አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በኮንስትራክሽን ውል ስለ ግንባታ ስራ ርክክብ/Acceptance/
======**=======
#በኮንስትራክሽን ውል ሁለት አይነት የግንባታ ስራ ርክክብ ያለ ሲሆን ይሄውም ግዚያዊ ርክክብ(provisional acceptance) እና የመጨረሻ ርክክብ(final acceptance) የሚያካትት ነው፡፡
#በዚህ ጽሁፍ በዋናነት በኮንስትራክሽን ውል ህግ እውቅና የተሰጣቸውን የርክክብ አይነቶች ምንነትና ተያያዥ ውጤታቸውን አስመልክቶ የህግ ድንጋጌዎችን እና አሁን ላይ በመንግስት ተቋማት እየተሰራበት ያለውን የፒፒኤ 2011 ጀኔራል ኮንዲሽን ድንጋጌዎችን ባካተተ ሁኔታ ለማብራራት ተሞክሯል፡፡
**
#ግዚያዊ ርክክብ/Provisional Acceptance/
#ግዜአዊ ርክክብ በተለይ በኮንስትራክሽን ውል የተመለከቱ የግንባታ ስራዎች ተከናውነው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ማለትም አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በስራው ላይ የሚደረግ የምርመራ ማረጋገጫ ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3274(1) ይደነግጋል፡፡ ይሄውም አሰሪው በትክክል የተገነባውን ግንባታ በእጁ አግብቶ መያዙን ጭምር ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ ጊዜአዊ ርክክብ በዋናነት የተሰራውን የግንባታ ስራ አሰሪው መብቱን ጠብቆ በመጀመሪያ የሚረከብበት ሂደት ነው ማለት ነው፡፡በስራው ላይ ምርመራ መደረጉንም የሚያረጋግጥ ነው፡፡
#ፒፒኤ 2011 ክሎስ 84.1 ላይ የስራ ምርመራ/verification and test/ በመሀንዲሱ ተቋራጭ ባለበት ሊደረግ እንደሚገባ በመርህ ደረጃ ተቀምጧል፡፡ሆኖም ግን ተቋራጩ ምርመራው ከሚካሄድበት እለት ከ30 ቀን በፊት በተገቢ ሁኔታ እንዲያውቀው ተደርጐ በምርመራው እለት ያልተገኘ እንደሆነ የስራ ምርመራው ተቋራጩ በሌለበት ሊካሄድ እንደሚችል ይፈቅዳል፡፡
#እንግዲህ መሀንዲሱ ስራውን ከመረመረ በኋላ ያላመነበትን የስራ ክፍል ፈርሶ እንደገና እንዲሰራ ወይም እንዲጠገን ተደርጐ የጥራት ደረጃውን ባሟላ ሁኔታ እንዲከናወን ለማዘዝ እንደሚችል ፒፒኤ ክሎስ 85 ይፈቅድለታል፡፡
#በዚህም መሰረት ግንባታው የስራ ምርመራውን ካለፈ አሰሪው ግንባታውን የሚረከበው ይሆናል ማለት ነው፡፡ስለዚሁም የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት ለተቋራጩ የሚሰጠው ይሆናል፡፡በመሰረቱ ተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንዲሰጠው መጠየቅ ያለበት ስራው ሊጠናቀቅ ይችላል ብሎ ከሚያስብበት ከ15 ቀን በፊት መሆን ይኖርበታል፡፡ከዚያም መሀንዲሱ ጥያቄው በደረሰው በ30 ቀን ውስጥ የስራ ምርመራውን አጠናቆ ሰርተፍኬቱን መስጠት ወይም ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡መሀንዲሱ ሰርተፍኬቱን ሳይሰጥ ወይም ጥያቄውን ውድቅ ሳያደርግ 30 ቀኑ ያለፈ እንደሆነ ለተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንደተሰጠው ግምት እንደሚወሰድ ፒፒኤ ክሎስ 87 ያስቀምጣል፡፡
#ሌላው ተቋራጩ በስራው ላይ ያደረገው መሻሻል/መለወጥ ቢኖር እንኳ በዝምታ ግዜአዊ ርክክብ ከተደረገ መሻሻሉ ተቀባይነት እንዳገኘ የህግ ግምት እንደሚያስወስድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(2) ይደነግጋል፡፡እዚህ ላይ ተቋራጩ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት የመስራት ግዴታ ያለበት መሆኑ ይታዎቅ፡፡ ስለዚህ የህግ ግምቱ እሳቤ ተቋራጩ ከዲዛይኑ በመውጣት አሻሽሎ የሰራው ስራ ኖሮ በግዜአዊ ርክክብ ወቅት በዝምታ አሰሪው ካለፈው እንደተቀበለው ይቆጠራል ነው፡፡
#እንዲሁም ግዜአዊ ርክክብ መደረጉ የመድህንነት ጊዜው(warranty period) መጀመሩን እንደሚያመለክት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(3) ይደነግጋል፡፡
**
#የመድህንነት ጊዜ(warranty period/Defects Liability period)
#የመድህንነት ጊዜ(warranty period) የሚባለው ከጊዜአዊ ርክክብ እስከ መጨረሻ ርክክብ ያለው ጊዜ ሲሆን አሰሪው ግንባታው በተቋራጩ በደህና ሁኔታ ስለመሰራቱ ለመመርመርና ለማረጋገጥ የሚያስችለው ጊዜ ነው፡፡የጊዜው ርዝማኔም በውላቸው ላይ የሚወሰን ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3277 ይደነግጋል፡፡ ሆኖም በውሉ ላይ የመድህንነት ጊዜው ርዝማኔ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ከጊዜአዊ ርክክብ ቀን ጀምሮ 365 ቀን ስለመሆኑ የፒፒኤ ክሎስ 88.7 ያስቀምጣል፡፡
#ተቋራጩ በዚሁ በመድህንነት ጊዜ በተለይ የተበላሹ ስራዎችን እንዲያድሳቸው በአሰሪው በታዘዘ ጊዜ የማስተካከል ግዴታ እንዳለበት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3278 ይደነግጋል፡፡ ለዚህም ለጥገና ወጭ ሲባል ከተቋራጩ ክፍያ ላይ ሪቴንሽን ገንዘብ(retention money or bond) 5% እየተቀነሰ በአሰሪው ይያዛል፡፡
#በመድህንነት ጊዜ ውስጥ የተለዩ ብልሽት ያለባቸው ስራዎችን እንዲያስተካክል ተቋራጩ ተጠይቆ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያላስተካከለ እንደሆነ አሰሪው የማስተካከያ ስራውን በተቋራጩ ወጭ በራሱ ወይም ሌላ ቀጥሮ ሊያሰራው ወይም ውሉን ሊያቋርጥ ስለመቻሉ ፒፒኤ ክሎስ 88.3 ለአሰሪው መብት ይሰጠዋል፡፡
**
#ከፊል ርክክብ/Partial Acceptance/
-በፒፒኤ ክሎስ 86 ላይ የግንባታ ስራው በከፊል እርክክብ የሚደረግበትንም አማራጭ ያስቀምጣል፡፡ይህ ማለት የተወሰነውን የስራ ክፍል(part of the work) ከአጠቃላይ ውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ በውል ላይ ከተቀመጠ ተቋራጩ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከአጠቃላይ የውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ ይገደዳል ማለት ነው፡፡በዚህም በአንድ ውል ውስጥ በተለያየ ጊዜ ጊዜአዊ ርክክብ ሊደረግ የሚችልበትን ሁኔታ ይፈጥራል ማለት ነው፡፡
**
#የመረሻ ርክክብ/Final Acceptance/
#የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/ በተለይ የመድህንነት ጊዜ ካለቀ በኋላ እና ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደህና ሁኔታ የፈጸመ መሆኑን አሰሪው ሲያረጋግጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በእጁ የሚያደርግበት(definitively appropriate) ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279 ይደነግጋል፡፡
#የመጨረሻ ርክክብ አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት በአስገዳጅ ሁኔታ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279(2) ላይ ተደንግጓል፡፡ሆኖም ጊዜአዊ ርክክብ/ Provisional Acceptance/ በሚመለከት ግን በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት የሚያስገድድ ግልጽ ህግ የለም፡፡ስለዚህ ስራው ተጠናቆ አሰሪው ግንባታውን በእጁ ካስገባ ጊዜአዊ ርክክብ መደረጉን የሚያስገነዝብ ይሆናል ማለት ነው፡፡በእርግጥ በጽሁፍ መደረጉ ይመከራል፡፡
#በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3282 ላይ እንደተቀመጠው ከመጨረሻ ርክክብ በኋላ ተቋራጩ እስከ 10 አመት ድረስ ስለስራው አሰራር ጉድለት ተቋራጩ ሀላፊነት አለበት፣መድህን ሆኖ ይቀጥላል፡፡በመጨረሻ ርክክብ ወቅት የሚታዩ ለነበሩ ጉድለቶች(apparent defect) ግን ተቋራጩ ሀላፊነት የለበትም፡፡ሀላፊነቱ የሚመለከተው ግንባታው በውሉ የተመለከተውን የታለመለትን ጥቅም እንዳይሰጥ የሚያደርጉ ወይም አጠቃቀሙን በጣም ውድ የሚያደርጉና አክሳሪ የሚያደርጉ ጉድለቶችን ነው፡፡
#henoktayelawoffice
👇👇👇👇👇👇የቀጠለ👇👇
#ጠበቆች የባለጉዳዮች ወኪል ብቻ ሳይሆኑ የፍትህ አስተዳደሩም ዋልታ በመሆናቸው ጭምር ፍርድ ቤቶች በእውነት ላይ እንዲያደርሱና ፍትሃዊና ሚዛናዊነትን የተላበሰ ውሳኔ እንዲሰጡ መርዳት አለባቸው፡፡
ከዚህ አንፃር የፌዴራል ፍ/ቤቶች ጠበቆች ስነ ምግባር ደንብ የሚከተሉትን ግዴታዎች በጠበቆች ላይ ጥሏል፡፡
I) #በምቀኝነት ወይም በክፉ ልቦና ተነሳስቶ ሌላውን ወገን የሚጎዳ ክስ ወይም ክርክር አለማቅረብ፣
#ደንበኛው የወራዳነት ወይም የማጭበርበር ድርጊት እንዲፈፅም አለማበረታታት ወይም አለመፍቀድ፣
#ዳኛን ወይም ሌላ የፍ/ቤት ሰራተኛን በህግ መሰረት ከማሳመን ውጪ ሌላ ተገቢ ያልሆነ ማንኛውም አይነት ዘዴ በመጠቀም ተፅህኖ ለማሳደር አለመሞከር ወይም ሌላ ሰው እንዲሞክር አለመገፋፋት ፣
#ሆነ ብሎ ፍ/ቤትን የሚያሳስት የተጋነነ ፅሁፈ ንግግር ለፍርድ ቤት አለማቅረብ፣
#በምስክርነት ቃል ወይም የሰነድ ይዘት ላይ የሀሰት ድርጊት በመፈፀም ፍርድ ቤትን ለማሳሳት አለመሞከር፣
#በግልፅ ለጉዳዮ አግባብነት የሌለውን ማስረጃ አግባብነት ያለው አስመስሎ ለፍርድ ቤት አለማቅረብ፣
#ለጉዳዮ በምስክርነት መቅረብ የሚገባው ሰው ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ አለማባበል ወይም አለመሞከር
አንድን ምስክር ተገቢ ባልሆነ መንገድ አለማመናጨቅ፣ አለማስጨነቅ፣ወይም አለማስፈራራት ናቸው፡፡
በጥቅሉ የባለጉዳይን ጥቅም ከማስጠበቅ የተሻገረ ኃላፊነት እንዳለበት አውቆ ፍርድ ቤቱ ከእውነተኛና ፍትሃዊ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ የሚጠበቅበት ሲሆን የጥብቅና ስራውንም በቅን ልቦና ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡

ሌላኛውና ዋንኛው የጠበቆች የስነ ምግባር ግዴታ ጠበቆች ከደንበኞቻቸው አንፃር ያለባቸው ግዴታ ነው፡፡
J) #በዚህ ረገድ የጠበቆች ዋንኛ ግዴታ የሚሆነው ባለጉዳዮች ዳኝነት ከጠየቁበት የክርክር ጭብጥ አንፃር ያላቸውን መብትና ግዴታ እንዲሁም መብታቸውን ለማስከበርና ግዴታቸውን ለመወጣት ህጉ የሚደነግጋቸውን አካሄዶችና ስነ ስርዓቶች እንዲያውቁ ማድረግ ነው፡፡ ከዚሀ ጋር ተያይዞ የባለጉዳዮችን መብትና ጥቅም ለማስከበር እነርሱን ወክሎ ክርክር በማቅረብ መብታቸውና ጥቅማቸው እንዲከበር ዕውቀቱንና የስራ ልምዱን ስራ ላይ ማዋል ነው፡፡ ከዚህም በላይ የደንበኛውን ጉዳይ ከመደበኛ ፍርድ ቤት ወይም አስተዳደራዊ የዳኝነት አካላት ዘንድ በመውሰድ የደንበኛውን ጉዳይ በትጋት መከታተል፣ አፋጣኝና ፍትሃዊ ውሳኔ እንዲያገኝም ሙያዊ ጥንቃቄ ብርቱ ጥረት ማድረግ ይገባዋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥም ጉዳዩ የደረሰበትን ደረጃ በየጊዜው ለደንበኛው የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡
ጠበቆች ሁሌም ቢሆን የደንበኞቻቸው ጥቅም ለማስጠበቅ ተገቢውን ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ለደንበኞቻቸው ጥቅም መከበርም በፍፁም ታማኝነት ማገልገል ይጠበቅባቸዋል፡፡

K) #በዚህ ረገድ በጠበቃውና በደንበኛው፣ ወይም በጠበቃው ዘመዶችና በደንበኛው፣ወይም ጠበቃው በወከላቸው የተለያዩ ደንበኞች መካከል የጥቅም ግጭት እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም በጥብቅና አገልግሎቱ ምክንያት ያወቃቸውን የደንበኛውን የግል ወይም የስራ ሚስጥሮችን መጠበቅ አለበት፡፡ ደንበኛው ሳይፈቅድለት በሙያው ምክንያት እጁ የገቡትን ማናቸውንም የደንበኛውን ሚስጥሮች ለሌላ አካል አሳልፎ ሊሰጥ አይችልም፡፡ ራሱም ቢሆን በህግ በተፈቀዱለት ጥቂት ሁኔታዎች ካልሆነ በቀር ሊጠቀምበት አይችልም፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ጠበቆች ለሌሎች ሶስተኛ ወገኖችም ቅን የመሆን ግዴታ አለባቸው፡፡ በተለይም ሌሎች ተከራካሪዎችን ለማጉላላት በማሰብ አከራካሪ የሆነ ጭብጥ ወይም በሌላኛው ተከራካሪ ላይ ኃላፊነትን ሊያስከትል የሚችል ውጤት የሌለ መሆኑ በግልፅ አኳኋን የሚታይበት ሁኔታ ቅንነትን በማጣት ተገቢ ያልሆነ ክርክር በተቃራኒ ወገኖች ላይ መጀመር የለበትም፡፡
L) #ከዚህ አንፃር በተለይም ከዚህ በታች ከተገለፁት ድርጊቶች መቆጠብ አለበት፡፡ እነዚህም፡-
ተቃራኒ ወገን ማስረጃ እንዳያገኝ ማንኛውንም እንቅፋት መፍጠር ወይም ሌሎች ሰዎች ይህን መሰል አድራጎት እንዲፈፅሙ መሞከር ወይም መረዳት፣
ማስረጃን ማሳሳት ወይም ሌሎች ሰዎች ይህን መሰል አድራጎት እንዲፈፅሙ መሞከር መርዳት፣
ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌለው ወይም በማስረጀ ሊደገፍ የማይችል ነገር ማቅረብ
በምስክርነት ካልቀረበ በቀር በግል የሚያውቀውን የጭብጥ ነገሮች መሰንዘር ወይም የጉዳዩን ፍትሃዊነት የአንድን ምስክር ተዓሚነት፣ የተከሳሽን ጥፋተኛ ወይም ተጠያቂ መሆንና አለመሆን አስመልክቶ የግል አስተያየቱን መስጠት
ደንበኛው ወይም ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ የማይገደዱ ሰዎችን በተመለከተ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ማንኛውንም ሰው ለተቃራኒ ወገን የምስክርነት ቃሉን ወይም ሌላ አግባብነት ያለው ማስረጃ እንዳይሰጥ መገፋፋት ናቸው፡፡
በመጨረሻም ጠበቆችም ፍትሃዊ ዳኝነት እንዲጎለብት እንዲሁም የደንበኞቻቸው መብትና ጥቅም እንዲጠበቅ የማድረግ ድርብ ኃላፊነት ሲኖርባቸው እነዚህን ኃላፊነቶች በተጣጣመ መልኩ ነው ማከናወን ያለባቸው፡፡ ከዚህ አኳያ ለሰብአዊ መብቶችና መሰረታዊ ነፃነቶች መከበር በትጋት መቆምና መስራት ይኖርባቸዋል፡፡
M) #በዚህ ረገድ የደንበኛቸውን ጥቅም ማስጠበቅና ለፍትህ መከበርም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ መካከል የሚታየውን ክፍተት ለማጣጣመና ሚዛናዊ ለማድረግ መጣር አለባቸው፡፡ ጠበቆች ሙያቸው የግለሰቦች መሠረታዊ መብቶችና ነፃነቶች እንደከበሩና እንዲጐለብቱ የማድረግ ልዩ ኃላፊነት ወይም ግዴታ እንደጣለባቸው በመገንዘብ ይህንን ከፍተኛ የሙያ ግዴታ ለመወጣት ከፍተኛ ስነምግባር መላበስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለፍትህ ሥርዓቱ መጐልበትና ለሰብዓዊ መብቶች መከበርም ዘወትር የበኩላቸውን ድርሻ ለማበርከት መሥራት እንደሚገባቸውና በዚህ ሂደት ውስጥም ለሙያቸው ስነምግባር መገዛት እንደሚጠበቅባቸው ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል፡፡
https://t.me/lawsocieties