በኢፌዲሪ ህገመንግስት አንቀፅ 34(1) ላይ ተጋቢዎች በትዳር ዘመናቸው በሁሉ ነገር ላይ እኩል መብት እንዳላቸው ይገልፃል፡፡ እንዲሁም በአንቀፅ 35(7) ላይ ሴቶች ንብረት በማስተዳደር ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው በማለት ደንግጎአል፡፡ እነኚህ የህገ መንግስቱ መርሆች በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 66(1)ላይ በማካተት ባልና ሚስቱ የጋራ ሀብታቸውን በጋራ ያስተዳድራሉ በማለት ገልጾታል፡፡ ስለዚህም በመርህ ደረጃ ባልና ሚስት የጋራ ንብረታቸውን በጋራ ያስተዳድራሉ፡፡ነገር ግን ባልና ሚስቱ በስምምነት የጋራ ንብረታቸውን አንዳቸው እንዲያስተዳድሩ ማድረግ ይችላሉ፡፡ይህም በውል ለአንደኛው ወገን እንዲያስተዳድር ሲሰጥ ነው፡፡ በተለያየ አጋጣሚ (ምክነያት) ከተጋቢዎች አንዱ ችሎታ ሲያጣ ወይም ንብረት የማስተዳደር መብቱ በፍ/ቤት ሊገፈፍ ይችላል፡፡ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሌላኛው ተጋቢ ንብረቱን የማስተዳደር ተግባር ያከናውናል፡፡ በውልም ሆነ ንብረት የማስተዳደር መብቱ በመገፈፉ ወይም ችሎታ በማጣቱ አንደኛው ተጋቢ ንብረቱን በሚያስተዳድርበት ጊዜ ሌላኛው ንብረቱን የሚያስተዳድረው ተጋቢ የንብረቱን አስተዳደር በተመለከተ ለሌላኛው ተጋቢ መረጃ የመስጠት ግዴታ እንዳለበት በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀፅ 67 ላይ ተቀምጧል፡፡
ተጋቢዎች በትዳር ተሳስረው የጋራ ንብረት አፍርተው ሲኖሩ ይህን የጋራ ንብረት በጋራ ማስተዳደር እንዳለባቸው ከላይ በተገለጸው መልኩ ለመረዳት ችለናል፡፡ እነዚህን የጋራ ንብረቶች ተጋቢዎቹ በጋራ በሚያስተዳድሩበት ወቅት ንብረቱን መሸጥ መለወጥ ያስፈልጋቸው ይሆናል፡፡ ይህ ጋራ ንብረት መሸጥ መለወጥ ከፈለጉ በሌላ የሕግ የተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር የተጋቢዎቹ የጋራ ስምምነት አስፈላጊ ነው፡፡ በአንቀጽ 68 የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው የጋራ ንብረትና ሀብት ወደሌላ ሶስተኛ ወገን በሽያጭ ሆነ በስጦታ የሚቀየረው በተጋቢዎቹ የጋራ ስምምነት ብቻ መሆኑን ይገልፃል፡፡ እዚህ ላይ በጋራ ንብረት የሆነውን አንደኛው ተጋቢ ሌላኛውን ተጋቢ ፈቃድ ወይም ስምምነት ሳያገኝ ብቻውን ለሌላ 3ኛ ወገን በሽያጭም ሆነ በሌላ መንገድ ቢያስተላልፍ ሌላኛው ተጋቢ ለፍርድ ቤት በሚያቀርበው ጥያቄ ግዴታው እንዲፈርስ መጠየቅ ይችላል፡፡ ይህ ግዴታ እንደፈረሰ የሚጠይቀው ተጋቢ ለፍ/ቤት ጥያቄውን የሚያቀርበው ግዴታው መገባቱን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ወይም በሌላ በማንኛውም ሁኔታ በ2 አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ይህ የተባለው ጊዜ ካለፈ ይህን ጥያቄ ማቅረብ እንደማይቻል በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 69(2) ላይ ተገልፆል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 38126 በአመልካች ዲያቆን ኃ/ጊዮርጊስ ወንድም እና ተጠሪዎች እነ የሺ ተፈሪ መካከል በነበረው ክርክር የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ባለቤት ከሆኑት የጋራ ንብረታቸው የሆነውን ቤት ለአሁኑ አመልካች በ01/03/1995 ዓ.ም ያለ 1ኛ ተጠሪ ፍቃድ ይሸጥለታል፡፡ 1ኛ ተጠሪም በስር ፍርድ ቤት ውሉ ያለ እሳቸው ፍቃድ የተፈጸመ በመሆኑ እነዲፈርስ በማለት በ09/08/1999 ዓ.