አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Ethio Life And General Insurance SC

Vacancy title:
Legal Aide

[ Type: FULL TIME , Industry: Insurance , Category: Legal ]

Jobs at:

Ethio Life and General Insurance S.C

Deadline of this Job:
04 February 2022  

Duty Station:
Within Ethiopia , Addis Ababa , Horn of Africa

Summary
Date Posted: Tuesday, February 01, 2022 , Base Salary: Not Disclosed

JOB DETAILS:
Job Requirement
• Qualification: Diploma in law from a recognized University/College
• Experience: A minimum of two (2) years relevant work experience in business organization


• Work experience on insurance company is preferable
• qualities & abilities Required:
• Ability to plan , standardize, execute & administer resources
• Good Interpersonal & Communication skill
• Highly oriented in customer service
• Ability to identify & resolve problems
• High dedication & hard working capacity
• Good knowledge of insurance business
• Good knowledge of commercial codes /only for Job no. 2/
• Dependable
• Team Player
• Salary and Benefits: As per the company salary scale and benefits

Work Hours: 8

Experience in Months: 24

Level of Education: Postgraduate Degree

Job application procedure
Interested and qualified employees (applicants) can submit their application and updated copies of testimonials in person within 5(five) working days from the date of this announcement to the following address:
Ethio Life and General Insurance S.C. HR & Facility Management Department Around Meskel Flower in front of Tulip in Hotel, Homes of Millions Building 5th floor. Tel: 011557 1579/ 011557 1848 Addis Ababa
#AddisAbaba

የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ እስኪጠናቀቀ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከልክሏል።

የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ- ኃይል 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በአዲስ አበባ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል።

ከነገ አርብ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት የፀጥታ አካላት ከሚጠቀሙባቸው ውጪ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም አከባቢዎች በማንኛውም ሰዓት መንቀሳቀስ ፍፁም ተከልክሏል።

የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች ሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንን መልእክት ተግባራዊ እንዲያደርጉ መልዕክት የተላለፈ ሲሆን ይህንን መልዕክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።

#tikvahethiopia
Junior Free Legal Aid officer (Head Office)

 Job Summary

Free Legal Aid Officer is reporting to the Free Legal Aid Section Head and responsible for the provision of free legal aid services to the need members of the society with the guidance of his supervisor.

Specific duties and responsibilities: 

Provide a free legal service in accordance with the policy and procedure outlined by EHRCO for a free legal aid services and also with the guidance of the Free Legal Aid Service of EHRCO at head office.

Receive and listen clients about the nature of their cases

meet with clients to gather information and take instructions

advise clients on the law and legal matters relating to their case

draft letters, or documents based on the client's needs

research similar cases within the archive (records) of EHRCO or from other sources to guide his/her current work

act on behalf of his/her clients as deemed necessary, and prepare cases for court as necessary

attend mediation or arbitration on behalf of  the client

calculate claims for damages, compensation, and if any

Report and document on the details of free legal aid services provided including the outcome of the services

Compile lesson learned from free legal aid services

Ensure the privacy the free legal service recipient and should not disclose any facts to other parties unless the provision of the information is a legal requirement or to the benefit of the service recipient and with his consent. 

DEPARTMENT:MDR              

REPORTS TO:  Free Legal Aid Section Head

Job Requirements:

Requirement

Qualifications

Degree in Human Rights, LL.M in International Law, LL.M in Law (Public Law relevant to Human Rights) or LL. B

Experience

2 years of relevant experience for BA and 0 years of relevant experience for MA.

Skills

Computer literate. 

Knowledge of multiple local languages is advantageous.

a passion for justice and fairness and for the respect of Human Rights

strong spoken and written communication skills

the ability to absorb and analyze large amounts of information

a high level of accuracy and attention to detail

the ability to explain legal matters clearly in non-legal language

confidence and a persuasive manner

the ability to work under pressure
time management and strong organizational skills.
Skill in computer and internet usage
Excellent documentation skills

How To Apply:
Interested candidates must send the following application documents by e-mail: “ehrcovacancy2022@gmail.com”, until the 9th of February 2022, 5:00 PM EAT with the subject line ‘EHRCO – Junior Free Legal Aid officer’:

Motivation/Cover letter (Not more than one page);

CV (not more than 4 pages) and relevant documents (education certificates, experience and others) (Please note the certificates and CV should be in one single file)

Please note that only selected candidates will contacted.

Please note that applicant/s that don’t follow the procedures will be disqualified immediately. 

Posted: 02.03.2022
Deadline: 02.09.2022
Ethiopian Human Rights Council (EHRCO)
ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ አሰባሰብ ስርዓቱን አዘመነ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ አሰባሰብ ስርዓቱን አዘምኗል፡፡

ፍርድ ቤቱ ማንኛውንም የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ በሚከፈለው ብር መጠን ሳይገድብ፣ ባለጉዳዮች ወደ ባንክ መሄድ እና ጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው ክፍያ መፈፀም የሚችሉበት የአሰራር ማሻሻያ አድርጓል፡፡ በዚህ የክፍያ አፈጻጸም ማሻሻያ ስርዓት፡-

1ኛ. ባለጉዳዮች የባንክ የገንዘብ መክፈያ ካርድ (ATM) ከያዙ እና በባንክ ሂሳብ ቁጥራቸው ላይ በቂ ገንዘብ ካለ በፍርድ ቤቱ ገንዘብ መሰብሰቢያ ክፍል በሚገኝ ``POS`` ማሽን በመጠቀም የአገልግሎት ክፍያቸውን መፈጸም ይችላሉ፡፡

2ኛ. ባለጉዳዮች በሞባይል ስልክ መተግበሪያ (Mobile Banking) ወይም በማንኛውም ሌላ ዘዴ ተጠቅመው ወደ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000280500376 የሚፈለግባቸውን የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ገቢ ማድረግ እንደሚችሉ እና ስለመክፈላቸው በፍርድ ቤቱ የሂሳብ ክፍል (ገንዘብ ቤት) ማረጋገጥ የሚችሉበት እንደሆነም አሳውቋል፡፡

ጠቅላይ ፍድር ቤቱ ባለጉዳዮች ከላይ ተገለጹትን ዘመናዊ የአከፋፈል ስልቶች ተጠቅመው የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያበረታታ እና ቅድሚያ የሚሰጠው እንደሆነ ገልጾ፤ አሰራሩ ያልተመቻቸው ባለጉዳዮች በቀድሞው አሰራር ከ1,000.00 ብር በታች ከሆነ ብቻ በፍርድ ቤቱ ገንዘብ ቤት በመቅረብ በጥሬ ገንዘብ የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም የሚችሉ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አሰራሮችን በመከተል የእርስዎንም ሆነ የፍርድ ቤቱን ጊዜ ይቆጥቡ!!

