አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
208865.pdf
477.1 KB
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 208865 በማኅበር ተደራጅቶ የቤት መሥሪያ ቦታ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ እያሉ በሥራ ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወር ከመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበር አባልነት የሚያሰርዝ ስላለመሆኑ የሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም፡፡
#ethiolawreview
👍52
👎🏿#አለሕግ አካታች መሰረተ ልማት ለህዝባችን! #share #ሼር!
👎39😡14😁8👍3🤔3
#በዋስትና በሚያስለቅቅ ጉዳይ ላይ ፖሊስ ያለበቂ ምክንያት ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ከጠየቀ ለችሎት ይህን ያሳስቡ። "በቅድሚያ ፖሊስ ምርመራውን ሳያጠናቅቅ እኔን ማሰሩ ተገቢ አልነበረም። አሁንም ቢሆን ምርመራውን ለማከናው ተጨማሪ ጊዜ የጠየቀባቸው ምክንያቶች ከእኔ መታሰር ጋር የሚያገናኘው አይደለም።
በመሆኑም በዋስትና እንድወጣ ውሳኔ ይሰጠኝ። ያ ካልሆነ ደግሞ የሚሰጠው ጊዜ ቀጠሮ አጭር ይሁንልኝ።"
#በዚህ አግባብ ዋስትና ያልተፈቀደለት ግለሰብ ግን በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 66 መሠረት በፍርድ ቤት ዋስትና እንዲፈቀድለት መጠየቅ ይችላል።
ይግባኝ መብት ነው!!!
via #ይግባኝምክረሕግ

ለበለጠ ሙያዊ ምክር የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ይጠይቁ፣
ይኸ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።


https://t.me/lawsocieties
ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👍102
በኢትዮጵያ ውስጥ የሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 17 በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጪ ማንኛውም ሰው ነፃነቱን እንደማያጣ ይደነግጋል።
በተጨማሪም ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጪ ሊያዝ፣ ክስ ሳይቀርብበት ወይንም ሳይፈረድበት ሊታሰር እንደማይችል በግልፅ ይደነግጋል።
ኢትዮጵያ ተቀብላ ያፀደቀችው የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን (ICCPR) አንቀፅ 9 ማንኛውም ሰው ነፃነቱ እና ደህንነቱ ተከብሮ የመኖር መብት እንዳለው እና በዘፈቀደ ከሚደረግ እስር ሊጠበቅ እንደሚገባ ይደነግጋል።
ሕግ አስከባሪዎች ማንኛውም ሰውን በቁጥጥር ስር ከማዋላቸው በፊት የዜጎች ነፃነትን ለመጠበቅ የወጡ ሕጎች የጣሉባቸውን ግዴታዎች በሙሉ መሟላታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።

ምስል-በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተቀናበረ
#AHRE( Association for Human Rights in Ethiopia)

Alternative legal enlightenment (ALE)አለ
አማራጭ የሕግ እውቀት፣🔴ሕግ

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
👍11
IB.pdf
348.8 KB
ሙዓለ: ንዋይ: ባንክ
ኢንቨሰትመንት ስንል በተለምዶ
“ሙዓለ ንዋይን”

(ገንዘብን ሰራ ላይ ማዋል) የሚልን ሃሳበ ለመግለጽ ሰንፈልግ የምንጠቀመው የእንግሊዝኛ ቃል ነው:: ከሰነደ ሙዓለ ንዋይ ጽንሰ ሃሳበ ጋር በተያያዘ
‹‹የኢንቨሰትመንት ባንክ››

የሚለውን ሰያሜ በቀጥታ ከመጠቀም ይልቅ ኢትዮጵያዊ ይዘት ያለው የአማርኛ ቃል ተጠቅመን ሰፊው የማህበረሰባችን ክፍል ሀሳቡን እንዲረዳው በማሰብ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር ፲፪፻፵፰/፳፻፲፫ ዓ.ም አንቀጽ ፴፬ ላይ ‹‹የኢንቨስትመንት ባንክ›› በሚል የተጠቀሰውን ሀረግ ሙዓለ ንዋይ ባንክ የሚል አቻ የአማርኛ ቃል ለመስጠት ሞክረናል። በዚህ መሰረት ሙዓለ ንዋይ ባንክ ማለት ‹‹የኢንቨስትመንት ባንክ›› እንደሆነ ልብ ይበሉ፡፡
አንብቡት ትጠቀሙበታላችሁ።
https://t.me/lawsocieties
👍142😁2
👍3
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ፈቃድ መስጠት እንደሚጀመር ገለፀ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከየካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ፈቃድ መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ ከተቋቋመ ጊዜ አንስቶ ራሱን በማደራጀት የሕግ ማዕቀፍ ሲያዘጋጅ መቆየቱን የገለፁ ሲሆን አሁን ላይ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ በማዘጋጀት ወደ ሥራ መግባቱን ገልፀዋል።