ም ክስ ታቀርባለች፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የሰበር ችሎት የአሁን 1ኛ ተጠሪ የሆነችው ክስ ያቀረበችው በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 69/2/ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ማለትም ሽያጩን ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ወይም በማንኛውም ሁኔታ በ2 አመት ጊዜ ውስጥ ክሶን ያላቀረበች ስለሆነ (ክሶን ያቀረበችው ከ4 አመት በሆላ ነው) ውሉ እንዲፈርስ ክስ የማቅረያ ጊዜ አልፎል፡፡ ስለሆነም ውሉ አይፈርስም በማለት ውሳኔ ሰጥቶላ፡፡
የሰው ልጅ በዚህ ምድር ላይ ሲኖር እለት በለት ኑሮውን ለመደጎም ወጪዎችን ያወጣል፡፡ በትዳር ውስጥም ተጋቢዎ ትዳራቸውን ለማቃናትና ዘላቂነቱን ለማስቀጠል የተለያዩ ወጪዎች ማውጣታቸው የማይቀር ሀቅ ነው፡፡ በመሆኑም ተጋቢዎች የትዳራቸውን ወጪ ለመሸፈን እያንዳንዳቸው እንዳቅማቸውና ችሎታቸው አስተዋፅኦ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡ የህይወት መንገድ ሁልጊዜም አልጋ በአልጋ አይሆንም ውጣ ውረድ በህይወት ውስጥ ማጋጠሙ አይቀርም፡፡ በዚህ ጊዜ ወደ ብድር እና እዳ መገባት ሊያጋጥም ይችላል፡፡ በትዳር ውስጥም ተጋቢዎቹ ለግላቸው ወይም ለትዳራቸው ሲሉ እዳ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ ይህ በሆነበት ጊዜ እዳውን ለመክፈል እዳው ለግል የተወሰደ ከሆነ ከባለእዳው ተጋቢ የግል ሀብት ይሸፈናል፡፡ ነገር ግን የግል ሀብቱ ይህን ለመሸፈን የማይችል ከሆነ ተጋቢዎች የመረዳዳትና የመተጋገዝ ግዴታ ስላለባቸው ይህ እዳ ከጋራ ሀብታቸው ይከፈላል፡፡ እዳው ግን ለትዳራቸው ጥቅም ከሆነ ከጋራ ሀብታቸው የሚከፈል ይሆናል፡፡ ነገር ግን የጋራ ሀብቱ በቂ ካልሆነ ከተጋቢወቹ የግል ሀብት ይከፈላል፡፡
#legalconsulting limited
@lawsocieties
@lawsocieties https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

ውል እንዲፈርስ ለመጠየቅ መብት ስላለው ሰው፣ ስለሚጠየቅበት ጊዜ እና ስለውል መፍረስ ውጤት
=========================
1. ውል እንዲፈርስ ለመጠየቅ መብት ስላለው ሰው እና ስለሚጠየቅበት ጊዜ
ለአንድ ውል ውጤት ማግኘት የሚያስፈልጉት ሁኔታዎች የተሟሉ እንደሆነ ይፈፀማሉ፡፡ የተጓደሉ እንደሆነ ግን ውሉ እንዲፈርስ ይደረጋል፡፡ ጥያቄውን ለማቅረብ የሚችለውም በፈቃዱ ጉድለት ወይም በችሎታው ማጣት ሰበብ በውሉ የተጎዳው ወገን ብቻ ነው፡፡ ሌላ ሰው ጥቅም ኖሮት ቢሆን እንኳ ለመጠየቅ አይፈቀድም፡፡ ውሉ ከህግ ውጪ ነው፣ ለህሊና ይቃረናል ወይም የተደነገገውን የአፃፃፍ ሥርዓት አልተከተለም በሚል ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ ሥልጣን የተሰጠው ግን ለተዋዋዮችና በጉዳዩ ላይ ጥቅም አለኝ ለሚል ማንኛውም ሰው ነው፡፡ ይህ ልዩነት የኋለኞቹ ምክንያቶች ጉዳቱ ከተዋዋዮች ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ደህንነትም በላይ ጠቅላላውን ህዝብ የበለጠ የሚጎዱ ቀውስን የሚፈጥሩ ናቸው በሚል ትኩረት የተደረገባቸው መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡
ከዚህ በተረፈ ጥያቄዎቹ የሚቀርቡበት ሁኔታ በጊዜ የተገደበ ስለመሆኑ ከፍ.ብ.ህ.ቁ.1810 (2) መረዳት ይቻላል፡፡ ውል የማይረጋበት ምክንያት ከቀረበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት አመት ውስጥ ውል እንዲፈርስ መጠየቅ አለበት፡፡ ውል የማይረጋበት ምክንያት ከቀረበት ማለቱ ውሉ የማይረጋበት ምክንያት የሚቀርባቸውን እንደችሎታ ማጣት፣ አቅመ-አዳም አለመድረስ ወይም መገደድ ያሉትን አጋጣሚዎች ለመግለጽ የታለመ ነው፡፡ ሌላው የጊዜ ገደብ የተቀመጠው በጉዳት ምክንያት unconscionable contracts የተደረጉ እና አካለ መጠን ያደረሰ ሰው ያደረጓቸውን ውሎች የሚመለከቱ ናቸው፡፡ ውሉ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲፈርሱ ካልተጠየቁ ይፀናሉ፡፡
2. የውል መፍረስ ውጤት
አንድ ውል የማይረጋ በመሆኑ ምክንያት እንዲፈርስ የተደረገ እንደሆነ በተቻለ መጠን ተዋዋዮች ወደነበሩበት ቦታ እንደመለሱ ማድረግ ይገባል፡፡ ውሉ የፀና ነው በሚል ዕምነት ውሉን በመፈፀም ረገድ የተደረጉ ስራዎች ካሉ ቀሪ ይሆናሉ፡፡ ውጤት ያሌላቸው ወይም የማያስገኙ ይሆናሉ፡፡ ይህ ማለት ስለውሉ አፈፃጸም የተደረጉትን አንዱ ለሌላው መመለስ ይኖርበታል ማለት ነው፡፡
ይህ የውል ማፍረስ ውጤት አንዱ ገጽታ ሲሆን ሌላው ደግሞ ተዋዋዮችን በተለያየ ምክንያት እነበሩበት ቦታ መመለስ የማይቻል፣ አስቸጋሪ ወይም ከፍ ያለ መሰናከል የሚያመጣ ሲሆን ህጉ የሚያስቀምጠው አማራጭ ነው፡፡ ስለውሉ አፈጻጸም የተሰሩ ሥራዎች ሁሉ እንደረጉ እንዲቀሩ ያዛል፡፡
ሁልጊዜም ማለት በሚቻል ደረጃ ውል ከፈረሰ በኋላ የመጀመሪያውን አማራጭ በመጠቀም ተዋዋዮች ወደነበሩበት እንዲመለሱ በማድረግ ውሳኔ የሚሰጥ ስለመሆኑ በርካታ የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን በማየት መረዳት ይቻላል፡፡ ፍርድ ቤቶች ሁለተኛውን አማራጭ ሲጠቀሙ አይታይም፡፡ መመላለስ የሚቻልበት ሁኔታ ሁልጊዜም ስላለ ነው ብሎ መደምደም ያስቸግራል፡፡ በቅርብ ጊዜያት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነ ወ/ሮ ጎርፌ ላይ የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ በየፍርድ ቤቱ የሚቀርቡ ጉዳዮች መብዛት ይህንን ክፍተት ለመጠቀም ከመሻት የሚነሱ ናቸው ብሎ በድፍረት ለመናገር ብዙ የሚያሳቅቅ አይደለም፡፡
Via Legal consulting limited
#join #join #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties

Forwarded from Entrust Consult 📗ኢንትረስት
የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
INSA
1. የይለፍ-ቃልዎን ደህንነት ማረጋገጥ
#_የፌስቡክ አካውንቶን ለሌላ ማንኛውም የኦንላይን አገልግሎት ላይ አይጠቀሙ፤
#_ የይለፍ-ቃልዎን በፍፁም ለሌላ ሰው አያጋሩ፤
#_የሚጠቀሙበት የይለፍ-ቃል ለመገመት አዳጋች የሆነ፣ በፍጹም የእርሶን ስም እና የተለመዱ ቃላትን ያልያዘ ሊሆን ይገባል፤
#_የይለፍ-ቃልዎ ፣ኢ-ሜይልዎን፣ የስልክ ቁጥሮን ወይም የልደት ቀንዎን በፍፁም የሚጠቀም መሆን የለበትም፤
2. የሚያስሱትን ድረ-ገጽ መረጃ በፍጹም አያጋሩ
#_አጥቂዎች ፌስቡክ የሚመስል የሐሰት ገጽ ፈጥረው በኢ-ሜይል አድራሻዎና በይለፍ ቃልዎ እንዲገቡ ሊጠይቁዎ ይችላሉ፤
#_ሁልጊዜም መረጃ የሚያስሱበትን ድረ-ገጽ URL ትክክለኝነት ያረጋግጡ፤
አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ www.facebook.com በማፈላለጊያው ላይ በመጻፍ ወደ ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ለመመለስ ይሞክሩ፤
#_ ከሜታ /Meta/ ወይም ፌስቡክ የሚላክሎትን ኢ-ሜይል በፍጹም ለሌላ ሰው አያጋሩ፣ በተለይም ስለ አካውንቶ ምስጢራዊ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ፤