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Federal High Court

1. Ledeta District Bench:

Location: Around Ledeta Church next to the Addis Ababa University Architectural College

Phone Number: +251-112-76-75-28

2. Bole District Bench

Location: Around Semit next Safari School

Phone Number: +251-118-69-72-05

3. Ledeta Civil District Bench

Location: Around Ledeta, in front of Dar Mar building next to Primary Kokeb School, behind Dashen Bank

4. Kalti District Bench

Location: : Around Akaki Kalti, in front of the Menahriya

Phone Number: +251-114-71-76-07

5. Dire Dewa District Bench

Location: Dire Dewa City Administration

Phone Number: +251-251-11-00-73
Federal First Instance Courts

1. Lideta District Bench

Location፡- Near Lideta Church, next to Ethiopian Institute of Architecture, Building Construction and City Development “ሕንጻ ኮሌጅ “, inside the compound of Federal High Court Building at Lideta

Phone፡- +251-118-69-40-55

2. Addis Ketema District Bench

Location፡- In front of Ammanuel Church at Addis Ketema Sub-city

Phone፡-

3. Yeka

Location፡- Around Shola Gebeya at Yeka Sub-city

Phone፡- +251-116-68-65-93

4. Arada District Bench

Location፡- In front of Sora Amba Hotel near the intersection of Giorgis and Addisu Gebeya

Phone፡- +251-111-26-42-55 (Civil Court)

5. Kolfe Keraniyo District Bench

Location፡- Next to Shoa Supermarket near the intersection of Tor Hayloch and Total at Kolfe Keraniyo Sub-city

Phone፡- +251-112-80-10-27

6. Bole District Bench

Location፡- Next to Safari Academy at Bole Sub-city

Phone፡- +251-667-99-56

7. Kirkos District Bench

Location፡- Next to Ethiopian Commercial Bank near Kera Taxi stop at Kirkos Sub-city

Phone፡- +251-118-69-37-04

8. Menagesha District Bench

Location፡- At Arbegnoch Building near 4 Kilo

Phone፡- +251-114-34-09-09

9. Akaki District Bench

Location፡- In front of 09 Stadium on the building of United Insurance at Akaki Sub-city

Phone፡- +251-114-39-09-09

10.Nefas Silk Lafto District Bench

Location፡- Near German Square on the road to Jemo at Nefas Silk Lafto Sub-city

Phone፡- +251-114-16-72-34

11. Dire Dawa District Bench

Location፡- At Dire Dawa City Administration

Phone፡- +251-251-13-10-97
Federal Supreme Court

Location:
6 Kilo, Next to Yekitit 12 Hospital in front of Anbessa Gebi

Phone Number:
+251-11-1-55-34-00 / 011-1-11-04-32

E-mail:
fscpublicrelation@gmail.com
በጽሑፍ የሰፈረን የውል ቃል የምስክርና ሌላ ዓይነት ማስረጃን በማቅረብ ማሻሻል ይቻላል?

Mulugeta Mengist Ayalew (PhD)

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ በመዝገብ ቁጥር 78398 በአቶ ሽፈራዉ ደጀኔ እና ወ/ሮ ጸሀይ ተስፋዬ በአንድ በኩልና በአቶ ሲሳይ አበቡ በሌላ በኩል በተደረገ ሙግት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ጥቅምት 19 2005 የሰጠዉ ዉሳኔ ነዉ፡፡

በመደምደሚያው

1. የፓሮል ሕግ የሚሉትና በተለይ የአንግሎ-አሜሪካን የሕግ ስልትን የሚከተሉ ሀገሮች እዉቅና የሚሰጡት በኢትዮጲያ ሕግ የለም፡፡በኢትዮጲያ የዉል ሕግ መሰረት፤ ሕጉ ወይም ተዋዋይ ወገኖች የተለየ ፎርም ካላስቀመጡ በስተቀር፤ ዉልን በማንኛዉም ፎርም በተደረገ ስምምነት ማሻሻልና መጨመር ይቻላል፡፡ ሕጉ ወይም ተዋዋይ ወገኖች የተለየ ፎርም ካስቀመጡ ግን፤ ዉሉ ሊሻሻል ወይም ሊጨመርበት የሚችለዉ በተመሳሳይ ፎርም በተደረገ ስምምነት ነዉ፡፡

2. የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2005ና 2006 የተቀመጡት ድንጋጌዎች የማስረጃ ድንጋጌዎች በመሆናቸዉ ስራ ላይ የሚዉሉት በsubstantive ሕጉ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች በማይሸረሽር መልኩ መሆን አለበት፡፡

3. ሰበር ሰሚ ችሎቱ የቤቱ ባለቤቶች ቤቱን በአርባ ሺ እንዲሸጡ ይገደዳሉ ያለዉ ምንም የሕግ መሰረት የሌለዉ ነዉ፡፡

4. ሰበር ሰሚ ችሎቱ ዉሉ ዋጋ የለዉም ብቻ ሳይሆን በእርግጥ በጽሁፉ እንደተገለጸዉ ሃያ ሺ ብር ተከፍሏል የሚለዉን በተጨማሪ ማስረጃ በመፈተሸ የተከፈለ ብር ካለ እንዲመለስ ማዘዝ ይኖርበታል፤ ወይም ይህን ጠቁሞ ጉዳዮን ለታችኛዉ ፍርድ ቤት መምራት ይገባዉ ነበር፡፡

5. ሰበር ሰሚ ችሎቱ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የ2005ና 2006ን በተመለከተ የማብራሪያ/አሳማኝ ትርጉም (obiter dictum) ሊሰጥ እየቻለ እድሉና አሳልፏል፡፡

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/1560-is-it-possible-to-justify-and-amend-a-written-contract-with-witnesses
ኃላፊነቱ የተወሰነ ሽርክና ማኅበር በአዲሱ የንግድ ሕግ

