አካለመጠን ያልደረሰ ልጅ አስተዳደግ በተመለከተ (ሞግዚት)
ልጁ የተወለደው የባልና ሚስት ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ከሆነ ወላጆቹ የልጁ አሳዳሪነትና ሞግዚትነት የጋራ ስልጣን አላቸው፡፡
ከወላጆቹ አንዱ በሞተ ጊዜ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ስልጣኑን ለማከናወን ካልቻለ አንደኛው ወገን ብቻ ሃላፊነት እንዲሸከም ይደረጋል፡፡
አያድርገውና የቀረው ወላጅ ልጁ አካለ መጠን ሳይደርስ የሞተ ከሆነ እና የኑዛዜ ቃል ትቶ ከሆነ ፡ አሳዳሪና ሞግዚት ለልጁ በዚሁ አግባብ ይሾምለታል፡፡
ነገር ግን ወላጁ ምንም አይነት ኑዛዜ ካልተወ የቤተሰብ ሕጉ እራሱ አሳዳሪ እና ሞግዚት እንዲሆኑ በቅደም ተከተል የሚሾሙትን ሰዎች ያስቀምጣል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ የልጁ አያቶች ይገኛሉ ፡ እነዕርሱ ከሌሉ፣ ህጉ የሚሾመው አካለ መጠን የደረሱ የልጁን ወንድም ወይም እህት ነው፡፡ እነዚህም ከሌሉ የልጁ አጎት እና አክስት ይሾማሉ፡፡ እንግዲህ ይህ ሁሉ ጥረት ተደርጎ ሃላፊነት ሊሰጠው የሚገባ ሰው ከታጣ ምንም ማድረግ ስለማይቻል ፡ ለፍርድ ቤት በሚቀርብ ጥያቄ ፡ ከልጁ ዘመዶች ውጪም ቢሆን አሳዳሪና ሞግዚት ይሾምለታል፡፡
ቢሆንም ግን ይህ ቅደም ተከተል አጠቃላይ አካሄድ የሚያሳይ እንጂ በሁሉም ጊዜ እና ሁኔታ ተፈፃሚነት የሚኖረው አይደለም፡፡ ይህ ቅደም ተከተል ፡ የልጁን ጥቅምና ደህንነት መሰረት ያደረገ ነው ተብሎ ነው የሚገመተው፡፡ ነገር ግን በዚህ ስርአት ማስኬዱ የልጁን ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ከተገነዘበ ይህ የአሳዳሪና ሞግዚት አመዳደብ ስርአት ፍርድ ቤቱ ላይከተለው ይችላል፡፡
በጠበቃ ሳሙኤል ግርማ
https://t.me/lawsocieties
0920666595 #ለጠበቃ
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍7❤1