በዚህ መሰረትም በዘርፉ ሥራ ላይ የሚገኙ አካላት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ መመዝገብ እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን ባለስልጣኑ 15 አዳዲስ ፈቃዶች መስጠት እንደሚጀምር ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ መስጠት እንደሚጀመርም የተገለፀ ሲሆን የመንግስት የልማት ድርጅቶችም በዚህ ማዕቀፍ ለመካተት ዝግጅት ማድረጋቸውን ተመላክቷል።

ሶስት ትላልቅ የውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮች መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እንደተሰጣቸውም ነው የተገለፀው።
#TikvahethMagazine
https://t.me/lawsocieties
👍61
የኢንቨስትመንት ባንክ ምንድነው ? ከሌሎች ባንኮች በምን ይለያል ?

የንግድ ባንኮች የሚባሉት ፦ በብሔራዊ ባንክ ስር የሚተዳደሩ ፤ ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ተሰጥቷቸው የሚተዳደሩ ናቸው።

ኢንቨስትመንት ባንክ ፦ በካፒታል ገበያ አዋጅ መሰረት የሚቋቋም፣ በካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፍቃድ የሚሰጠው ነው። ከግለሰቦች ተቀማጭ የሚወስድ ከሆነ የኢንቨስትመንት ባንክ መሆን አይችልም።

የኢንቨስትመንት ባንኪግ ስራ ምንድነው ?

ዋና ስራው ወደ ካፒታል ገበያ የሚመጡትን ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች ፣ መንግስት ፣ ከተሞች ሊሆኑ ይችላሉ ቦንድ መሸጥ ሲፈልጉ ፣ አክሲዮን መሸጥ ሲፈልጉ ፦
* አክሲዮኑ ምን ይመስላል ?
* አክሲዮኑ በምን ያህል ዋጋ ይሸጥ ?
* መቼና ለማን ይሸጥ ? የሚለውን የፋይናንስ ስትራተጂ ላይ የምክር አገልግሎት የሚሰጡና የሚያገናኙ በካፒታል ገበያ ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚጫወቱ ናቸው።

ለምሳሌ ፦ አንድ በግል የተያዘ ድርጅት ፤ ወደ ህዝብ ድርጅት ነው መቀየር የምፈልገው ፣ የሼር ኩባንያ ነው መሆን የምፈልገው ብሎ ሼሩን የካፒታል ማርኬት ላይ መሸጥ ቢፈልግ ድርጅቱ ምን ያህል ነው ዋጋው ? ለአብነት ወደ 2000 ሼር ቀይሬ 2 ሺህ ሼር ለገበያው ሸጣለሁ ቢል እያንዳንዱ ሼር ዋጋው ምን ያህል ነው የሚለውን አጠቃላይ ስራ የሚሰራው ኢንቨስትመንት ባንክ ነው።

በተጨማሪ ኢንቨስትመንት ባንክ ፦

* price discovery / ገበያው ላይ ኩባንያዎች ያላቸው እውነተኛ ዋጋቸው ምንድነው የሚለውን ያጣራል።
* የካፒታል ገበያ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ያማክራል።
* የካፒታል ብክነት እንዳይኖርና ካፒታል ወደአስፈላጊው ቦታ እንዲሄድ ያደርጋል።

ኢንቨስትመንት ባንኮች እንደ ሌሎች የንግድ ባንኮች ከሰዎች ላይ ተቀማጭ ገንዘብ / deposit አይወስዱም።

የኢንቨስትመንት ባንኮች የማማከር ስራን የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ ኩባንያዎች የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ለመግባት ሲወስኑ ኩባንያውን ማዛጋጀት፣ ሼሩ ምን ያህል ነው የሚለውን መለየት ፣ ምን ያህል ሼር ለምን ያህል ሰው የሚለውን መለየት ስራዎችን ይሰራሉ።

የካፒታል ገበያውን የሚቆጣጠረው አካል ፤ በካፒታል ገበያው ለሚሳተፉ አካላት ፍቃድ ከመስጠት እና ሂደቱን ከመቆጣጠር ባለፈ ኢንቬስተሮች በየትኛው ዘርፍ መሳተፍ አለባቸው የሚለውን አይወስንም ሃሳብም አይሰጥም ፤ ይህን የሚያደርጉት የአዋጭነት ትንተናዎችን በመስራት የኢንቨስትመንት ባንኮች ናቸው።

ማማከር፣ ኢንቬስተሮችን እና ተፈላጊ የፋይናንስ ሃብት ማገናኘት የኢንቨስትመንት ባንኮች ስራ ይሆናል። የካፒታል ገበያ ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶችን ወክለው ከሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያው ሆነ ከተቆጣጣሪ መ/ቤቱ ጋር በመሆን ብዙ ስራዎች ይሰራሉ።

ለኢንቨስትመንት ባንክ መስረታ የሚጠየቀው ካፒታል ለንግድ ባንኮች ከሚጠየቀው #ያነሰ ነው።

የንግድ ባንኮች በዚህ ላይ መሳተፍ ይችላሉ ?