አዲሱ የሀገራችን የንግድ ህግ የተለያዩ ጉዳዮችን በአዲስ መልክ አካቶ ወጥቷል፡፡ በህጉ ለውጥ ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል ከንግድ ማህበራት አንፃር ያለው ለውጥ አንዱ ሲሆን ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር /Limited liability partnership/ በአዲስ መልክ እውቅና ተሰጥቶት በህጉ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህ ጽሁፍ ኃላፊነቱ የተወሰነ ሽርክና ማኅበር ምንነት እና አመሠራረት፣ የሽርክና ማህበራትና ኃላፊነቱ የተወሰነ ሽርክና ማህበር ባህርያት፤ ስለኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር ሥራ አመራር፣ ውሳኔ አሰጣጥ እና ኃላፊነት፤ የማህበሩ ሸሪክ ስለሚወጣበት መንገድ፤ ስለማህበሩ መፍረስ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ተደሰዋል፡፡

1. ኃላፊነቱ የተወሰነ ሽርክና ማህበር ምንነት እና አመሠራረት
በአዲሱ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 221 መሰረት ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር ማለት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች የሙያና ለሙያው ደጋፊ የሆነ አገልግሎት (professional and complementary service) ለመስጠት የሚያቋቁሙት የማህበርተኞቹ ኃላፊነት በመዋጮዋቸው የተወሰነ የንግድ ማኅበር ነው። ይህ ማለት ሰዎች በተለይም የሙያ ስራዎችን ለመስራት በሙያ ከሚመስሏቸው ሌሎች ሰዎችና ለሙያው ደጋፊ የሆነ አገልግሎት ሊሰጡ ከሚችሉ አጋሮቻቸው ጋር ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሆነው የሚያቋቁሙት የሽርክና ማኅበር ነው፡፡

ማህበሩ ስም ለማውጣት የተቀመጡት ማለትም ከሌላ ነጋዴ ወይም ጥቅም ጋር የማይጋጭ፣ የሦስተኛ ወገኖችን መብት የማይነካ እና የተቋሙን ዓላማ የሚገልጽ ማኅበርተኞች የፈቀዱት የመጠሪያ ስም ይኖረዋል፡፡ ከማህበሩ ስም በስተመጨረሻ ላይ "ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር" የሚል ሐረግ መጨመር አለበት፡፡ ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር ጠበቆች፣ ኦዲተሮች፣ የሒሳብ ባለሙያዎች፣ አርክቴክቶች፣ የሥራ አመራር አማካሪዎች እና የመሳሰሉት ባለሙያዎች (የተፈጥሮ ሰዎች አለያም ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበራት) ሙያቸውን መሠረት በማድረግ የሚያቋቁሙት፣ ለባለሙያዎች ሥራ ቅልጥፍናና ውጤታማነት አስተዋጽኦ የሚያደርግ ነው፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ሙያ የሚጠይቀውን ሥነ ምግባር ይዘው ደንበኞቻቸውን የሚያስተናግዱ የሽርክና የሙያ ማኅበራት እንዲስፋፉ ያስችላል። ይህ አይነቱ የሽርክና ማኅበር የህግ አገልግሎትን፣ የሂሳብ መዝጋትና ኦዲት ወይም ሌላ አይነት ቴክኒካዊ እውቀትን በሚጠይቁና የሙያ ፈቃድ ቁጥጥር በሚደረግባቸው የስራ ዘርፎች ላይ በቅንጅት መስራት ለሚሹ ሙያተኞች አይነተኛ ምርጫ እንደሚሆን ይገመታል።

2. የሽርክና ማኅበራት አጠቃላይ ባህሪያት
የሽርክና ማኅበራት የሚጋሩት የጋራ ባህሪ ያላቸዉ ሲሆን ፡-
• የሽሪኮች አነስተኛ ቁጥር ሁለት ብቻ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ግን ያለተገደ በመሆኑ፣
• የአንስተኛ ካፒታል መጠን በህግ ያልተደነገገ መሆኑ፣
• ማህበሩ የሚመሰረተው በአባላት መዋጮ መሆኑ፣
• አስተዳደራዊ ሥራዎችን በሚመለከት አባላቱ የሚወስኑ መሆኑ፣
• የሙያ ወይም የአገልግሎት መዋጮ የተፈቀደ መሆኑ፣
• የሥራ አስኪያጅ ብዛት አንድና ከአንድ በላይ ሊሆኑ እንደሚችሉ የተፈቀደ መሆኑ፣
• ከሁለት አይነት ኃላፊነት ያለበት የሽርክና ማህበር በስተቀር ሥራ አስኪያጆች ከአባላቱ መካከል ወይም ከውጭ ሊሆኑ የሚችሉ መሆኑ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
3. ኃላፊነቱ የተወሰነ ሽርክና ማኅበር ልዩ ባህርያት
ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር እንደ ሌሎቹ የሽርክና ማህበራት ሁሉ የራሱ የሆነ ባህሪያት አሉት፡፡ በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀፅ 222 መሰረት ይህ ማህበር ከአባላቱ የተለየ ህግ ሰውነት ያለው፣ እንደ መክሰስ መከሰስ እና በራሱ ስም ውል መዋዋል የመሳሰሉ ህጋዊ ድርጊቶች በራሱ ስም መፈፀም የሚችል ሲሆን የሽሪኮቹ መሞት፣ መክሰር፣ ከማህበሩ መውጣት ወይም በሽርኮቹ ላይ የሚደረግ ማንኛውም ለውጥ በማህበሩ ሕልውና፣ መብት ወይም ግዴታ ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም፡፡

ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር እንደሌሎቹ ማህበራት (ከባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ውጪ) የሚቋቋመው በመመስረቻ ፅሁፍ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በቀድሞ ሕግ የነበረው መተዳደሪያ ደንብ በአዲሱ ሕግ ቀሪ ተደርጓል፡፡ የዚህን ዓይነት ማኅበራት መመስረት የሚችሉት የሙያ ፈቃድ ባላቸው የተፈጥሮ ሰዎች ወይም ኃላፊነቱ በተወሰነ የሽርክና ማኅበራት ነው፡፡

4. ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር ተመራጭ የሚያደርጉ ጉዳዮች
በቀላሉ ለመመስረት የሚቻል መሆኑ፡- ከሌሎች ማህበራት ጋር ሲነፃፀር የሽርክና ማህበርን ለመመስረት የሚወስደው ጊዜና ገንዘብ አነስተኛ በመሆኑ በቀላሉ ህጋዊነትን በማግኘት ወደ ሥራ ለመግባት ያስችላል፡፡

