African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ #RIGHT_TO_PLAY ለተባለ ዓለምአቀፍ ድርጅት ሲሰጥ የነበረው የአመራር ልማት የአቅም ግንባታ መርሐ-ግብር ተጠናቀቀ።

የአቅም ግንባታ መርሐ-ግብሩ ለሁለት ቀናት የቆየ ሲሆን Concepts, Principles & Components of RBM, Results-Based Monitoring and Evaluation, Performance Indicators, Performance Management Framework እና Risks and Assumptions በሚሉ ዋና ዋና ርዕሶች ላይ ያተኮረ ነበር።

ስልጠናው በዘርፉ ሰፊ ልምድ እና አቅም ባላቸው የአመራር ልማት ባለሙያ ጥላዬ ካሳዬ (ዶ/ር) የተሰጠ ሲሆን ንድፈ ሀሳብን ከተግባራዊ ልምምድ ጋር ያጣመረ በመሆኑ ሰልጣኞች ችግር ፈች የሆነ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዳገኙ ተገልጿል።

#RIGHT_TO_PLAY የተሰኘው ዓለምአቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እ.ኤ.አ በ2000 የተቋቋመ ሲሆን ዋና መቀመጫውን #በካናዳ_ቶሮንቶ አድርጎ በአስራ አምስት ሀገራት ላይ ከህጻናት መብትና ትምህርት ጋር በተገናኘ የሚሰራ ተቋም ነው።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ፕሬዚደንት #ዛዲግ_አብርሃ በሙሐዘ ጥበባት #ዳንኤል_ክብረት በተጻፈው “የትርክት ዕዳና በረከት” በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ያቀረቡት ዳሰሳ እና የውይይት መነሻ ሀሳብ ክፍል አንድ እነሆ፡-
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ፕሬዚደንት #ዛዲግ_አብርሃ በሙሐዘ ጥበባት #ዳንኤል_ክብረት በተጻፈው “የትርክት ዕዳና በረከት” በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ያቀረቡት ዳሰሳ እና የውይይት መነሻ ሀሳብ ክፍል ሁለት እነሆ፡-
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ፕሬዚደንት #ዛዲግ_አብርሃ በሙሐዘ ጥበባት #ዳንኤል_ክብረት በተጻፈው “የትርክት ዕዳና በረከት” በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ያቀረቡት ዳሰሳ እና የውይይት መነሻ ሀሳብ ክፍል ሶስት እነሆ፡-
#አሁን
#Happening_now

#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ፕሬዚደንት #ዛዲግ_አብርሃ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተዘጋጀው የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ላይ ተገኝተው The Future of Urban Leadership በሚል ርዕስ ፅሁፍ እያቀረቡ ነው::

የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም "ዘላቂ የከተሞች ልማት ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ 2063" በሚል መሪ ኃሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት በአዲስ አበባ የአድዋ መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል።

በፎረሙ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ከ47 በላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ተመራማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚካሄደው አህጉራዊ ፎረም በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም እና #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ የኢትዮጵያ ከተሞች ተሞክሯቸውን በማጋራት ከአቻ የአፍሪካ ከተሞች የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ይሆናል።
#አሁን
#Happening_now

#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #የከተማ_እና_መሰረተ_ልማት_ሚኒስቴር
በጋራ ያዘጋጁት የተተኪ ወጣቶች ስልጠና #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ እየተሰጠ ነው::
#በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የስራ አመራር ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ #ወንድዬ_ለገሰ (ዶ/ር) በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት አካዳሚው የወጣቶችን አቅም ለመገንባት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ጠቅሰው ወጣቶች የወደፊት አገር ተረካቢ መሆናቸውን ተገንዝበው የመሪነት አቅማቸውን በሚያሳድጉ ተግባራት ውስጥ በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው ተናግረዋል::

ስልጠናው የአፍሪካን የወደፊት የከተማ አመራር ማብቃት (Future urban leaders for Africa) በሚል እየተሰጠ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት: ከተለያዩ ሲቪል ማህበራት: መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የተውጣጡ አንድ መቶ ወጣቶች እየተሳተፉ ነው::

በዘርፉ ልምድ ያላቸው ከፍተኛ አመራሮችና ሙሁራንና ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን ያካበቱትን ልምድና የህይወት ተሞክሮ ለውጣቶቹ አካፍለዋል::

#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚን የሪፎርም: ማስፋትና ሽግግር ፕሮግራም #በእሸቴ_አበበ (ዶ/ር) ቀርቧል::
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ_ፕሬዚደንት_ዛዲግ_አብርሃ በኢቴቪ መዝናኛ ቻናል ላይ ከተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ሆነው #የአዲስ_ዓመት #ትዝታቸውን እና #የልጅነት_ትውስታቸውን አጋርተዋል። ፖለቲከኛ እንደሰው ያዝናል፤ ያለቅስማል ይላሉ። ክፍል አንዱን እንድትመለከቱ ጋበዝናችሁ፦
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቅት_አካዳሚ #ፕሬዚደንት_ዛዲግ_አብርሃ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፀዋል::

ፕሬዚደንቱ ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ፤ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሰላማዊ የትግል አስተዋፅዖ አበርክተዋል ብለዋል።

#ዛዲግ_አብርሃ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ገልፀው፤ ፈጣሪ ነብሳቸውን በአፀደ ገነት እንዲያኖርም ተመኝተዋል፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ_ፕሬዚደንት_ዛዲግ_አብርሃ በኢቴቪ መዝናኛ ቻናል ላይ ከተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ሆነው
#አዲስ_ዓመት እንደ #አዲስ_ለመነሳሳት እና #ለመነቃቃት የሚያበረክተውን በጎ ነገር ያካፍሉናል።
#እ_ኤ_አ #2040 ለአሜሪካ፤ ለቻይና፤ ለአውሮፓውያን እና ለአፍሪካውያን ሊኖረው የሚችለውን ገጸ-በረከት እና ዕዳ ያመላክታሉ። እንድትመለከቱ ጋበዝናችሁ፦
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዓለማችን በዘመን የሽግግር ሀዲድ ላይ ተሳፍራለች። በአንድ በኩል #ፈጣን_የለውጥ_ሂደት፤ በሌላ በኩል #የግርታ_ማዕበል ላይ ነን።

የሀገራት ዕጣ-ፈንታ ለጥያቄ ቀርቦ መልስ የሚያስፈልግበት ዘመን ላይ ደርሰናል። #ከጨለማ_ወደ_ብርሀን_የሚያሸጋግር #መሪ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ነን።

በተለይ #የሀሳብ_ግልጽነት_ያላቸው_መሪዎች ያስፈልጋሉ። #የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ለዚህ ስራ ራሱን እያዘጋጀ ነው።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#“ሱሉልታን_እንደ_ዳቮስ” #የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ከቀረጻቸው 13 ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን #የአመራር_ልማት_ማዕከሉን የዓለምአቀፍ ጉባኤ ማዕከል ለማድረግ የሚያስችል ነው።
አውሮፓውያን ችግር ሲገጥማቸው፤ ችግሮቻቸውን በጋራ ለመመከት፤ #የአውሮፓ_ማኔጅመንት_ኢንስቲትዩትን መስርተው ተሻግረዋል። ይህ ተቋም በጊዜ ሒደት አድጎና በልጽጎ ዳቮስ ላይ አድርሷቸዋል።
#በዳቮስ የማይፈቱ ችግሮች እንደሌሉ ይነገራል።
#አፍሪካዊ_ዳቮስን #በሱሉልታ ላይ ለማቋቋም ያስፈለገበትን ምክንያት #የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ፕሬዚደንት #ዛዲግ_አብርሃ እንዲህ ይገልጻሉ፦
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#መሪነት እና #ሀሳብ_ማፍለቅ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች!!

ሀሳብ ማመንጨት እንደስራ የሚቆጠርበት የመሪነት መንገድ!!

#የሀሳብ_ግልጽነት_ያላቸው_መሪዎች ሀሳባቸውን የሚያመነጩበት ማዕከል ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ #የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ መንገድ ጀምሯል።
#ዛዲግ_አብርሃ_የአፍሌክስ_ፕሬዚደንት ይህን ይላሉ፦

#Idea_Generation_center

#Thought_Leadership

#AFLEX_Leadership_Development_Program

#General_Leadership_Development_Program

#Speciallized_Leadership_Development_Program
በሱሉልታ የአመራር ማዕከል ውስጥ ከሚገኙ የቀድሞ ህንጻዎች መካከል የአስተዳደር ህንጻውን በማደስ ለቢሮ አገልግሎት እንዲውል ስራ መጀመሩ ተገለጸ።
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ #ለውጥ_Reform #ማስፋት_Scaling_Up እና #ሽግግር_Transformation ስራዎች መካከል አንዱ ሱሉልታ ውስጥ የሚገኙትን የቀድሞ ህንጻዎች በአዲስ መልክ በማደስ ወደ ስራ ማስገባት መሆኑም ተጠቅሷል።
ለአስተዳደር ቢሮው እድሳት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን (ERA) ወጭውን የሚሸፍን ሲሆን ህንጻውን ለማደስ ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ECC) ውል መግባቱንና ስራ መጀመሩ ተገልጿል።
የአስተዳደር ቢሮው እድሳት ከአምስት እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የተገለጸ ሲሆን; አጠቃላይ ወጭውም ወደ 200 ሚሊየን ብር እንደሚሆን ተነግሯል።
የህንጻው እድሳት እንደተጠናቀቀም የአካዳሚው ሰራተኞች ወደ አዲሱ ህንጻ ተዛውረው ስራ እንደሚጀምሩ የተጠቀሰ ሲሆን፤ ይህም አካዳሚው ለቢሮ ኪራይ የሚያወጣውን ገንዘብ ከማስቀረቱም በላይ የአመራር ልማት ስራውን በቅርበት ሆኖ ለማገዝ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #እናት_ባንክ በጋራ በሚሰሩባቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ላይ ምክክር አድርገዋል።