#_ስለፊሺንግ ጥቃት እና ጠንካራ የይለፍ-ቃል አጠባበቅ ላይ ያለዎትን እውቀትና ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤
3. ኮምፒውተርዎን ለሌላ ሰው የሚያጋሩ ከሆነ የፌስቡክ አካውንቶን ዘግተው መውጣትዎን /Log Out/ ማድረግዎን አይዘንጉ፤
#_ኮምፒውተርዎን ዘግተው ሳይወጡ ወይም መሣሪያዎን ያዋሱ ከሆነም ከርቀት እንዴት መውጣት /Log Out Remotely/ እንደሚችሉ ይወቁ፤
#_ከርቀት ሆነው ለሌላ አካል ካዋሱት ኮምፒውተር ላይ ለመውጣት(log out) ለማድረግ ወደ ፌስቡክ "Security and Login Setting" ሲገቡ ከዚህ በፊት ይገቡባቸው የነበሩ መሣሪያዎችን ዝርዝር የሚያቀርብልዎ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሚፈልጉት መሣሪያ ላይ "Logout" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን መውጣት ይችላሉ፤
4. ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄ ሲላክልዎ አይቀበሉ
#_ጠላፊዎች ሰዎችን ለማጥመድ ሲፈልጉ ሀሰተኛ አካውንት ሊፈጥሩ ይችላሉ፤
#_የጠላፊዎች ጓደኛ መሆን ምን አልባት የእርሶን የፌስቡክ የፊት ገጽን /Timeline/ ሊበክሉ፣ የተለያዩ ጉዳዮችን በገጾ ላይ ሊያጋሩ ወይም በካይ መልዕክቶችን በመልዕክት መቀበያዎ ሊልኩብዎ ይችላሉ፤
5. ከበካይ ሶፍትዌሮች እራሶን ይጠብቁ
#_አጥፊ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተሮች፣ ሰርቨሮች /Server/ ወይም የኮምፒውተር ኔትወርክ ላይ ጉዳት ሊጥሉ ይችላሉ፤
#_የተበከለ ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ምን ዓይነት ባህሪያት እንደሚያሳዩ እና እነዚህን በካይ ሶፍትዌሮችን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ በሚመለከት ያለዎትን እውቀት ያዳብሩ፤
#_ማፈላለጊያዎትን በየጊዜው ያዘምኑ፣ አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን እና የማፈላለጊያ ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ፤
6. አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን /Links/ ከሚያውቁት ጓደኛ ወይም ድርጅት እንኳ ቢላክልዎ ከመክፈት ይቆጠቡ
#_እነዚህ በፌስቡክ ወይም በኢ-ሜይል የሚላኩ ማስፈንጠሪያዎች /Links/ ሊሆኑ ይችላሉ፤
#_ፌስቡክ ወይም Meta የይለፍ-ቃሎን በኢ-ሜይል እንዲያስገቡ በፍጹም እንደማይጠይቅዎ ይወቁ፤
#_አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያ ሲያጋጥሞ ለፌስቡክ ሪፖርት /report it/ ያድረጉ፤
7. ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ መንገዶችን ይተግብሩ
#_ከማይታወቁ አድራሻዎችና መሣሪያዎች ወደ አካውንትዎ የመግባት ሙከራ ሲደረግ የጥቆማ መረጃ እንዲደርሶ /get alerts about unrecognized logins/ ያድረጉ፤
#_ባለሁለት ደረጃ የማንነት ማረጋገጫ ዘዴ /Set up two-factor authentication/ ይጠቀሙ፤
#_ሌሎች የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የፌስቡክ Help & Support ላይ በመግባት ያለዎትን ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤
https://t.me/GudayAsfetsami
#Share
Muktarovich O.

#
Muktarovich O.