በአነስተኛ ካፒታል መመስረት የሚቻል መሆኑ፡- ከግለሰብ ነጋዴ ቀጥሎ በአነስተኛ ካፒታል ሊመሰረት የሚችለው የንግድ ማህበር የሽርክና ማህበር ነው፡፡
የተሻለ ካፒታል ለማሰባሰብ የሚያስችል መሆኑ፡- የሽርክና ማህበራት ከግለሰብ ነጋዴ የሚለዩት ሁለትና ከሁለት በላይ ሆነው የሚመሰርቱት በመሆኑ እያንዳንዳቸው ሽሪኮች ከግለሰብ ነጋዴ የተሻለ በዓይነትና በገንዘብ በማዋጣት ካፒታላቸውን የተሻለ ማድረግ መቻላቸው ነው፡፡ የተሻለ ካፒታል ማዋጣት ከቻሉ ደግሞ የተሻለ የንግድ ሥራ ላይ የተሻለ አቅም ኢንቨስት ማድረግ ይችላሉ ማለት ነው፡፡

የሽርክና ማህበራት አባላት ድርጅታቸውን በራሳቸው ማስተዳደርና መምራት መቻላቸውም ይህን አይነት ማህበር ተመራጭ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው፡፡
5. ስለማህበሩ ሥራ አመራር፣ ውሳኔ አሰጣጥ እና ኃላፊነት
ማህበሩ ምንም እንኳን ከተፈጥሮ ሰው በተጨማሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበርን በአባልነት መያዝ የሚችል ቢሆንም ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ መሾም የሚችለው የተፈጥሮ ሰው የሆነ እና ማህበሩ አገልግሎት በሚሰጥበት ሞያ ፈቃድ ያለው ሸሪክ ብቻ ነው፡፡ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ የማህበሩን ዓላማ ለማሳካት በማህበሩ ስም ማንኛውንም ሕጋዊ ተግባር ለማከናወን የሚችል ሲሆን ይህን ሥልጣን የሚገድቡ ስምምነቶች ሶስተኛ ወገኖችን መቃወሚያ የሚሆኑት በንግድ መዝገብ የተመዘገቡ ወይም ሦስተኛ ወገኖች የሥራ ኃላፊነቱን የሚያውቁ መሆናቸው የተረጋገጠ እንደሆነ ነው፡፡

የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር የሚደነግገው የማህበሩ መመስረቻ ፅሁፍ ሲሆን ይህም መመስረቻ ፅሁፍ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በአባላት ሁለት ሶስተኛ (2/3) ድምፅ በሚሰጥ ውሳኔ ሊሻሻል ይችላል፡፡ ሌላ ማንኛውም ውሳኔ በአብዛኛዎቹ አባላት የድምፅ ድጋፍ ማለትም (50+1) ሊፀድቅ ይችላል፡፡ የማህበሩ ዜግነት ወይም የሥራ መስክ ለመለወጥ የሚሰጥ ውሳኔ የሚፀናው በ3/4ኛ (ሶስት አራተኛ) ድጋፍ ድምፅ ነው፡፡

የማህበሩ እና የአባላት ኃላፊነት ሌላኛው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነጥብ ነው፡፡ በመሠረቱ ህጋዊ ሰውነት እና የማህበሩ ኃላፊነት ውስንነት የማይነጣጠኑ ሀሳቦች ናቸው (corporate existence and limited liability are inseparable):: ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር የሚለው ስም ሲታይ ኃላፊነቱ የተወሰነው የማህበሩ ቢመስልም ዝርዝሩ ሲታይ ኃላፊነቱ የተወሰነው የሽሪኮች መሆኑን ማየት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም የሽሪኮች ኃላፊነት በመዋጮዋቸው የተወሰነ ነው፡፡ በእርግጥ የማህበሩ ኃላፊነትም ቢሆን በግልፅ አልተጠቀሰም እንጂ የኃላፊነቱ መጠን በማህበሩ ሀብት /capital/ ልክ ነው፡፡ ሥራ አስኪያጅ ወይም ሸሪክ
ከመዋጮ ባለፈ ኃላፊ ሊሆን የሚችልበት አግባብ አለ፡፡ ሥራ አስኪያጁ ከሥልጣኑ በላይ ለሚሠራው ሥራ ሁሉ ኃላፊነቱ የማህበሩ ሳይሆን የሥራ አስኪያጁ ብቻ ነው፡፡ በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 228 እንደሚደነግገው ሸሪኩ ወይም ሠራተኛው የማህበሩን ሥራ በሚያከናውንበት ወቅት ሆን ብሎ ወይም የማታለል ተግባር በመፈፀም ወይም በቸልተኝነት ለሚፈፅመው ጥፋት ወይም ለሚያደርሰው ጉዳት ጥፋቱን ካደረሰው ሸሪክ ወይም ሠራተኛ ጋር ማኅበሩ በአንድነትና በተናጠል ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ማህበሩ ጉዳት የደረሰበት አካል ጉዳት አድራሹ ሥልጣን ያልተሠጠው መሆኑን ያስረዳ እንደሆነ ከኃላፊነት ነፃ ይሆናል፡፡ ማህበሩ ይህን መሰል ዕዳዎች ለመሸፈን የመድን ሽፋን እንዲኖረው በህግ ይገደዳል፡፡

6. የማህበሩ ሸሪክ ከማህበሩ የሚወጣበት መንገድ
አንድ ሸሪክ ከማህበሩ ሊወጣ የሚችለው የሶስት ወር ቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት (ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ)፣ ሲሞት ወይም ህጋዊ ሰውነት ሲያጣ፣ ድርሻው በገንዘብ ጠያቂዎች በሙሉ ሲወሰድ፣ በፍርድ ሲሸጥበት ወይም በሸሪኩ ላይ የኪሳራ ውሳኔ ሲወሰንበት፣ የሞያ ፈቃዱ ሲሰረዝ ወይም ለረጅም ጊዜ ሲታገድ፣ በሕመም ወይም አካል ጉድለት ወይም ሌሎች ምክንያቶች ግዴታውን ለመወጣት የማያስችለው ሲሆን ወይም ፍርድ ቤት በበቂ ምክንያት ከማህበሩ እንዲወጣ ሲወስን መሆኑ በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 229 ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ አንድ ሸሪክ ከማህበሩ ከመውጣቱ በፊት ለሶስተኛ ወገኖች የነበረበት ዕዳ ኃላፊነት ከማህበሩ በመውጣቱ ቀሪ አይሆንም፡፡ አንድ ሽሪክ ድርሻውን በሌሎች ማህበርተኞች ተቀባይነት ላገኘ ሌላ ማህበርተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሳያስተላልፍ የወጣ እንደሆነ ህጋዊ መብት ያለው ወራሽ ወይም ባለመብት ድርሻው ተሰልቶ እንዲሰጠው ከመጠየቅ ውጪ አባል ለመሆን የሚያቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፡፡

7. ስለማህበሩ መፍረስ እና የማፍረሻ ምክንያቶች
አንድ የንግድ ማኅበር በመመስረቱ ህልውና ያለው ሆኖ ከቆየ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች ሊፈርስ ይችላል፡፡ ማኅበሩ ፈረሰ የሚባለዉም መኖር ሲያቆም (ህልውናውን ሲያጣ) ነዉ፡፡ ማኅበሩ የሚፈርሰው ግን በአንድ ጀንበር አይደለም፡፡ አፈራረሱ ራሱን የቻለ ሂደት እና ሥነ-ሥርዓት አለው፡፡ የማፍረስ ሂደት ማጣራት ይባላል፡፡ የንግድ ማኅበር የሚፈርሰው የማጣራቱ ሂደት ሲያበቃ ነው፡፡ የንግድ ማኅበር የሚቋቋመው በህግ እንደመሆኑ ሁሉ የሚፈርሰዉም በህግ በተቀመጠ ሥነ-ሥርዓት (ሂደት) ነው፡፡

በንግድ ሕግ አንቀጽ 181 ንግድ ማህበራት ከሚፈርሱበት ሁኔታ በተጨማሪ የሸሪኮች ቁጥር ወደ አንድ ዝቅ ያለ እንደሆነ እና በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ሌላ ሸሪክ መተካት ሳይቻል ሲቀር ማኅበሩ እንዲፈርስና ሒሳቡ እንዲጣራ መደረግ አለበት፡፡ የስድስት ወራት የጊዜ ገደብ ከማለፉ በፊት በማኅበሩ የቀረዉ ሸሪክ ጥያቄ ሲቀርብና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የንግድ መዝጋቢው አካል የስድስት ወራቱ የጊዜ ገደብ በሦስት ወራት እንዲራዘም ሊፈቅድ ይችላል፡፡ በዚህ መሰረት ካልሆነ በስተቀር የሼሪኮች ቁጥር ከሁለት በታች መቀነሱን የሚያውቅ ሸሪክ ማኅበሩ በዚህ ሁኔታ ከስድስት ወራት በላይ ሥራውን እንዲቀጥል ካደረገ የማኅበሩ ዕዳና ግዴታዎች ከማኅበሩ ጋር በአንድነትና በተናጠል ተጠያቂ ይሆናል፡፡
የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኞች ከባድ የሥነምግባር ደንብ ጥሰት
************
በሀገር ቀፍ ደረጃ የጣዉን ለዉጥ ከትሎ የፌደራ ጠቅላይ ፍር ቤትም የህግ የበላይነትን ማስፈንና የህዝብ አመኔታ የተቸረዉ ተቋም መገንባትን እንደ ግብ ይዞ በርካታ ዉስጣዊና ዉጫዊ የሆኑ ለዉጥና ማሻሻያዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በርካታ ድንጋጌዎችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን አፅድቆና አፀድቆ ስራ ላይ ማዋሉ ይታወቃል፡፡ ከዚህም አኳያ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም ”የፌደራል ዳኞች የሥነ-ምግባርና የዲስፕሊን ክስ ሥነ-ሥርዓት ደንብ” በሚልና በደንብ ቁጥር 1/2013፣ አንቀጽ 16 ስር የተደነገገዉንና ከዳኝነት ስራ ጋር ተያይዞ ከባድ የሥነ ምግባር ደንብ ጥሰት ባህሪያት እንደሚከተለዉ ዘርዝሯል::

ከባድ የሥነ ምግባር ደንብ ጥሰት ማለት ከዳኝነት ሥራ አገልግሎት ጋር የማይጣጣምና በኢትዮጵያ ፌደራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የፍትሕ አስተዳደር ላይ ወይም በፍርድ ቤቶች የውስጥ አሰራር ላይ ከባድ ጉዳት የሚያስከትል ወይም ያስከትላል ተብሎ የሚገመት ድርጊት ሲሆን ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ጨምሮ በደንቡ አባሪ «ሀ» (ገፅ 69 ይመልከቱ) የተጠቀሰው ነው፡፡

(1) በፍርድ ቤቱ በሚታዩ ጉዳዮች በዳኝነት ሥራ ምክንያት የታወቁ ፍሬ ነገሮችን ወይም መረጃዎችን ምስጢራዊነት መግለጽና በዚህም ምክንያት በፍርድ ቤቱ በሚታዩት ጉዳዮች ላይ ወይም በማንኛውም ሰው ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሲሆን፣

(2) አንድ ዳኛ በዳኝነት ለመሾም የሚከለክለውን መረጃ ወይም ከባድ የሆነ የአካባቢ ሁኔታ መደበቅ ወይም ሳይገልጹ መቅረት፣

(3) ከማናቸውም ባለሥልጣኖች፣ ተሿሚዎች ወይም ባለሙያዎች የተሻለ መስተንግዶ ለማግኘት በማሰብ የዳኝነት ሥልጣንን አላግባብ መጠቀም፤ የዳኛውን ታማኝነትና ሐቀኛነት በእጅጉ የሚጎዳ ወንጀል ፈጽሞ መገኘት፣ መደለያ መቀበል እና በአማላጅ መስራት ወይም የመተናኮል፣ በሥልጣን አላግባብ መገልገል፣ ታማኝነትን ማጓደል፣ በማጭበርበር፣ በማታለል ወይም የተሳሳተ መረጃ የመስጠት ድርጊት መፈጸም፤ ወይም፣

(4) ብዙ ዳኞች በሚያስችሉበት ችሎት፣ ለአንድ ውሳኔ ትክክለኛነት ሁሉም ዳኞች ኃላፊነት የሚወስዱ ቢሆንም በተለይ መዝገብ መርምሮ ለቀሩት ዳኞች ውይይት ውጤቱን እንዲገልጽ ሃላፊነት የወሰደ ዳኛ ከተመደበለት ጉዳይ ላይ ከሰፈሩት ፍሬ ነገሮች እና /ወይም አግባብነት ካለው ሕግ ውጭ በጉዳዩ አወሳሰን ላይ ያልተገባ ውጤት ሊያስከትል የሚችል በፍሬ ነገርና በሕግ የማይደገፍ የተሳሳተ መረጃ መስጠት::

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Senegal is a country in West Africa. Senegal is bordered by Mauritania in the north, Mali to the east, Guinea to the southeast, and Guinea-Bissau to the southwest. Senegal nearly surrounds The Gambia, a country occupying a narrow sliver of land along the banks of the Gambia River, which separates Senegal's southern region of Casamance from the rest of the country. Senegal also shares a maritime border with Cape Verde. Senegal's economic and political capital is Dakar.

