ የቀብድ ተጠቃሚ ሻጭ ነው። በቀብድ 4ሺ ብር ያሰረው ዋጋ በገበያ ተመን 3ሺ ብር ቢወርድ ዋጋ ለመቀነስ ላይገደድ ይችላል።
የዋጋ ንረት እና የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከሙ ካልቀረ ለመሸመት ያሰቡትን በፍጥነት መሸመት ወይም እድሉ ካለ በቀብድ የጊዜ የዋጋ ለውጥን መቀነስ ይቻላል።
በቅርቡ አንዲት ልጅ ፈርኒቸር ቤት ትከራከራለች። "የዛሬ ወር ጫማ መደርደሪያ 2,800ብር እንዲሰራልሽ 500ብር ቀብድ ስጪ ሲለኝ ስላልወሰንኩ ዛሬ ላይ ያንኑ ምርት 4,000ብር ገብቷል አለኝ" ትላለች ሻጭ "ያንቺ ጥፋት ነው! ያኔ ወስነሽ ቢሆን በቅናሹ ይሰራልሽ ነበር! አሁንም ካልወሰንሽ በቀጣይ የሚደርስበትን የግብዓት ዋጋ አላውቅም" ይላል። Via #WaseAlpha

#Concept_Note _አሰራር
አንድ ጥናት ወይም ፈንድ ለማፈላለግ ከሚሰራ ፕሮጀክት (ከፕሮፖዛል በፊት) በፊት የሚዘጋጅ ሃሳባዊ መግለጫ ሲሆን ከተቻለ በአንድ ገጽ ካልተቻለ በሁለት ገጽ እንዲሆን ይመከራል (ነገር ግን እንደ ተቀባይ ድርጅት ወይም የትምህርት ተቋም የገጽ መጠኑ በጥቂቱ ከፍ ሊል ይችላል)፡፡
ርዕስ
1.የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ (የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ለመጠየቅ የሚሰራ) አልያም ለመስራት የምታስቡትን ማንኛውም የጥናት ርዕስ በተገቢው መጥቀስ::
መግቢያ (Introduction)
1.ለመስራት ያሰባችሁት ጥናት አልያም የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ ጥያቄ ጭብጥ በአጭሩ ማስረዳት፤
2.የጥናቱን ወይም የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ ጥያቄ አስፈላጊነት በአግባቡ ማስረዳት፤
3.የጥናቱን ወይም የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ ጥያቄ ስለሚፈታቸው ችግሮች ወይም ስለሚያረጋግጠው ጉዳይ ማስረዳት፤
4.እንደ አስፈላጊነቱ ከማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ፋይዳዎች አንጻር ምን እንደሚመስል ማስረዳት፤
ዓላማ (Objectives)
1.ዋና የጥናቱ ውጤት መግለጫ ዓላማ (General Objective) እና ትክክለኛ ገላጭ የሆኑ ዝርዝር ዓላማዎች (Specific Objectives) መግለጽ፤
የጥናት ስልት (Research Methodology)
1.የታሰበውን ጥናት ከክፍተት መነሳቱን ማረጋገጥ (Research Gaps)፤
2. የታሰበውን ጥናት ትክክለኛ ስልት (Research Design) ማቅረብ፤
3. የታሰበውን ጥናት ትክክለኛውን የናሙና አመራረጥ/ስብጥር ስልት ማቅረብ፤
4.የታሰበውን ጥናት የውጤት ትንተና ስልቶቹ (Data Analysis Methods) ትክክለኛነት ማረጋገጥ፤
5.የታሰበውን ጥናት የጥናቱን ጥራት (Validity እና Reliability) ስለሚረጋግጥበት መንገድ ማስረዳት፤
የሚጠበቅ ውጤት (Impact)
1.ከታሰበው ጥናት ይመጣሉ የሚባሉ ውጤቶች እንዴት እንደሚለኩ ማስረዳት፤
2. የሚመጣውን ጥናት ግኝት እንዴት ወደ ተጠቃሚዎች ማስተላለፍ እንደሚቻል ማስረዳት፤
የጊዜ እና የወጪ ሰሌዳ (Work Plan and Budget Schedule)
1.ትክክለኛ የጥናቱን እና የፕሮጀክቱን የጊዜ ሰሌዳ መግለጽ፤
2.ለጥናቱ ወይም ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልግ የበጀት ዝርዝር ማቅረብ፤
ዋቢ ጽሁፍ (Reference)
1. በአጭር ሰነድ ውስጥ የተጠቀማችሁት ዋቢ ካለ ትክክለኛ መንገዱን ተከትሎ መጥቀስ፤
Via #WaseAlpha
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig