African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #እናት_ባንክ በጋራ በሚሰሩባቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ላይ ምክክር አድርገዋል።

የአፍሌክስ የፕሮግራም ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ተወካይ #እሸቴ_አበበ /ዶ/ር/ አካዳሚው በሶስት ዓመታት ሊሰራቸው ያቀዳቸውን የለውጥ ፣ ማስፋት እና ሽግግር ፕሮጀክቶች በእናት ባንክ የኮርፖሬት ሰርቪስ ፕሬዚደንት፣ የሰው ሃብት ዳይሬክተር እና የሰው ሃብት ልማት ሲኒየር ስፔሻሊስት በተገኙበት በፓወር ፖይንት የተደገፈ ገለጻ አድርገዋል።

አካዳሚው ሊሰራቸው ያቀዳቸውን ተግባራት ከግብ ለማድረስ ከግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት #እሸቴ_አበበ /ፒኤች ዲ/ በተለይም የቢዝነስ አመራሩን አቅም በልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራም ለማልማት የስርዓተ ስልጠና (Specialzed_Leadership_Development_Program_Curriculum) እንደተዘጋጀም ገልጸዋል::