አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
🛑አመክሮ ማለት ምን ማለት ነው ?
🛑ለሕግ ታራሚ የሚሰጠው ጥቅ
ምን እንደሆን ስንቶቻችን እናውቃለን ?
››››››››››››››››››››››››››››››››››
ሰላም የተወደዳቹሁ እንባቢያ!! በአገራችን እንድ የሕግ
ታራሚ በአመክሮ ተለቀቀ ሲባል በሚዲያ ሁሌ
የምንሰማው ከጀሮችን ብዙ ያራቀ ግን በውል የማንረዳው
ቃል ነው፡፡ ለመሆኑ አመክሮ ማለት ምን ማለት ነው
ለሕግ እስረኛ የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው በሚል
ርዕሰ ጉዳይ ያላቹሁን ግንዛቤ ለማሳደግ ይረዳ ዘንድ
ይህንን አሰረጂ ጥንቅር ይዘን ቀርበናል ተከታተሉን፡፡
አመክሮ የምንለው አንድ የሕግ እስረኛ የእስራት ቅጣት
ተወስኖበት ከእስራት ዘመኑ ሁለት ሦስተኛውን እንደፈጸመ
የጠባዩ መሻሻል በበቂ ሁኔታ ሲመሰከር ከእስር ቤት
እንዲፈታ የሚፈቀድበት ሁኔታ ነው፡፡ ይህም ሲባል በሕጉ
የተወሰነው የአፈጻጸም ጊዜ ሲደርስና ጠቅላላው ሁኔታ
ተሟልቶ ሲገኝ ጥፋተኛውን በአመክሮ አስቀድሞ መልቀቅ
የሚቻል መሆኑን ያመለክታል፡፡ አመክሮ ጠባይ ማሻሻያና
ወደ ማህበራዊ ኑሮ መመለሻ መሳሪያ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ
አመክሮ የሚፈቀደው እስረኛው በጠባዩ ሆነ በጠቅላላ
ሁኔታው የሚሻል መሆኑ ሲታመንና ይህም ውጤት
የሚያስገኝ መሆኑ ሲታመን ነው፡፡
የአመክሮ ጊዜ አንድ የሕግ እስረኛ የተበየነበት ረጅም
የእስራት ጊዜ ከማለቁ በፊት ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅሎ
ከአደገኛ ጥፋትና የወንጅል ድርጊት ተገትቶ የመልካም ስነ
- ምግባር ተገዥ ሆኖ ይኖር እንደሆነ የሚፈተሸበት ወቅት
ነው፡፡
በእስራት የተቀጣን የሕግ እስረኛ በአመክሮ ለመልቀቅ
በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 207 የተጠቀሱትን
ቀጥለው የተመለከቱት ሁኔታዎች መታየት ይኖርባቸዋል፡፡
1. የሕግ እስረኛው ከተፈረደበት የአስራት ዘመን ሁለት
ሦስተኛውን መፈጸሙን
2. እስረኛው በወኒ ቤት በነበረበት ጊዜ መልካም ጠባይ
ያሳየ
ለመሆኑ በቂና አጥጋቢ የምስክር ወረቀት ማግኘት
3. እስረኛው ከወኒ ቤት ሲወጣ ሥራ የሚያገኝ መሆኑ
መረጋገጡ
4. እስረኛው በተቀጣበት የወንጅል ክስ ከባላጋራው ጋር
ታርቆ
እንደሆነ የሚሉት ናቸው፡፡
የአመክሮ ሁኔታ ለሕግ እስረኛው ሊገለጽለት ይገባል፡፡
እስረኛው የተፈረደበት የእስራት ጊዜ ከማለቁ በፊት
የመፈታት ዕድል እንዲያጋጥመው ቢያውቀው መልካም
ነው፡፡ በእስራት ወቅት ምን አይነት ጠባይ ማሳየት
እንደሚገባው እንዲረዳ ማድረግ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
በተለይ የእስር ቤት ሹም በጠባዩ መሻሻል የሚያሳይ
እስረኛን ሁኔታ በመከታተል በአመክሮ ስለመፈታት የታዘዙት
ድንጋጌዎች የተፈጸሙ መሆናቸውን ሲረጋገጥ ራሱ ሹሙ
ስለ እስረኛው አስተያየት ለበላይ በማቅርብና የሕግ
እስረኛው አመክሮ እንዲታይለት የሚያቀርበውን ማመልከቻ
ተቀብሎ የድጋፍ አስተያየቱን በማስፈር ለሚመለከተው
አካል በማስተላለፍ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
አመክሮ የጊዜ ገደብ እንዳለውም በሕጉ ተመልክቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ አመክሮ የሚቆይበትን ጊዜ የመወሰን ሥልጣን
አለው፡፡ የዚህም ጊዜ ልክ ከሁለት አመት ያነሰ ከአምስት
አመት ሊበልጥ አይችልም፡፡ በተለይ በጽኑ እስራት ተወስኖ
እንዲኖር የተደረገና በተደጋጋሚ በወንጅል ድርጊት
የተሰማራ ግለሰብ ሲሆን የአመክሮ ጊዜው ከሁለት ዓመት
ሊያንስ አይችልም፡፡ በሌላ በኩል የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት
የተበየነበት ወንጀለኛ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ የአመክሮው ጊዜ
ከአምስት ዓመት የማይወርድ ይሆንል፡፡
በአመክሮ የተለቀቀ አጥፊ ተገቢ የሆነውን የጠባይ
አመራር ሥርዓት እንዲከተል ውሳኔ ማስተላለፍ ይቻላል፡፡
በዚህ ጊዜ የእስረኛው የዕድሜ መጠን፣ የአመሉን ሁኔታ፣
ሊደርስበት የሚችለውን የአደጋ ሁኔታ፣ ከእስር ቤት ከወጣ
በኃላ ለሚኖርው የኑሮ ሁኔታ፣ የሙያ፣ ሥራውንና
የማህበራዊ ኑሮውን በተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ
ማስገባት አሰፈላጊ ይሆናል፡፡
በአመክሮ የመለቀቅ ትዕዛዝ የሚሻርበትም ሁኔታ በሕጉ
ተገልጿል፡፡ አመክሮ የመለቀቅ ትዕዛዝ በአጥገቢ ሁኔታ
ቢሻር እስረኛው መጀመሪያ ወደነበረበት ሁኔታ እንዲመለስ
ማድርግ ይቻላል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ በአመክሮ
ተለቅቆ ያሳለፈውን ጊዜ ሊፈጸም የሚገባውን ቅጣት
ወይም የጥንቃቄ ተግባር መፈፀሚያ ከተወሰነበት ጊዜ
ጋር ሊታሰብበት አይችልም፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የሕግ
እስረኛው በመካከል አዲስ ጥፋት ፈጽሞ ቢገኝ የቅጣቱ
ወይም የጥንቃቄው ተግባር ውሳኔው የሚፈጸመው
በደንበኛው ድንጋጌ ላይ በተመለከተው መሰረት ይሆናል፡፡
በአንጻሩ የሕግ እስረኛው ለአመክሮ የተወሰነለትን ጊዜ
በመልካም ጠባይና አመራር የፈጸመ እንደሆነ፣
እስከመጨረሻው ነፃነቱን አግኝቶ ቅጣቱን በሙሉ
እንደሚቀርለት ሕጉ ለዚሁ አመች ሁኔታን ፈጥሮለታል፡፡
አንድ የሕግ እስረኛ ላይ በአንዳንድ ሥፍራ ከመድረሱ
የመከላከል፣ በአንድ የተወሰነ ሥፍራ ተገዶ የመኖርና
ከአገር ያለመውጣት ውሳኔ ተላልፎበት ከሆነ በአመክሮ
ጊዜ ፍርድ ቤት ይህን ሁኔታ አግዶ የሚቆይበትም ገደብ
በሕግ ተመልክቷል፡፡ይህ በሚደረግበት ጊዜ እስረኛው
የጠባይ መሻሻል ማሳየቱን፣ አደገኛ አዝማሚው
መለወጡን… ወዘተ.ከግምት ውስጥ ማስገባት
ያስፈልጋል፡፡ ፍርድ ቤት ይህን ሲያደርግ የሚመለከታቸውን
አስታዳዳሪዎች አስተያየት ይጠይቃል፡፡ እስረኛው በአመክሮ
ከተለቀቀ በኋላ ያሳየው ጠባይ አጥጋቢ ከሆነ ከአገር
እንዳይወጣ የሚከለክለውና ነፃነቱን የሚያሳጣውን ቅጣት
ጥፋቱን ሁለተኛ አይሰራውም ተብሎ ከተገመተ ሊነሳ
ይችላል፡፡
አንድ የሕግ እስረኛ የረጅም ጊዜ የእስራት ቅጣት
ቢበየንበት መደናገጡ የማይቀር ነው፡፡ መደናገጡ
አይበዛበትም፣ ምክንያቱም አስከፊ በሆነ ወንጀል ድርጊት
ባይዘፈቅ ኖሮ ይህ ዓይነቱ እጣ አይገጥመውም ነበርና፡፡
እስረኛው አሁን የረጅም ጊዜ እስራት ሲበየንበት አንድ
ሊያደርገው የሚችለው ነገር ይኖራል፡፡ይህም በጥፋት
ተጸጽቶ መልካም ዜጋ ለመሆን መጣር ነው፡፡ ዳግመኛ
በወንጀል ድርጊት እንዳይዘፈቅ ህብረተሰቡ የተቀበለውን
ሕግ እንዳይጥስ ጥንቃቄ ማድርግ ይኖርበታል፡፤ በእስር
ቤት ቆይታው ለዲሲፕሊን ተገዥ የመልካም ጠባይ
ባለቤት ሆኖ መታየት ይኖርበታል፡፡
በመልካም ዲሲፕሊን የታነጸ ዜጋ መሆን እንደሚችል
ማስመስከር ይጠበቅበታል፡፡ ይህን ካደረገ ይቅርታ
ሊያገኝ፣ የሕግና የመንግስትን እንዲሁም የሕዝብን
ምህረት ሊጉናጸፍ ይችላል እያልን የኢትዮጵያ ተስፋ
በልጆቿ እጅ በመሆኑ የአገር ጉዳይ ያገባናል የሚሉ
ኢትዮጵያዊያን ለአገራቸው ሰላም፣ ዕድገት፣ ዴሞክራሲ
በአንድነት መቆም ይጠበቅባቸዋል፡፡ከአገር የሚበልጥ
ምንም ዓይነት ግላዊም ሆነ ቡድናዊ ጥቅም የለም፡፡
ለሕግ የበላይነት ክብደትና ክብር የማይሰጥ ሕገ-ወጥ
ብቻ ነው፡፡ መልካም ዜጋ የመልካም ፀባይ ባለቤት ነው፡፡

ALE (አለ) 👍
ሸር ...............
share........................
🔴🔴🔴🔴🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
#አለ 🛑 #ALE
ከጤና ሙያ ጋር የተያያዙ ጥፋቶች የአስተዳደርና የፍትሐብሔር ኃላፊነት
---------------------------

1. የሕክምና የሙያ ስህተት / Medical Malprctice /
የህክምና የሙያ ስህተት የሚለዉ ፅንሰ ሀሳብ ወጥ የሆነ የሕግ ትርጉም አልተሰጠዉም፡፡ ነገር ግን በጥቅሉ የህክምና ስህተት ማለት አንድን የህክምና ባለሙያ ባለዉ አቅምና ችሎታ የህክምና ሥራዉን በሚያከናዉንበት ጊዜ ለሚሰራዉ ሥራ ጥንቃቄ በጎደለዉ መልኩ ወይም ጥንቃቄ መዉሰድ ሲገባዉ ሊመጣ የሚችለዉን ጉዳት እያወቀ ወይም ማወቅ ሲኖርበት በታካሚዉ ላይ ጉዳት ማድረስ ነዉ፡፡ ታካሚዉና የህክምና ጤና ተቋሙ የህክምና ዉል በመፈጸም ግዴታ ሲያቋቁሙ ታካሚዎች በሚታከሙበት ጊዜ በታካሚዉ ላይ ሊመጣ የሚችለዉ ጉዳትና አዳጋ በመገንዘብ አካሚዉ ጥንቃቄ በጎደለዉ መልኩ ከተከናወነ ለሚደርሰዉ ጉዳት እንደዉሉ ያልተፈፀመ በመሆኑ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በ1962 የወጣዉ የፍትሐብሔር ሕግ የጤና ባለሙያዉ የማዳን ዋስትና የለዉም እንደሚል በመጥቀስም የጤና ባለሙያ ለማዳን ዋስትና እንዲሰጥ እንደማይገደድ ተደንግጓል፡፡ ለዚህም ነዉ አንድ ታካሚ የሚጠበቀዉን የሕክምና ዉጤት አላገኘሁም በማለት የሕክምና ባለሙያን ለመክሰስ የማይችለዉ፡፡ የሕክምና ስህተት ሕግ ሀኪሞች ወይም ሌላ የሕክምና አገልግሎት ሰጪ አካላት የሕክምና አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት በታማሚው ላይ በቸልተኝነት ለሚያደርሱት ጉዳት ያለባቸውን ተጠያቂነት የሚገዛ ሕግ ነው፡፡ ቸልተኝነት ከደረጃዉ ዉጪ ሕክምና መስጠት ወይም የታወቀ የሕክምና ሥነ-ሥርዓትን በጤና ባለሙያዎች የተለመደ አሰራር መሰረት አለመከተል ነዉ፡፡ አንድ የሕክምና ባለሙያ የሕክምና አገልግሎት ሲሰጥ በተመሳሳይ ጉዳይ ሌሎች የሕክማና ባለሙያዎች ሊያከብሯቸው ወይም ሊፈጽሟቸው የሚገባውን መደበኛ ጥንቃቄ (“standard of care”) ሊያከናውን ወይም ሊከተል ባለመቻሉ ምክንያት በታማሚው ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ የሕክምና ባለሙያው ለጥፋቱ ተጠያቂ የሚሆንበት አሠራር የሕክምና ስህተት ሕግ ይባላል፡፡

1.1 የህክምና ስህተት ተፈጽሟል የሚባለዉ ምን ምን ሲሟላ ነዉ?

1. ሐኪሙ ለታካሚዉ ሕክምና የመስጠት ግዴታ አለመወጣቱ፤
አንድ የህክምና ባለሙያ ለአንድ ታካሚ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ግዴታ ያለበት መሆኑን ወይም ሕክምናዉን የሰጠዉ እርሱ መሆኑን በማረጋገጥ የህክምና ስህተት ተፈጥሯል የሚለዉን ጉዳይ ለመወሰን ከሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ ነዉ፡፡ ይህ የሚሆነዉ የአካሚና ታካሚ ሕጋዊ ግንኙነት መኖሩ ሲረጋገጥ ነዉ፡፡
አንድ የህክምና ባለሙያ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እስከተሰማራና የህክምና ተግባራትን የሚያከናውን እስከሆነ ድረስ የሚያከናውናቸውን ተግባራት እና በዘርፉ ያሉትን የህክምና አሰራሮች ላይ እውቀትና ክህሎቱን በየጊዜው መገንባት አለበት፡፡ ለዚህም ነው ከሐኪም ቀዳሚ ግዴታዎች መካከል ዋነኛዉ በሚያከናዉነዉ ተግባር ብቁ ባለሙያ ሆኖ መገኘት ነዉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለተገልጋይ የሚሰጠዉ አገልግሎትና እንክብካቤ የዘር፣ የጾታ፣ የሃይማኖት ወዘተ… መድልኦ የሌለበትና ተመሳሳይነት ሊኖረዉ ይገባል፡፡

አንድ ሐኪም ተገቢዉን የሙያ ትጋትና ጥረት በማድረግ ጥንቃቄ የተሞላበት የህክምና አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ በዚህ መሰረት ሐኪሙ በህክምና ሙያዉ ጥበብ ወይም አሰራር መሰረት ማድረግ የሚጠበቅበትን እንዲሁም ከታካሚዉ ጋር በገባዉ የዉል ስምምነት ወይም በሕግ መሰረት የተጣለበትን ግዴታ ሳይወጣ ቀርቶ በታካሚዉ ላይ ጉዳት ካደረሰ እና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ የሕክምና ስህተት ፈጽሟል ለማለት ይቻላል፡፡ አንድ ሐኪም ከህክምና ሙያዉ አሰራርና ጥበብ ዉጭ የሕክምና አገልግሎት መስጠት አለመስጠቱ የሚረጋገጠዉ በተመሳሳይ ሙያ ላይ በተሰማሩ የሕክምና ባለሙያዎች ነዉ፡፡ ስለሆነም አንድ ሐኪም ግዴታዉን አልተወጣም ሊባል የሚችለዉ ከሕክምናዉ አሰራር ጥበብ ዉጭ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት በታካሚዉ ላይ ጉዳት ካደረሰ ነዉ፡፡

2. የመንስኤ (ምክንያት) እና የዉጤት ግንኙነት፤

አንድ የህክምና ባለሙያ የህክምና ስህተት ፈጽሟል ለማለት እና በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በታካሚዉ ላይ የደረሰዉ የአካል ወይም የህይወት አደጋ የተፈጠረዉ በሐኪሙ ስህተት መሆን ይኖርበታል፡፡ በምክንያቱና በወጤቱ መካከል ግንኙነት አለ የሚባለዉ በነገሮች የታወቀ ወይም የተለመደ ሂደት የሀኪሙ ድርጊት ወጤቱን ለማስገኘት የሚችል ሆኖ ሲገኝ ነዉ፡፡ ይህ አይነቱ መርህ ወንጀልን ለማቋቋም እንደ አንድ መስፈርት የተቀመጠ ሲሆን በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 24 ንዑስ አንቀጽ 1 ስር በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ የህግ ስርአት የቅርብ ምክንያትን እንጂ የሩቅ ምክንያትን አይቀበልም፡፡ በሌላ በኩል ጉዳት ባይደርስም ነገር ግን የህክምና ባለሙያው መከተል ያለበትን የተለመደ ሥርዓት ባለመከተል የፈፀመው ተግባር ካለ የህክምና ስህተት የለም ማለት አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

3. ጉዳት መድረስ፤

ጉዳት ደረሰ የሚባለዉ የህክምና ባለሙያዉ በቸልተኝነት ጉዳቱን ያደረሰ ስለመሆኑ ሲረጋገጥ ሲሆን አንድ ሀኪም ለታካሚዉ የሕክምና አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት ወይም ከዚያ በኋላ በታካሚዉ ላይ ጉዳት አድርሶ እንደሆነ ነዉ፡፡ ጉዳት ማለት ከቀላል የአካል ጉዳት እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል እና በሀኪሙ ስህተት ምክንያት የተፈፀመ ማለት ነዉ፡፡ ለምሳሌ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት አንድ ሐኪም ከህክምናዉ አሰራር ዉጭ ሕክምና በማድረግ በታካሚዉ ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት መጥቀስ ይቻላል፡፡

4. በታካሚው ላይ የደረሰው ጉዳት ወደ ሚታወቅ ሌላ ጉዳት ያጋለጠው መሆንን ማረጋገጥ፣

ምንም እንኳን የሕክምና ባለሙያው የሕክምና ስህተት ቢፈጽምም ወይም የፈጸመው ድርጊት በተመሳሳይ የሕክምና ባለሙያ መስፈርት ከደረጃ በታች ቢሆንም ስህተት የተፈጸመበት ታማሚ ጉዳት እንደደረሰበት እስካላረጋገጠ ድረስ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዞ ለመሔድ አይችልም፡፡ ምክንያቱም ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው መፍትሄ በአንድ አጥፊ ምክንያት ጉዳት መድረሱን ማረጋገጥና የደረሰውን ጉዳት የሚክስ ውሳኔ የመስጠት ተግባር በመሆኑ ነው፡፡ ሆኖም በአስተዳደራዊ ጥፋት ረገድ በዲስፕሊን የህክምና ባለሙያውን ሊጠይቅ ይችላል፡፡
ምን ዓይነት ስህተቶች ናቸው የሕክምና ስህተት የሚባሉት ለሚለዉ ስህተቶች የሕክምና ስህተት የሚባሉት በተለያዩ ዘርፍ ውስጥ ሊወድቁ ይችላሉ፡፡

ከእነዚህም መካከል፡-•

 በምርምራ ወቅት ታማሚውን በተገቢዉ ሁኔታ አለመመርመር ወይም የታማሚውን ሁኔታ ለመመርመር መዘግየት፣
 የምርመራ ውጤቶችን በተሳሳተ መንገድ መረዳት ለምሳሌ የኤክስሬይ ዉጤቶችን አሳስቶ ማንበብ ወይም መረዳት፣
 መድኃኒት ከመስጠት ጋር በተያያዘ ለምሳሌ ትክክል ያልሆነ፣ የተሳሳተ ወይም የሚጋጭ የመድኃኒት ትዕዛዝ መስጠት፣
 አንድ የሕክምና ሥነ ሥርዓት ያለውን ጉዳት ወይም ሥጋት ለታማሚው አለመንገር፣ አለማስረዳት ወይም አለማስጠንቀቅ፣
የወጣት ጥፋተኞች የወንጀል ተጠያቂነት እና የሚወሰዱ የጥንቃቄ እርምጃዎች
------------------------------
1. የወጣትነት እና ወጣት ጥፋተኛነት ትርጉም

የወጣትነት የእድሜ ክልል በአለም አቀፍ ደረጃ ወጥነት የሌለው ሲሆን የተለያዩ አለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እና ብሄራዊ ህጎች የተለያየ እድሜን ያስቀምጥሉ፡፡ ለምሳሌ የአፍሪካ ህብረት 15-35 ዓመት ያሉ ሰዎችን ወጣት ተደርገው የሚወሰዱ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የወጣትነት ፖሊሲ 15-29 ዓመት የወጣትነት የእድሜ ክልል እንደሆነ ይገልፃል፡፡ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መብት ኮንቬክሽን አካል መጠን ካልደረሰ ህፃን ማለት እድሜው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆነ ሰው እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ ለወጣትነት እና ለህፃናት በእነዚህ ስምምነቶች የተቀመጠውን የእድሜ ገደብ ስንመለከት ህፃንነት በወጣትነት ውስጥ ተካቶ እናገኘዋለን፡፡ እነዚህ የእድሜ ክልሎች የወጣቶችን መብት እና ግዴታ ከሌላው አዋቂ ሰው በተለየ መልኩ ለመወሰን ጠቀሜታ አላቸው፡፡

ከወንጀል ሀላፊነት አንፃር ለወጣት ጥፋተኝነት በብላክስለው የህግ መዝገበ ቃላት የተሰጠውን ትርጉም ስንመለከት ወጣት ማለት በወንጀል ህግ ስርዓት ውስጥ እንደ አዋቂ የመታየት ዕድሜ ላይ ያልደረሰ ሰው ነው በማለት ይተረጉመዋል፡፡ እንዲሁም ወጣት ጥፋተኝነትን በህፃናት የሚፈፀሙ ፀረ-ማህበራዊ በተለይ በአዋቂ ቢፈፀሙ ኖሮ በወንጀል ሊያስጠይቁ የሚችሉ ባህሪያትን የያዘ ሆኖ ለህፃናቱ ብቻ በተዘረጋ ልዩ ህግ መሠረት የሚያስቀጣ ማለት ነው በሚል ትርጉም ሰጥቶታል፡፡ ይህም ለአካለ መጠን ያላደረሰ በማለት የሚታወቅ ሲሆን ወጣት ማለት ጨቅላ ህፃንም አዋቂም ያልሆነ በዚህ መካከል ያለ ሰው ማለት ነው፡፡

ከወጣት ጥፋተኝነት የዕድሜ ወሰን ጋር ተያይዞ በህፃናት መብቶች ኮንቬንሽን ላይም ሆነ በአፍሪካ የህፃናት መብቶችና ደህንነት ቻርተር ላይ የወጣት አጥፊዎች የዕድሜ ወሰን ያልተመለከተ በመሆኑ በተለያዩ ሀገሮች ላይ የተለያየ ትርጉም እንዲሰጠው ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህ ልዩነት የብዙ ችግሮች ምክንያት በመሆኑ የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ ከ12 ዓመት በታች የወንጀል ተጠያቂነት እንዲኖር ማድረግ እና የወጣት አጥፊነትን የዕድሜ ጣሪያ እስከ 18 ዓመት ድረስ አለማድረግ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ አባል ሀገራት የዕድሜውን ወሰን በ12 እና 18 ዓመት መካከል እንዲያደርጉ ገልጿል፡፡

2. የወጣት ጥፋተኛነት ምድብ
በኢትዮጵያ የወንጀል የፍትህ ስርዓት ውስጥ ወጣት ጥፋተኝነት እውቅና የተሰጠው ሲሆን የወንጀል ህግ ከ18 ዓመት በታች ያሉ ህፃናትን ለወንጀል ፍትህ አስተዳደር ሂደት ሲባል ለሦስት ምድብ ከፍሎአቸዋል፡፡
1ኛ. ከ9 ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ ህፃናት ሲሆኑ በወንጀል አንቀጽ 52 መሠረት የወንጀል ኃላፊነት የሌለባቸው በመሆኑ ቤተዘመዶቻቸው፣ አስተማሪዎቻቸው፣ አሳዳሪዎቻቸው ወይም ሌሎች የቅርብ አካላት ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉላቸው እንደሚገባ ተቀምጧል፡፡

2ኛ. ከ9-15 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ህፃናት በወንጀል ውስጥ ተካፋይ ሆነው በተገኙ ጊዜ እንደወጣት አጥፊ ተቆጥረው የወንጀል ተጠያቂነት ያለባቸው መሆኑን አንቀጽ 53 ስር ተደንግጓል። ይሁንና እነዚህ ወጣት አጥፊዎችን በተመለከተ የምርመራውንም ሆነ የፍርድ ሂደቱን ከአዋቂዎች በተለየ መንገድ በልዩ ድንጋጌዎች የሚመራ ነው፡፡ ለአዋቂ ጥፋተኞች የተደነገጉ መደበኛ ቅጣቶች ለወጣት ወንጀል አድራጊዎች ተፈፃሚነት አይኖራቸውም፡፡ ከአዋቂዎች ጋርም አይታሰሩም፡፡
3ኛ. ከ15 እስከ 18 ዓመት የዕድሜ ክልል ያሉ ወጣቶች በወንጀል ህጉ አንቀጽ 56 መሠረት የወንጀል ኃላፊነት ያለባቸው ሲሆን እንደ አዋቂ ተቆጥረው በመደበኛው ፍርድ ቤት ጉዳያቸው የሚታይ ነው፡፡ ይሁንና በዚህ ምድብ ውስጥ የሚገኙ ህፃናትን በተመለከተ የዕድሜያቸውን ትንሸነት ፍ/ቤቱ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ቅጣቱ ሊቀልላቸው እንደሚችል በዚሁ ድንጋጌ ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

3. የቅጣት ወይም የጥንቃቄ እርምጃ አወሳሰን
ፍርድ ቤቱ በወጣት ጥፋተኛው ላይ ቅጣት ወይም የጥንቃቄ እርምጃ በሚወሰንበት ጊዜ ዕድሜውን፣ ጠባዩን፣ የአዕምሮና የሞራል ዕድገቱን ሁኔታ እንዲሁም ቅጣት ወይም የጥንቃቄ እርምጃው በጥፋተኛው ላይ ሊያመጣ የሚችለውን መልካም ለውጥ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡
3.1. እድሜያቸው ከ9-15 ዓመት ባሉ ወንጀል አድራጊዎች ላይ የሚወሰኑ የቅጣትና የጥንቃቄ እርምጃዎች

i. መደበኛ የጥንቃቄ እርምጃዎች
በወንጀል ህጉ የተካተቱ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ስንመለከት ለአካለመጠን ያልደረሰውን ሰው ሕክምና ወደሚያደርግበት ተቋም መላክ፣ ቁጥጥር በማድረግ ትምህርት መስጠት፣ ተግሳፅ እና ወቀሳ ማድረግ፣ በትምህርት ቤት ወይም በመኖሪያ ቤት ተወስኖ እንዲቆይ ማድረግ እንዲሁም ወደ ጠባይ ማረሚያ ተቋም መላክ ያካተተ ነው፡፡ የጥንቃቄ እርምጃዎቹ የሚቆዩበት ጊዜ እንደየ እርምጃዎቹ እና ሊያሳኩ እንደፈልጉት ግብ ይለያያል፡፡ ህክምና እና እየተጠበቁ የመማር የጥንቃቄ እርምጃዎች ፀንተው የሚቆዩት የህክምናው ባለስልጣን ወይም የጥበቃው ባልደረባ ያስፈልጋል በማለት ወስኖ ባቀረበው ጊዜ ልክ ሲሆን ወንጀል አድራጊው ለአካለ መጠን እስከሚደርስበት ጊዜም ሊቀጥሉ ይችላሉ፡፡ የጥንቃቄ እርምጃዎቹ ዓላማቸውን ከግብ ያደረሱ መሆናቸውን በመግለፅ ኃላፊነት የተሰጣቸው ባለስልጣኖች የሚያቀርቡት አስተያየት ፍርድ ቤቱ ሲያምንበት የጥንቃቄ እርምጃዎቹ ቀሪ ይሆናሉ፡፡

በሌላ በኩል ወደ ጠባይ ማረሚያ ተቋም የመላክ ውሳኔ የሚታዘዘው ቢያንስ አንድ ዓመት ቢበዛ አምስት ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ነው፡፡ ይሁንና በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን ወጣቱ በህግ የተወሰነለት ለአካለመጠን ከሚደርስበት ዘመን በላይ አያልፍም፡፡ እንዲሁም ፍርድ ቤቱ ለወጣት ወንጀል አድራጊው ጠቃሚ ሆኖ ሲያገኘው የሰጠውን ትዕዛዝ ሊለውጥ ይችላል፡፡ የጥንቃቄ እርምጃዎቹን ህጋዊ ውጤት በተመለከተ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 165 ስር የተደነገገ ሲሆን ይህውም የህክምና፣ የትምህርት ወይም የማረም የጥንቃቄ እርምጃዎች አንዱ የተወሰነበት ወጣት በወንጀል አድራጊነት በወንጀል እንደተቀጣ አይቆጠርም፡፡ ይህም እንደ ሪከርድ አይያዝም ማለት ነው፡፡

ii. ቅጣቶች
በመርህ ደረጃ በወጣት ጥፋተኞች ላይ ቅጣት የሚጣለው የተወሰዱ የጥንቃቄ እርምጃዎች ፍሬ ሳያገኙ የቀሩ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ለአካለመጠን ያልደረሰው ወንጀል አድራጊው የፈፀመውን ጥፋት በማመዛዘን አስፈላጊ ከሆነ የልዩ አዋቂ ምስክርነትና ምርመራዎች እንዲደረጉ ካደረገ በኃላ ነው፡፡ የገንዘብ መቀጮ እና እስራት ለአካለመጠን ያልደረሰ ወንጀል አድራጊ ላይ ሊጣሉ የሚችሉ ቅጣቶች ሲሆኑ ወንጀል አድራጊው መቀጮ መክፈሉ ቅጣት ሆኖ የሚሰማው፣ የሚያስተምረውና ከጥፋቱ የሚመልሰው መስሎ ሲታየውና ራሱ መቀጮውን ለመክፈል የሚችል መሆኑን ሲረዳው ፍርድ ቤቱ እንደጥፋቱ ከባድነትና እንደገንዘብ አቅሙ መቀጮ እንዲከፍል ሊፈርድበት ይችላል፡፡ መቀጮ ከሌላ ቅጣት ጋር እንደተጨማሪ ቅጣት ሊጣል የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ህጉ ያስቀምጣል፡፡
የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
INSA

1. የይለፍ-ቃልዎን ደህንነት ማረጋገጥ

#_የፌስቡክ አካውንቶን ለሌላ ማንኛውም የኦንላይን አገልግሎት ላይ አይጠቀሙ፤

#_ የይለፍ-ቃልዎን በፍፁም ለሌላ ሰው አያጋሩ፤

#_የሚጠቀሙበት የይለፍ-ቃል ለመገመት አዳጋች የሆነ፣ በፍጹም የእርሶን ስም እና የተለመዱ ቃላትን ያልያዘ ሊሆን ይገባል፤

#_የይለፍ-ቃልዎ ፣ኢ-ሜይልዎን፣ የስልክ ቁጥሮን ወይም የልደት ቀንዎን በፍፁም የሚጠቀም መሆን የለበትም፤

2. የሚያስሱትን ድረ-ገጽ መረጃ በፍጹም አያጋሩ

#_አጥቂዎች ፌስቡክ የሚመስል የሐሰት ገጽ ፈጥረው በኢ-ሜይል አድራሻዎና በይለፍ ቃልዎ እንዲገቡ ሊጠይቁዎ ይችላሉ፤

#_ሁልጊዜም መረጃ የሚያስሱበትን ድረ-ገጽ URL ትክክለኝነት ያረጋግጡ፤
አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ www.facebook.com በማፈላለጊያው ላይ በመጻፍ ወደ ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ለመመለስ ይሞክሩ፤

#_ ከሜታ /Meta/ ወይም ፌስቡክ የሚላክሎትን ኢ-ሜይል በፍጹም ለሌላ ሰው አያጋሩ፣ በተለይም ስለ አካውንቶ ምስጢራዊ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ፤

#_ስለፊሺንግ ጥቃት እና ጠንካራ የይለፍ-ቃል አጠባበቅ ላይ ያለዎትን እውቀትና ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

3. ኮምፒውተርዎን ለሌላ ሰው የሚያጋሩ ከሆነ የፌስቡክ አካውንቶን ዘግተው መውጣትዎን /Log Out/ ማድረግዎን አይዘንጉ፤

#_ኮምፒውተርዎን ዘግተው ሳይወጡ ወይም መሣሪያዎን ያዋሱ ከሆነም ከርቀት እንዴት መውጣት /Log Out Remotely/ እንደሚችሉ ይወቁ፤

#_ከርቀት ሆነው ለሌላ አካል ካዋሱት ኮምፒውተር ላይ ለመውጣት(log out) ለማድረግ ወደ ፌስቡክ "Security and Login Setting" ሲገቡ ከዚህ በፊት ይገቡባቸው የነበሩ መሣሪያዎችን ዝርዝር የሚያቀርብልዎ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሚፈልጉት መሣሪያ ላይ "Logout" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን መውጣት ይችላሉ፤

4. ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄ ሲላክልዎ አይቀበሉ

#_ጠላፊዎች ሰዎችን ለማጥመድ ሲፈልጉ ሀሰተኛ አካውንት ሊፈጥሩ ይችላሉ፤

#_የጠላፊዎች ጓደኛ መሆን ምን አልባት የእርሶን የፌስቡክ የፊት ገጽን /Timeline/ ሊበክሉ፣ የተለያዩ ጉዳዮችን በገጾ ላይ ሊያጋሩ ወይም በካይ መልዕክቶችን በመልዕክት መቀበያዎ ሊልኩብዎ ይችላሉ፤

5. ከበካይ ሶፍትዌሮች እራሶን ይጠብቁ

#_አጥፊ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተሮች፣ ሰርቨሮች /Server/ ወይም የኮምፒውተር ኔትወርክ ላይ ጉዳት ሊጥሉ ይችላሉ፤

#_የተበከለ ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ምን ዓይነት ባህሪያት እንደሚያሳዩ እና እነዚህን በካይ ሶፍትዌሮችን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ በሚመለከት ያለዎትን እውቀት ያዳብሩ፤

#_ማፈላለጊያዎትን በየጊዜው ያዘምኑ፣ አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን እና የማፈላለጊያ ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ፤

6. አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን /Links/ ከሚያውቁት ጓደኛ ወይም ድርጅት እንኳ ቢላክልዎ ከመክፈት ይቆጠቡ

#_እነዚህ በፌስቡክ ወይም በኢ-ሜይል የሚላኩ ማስፈንጠሪያዎች /Links/ ሊሆኑ ይችላሉ፤

#_ፌስቡክ ወይም Meta የይለፍ-ቃሎን በኢ-ሜይል እንዲያስገቡ በፍጹም እንደማይጠይቅዎ ይወቁ፤

#_አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያ ሲያጋጥሞ ለፌስቡክ ሪፖርት /report it/ ያድረጉ፤

7. ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ መንገዶችን ይተግብሩ

#_ከማይታወቁ አድራሻዎችና መሣሪያዎች ወደ አካውንትዎ የመግባት ሙከራ ሲደረግ የጥቆማ መረጃ እንዲደርሶ /get alerts about unrecognized logins/ ያድረጉ፤

#_ባለሁለት ደረጃ የማንነት ማረጋገጫ ዘዴ /Set up two-factor authentication/ ይጠቀሙ፤

#_ሌሎች የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የፌስቡክ Help & Support ላይ በመግባት ያለዎትን ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

https://t.me/GudayAsfetsami
#Share
Muktarovich O.
በስልካችን ላይ ሊኖሩ የማይገቡ አደገኛ መተግበሪያዎቸ

በውስጣቸው አጥፊ ቫይረሶችን የያዙ ነገር ግን አገልግሎት የሚሰጡ በመመስል የተሰሩ መተግበሪያዎች አሉ። ቀጥለው የተዘረዘሩ መተግበሪያዎች በስልኮቻችን ላይ ካሉ ልናጠፋቸው ይገባል።
የመተግበሪዎቹን መጠሪያ በተከታዩ ሊንክ ያገኛሉ፤ https://am.al-ain.com/article/apps-you-have-delete-from-smartphones