የአፍሌክስ የፕሮግራም ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ተወካይ #እሸቴ_አበበ /ዶ/ር/ አካዳሚው በሶስት ዓመታት ሊሰራቸው ያቀዳቸውን የለውጥ ፣ ማስፋት እና ሽግግር ፕሮጀክቶች በእናት ባንክ የኮርፖሬት ሰርቪስ ፕሬዚደንት፣ የሰው ሃብት ዳይሬክተር እና የሰው ሃብት ልማት ሲኒየር ስፔሻሊስት በተገኙበት በፓወር ፖይንት የተደገፈ ገለጻ አድርገዋል።

አካዳሚው ሊሰራቸው ያቀዳቸውን ተግባራት ከግብ ለማድረስ ከግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት #እሸቴ_አበበ /ፒኤች ዲ/ በተለይም የቢዝነስ አመራሩን አቅም በልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራም ለማልማት የስርዓተ ስልጠና (Specialzed_Leadership_Development_Program_Curriculum) እንደተዘጋጀም ገልጸዋል::
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል #የአመራር_ልማት_ስርዓተ_ስልጠና ዝግጅትን በጋራ ገምግመዋል።
ግምገማው የተካሄደው የአካዳሚው የፕሮግራም ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ተወካይ #እሸቴ_አበበ /ዶ/ር/ እና የሪፎርም ኮሚቴ ሰብሳቢ #ሞገስ_ሎጋው /ዶ/ር/ እና የካሪኩለም ዝግጅት ቡድን ባሉበት ሲሆን፣ በግምገማውም በአፍሌክስና በኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል በትብብር የተዘጋጀው የአመራር ልማት ስርዓተ ስልጠና ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የተከናወነ መሆኑ ተጠቅሷል።
#ወንድወሰን_ካሳ ዶ/ር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል #የሰው_ኃይል_ልማት_ዳይሬክተር እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት የስርዓተ ስልጠና ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ለቫሊዴሽን ግምገማ /Validation Workshop/ የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይ ከቫሊዴሽን/ የሚገኘውን ግብዓት በማካተት ስርዓተ ስልጠናውን በበላይ ሃላፊዎች በማስጸደቅና ሞጁል በማዘጋጀት የአመራር ልማት ፕሮግራም ለማስጀመር የሚያስችል ስራዎች ማጠናቀቅ እንዲሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የጋራ ትርክት ሀገራዊ ህልምን ዕውን ለማድረግ አጋዥ መሆኑን አቶ #ዛዲግ_አብርሐ ገለፁ
--------------------------
(ዜና ፓርላማ) ጥቅምት 08 ቀን፣ 2017 ዓ.ም፤ ሱሉልታ፤ የኢትዮጵያን ህልም ዕውን ለማድረግ የጋራ ትርክት መፍጠር አስፈላጊና አጋዥ ነው ሲሉ #የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ_ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ዛዲግ አብርሐ ገለፁ።

ክቡር አቶ ዛዲግ ይህን የገለፁት #"የትርክት_እመርታ_ከታሪካዊ_ስብራት_ወደ_ሀገራዊ_ምልአት" በሚል ርዕስ በሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በተሰጠው የሥልጠና ርዕስ ጉዳይ ላይ ለኢፌድሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና ከፍተኛ አመራሮች ማጠቃለያ በሰጡበት ወቅት ነው።

ክቡር አቶ ዛዲግ ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት #የኢትዮጵያ ታሪክ አጻጻፍ ላይ በሚነሱ አንዳንድ ክፍተቶች ምክንያት የጋራ ታሪክና የወል ትርክቶች መፍጠር አለመቻሉን ገልፀዋል ።

በመሆኑም እነዚህ አሉ የሚባሉ የታሪክ አተራረክ ክፍተቶችን በማረቅ ከነጠላ ትርክት ይልቅ አሰባሳቢና የጋራ የሆነ ትርክት መፍጠር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
#ዜና_ሹመት

ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #ወ_ሮ_መሠረት_ደስታን #የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ_ምክትል_ርዕሰ_አካዳሚ እንዲሆኑ ሹመት ሰጥተዋል።

የአካዳሚው አመራር እና ሰራተኛ መልካም የስራ ዘመንን ይመኛል።
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #የኢፌዴሪ_መከላከያ_ዋር_ኮሌጅ በሰላም እና ደህንነት ዘፍ አብረው ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