አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የመንግስት ሰራተኞች ግብር ቅነሳን እና ዝቅተኛውን የደመወዝ ወለል በተመለከተ ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ገለጸ‼️

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልና ግብር ቅነሳን በተመለከተ የፍትሕና የገንዘብ ሚኒስቴርን ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ለሰራተኞች የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል እንዲቀመጥና ሰራተኛው ላይ የተጫነው ግብር እንዲቀነስ ጠቅላይ ሚኒስትሩን መጠየቁ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ በሁሉም የቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተለያዩ ተቋማት አቅጣጫ ሰጥተዋል የሚሉት የኮንፌደሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው አህመድ እስካሁን የተሰጠ ምላሽ እንደሌለ ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
አቅጣጫ ከተሰጣቸው ተቋማት መካከል የገንዘብ ሚኒስቴር እና የፍትህ ሚኒስቴር ተጠቃሽ ሲሆኑ ከተቋማቱ የሚሰጠውን ምላሽ እየተጠባበቅን ነው ብለዋል፡፡
ኮንፌዴሬሽኑ ጉዳዩን እየተከታተለ ነው ያሉት አቶ አያሌው፥ የሚዘገይ ከሆነ በድጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንደሚጠይቁም ገልፀዋል።
የኑሮ ውድነቱ በየጊዜው እየተባባሰ ሰራተኛው ቤተሰቡን ለማስተዳደደርም ሆነ እራሱን ለመደጎም መቸገሩን በመጥቀስም፥ ለዚህ ጉዳይ አፋጣኝ ምላሽ እንደሚያስፈልግ ማንሳታቸውን ገልፀዋል::
#healthinovation
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
0920666595
👍102🤔1
በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የሠራተኛ እና አሠሪዎች ማኅበራትን በተመለከተ በስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ ለተደረገ ጥናት መረጃ የሰጡ ባለሙያዎች በኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ላይ የመብት ጥሰት እንደሚፈፀም አስረድተዋል።ከሥራው ጋር ያልተመጣጠነ አነስተኛ ደመወዝ ክፍያ፣ ያለምንም ክፍያ ትርፍ ሰዓት ማሠራት እና ለሥራ አስፈላጊ የሆኑ የደኅንነት እና የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች ሳይሟሉ እንዲሠሩ መገደደ ከመብት ጥሰቶቹ መካከል ተጠቀሱ ናቸው።

ሠራተኞች በአግባቡ የተወሰነ የሥራ ሰዓት ዕረፍት፣ የመዝናኛ ጊዜ፣ በየጊዜው ከክፍያ ጋር የሚሰጡ የዕረፍት ቀኖች፣ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የሕዝብ በዓላት እንዲሁም ጤናማ እና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብት እንዳላቸው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 43 ስር ተደንግጓል።
#healthinovation
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍51👏1