አሁን በኢትዮጵያ ስራ ላይ ያሉ የንግድ ባንኮች ጎን ለጎን የኢንቨስትመንት ባንክ ተሳትፎ የሚያደርጉበት እድል አላቸው።

እንደ ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን መረጃ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መስፈርቱን ለሚያሟሉ የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ መስጠት የሚጀምር ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ያሉና ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ባንኮችም የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠብቅ ተስፋ ተደርጓል።

Credit ፦
#DrBirukTaye (ECMA Director)
#SirakSolomon (ECMA Senior Legal Advisor)
#YohanessArega (ECMA Senior Advisor)
#WuberstTessema (Journalist , FBC)

ዝግጅት ፦ #TikvahEthiopia

#tikvahethiopia
👍14🎉1
Bench book for civil proceedings.pdf
314.1 KB
ስርዓተ ችሎት (Bench- Book)

ለማዘጋጀት ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት በዕለት ተዕለት የችሎት አካሄድ ስርዓት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሁኔታዎችን ዳኛው በቀላሉና በፍጥነት ሊፈታ የሚችልበትን ማጣቀሻ (guideline) ለማዘጋጀት ነው ::
ስርዓተ ችሎቱ መደበኛውን የፍ/ሥ/ሥ/ህግ የሚተካ አይደለም :: በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ውስጥ የተካተቱትን ጉዳዬች በሙሉ የያዘም አይደለም ፡፡

የዚህ ስርዓተ - ችሎት ዋና መሠረት የፍ/ሥ/ሥ/ህጉ ሆኖ ነገር ግን :-

1. በሥ/ስርዓት ህጉ ውስጥ የተካተቱ ሆነው ነገር ግን ጠቅለል ባለ አገላለጽ የተደነገጉ በመሆናቸው ማብራሪያ የሚሹ ጉዳዬችን ለማብራራት ተሞክሯል ፡፡

2. በህጉ በግልፅ ያልተሸፈኑ ነገር ግን በዕለት ተዕለት የፍ/ቤቶች ሥራ ውስጥ በብዛት የሚያጋጥሙ የሥነ ስርዓት ጉዳዩችን በተመለከተ ያለውን ክፍተት ለመሙላት ጥረት ተደርጓል ።

3. በስነ - ስርዓት ህጉ የተሸፈኑ ሆነው ነገር ግን በአተረጓጎምና በአተገባበር ረገድ በፍ/ቤቶች ወይም በዳኞች መካከል ልዩነት የሚታይባቸውን ዋና ዋና የስነ ስርዓት ጉዳዩች በተመለከተ በተቻለ መጠን ልዩነቶቹ የሚጠቡበትንና ህጎች በተመሣሣይ ሁኔታ የሚተረጐሙበትንና የሚተገበሩበትን አቅጣጫ ለማሣየት ተሞክሯል ።

ከላይ እንደተገለፀው የስርዓተ- ችሎቱ ዋና መሠረት የሥ/ሥርዓት ህጉ ቢሆንም ማብራሪያ የሚሹ ነጥቦችን ለማብራራትና ክፍተቶችን ለመሙላት ግን ልምድ ያላቸው ዳኞችን ፣ ጠበቆችንና ሌሎች የህግ ሰዎችን በቃልና በጽሁፍ በመጠየቅና በማማከር የተገኙ ሃሣቦች እንዲሁም የሌሎች ሀገሮች ልምድ እንደመነሻ ሃሣብ በጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ስርዓተ- ችሎቱ እንደ ህግ አዛዥነት ባይኖረውም እንዲቀላል ማጣቀሻ ፣ እንደማብራሪያና እንደ ክፍተት መሙያ ግን ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ይታመናል ፡፡
https://t.me/Ethiopialegalinfo
👍17
አካለመጠን ያልደረሰ ልጅ አስተዳደግ በተመለከተ (ሞግዚት)

