አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በኢትዮጵያ ውስጥ የሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 17 በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጪ ማንኛውም ሰው ነፃነቱን እንደማያጣ ይደነግጋል።
በተጨማሪም ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጪ ሊያዝ፣ ክስ ሳይቀርብበት ወይንም ሳይፈረድበት ሊታሰር እንደማይችል በግልፅ ይደነግጋል።
ኢትዮጵያ ተቀብላ ያፀደቀችው የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን (ICCPR) አንቀፅ 9 ማንኛውም ሰው ነፃነቱ እና ደህንነቱ ተከብሮ የመኖር መብት እንዳለው እና በዘፈቀደ ከሚደረግ እስር ሊጠበቅ እንደሚገባ ይደነግጋል።
ሕግ አስከባሪዎች ማንኛውም ሰውን በቁጥጥር ስር ከማዋላቸው በፊት የዜጎች ነፃነትን ለመጠበቅ የወጡ ሕጎች የጣሉባቸውን ግዴታዎች በሙሉ መሟላታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።

ምስል-በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተቀናበረ
#AHRE( Association for Human Rights in Ethiopia)

Alternative legal enlightenment (ALE)አለ
አማራጭ የሕግ እውቀት፣🔴ሕግ

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
በሕግ አስከባሪ አካላት በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎች በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አላቸው። ተጠርጣሪዎች የቀረቡበት ፍርድ ቤት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆዩ በሚፈቅድበት ጊዜ ኃላፊ የሆኑት የሕግ አስከባሪዎች ምርመራውን አጣርተው የተያዘው ሰው በተቻለ ፍጥነት ፍርድ ቤት እንዲቀርብ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 19 ስር ተደንግጓል።
በተጨማሪም የሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 20 የተከሰሱ ሰዎች ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ በመደበኛ ፍርድ ቤት ለሕዝብ ግልፅ በሆነ ችሎት የመስማት መብት እንዳላቸው ይደነግጋል።

የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን አንቀፅ 14-3(C) ማንኛውም ክስ የቀረበበት ሰው ያለምንም መዘግየት ፍርድ የማግኘት መብቱ ሊጠበቅ እንደሚገባ አስፍሯል።

የሕግ አስከባሪ አካላት እና ፍርድ ቤቶች በቅጥጥር ስር ያሉ እና ክስ የተመሰረተባቸው ዜጎች የተፋጠነ ፍርድ እንዲያገኙ በሕገ መንግሥቱ እና ኢትዮጵያ ተቀብላ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን ሰነዶች የተጣለባቸውን ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅባቸዋል።
Via #AHRE( Association for Human Rights in Ethiopia)
ምስል፡ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተቀናበረ
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
0920666595