https://t.me/allafrican
የንግድ ተላላኪዎች እና እንደራሴዎች በንግድ ስራ ያላቸው ሚና

አንድ ነጋዴ የተሰማራበትን የንግድ ስራ በውጤታማነት፣ በቅልጥፍናና በጥራት ለመስራት እንዲሁም የሚያመርተውን ምርት ወይም የሚሰጠዉን አገልግሎት ለሸማች/ለተጠቃሚዉ በአግባቡ ለማደረስ እንዲያስችለዉ የተለያየ ዘዴዎችን ይጠቀማል፡፡ በዚህ መሰረት የንግድ ሰራተኞችን በስራ ውል ቀጥሮ ማሰራት፣ የንግድ ወኪሎችን በየቦታዉ ማስቀመጥ እንዲሁም ከንግድ ተላላኪዎችና እንድራሴዎች ጋር የሚሰራ ሲሆን በዚህ ጽሑፍ በአዲሱ ንግድ ህጋችን እዉቅና ስላላቸዉ የንግድ ተላላኪዎችና እንድራሴዎች ምንነትና ስራዎቻቸው ተዳሰዋል፡፡

1. የንግድ ተላላኪዎች፣ የንግድ እንደራሴዎች እና ያላቸው ሚና

1.1. የንግድ ተላላኪዎች
ከላይ እንደተጠቀሰው ነገዴዎች የተለያዩ ሰዎችን በመጠቀም ከሸማቹ ወይም ከአገልግሎት ፈላጊዉ ጋር ከሚገናኙባቸዉ መንገዶች ዉስጥ አንዱ የንግድ ተላላኪዎችን በመጠቀም ነዉ፡፡ በንግድ ህጉ አንቀጽ 36(1) መሰረት የንግድ ተላላኪ ማለት መኖሪያው የንግድ መደብር ዋና መሥሪያ ቤት ባለበት የሆነና ከነጋዴዉ ጋር በተዋዋሉት የሥራ ውል መሠረት ከነጋዴዉ ጋር የሚሠራ፤ ነጋዴዉ እያዘዘው የነጋዴዉ ደንበኞች በሚገኙበት ቦታ እየተዘዋወረ በነጋዴዉ ስምና ምትክ ሆኖ ዕቃ የሚያቀርብ ወይም አገልግሎት የሚሰጥ ሰው ነው፡፡ በህጉ አንቀጽ 36(2) መሰረት የንግድ ተላላኪዎች በነጋዴዉ ስምና ምትክ ሆነው ዕቃ ሲያቀርቡ ወይም አገልግሎት ሲሰጡ በመካከላቸዉ ሌላ የዉል ቃል ከሌለ በስተቀር የንግድ ተላላኪዎች የተዋዋሏቸዉ ውሎች ለነጋዴዉ ቀርበው መጽደቅ ይኖርባቸዋል፡፡

1.2. የንግድ እንድራሴዎች
በንግድ ህጉ አንቀጽ 37 ስር የንግድ እንድራሴዎች መኖሪያቸው የወካዩ ነጋዴ የንግድ ማህበር ዋና መሥሪያ ቤት ባለበት ሥፍራ ያልሆነና ከነጋዴዉ ጋራ በተዋዋሉት የሥራ ውል መሠረት ነጋዴዉ እንዲሠሩ እያዘዛቸው በተወሰኑ ቦታዎች የነጋዴውን ምርቶች እና አገልግሎቶች የሚያስተዋውቁ፣ የገበያ ጥናትና ለነጋዴዉ ሥራ መስፋፋት የሚረዱ ተመሳሳይ ሥራዎች የሚሰሩ ሰዎች እንደሆኑ ትርጉም ተሰጥቷቸዋል፡፡

የንግድ እንድራሴዎች ከንግድ ተላላኪዎች የሚለዩት የንግድ ተላላኪዎች መኖሪያቸው የንግድ መደብር ዋና መሥሪያ ቤት ባለበት በማድረግ በተዋዋሉት የሥራ ዉል መሠረት ከነጋዴዉ ጋር የሚሠሩ፤ ነጋዴዉ እያዘዛቸው የነጋዴዉ ደንበኞች በሚገኙበት ቦታ እየተዘዋወሩ በነጋዴዉ ስምና ምትክ ሆነው ዕቃ የሚያቀርቡ ወይም አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎች ሲሆኑ የንግድ እንድራሴዎች ደግሞ የወካዩ ነጋዴ የንግድ ማህበር ዋና መሥሪያ ቤት በሌለበት ቦታ ነጋዴዉ በሚያዛቸዉ መሰረት በተወሰኑ ቦታዎች ላይ የነጋዴዉን ምርቶች እና አገልግሎቶች የሚያስተዋውቁ፣ የገበያ ጥናትና ለነጋዴዉ ሥራ መስፋፋት የሚረዱ ተመሳሳይ ሥራዎች የሚሰሩ ሰዎች ናቸዉ፡፡

1.3. የንግድ ተላላኪዎችና እንድራሴዎች ነጋዴ ስላለመሆናቸው
በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀጽ 5 ሥር የተዘረዘሩትንና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች በቋሚነት ለትርፍ የሚሠሩ ሰዎች እንደ ነጋዴ እንደሚቆጠሩ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ የንግድ ተላላኪዎችና እንድራሴዎችን በሚመለከት ህጉ በግልጽ በአንቀጽ 36(3) እና 37(2) ላይ ነጋዴዎች እንዳልሆኑ አስቀምጧል፡፡ በመሆኑም የንግድ ተላላኪዎችና እንድራሴዎች ነጋዴ ሳይሆኑ በስራ ዉል ስምምነት በደመወዝ ወይም በኮሚሽን ወይም ሁለቱንም በማጣመር በሚደረግ ክፍያ በነጋዴዉ በሚታዘዙት መሰረት የሚሰሩ ሰዎች ናቸዉ፡፡

2. በንግድ ተላላኪዎችና እንድራሴዎች ላይ የተጣሉ ክልከላዎች

2.1. የንግድ ተላላኪዎችና እንድራሴዎች የግል ንግድ እንዳይፈጽሙ ስለመከልከላቸዉ
የጥቅም ግጭት እንዳይፈጠር ለመከላከል በማሰብ ህጉ በአንቀጽ 38 ላይ ነጋዴዉና የንግድ ተላላኪዎች ወይም እንድራሴዎች በስራ ውላቸዉ ዉስጥ በግልጽ ካልተስማሙ በስተቀር የንግድ ተላላኪዎችና የንግድ እንድራሴዎች ስለ ራሳቸውም ሆነ ስለ ሌላ ሦስተኛ ወገን ሆነው እነሱን የቀጠራቸው ነጋዴ ከሚሠራው የንግድ ሥራ ጋራ ተመሳሳይ የሆነ የግል ንግድ እንዳይነግዱ ከልክሏል፡፡ ይህንን ክልከላ በመተላለፍ የግል ንግድ ሲነግዱ በተገኙ ጊዜ የሚከተሉት እርምጃዎች እንደሚወሰዱ በአንቀጽ 38(1) እና (2) ተቀምጧል፡፡
• የሚከፈላቸዉን ደመወዝ ወይም ኮሚሽን ወይም ሁለቱንም የመከፈል መብታቸዉን ያጣሉ፡፡
• ዉል እንዳይቀጥል በተሰረዘ ጊዜ ሊያገኙ የሚችሉ ካሳ የመከፈል መብታቸዉን ያጣሉ፡፡
• ቀጣሪዉ አካል/ነጋዴዉ ኪሳራ መጠየቅ ይችላል፣ የስራዉንም ዉል ለመሰረዝ ወይም ዉሉን አላድስም ለማለትም በቂ ምክንያት ይሆናል፡፡

2.2. ለሌሌች ነጋዴዎች ተተክቶ አለመስራት
ተቃራኒ የዉል ስምምነት ከሌለ በስተቀር የንግድ ተላላኪዎችና እንድራሴዎች በውል ግዴታ ለገቡለት ነጋዴ ብቻ እንጂ ስለሌሎች ነጋዴዎች ተተክተው መሥራት የማይችሉ ሲሆን ለሌሎች ነጋዴዎች ተተክተው ሲሠሩ በተገኙ ጊዜ የሚከፈላቸዉን ደመወዝ ወይም ኮሚሽን ወይም ሁለቱንም እንዲሁም ካሳ የመከፈል መብታቸዉን እንደሚያጡ የህጉ አንቀጽ 39 ይደነግጋል፡፡

በውላቸዉ ላይ ለሌሎች ነጋዴዎች ተተክቶ መሥራት እንደሚቻል ከተስማሙ ስለሌሎች ነጋዴዎች ተተክተው መሥራት የሚችሉ መሆኑን ህጉ የፈቀደ ቢሆንም ነገር ግን በምንም አኳኋን ቢሆን ግዴታ የገቡለት ነጋዴ ከሚሸጠው ዕቃ ወይም ከሚሰጠው አገልግሎት ጋር ተመሳሳይ የሆነ ዕቃ ለመሸጥ ወይም አገልግሎት ለመስጠት ለሌላ ነጋዴ ተተክቶ ለመሥራት እንደማይፈቀድ በአንቀጽ 39(2) ስር በግልጽ ተደንግጓል፡፡

3. የንግድ ተላላኪዎችና እንድራሴዎች ስላለባቸዉ ሃላፊነትና ተጠያቂነት
በኢትዮጵያ የፍትሃብሄር ሕግ አንቀጽ 2179 ውክልና ወይም እንደራሴነት አንድም ከሕግ በሌላ መልኩ ደግሞ ከውል ሊመነጭ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡ የንግድ ተላላኪዎችና እንድራሴዎች ከነጋዴዉ ጋር በሚገቡት የስራ ዉል መሰረት በነጋዴዉ የሚታዘዙትን ስራዎች ለመስራት የሚስማሙ በመሆኑ ከውል የሚመነጭ የውክልና ወይም የእንደራሴነት ባህሪያት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከነጋዴዉ ጋርና ከሶስተኛ ወገኖች ጋር ያላቸዉን ግኙነት በተመለከተ ስለ ውክልና/እንድራሴነት የተመለከቱት የፍትሃብሄር ሕግ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት እንዳላቸዉ መረዳት ይቻላል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ለአብነት የፍትሐብሔር ህጉ በአንቀጽ 2189(1) ስር እንደራሴዉ ከወኪልነቱ ስልጣን ሳያልፍ በሌላ ሰዉ ስም የመዋዋል ተግባሮችን የፈጸመ እንደሆነ በእርሱ የተፈጸሙት ተግባሮች በቀጥታ በሾመዉ ሰዉ እንደተፈጸመ ይቆጠራል የሚል በመሆኑ አሁን በያዝነዉ ጉዳይ ላይ የንግድ ተላላኪዉ ወይም እንድራሴዉ በነጋዴዉ ስም የሚሰሩ እንደመሆናቸዉ በተሰጣቸዉ ስልጣን መሰረት ወይም በታዘዙት መሰረት የሚፈጽሙት ዉል በነጋዴዉ እንደተፈጸመ የሚቆጠር ይሆናሉ፡፡ ሆኖም ግን ከተሰጣቸዉ ስልጣን ወሰን ዉጪ በማለፍ የሰሩት ስራ ካለ ነጋዴዉ የተፈጸመዉን ተግባር ለማጽደቅ ወይም ለማፍረስ እንደሚችል የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 2190(1) ይደንጋገል፡፡

የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 2208(1) እንዳስቀመጠው ተወካዩ ከወካዩ ጋር በሚያስተሳስረው ግንኙነት ውስጥ ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እንደሚገባ የሚደነግግ በመሆኑ የንግድ ተላላኪዉ ወይም እንድራሴዉ ከነጋዴ ትዕዛዝ በመዉሰድ በሚሠራቸው በማንኛውም እንቅስቃሴዎች ውስጥ ለለጋዴዉ የተሻለ ጥቅም ሲል በቅንነት ሊሠራ ይገባዋል፡፡ የሚሠሯቸው ድርጊቶች ሁሉ ነጋዴውን ተጠያቂ የሚያደርጉ ስለሆነ በማን አለብኝነት ስሜት ሥራውን መሥራት የለባቸዉም፡፡ የንግድ ተላላኪዉ ወይም እንድራሴዉ የራሱን ጉዳይ
ሲሰራ ሊወስደው የሚችለውን ጥንቃቄና ጭንቀት ለነጋዴዉ በሚሠራበት ጊዜ ማድረግ አለበት። ከዚህ በተጨማሪ በፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 2209(1) እና 2211(1) እንደ ቅደም ተከተላቸዉ የንግድ ተላላኪዉ ወይም እንድራሴዉ ለሚሰራዉ ስራ ታማኝነት/ታማኝ የመሆን ግዴታ/ ታታሪነት /ትጉህ የመሆን ግዴታ ይኖርበታል፡፡
የተጠቃለሉ ህጎችን መጠቀም ለምትፈልጉ ሁሉ

የተቋማችንን ድረ ገጽ www.eag.gov.et ላይ በመግባት ከሚመጡ አማራጮች ውስጥ ሕጎች የሚለውን በመክፈት ከሚመጡ ሶስት አማራጮች ውስጥ ደግሞ የተጠቃለሉ ሕጎች የሚለውን በመምረጥ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን ወይም በጎግል መፈለጊያ ሳጥን ውስጥ http://laws.eag.gov.et/Layout/ventivell/AEAG.aspx በማስገባት በቀጥታ ወደ ተጠቃለሉ ህጎች መሄድ ትችላላችሁ ፡፡
የፌስቡክ አካውንትዎን ደህንነት ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
INSA

1. የይለፍ-ቃልዎን ደህንነት ማረጋገጥ

#_የፌስቡክ አካውንቶን ለሌላ ማንኛውም የኦንላይን አገልግሎት ላይ አይጠቀሙ፤

#_ የይለፍ-ቃልዎን በፍፁም ለሌላ ሰው አያጋሩ፤

#_የሚጠቀሙበት የይለፍ-ቃል ለመገመት አዳጋች የሆነ፣ በፍጹም የእርሶን ስም እና የተለመዱ ቃላትን ያልያዘ ሊሆን ይገባል፤

#_የይለፍ-ቃልዎ ፣ኢ-ሜይልዎን፣ የስልክ ቁጥሮን ወይም የልደት ቀንዎን በፍፁም የሚጠቀም መሆን የለበትም፤

2. የሚያስሱትን ድረ-ገጽ መረጃ በፍጹም አያጋሩ

#_አጥቂዎች ፌስቡክ የሚመስል የሐሰት ገጽ ፈጥረው በኢ-ሜይል አድራሻዎና በይለፍ ቃልዎ እንዲገቡ ሊጠይቁዎ ይችላሉ፤

#_ሁልጊዜም መረጃ የሚያስሱበትን ድረ-ገጽ URL ትክክለኝነት ያረጋግጡ፤
አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥሞ www.facebook.com በማፈላለጊያው ላይ በመጻፍ ወደ ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ለመመለስ ይሞክሩ፤

#_ ከሜታ /Meta/ ወይም ፌስቡክ የሚላክሎትን ኢ-ሜይል በፍጹም ለሌላ ሰው አያጋሩ፣ በተለይም ስለ አካውንቶ ምስጢራዊ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ፤

#_ስለፊሺንግ ጥቃት እና ጠንካራ የይለፍ-ቃል አጠባበቅ ላይ ያለዎትን እውቀትና ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

3. ኮምፒውተርዎን ለሌላ ሰው የሚያጋሩ ከሆነ የፌስቡክ አካውንቶን ዘግተው መውጣትዎን /Log Out/ ማድረግዎን አይዘንጉ፤

#_ኮምፒውተርዎን ዘግተው ሳይወጡ ወይም መሣሪያዎን ያዋሱ ከሆነም ከርቀት እንዴት መውጣት /Log Out Remotely/ እንደሚችሉ ይወቁ፤

#_ከርቀት ሆነው ለሌላ አካል ካዋሱት ኮምፒውተር ላይ ለመውጣት(log out) ለማድረግ ወደ ፌስቡክ "Security and Login Setting" ሲገቡ ከዚህ በፊት ይገቡባቸው የነበሩ መሣሪያዎችን ዝርዝር የሚያቀርብልዎ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሚፈልጉት መሣሪያ ላይ "Logout" የሚለውን ትዕዛዝ በመጫን መውጣት ይችላሉ፤

4. ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄ ሲላክልዎ አይቀበሉ

#_ጠላፊዎች ሰዎችን ለማጥመድ ሲፈልጉ ሀሰተኛ አካውንት ሊፈጥሩ ይችላሉ፤

#_የጠላፊዎች ጓደኛ መሆን ምን አልባት የእርሶን የፌስቡክ የፊት ገጽን /Timeline/ ሊበክሉ፣ የተለያዩ ጉዳዮችን በገጾ ላይ ሊያጋሩ ወይም በካይ መልዕክቶችን በመልዕክት መቀበያዎ ሊልኩብዎ ይችላሉ፤

5. ከበካይ ሶፍትዌሮች እራሶን ይጠብቁ

#_አጥፊ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተሮች፣ ሰርቨሮች /Server/ ወይም የኮምፒውተር ኔትወርክ ላይ ጉዳት ሊጥሉ ይችላሉ፤

#_የተበከለ ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ምን ዓይነት ባህሪያት እንደሚያሳዩ እና እነዚህን በካይ ሶፍትዌሮችን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ በሚመለከት ያለዎትን እውቀት ያዳብሩ፤

#_ማፈላለጊያዎትን በየጊዜው ያዘምኑ፣ አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን እና የማፈላለጊያ ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ፤

6. አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን /Links/ ከሚያውቁት ጓደኛ ወይም ድርጅት እንኳ ቢላክልዎ ከመክፈት ይቆጠቡ

#_እነዚህ በፌስቡክ ወይም በኢ-ሜይል የሚላኩ ማስፈንጠሪያዎች /Links/ ሊሆኑ ይችላሉ፤

#_ፌስቡክ ወይም Meta የይለፍ-ቃሎን በኢ-ሜይል እንዲያስገቡ በፍጹም እንደማይጠይቅዎ ይወቁ፤

#_አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያ ሲያጋጥሞ ለፌስቡክ ሪፖርት /report it/ ያድረጉ፤

7. ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ መንገዶችን ይተግብሩ

#_ከማይታወቁ አድራሻዎችና መሣሪያዎች ወደ አካውንትዎ የመግባት ሙከራ ሲደረግ የጥቆማ መረጃ እንዲደርሶ /get alerts about unrecognized logins/ ያድረጉ፤

#_ባለሁለት ደረጃ የማንነት ማረጋገጫ ዘዴ /Set up two-factor authentication/ ይጠቀሙ፤

#_ሌሎች የደህንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የፌስቡክ Help & Support ላይ በመግባት ያለዎትን ግንዛቤ በየጊዜው ያሳድጉ፤

https://t.me/GudayAsfetsami
#Share
Muktarovich O.
በፌደራል ፍ/ቤት መስራት ለምትፈልጉ
የሥራ መደቡ ተከላካይ ጠበቃ
ደሞዝ 22 ሺ 👇🛑share
Via henok taye law office

https://t.me/LawyerEthiopia
https://t.me/LawyerEthiopia