ልጁ የተወለደው የባልና ሚስት ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ከሆነ ወላጆቹ የልጁ አሳዳሪነትና ሞግዚትነት የጋራ ስልጣን አላቸው፡፡
ከወላጆቹ አንዱ በሞተ ጊዜ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ስልጣኑን ለማከናወን ካልቻለ አንደኛው ወገን ብቻ ሃላፊነት እንዲሸከም ይደረጋል፡፡
አያድርገውና የቀረው ወላጅ ልጁ አካለ መጠን ሳይደርስ የሞተ ከሆነ እና የኑዛዜ ቃል ትቶ ከሆነ ፡ አሳዳሪና ሞግዚት ለልጁ በዚሁ አግባብ ይሾምለታል፡፡
ነገር ግን ወላጁ ምንም አይነት ኑዛዜ ካልተወ የቤተሰብ ሕጉ እራሱ አሳዳሪ እና ሞግዚት እንዲሆኑ በቅደም ተከተል የሚሾሙትን ሰዎች ያስቀምጣል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ የልጁ አያቶች ይገኛሉ ፡ እነዕርሱ ከሌሉ፣ ህጉ የሚሾመው አካለ መጠን የደረሱ የልጁን ወንድም ወይም እህት ነው፡፡ እነዚህም ከሌሉ የልጁ አጎት እና አክስት ይሾማሉ፡፡ እንግዲህ ይህ ሁሉ ጥረት ተደርጎ ሃላፊነት ሊሰጠው የሚገባ ሰው ከታጣ ምንም ማድረግ ስለማይቻል ፡ ለፍርድ ቤት በሚቀርብ ጥያቄ ፡ ከልጁ ዘመዶች ውጪም ቢሆን አሳዳሪና ሞግዚት ይሾምለታል፡፡
ቢሆንም ግን ይህ ቅደም ተከተል አጠቃላይ አካሄድ የሚያሳይ እንጂ በሁሉም ጊዜ እና ሁኔታ ተፈፃሚነት የሚኖረው አይደለም፡፡ ይህ ቅደም ተከተል ፡ የልጁን ጥቅምና ደህንነት መሰረት ያደረገ ነው ተብሎ ነው የሚገመተው፡፡ ነገር ግን በዚህ ስርአት ማስኬዱ የልጁን ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ከተገነዘበ ይህ የአሳዳሪና ሞግዚት አመዳደብ ስርአት ፍርድ ቤቱ ላይከተለው ይችላል፡
በጠበቃ ሳሙኤል ግርማ
https://t.me/lawsocieties
0920666595 #ለጠበቃ
👍71
የመንግስት ሰራተኞች ግብር ቅነሳን እና ዝቅተኛውን የደመወዝ ወለል በተመለከተ ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ገለጸ‼️

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልና ግብር ቅነሳን በተመለከተ የፍትሕና የገንዘብ ሚኒስቴርን ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ለሰራተኞች የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል እንዲቀመጥና ሰራተኛው ላይ የተጫነው ግብር እንዲቀነስ ጠቅላይ ሚኒስትሩን መጠየቁ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ በሁሉም የቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተለያዩ ተቋማት አቅጣጫ ሰጥተዋል የሚሉት የኮንፌደሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው አህመድ እስካሁን የተሰጠ ምላሽ እንደሌለ ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
አቅጣጫ ከተሰጣቸው ተቋማት መካከል የገንዘብ ሚኒስቴር እና የፍትህ ሚኒስቴር ተጠቃሽ ሲሆኑ ከተቋማቱ የሚሰጠውን ምላሽ እየተጠባበቅን ነው ብለዋል፡፡
ኮንፌዴሬሽኑ ጉዳዩን እየተከታተለ ነው ያሉት አቶ አያሌው፥ የሚዘገይ ከሆነ በድጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንደሚጠይቁም ገልፀዋል።
የኑሮ ውድነቱ በየጊዜው እየተባባሰ ሰራተኛው ቤተሰቡን ለማስተዳደደርም ሆነ እራሱን ለመደጎም መቸገሩን በመጥቀስም፥ ለዚህ ጉዳይ አፋጣኝ ምላሽ እንደሚያስፈልግ ማንሳታቸውን ገልፀዋል::
#healthinovation
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
0920666595
👍102🤔1
በሕግ አስከባሪ አካላት በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎች በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አላቸው። ተጠርጣሪዎች የቀረቡበት ፍርድ ቤት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆዩ በሚፈቅድበት ጊዜ ኃላፊ የሆኑት የሕግ አስከባሪዎች ምርመራውን አጣርተው የተያዘው ሰው በተቻለ ፍጥነት ፍርድ ቤት እንዲቀርብ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 19 ስር ተደንግጓል።
በተጨማሪም የሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 20 የተከሰሱ ሰዎች ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ በመደበኛ ፍርድ ቤት ለሕዝብ ግልፅ በሆነ ችሎት የመስማት መብት እንዳላቸው ይደነግጋል።

የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን አንቀፅ 14-3(C) ማንኛውም ክስ የቀረበበት ሰው ያለምንም መዘግየት ፍርድ የማግኘት መብቱ ሊጠበቅ እንደሚገባ አስፍሯል።

የሕግ አስከባሪ አካላት እና ፍርድ ቤቶች በቅጥጥር ስር ያሉ እና ክስ የተመሰረተባቸው ዜጎች የተፋጠነ ፍርድ እንዲያገኙ በሕገ መንግሥቱ እና ኢትዮጵያ ተቀብላ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን ሰነዶች የተጣለባቸውን ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅባቸዋል።
Via #AHRE( Association for Human Rights in Ethiopia)
ምስል፡ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተቀናበረ
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
0920666595
👍71
ማዳጋስካር ህጻናትን የሚደፍሩ ወንዶች ብልት እንዲቆረጥ የሚያዝ ህግ አዘጋጀች

በማዳጋስካር ህጻናትን የደፈሩ ወንጀለኞች በአምስት ዓመት እስር እየተቀጡ ናቸው
ማዳጋስካር ህጻናትን የሚደፍሩ ወንዶችን ብልት እንዲቆረጥ የሚያዝ ህግ አዘጋጀች፡፡
በደቡብ ምዕራብ አፍሪካ የምትገኘው ማዳጋስካር ህጻናትን የሚደፍሩ ወንዶችን ብልት እንዲቆረጥ የሚያስገድድ ህግ አውጥታለች፡፡
ሀገሪቱ ህጻናቶቿን ከመደፈር አደጋ ለመጠበቅ ጥብቅ ረቂቅ ህግ ያዘጋጀች ሲሆን በዚህ ህግ መሰረት ደፋሪዎች ብልታቸው እንዲቆረጥ ይገደዳሉ፡፡
ከ10 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን የደፈሩ ወንዶች ብልታቸው በቀዶ ጥገና ሐኪም ተቆርጦ እንዲጣል ይደረጋል የተባለ ሲሆን ከ13 እስከ 18 ዓመት የሆናቸው ህጻናትን የደፈሩ ሰዎች ደግሞ በኬሚካ አማካኝነት ብልታቸው እንዲጎዳ ይደረጋል ተብሏል፡፡
የማዳጋስካር ፍትህ ሚኒስትር ላንዲ በጉዳዩ ዙሪያ ለኤፍፒ በሰጡት ማብራሪያ በሀገሪቱ የሚደፈሩ ህጻናት ቁጥር እየጨመረ ሲሆን ይህንንም ለመከላከል የግድ ጠንካራ ህግ ማዘጋጀት አስፈልጎናል ብለዋል፡፡
በ2023 ብቻ 600 ህጻናት ተደፍረዋል ያሉት ሚኒስትሯ ላንዲ ጥፋተኛ የሆኑ ተከሳሾች በትንሹ ከአምስት ዓመት ጀምሮ እስር እየተላለፈባቸው ቢሆንም ለውጥ አለመምጣቱንም ጠቅሰዋል፡፡
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ ተቋም አምንስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ ድርጊቱ ጭካኔ እንጂ ጥፋተኞችን አያስተምርም ሲል አዲሱን የማዳጋስካር ህግ ተችቷል፡፡
የማዳጋስካር ፕሬዘዳንት ሁሉንም ሚኒስትሮች ከስራ አገዱ
ህጻናት ከጥቃት መጠበቅ አለባቸው፣ ደፋሪዎችም በህግ መጠየቅ አለባቸው ያለው አምንስቲ ኢንተርናሽናል ነገር ግን እርምጃው በሰዎች ላይ መገለልን እና የባሰ ጨካኝ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነውም ብሏል፡፡
ድርጅቱ አክሎም ወንጀሉን ሳይፈጽሙ ነገር ግን በብዙ ምክንያቶች ጥፋተኛ የሚባሉ ሰዎች ይኖራሉ በዚህ ጊዜ ህጉ ተግባራዊ ከተደረገ ሊቀለበስ የማይችል ጉዳት በሰዎች ላይ ሊደርስም ይችላል ሲል አሳስቧል፡፡
ይህ አከራካሪ ህግ አስገዳጅ ህግ ለመሆን ከግማሽ በላይ ያሉ ሂደቶችን አልፏል የተባለ ሲሆን የላይኛው ምክር ቤት ውሳኔ እና የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፊርማ ይቀረዋል ተብሏል፡፡
https://am.al-ain.com/article/madagascar-passes-a-bill-to-cut-rapist-manhood

https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ! 0920666595
February 10, 2024
👍87
አዲሱ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበር ረቂቅ አዋጅ . . .

ላለፉት 49 ዓመታት በሥራ ላይ የቆየው የሕዝብ በዓላትን እና የእረፍት ቀንን ለመወሰን የወጣ አዋጅ በአዲስ ሊተካ ረቂቅ መዘጋጀቱ ሲገለፅ ፓርላማው መጋቢት ወር ላይ ወደ ሥራ ሲመለስ ይመለከታቸዋል ተብሎ ከሚጠበቁ አዋጆች መካከል ይህ ረቂቅ አዋጅ የሚገኝበት መሆኑ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ያለው በደርግ መንግሥት የወጣው አዋጅ 13 የሕዝብ እና ሃይማኖታዊ በዓላትን በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበሩ የደነገገ ሲሆን ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ በዚህ አዋጅ ውስጥ የድል ቀን ላይ ብቻ ማሻሻያ በማድረግ ይሄንን አዋጅ መተግበር መቀጠሉና አሁን በሥራ ላይ ባለው አዋጅ እና በአተገባበሩ ላይ ክፍተቶች እንዳሉት ተጠቁሟል።

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ያመጣቸው ለውጦች ምንድናቸው?

- አዲሱ ረቂቅ አዋጅ፤ ከቀድሞው አዋጅ የሚለየው ዋነኛ ጉዳይ የበዓላት አከባበርን በተመለከተ ዝርዝር ሁኔታዎችን የያዘ ሲሆን ረቂቅ አዋጁ የሕዝብ በዓላትን “ተከብረው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት” ፣ “ታስበው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት” እና “ሃይማኖታዊ በዓላት” ሲል ይከፋፍላቸዋል።

- ተከብረው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት መደበኛ ሥራ ዝግ የሚሆንባቸው ቀናት እንደሆነ ረቂቁ ላይ የሰፈረ ሲሆን እነዚህም የዘመን መለወጫ፣ የአድዋ ድል፣ የላብአደሮች ቀን እና የአርበኞች (የድል) ቀን ናቸው።

- ሥራ ሳይዘጋ ታስበው የሚውሉ ብሔራዊ በዓላት 2የሰማዕታት ቀን እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን መሆናቸው ሲገለፅ ወደ ም/ቤቱ የተላከው ረቂቅ ላይ በሃይማኖታዊ በዓልነት የተቀመጡት አምስት የክርስትና እንዲሁም ሦስት የእስልምና እምነት በዓላት ሲሆኑ ከዚህ ቀደም ከነበረው ዝርዝር ውስጥ የተደረገ ለውጥ የለም ተብሏል።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛ ነው
#TikvahethMagazine
👍20👎72🔥1
Dear CEHRO members and partners, we have an ezciting news from the SIHA Network. ,

We hope this message finds you well.

We are excited to share an opportunity that we believe would be beneficial for our network members ,partners and allies . As part of our commitment to building capacity and extending our reach, we have opened a call for applications for an upcoming Training of Trainers (ToT) for female lawyers from Ethiopia. This initiative is a collaborative effort between the SIHA Network and FIDA-Uganda, aiming to empower participants with skills in policy and law reform, strategic litigation, and documenting sexual violence in conflict settings.

This training is particularly geared towards enabling female lawyers to become trainers, who will then disseminate their knowledge to Women’s Rights Activists and other female lawyers in Ethiopia.

Key Details:

- Training Dates: March 4th - 7th, 2024

- Location: Kampala, Uganda

- Provided: All travel and accommodation costs for participants

We seek applications from dedicated women lawyers who are passionate about women's rights advocacy and have a commitment to effecting change through legal reform.

To apply, please complete the form linked below with the required information, including a 2-page summary of your CV/Resume.


Application Form: https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSco9dRzfxSyC9PsVF7-EtDzze5LIcpc1mb4TtCtHVU7Go-zfQ/viewform

Google Forms: Sign-in
Access Google Forms with a personal Google account or Google Workspace account (for business use).
docs.google.com

We encourage all eligible candidates to apply by Monday, February 19, 2024, and take part in this transformative experience. Please share among your networks.
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍171
#vacancy for lawyers
1
20 ፓኬት ሲጋራ በእንጀራ ውስጥ ደብቆ ተጠርጣሪ ለመጠየቅ የሄደው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አንበሳ ጋራዥ ጀርባ ወደሚገኘው የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ስንቅ ለማቀበል በሚመስል መልኩ በያዘው ሳህን ውስጥ ወደ ተጠርጣሪ ማቆያ ቤት ሲጋራ ለማስገባት የሞከረው ግልሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

በፖሊስ መምሪያው የተጠርጣሪ ማረፊያ ቤት አካባቢ የፍተሻ እና የማረጋገጥ ስራ የሚሰሩ የፖሊስ አባላት በወቅቱ ግለሰቡ ምግብ አስመስሎ የያዘውን ሳህን እንዲከፍት አድርገው ሲመለከቱ 20 ፓኬት ሲጋራ ከላይ በእንጀራ ተሸፍኖ ማግኘታቸው ተገልጿል።

በወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ጣቢያ የተጠርጣሪ ማቆያ ቤት ለሚገኙ ሰዎች ሲጋራ ማስገባት የተከለከለ ሲሆን፤ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በወጣው ደንብ ቁጥር 299/2006 ላይ በተደነገገው መሰረት ትምባሆን በማንኛውም ህዝብ በሚሰበሰብበት ወይም በሚገለገልበት ቦታ ማጨስ ክልክል እንደሆነ ተደንግጎ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
#TikvahethMagazine
👍131👏1
የጋብቻ አፈፃፀም በተሻሻለው የፌዴራል ቤተሰብ ህግ


መግቢያ

ጋብቻ በሀገራችን ለዘመናት አክብሮት ተሰጥቶት የኖረ የማህበራዊ መስተጋብራችን አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ጋብቻ ዘርፈ ብዙ ውጤቶችን የሚያስከትል እንደመሆኑ ከምስረታው ጀምሮ በህግ የሚገዛ እና ጥበቃ የሚደረግለት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ ፅሁፍም የጋብቻን ምንነት፣ በህጉ እውቅና ያላቸውን የአፈፃፀም ሥርአቶች እና ጋብቻ ለመመስረት ሊሟሉ የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በአጭሩ የምንመለከት ይሆናል፡
የጋብቻ ምንነት
ጋብቻ በተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ ቀጥተኛ ትርጓሜ ባይሰጠውም ከህጉ ጠቅላላ መንፈስ መረዳት የሚቻለው አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ህጋዊ እና ማህበራዊ ተቀባይነት ባለው ሥርአት የሚፈጥሩትን ጥምረት የሚወክል ነው፡፡
ጋብቻ ያለው የህግ ጥበቃ
ጋብቻ ህጋዊ እና ማህበራዊ ውጤቶችን የሚያስከትል እንደመሆኑ ሀገራችን ተቀብላ ባፀደቀቻቸው አለም አቀፍ እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ሰነዶች፣ በእነዚህ የሰብአዊ መብት ሰነዶች መሰረት በተቃኘው የኢፌድሪ ህገ መንግስት እንዲሁም በተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ የቤተሰብ መመስረቻ መንገድ መሆኑ ታውቆ የህግ ጥበቃ ይደረግለታል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት በአንቀፅ 34(3) ቤተሰብ የህብረተስብ የተፈጥሮ መሰረታዊ መነሻ እንደሆነ እና የህብረተሰብ ብሎም የመንግስትን ጥበቃ የማግኘት መብት እንዳለው ደንግጓል፡፡ ጋብቻም የዚህ ቤተሰባዊ ግንኙነት ዋነኛ መመስረቻ ሥርአት እንደመሆኑ ጥበቃ የሚደረግለት ነው፡፡ በተጨማሪም በ1992 ዓ.ም የወጣው የተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ 213/1992 የቤተሰብ ህግ ከምስረታው ጀምሮ በሚኖረው ቆይታ እንዲሁም በሚፈርስበት ሂደት የሚደረግለትን ጥበቃ በዝርዝር የደነገገ ህግ ነው፡፡
የጋብቻ አፈፃፀም ሥርአቶች
በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 1 መሰረት ሶስት አይነት የጋብቻ አፈፃፀም ሥርአቶች አሉ፡፡ ይኸውም፡-

• በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈፀም ጋብቻ
በተሻሻለው በቤተሰብ ህግ አንቀፅ 2 መሰረት አንድ ወንድ እና ሴት ጋብቻ ለመፈፀም ተስማምተው በክብር መዝገብ ሹም ፊት በመቅረብ ፈቃዳቸውን ሲገልፁ እና የክብር መዝገብ ሹሙም ይህንኑ ፈቃዳቸወን ሲቀበል ጋብቻ የሚፈፀምበት ሥርአት ነው፡፡
• በሀይማኖት ሥርዐት መሠረት የሚፈፀም ጋብቻ
በተሻሻለው በቤተሰብ ህግ አንቀፅ 3 መሰረት አንድ ወንድ እና አንድ ሴት በሀይማኖታቸው ወይም ከሁለቱ በአንዳቸው ሀይማኖት መሠረት የሚፀና ጋብቻ ለማቋቋም የሚያስፈልገውን ሥርዐት ሲፈፅሙ ጋብቻ የሚፈፀምበት ሥርአት ነው፡፡ ይህ አማኞች በሚከተሉት እምነት ማለትም በእስልምና፣ በክርስትና እንዲሁም በሌሎች እምነቶች መሰረት የሚፈፀም ጋብቻ ነው፡፡
• በባህል ሥርዐት መሰረት የሚፈፀም ጋብቻ
በተሻሻለው በቤተሰብ ህግ አንቀፅ 4 መሰረት አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት በሚኖሩበት አካባቢ ባህል ወይም በሁለቱ ተጋቢዎች ወይም ከሁለቱ ተጋቢዎች በአንዳቸው ባህል መሰረት የሚፀና ጋብቻ ለማቋቋም የሚያስፈልገውን ሥርዐት ሲፈፅሙ ጋብቻ የሚፈፀምበት ሥርአት ነው፡፡
ጋብቻ ለመፈፀም መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
ጋብቻው በየትኛውም አይነት አፈፃፀም ሥርአት የሚፈፀም ቢሆንም ከመፈፀሙ በፊት የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላትታቸው መረጋገጥ አለበት፡፡
• ፈቃድ
ጋብቻ በተጋቢዎች ነፃ እና ሙሉ ፍቃድ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ ይህ ማለት ተጋቢዎች ወይም ከተጋቢዎቹ አንዱ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ጋብቻ እንዲፈፅሙ ሊገደዱ አይችሉም ማለት ነው፡፡ ይህ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 34(2) እና በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 6 የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ተጋቢዎች እራሳቸው ፈቃዳቸውን መግለፅ ያለባቸው ሲሆን በማስገደድ፣ በማሳሳት እና በመሳሰሉት መንገዶች ጋብቻው ቢፈፀም እንኳል ሊፀና አይችልም (የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 13 እና 14)፡፡
• እድሜ
በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 7 መሰረት ወንዱም ሆነ ሴቷ 18 አመት ካልሞላቸው ጋብቻ አይፈፀምም፡፡ ሆኖም ከባድ ምክንያት ባጋጠመ ጊዜ ተጋቢዎቹ ወይም ከተጋቢዎቹ የአንዳቸው መላጆች ወይም አሳዳሪ ጥያቄ ሲቀርብ ፍትህ ሚኒስቴሩ ከመደበኛ የጋብቻ እድሜ ከ2 አመት ያልበለጠ ጊዜ ቀንሶ እንዲጋቡ በልዩ ሁኔታ ሊፈቅድ ይችላል፡፡
• የሥጋ እና የጋብቻ ዝምድና
በተሸሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 8 መሰረት በቀጥታ የሥጋ ዘመዳሞች ማለትም በወላጆችና በተወላጆች፣ ወደ ጎን በሚቀጠሩ የሥጋ ዘመዶች ማለትም በወንድምና እህት እንዲሁም የአክስትና የአጎት ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካካል ጋብቻ ሊፈፀም አይችልም፡፡ በተመሳሳይ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 9 መሰረት በቀጥታ የጋብቻ ዘመዳሞች፣ ወደ ጎን በሚቆጠር የጋብቻ ዘመዳሞች ማለትም አንደኛው ተጋቢ ከሌላኛው ተጋቢ እህትና ወንድም ጋር ጋብቻ መፈፀም የተከለከለ ነው፡፡
• የቀደም የፀና ጋብቻ መኖር
አስቀድሞ ጋብቻ የፈፀመ ሰው የቀደመ ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ሌላ ጋብቻ እንዲፈፅም አይፈቀድለትም (የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 11)፡፡
• የፍርድ ክልከላ መኖር
የህግ ውጤት ያላቸውን ተግባራት እንዳያከናውን በፍርድ ቤት ክልከላ የተደረገበት ሰው ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቦ ካልፈቀደለት በስተቀር ጋብቻ መፈፀም አይችልም (የቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 15)፡፡
የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች ጥሶ ጋብቻ ሊፈፅም ያሰበ ቢኖር በሚመለከተው ወገን ተቃውሞ የሚቀርብ ሲሆን ይኸውም ተቃውሞው
• በእድሜ ምክንያት ሲሆን ወላጆች፣ ዐቃቤ ህግ ወይም ሌላ ማንኛውም ሰው
• በሥጋ ወይም በጋብቻ ዝምድና ምክንያት ከሆነ የተጋቢዎቹ ወላጆች፣ 18 አመት የሞላቸው ወንድምና እህቶች ወይም ዐቃቤ ህግ
• በጋብቻ ላይ ጋብቻ ከሆነ ጋብቻ ከሚፈፅመው ሰው ጋር የቀደመ የፀና ጋብቻ ያለው ሰው ወይም ዐቃቤ ህግ
• በፍርድ ክልከላ የተደረገበት ከሆነ ደግሞ አሳዳሪው ወይም ዐቃቤ ህግ
በተሸሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 18 መሰረት ጋብቻው እንዳይፈፀም መቃወም ይችላሉ፡፡
ማጠቃለያ
ጋብቻ የማህበረሰብ መሰረት የሆነው ቤተሰብ የሚመሰረትበት ሥርአት ሲሆን ከአመሰራረቱ ጀምሮ የህግ ጥበቃ የሚደረግለት እና አፈፃፀሙም በህግ የሚመራ ነው፡፡ ስለሆነም ጋብቻ ህጉን ተከትሎ እንዲመሰረትና ጥሰቶችም ሲገኙ እነዲታረሙ በማድረግ ጤነኛ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሁሉም ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል፡፡
በንቃተ ህግ ተምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍141