የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ አባላትን ያሳተፈው ይህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር፣ የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን የአገር በቀል ተክሎች በጊቢው ውስጥ በመትከል ተከናውኗል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የአፍሌክስ የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሃገራዊ ንቅናቄን በመፍጠር ባለፉት አመታት ውስጥ የሚታይ ለውጥ ማምጣት የቻለ ታላቅ ተነሳሽነት ነው ብለዋል።
ምክትል ርዕሰ አካዳሚዋ አክለውም "እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከግብ ለማድረስ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅበታል" ሲሉ ይህንን ታላቅ ጅማሮ ከግብ ለማድረስ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ርብርብ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
"ዛሬ እዚህ ስንተክል እያንዳንዳችን እንደ ዜጋ የግል ሃላፊነታችንን እየተወጣን፤ እንዲሁም እንደ አፍሌክስ አካዳሚያችን ትልቅ ሃገራዊ ሚና እንዲጫወት እያስቻልን መሆኑን ልብ ልንል ይገባል" ብለዋል ወ/ሮ መሰረት፡፡
የአካዳሚው የአስተዳደር እና ቢዝነስ ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ አካዳሚው እንደ ቀዳሚ ሃገራዊ ተቋም እንደ አረንጓዴ አሻራ ባሉ ብሄራዊ ንቅናቄዎች ላይ በግንባር ቀደምትነት የሚሳተፍ መሆኑን አስታውሰዋል። ባለፉት አመታት በቅጥር ጊቢው እና በተለያዩ አካባቢዎች በአመራር እና ሰራተኛው ብዙ ቁጥር ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን የገለጹት ዶ/ር ወንድዬ፣ በዘንድሮው መርሃ ግብርም ከሁለት ሺህ በላይ ችግኞች እና የመትከያ ቦታ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአካዳሚው ግቢ ውስጥ ከተተከሉ ችግኞች መካከል አብዛኞቹ መጽደቃቸው ጥሩ እመረታ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ችግኞቹ በመስሪያ ቤት አካባቢ መተከላቸው ለመንከባከብ ምቹ እንደሚያደርጋቸውም በመርሃ ግብሩ ላይ ተጠቁሟል፡፡
በችግኝ ተከላው ላይ በንቃት የተሳተፉት የአካዳሚው ማህበረሰብ አባላት፣ የተከሏቸውን ችግኞች በመንከባከብ የተጀመረውን የአረንጓዴ ልማት ስራ ከግብ ለማድረስ በትጋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

👍10
“መሰናክሎቻችንን ሁሉ የእንቧይ ካብ አድርገን ሪቫን ለመቁረጥ ተዘጋጅተናል” ዛዲግ አብርሃ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)፡- “ታላቁን የህዳሴ ግድብ እንዳንገነባ መሰናክሎቻችንን የነበሩትን ሁሉ የእንቧይ ካብ አድርገን ሪቫን ለመቁረጥ ተዘጋጅተናል” አሉ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ።
ፕሬዚደንቱ ለህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ምክር ቤት አመራርና ባለሙያዎች ስለ ግድብ ሀይል ስልጠና ሲሰጡ እንደተናገሩት “የህዳሴ ግድብን ገንብተን የታሪክ እጥፋትን ለመቀየር መንገድ መጀመራችን፤ ቆርጠን ወደ ስራ መግባታችን፤ ወደ ፊት ለመገስገስ ማለማችን፤ ውሀን ማርከን ለብሄራዊ ኩራት የማዕዘን ድንጋይ እንዲሆን መስራታችን ያልተመቻቸው በግራም በቀኝም የነበሩ ሀይሎች የሰጡንን ፈተና በድል ተወጥተን፤ መሰናክሎቻችንን ሁሉ የእንቧይ ካብ አድርገን ለመጨረሻዋ የብርሀን ቀን ደርሰናል” ብለዋል።

👍5
“ኢትዮጵያ ውጊያውን ሳይሆን ጦርነቱን አሸንፋ ሪቫን ልትቆርጥ ተዘጋጅታለች” የሚሉት አቶ ዛዲግ “ከግድቡ ጋር ተያይዘው ያጋጠሙንን ቀውሶች ታግለን፤ መንበርከክን ከአያቶቻችን አልወረስንም ብለን፤ ስነ-ልቦናዊ መዳንን ሽተን በድህነት የሚወሳውን ብሄራዊ ሀፍረታችንን አሽቀንጥረን ጥለን፤ አዲስ ታሪክ ልናዋልድ የወራት እድሜ ቀርተውናል” ሲሉም አክለዋል።
ኢትዮጵያ በድህነቷ ምክንያት ተጣብቷት የኖረውን ስነ-ልቦናዊ ቁስል ልታክም ከጫፍ እንደደረሰች የሚገልጹት አቶ ዛዲግ “ዓባይ ከህዳሴ ግድብ በፊት የቁጭት ዋርካ ሆኖ፤ ዜማ እና ግጥም ተደርሶለት አለመቻላችንን ሲተርክ ነበር። ከ85 በመቶ በላይ የውሀው ምንጭ ሆነን ሳለ፤ ከስምምነቶች ሁሉ እንድንርቅና ህጋዊ መሰረት እንዳይኖረን፤ በቤታችን ባይተዋር እንድንሆን ተደርገን ዓመታትን ተሻግረናል። ጎረቤቶቻችን ተባብረው ሲጥሉን የሚገባንን ሲነጥቁን ኖረዋል። ተጠራርተው ህልማችንን ሲያጨናግፉ ጉልበት አልባ ሆነን ስንከተላቸው ኖረናል” ዛሬ ግን ይላሉ አቶ ዛዲግ “ዛሬ ግን ያ አለመቻላችን አብቅቶ፤ የታሪክ ጠረጴዛ በአፍጢሙ ተደፍቶ፤ የስምምነቱ አካል ብቻ ሳይሆን የስምምነቱ ጸሀፊዎች እኛ ሆነናል። የመደራደር አቅማችን ወሰኑን ተሻግሮ፤ የጥያቄው መልክና ቅርጽ ተቀይሮ፤ ከሳሽ ሳንሆን ተከሳሽ ሆነናል” ብለዋል።
የገንዘብ እጥረት፤ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ዓለም አቀፍ ተቃውሞ ቆመን እንድንቀር የሚያደርጉ ስብራቶቻችን ቢሆኑም ተሻግረናቸዋል የሚሉት አቶ ዛዲግ “ኢትዮጵያ ለጠላቶቿ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ጆሮ ሳትሰጥ፤ የህዝቧን ሀብት፤ ዕውቀት እና ጉልበት ተመክታ በትውልድ ቅብብሎሽ ያሰበችውን አሳክታለች። ታላቁ የህዳሴ ግድብ የመንግስትን ቅቡልነት ያረጋገጠ ማህተም፤ የተቋማት የመፈጸም አቅም ፊርማ፤ የህዝብ ተሳትፎ ማረጋገጫ ሰነድ ሆኖ ሊመረቅ ነጋሪት ተመቷል” ሲሉ ገልጸዋል።
“ታላቁ የህዳሴ ግድብ የትውልድ ወጌሻ ሆኖ የተጣመመውን እያቃና፤ ዋልታ ረገጥነትን ድል እየነሳ፤ ብሄርተኝነትን እየሞረደ፤ አዲስ የብሄራዊ ትርክት መሰረት ጥሏል” የሚሉት አቶ ዛዲግ “ግድቡ ትውልዶችን ያስተሳሰረ፤ ከዚህ ቀደም በታሪካችን ያልነበረ ቁርኝትን የፈጠረ፤ ልዩነትን ያጠበበ፤ አዲስ ብሄራዊ ዓላማ እና ኩራትን የወለደ ነው። መጪው ትውልድ ዓባይን የሚያውቀውና የሚረዳው በሞገደኝነቱ ሳይሆን በአባቶቹ ተማርኮ እጅ እንደሰጠ ወንዝ ነው። ይህ ደግሞ አዲሱ የትርክት መንገድ ሲሆን አደራን የሚያስተላልፍ፤ ወኔን የሚያጋባ፤ የዜግነት ንቅናቄ መሳሪያ ሆኖ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሻገር ይኖራል” ብለዋል።
“ይህ ትውልድ ዓባይን ከእዳ ወደ ምንዳ ያሸጋገረ፤ ያልሻረ ያልጠገገ ስነ-ልቦናዊ ቁስልን ያከመ፤ ታሪካዊ ጠላቶቻችን በር ዘግተው የተዋዋሉትን ስምምነት የወረቀት ላይ ጥርስ አልባ አንበሳ ያደረገ፤ የሀገሩ ቀጠናዊ ተጽዕኖ እንዲያይል የሰራ ነው” የሚሉት አቶ ዛዲግ “በቀጠናው አዲስ ስርዓት እንዲዋለድ የምጥ መርፌ የታጠቀ ታሪካዊ ትውልድ ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር ቆሟል፤ ሀገሩ ድምጽዋ እንዲሰማ የሚሰራ፤ ውሳኔዋ ወሳኝ እንዲሆን የሚተጋ ወራሽ ትውልድ የራሱን ዕጣ ፈንታ ለመወሰን በስራ ላይ ነው” ሲሉም አክለዋል።

👍2
አቶ ዛዲግ አብርሃ ለህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ምክር ቤት አመራርና ባለሙያዎች ስለ ግድብ ሀይል ስልጠና ሲሰጡ እንደጠቀሱት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካ ሀገራት ኩራት ብቻ ሳይሆን እንደ ትልቅ ሀብት የሚቆጠር በመሆኑ፤ አህጉሪቷ ካላት ተፈጥሮአዊ ጸጋዎች ውስጥ አውራ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን አስታውሰው “ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የሚኖረው ትዕምርታዊ ሀይል በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም። ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካኒዝምን የዕድገት ሞዴል ተከትላ የማንንም ደጅ ሳትጠና በራሷ አቅም መገንባቷ ለቀጠናውና ለአፍሪካ የሚኖረው በጎ መልዕክት ከቃል በላይ ነው። አፍሪካውያን ሲተርኩት የሚኖሩት ከትውልድ ወደ ትውልድ በኩራት የሚያሻግሩት ብሔራዊ ሀብታቸው አድርገው እንደ አይናቸው ብሌን የሚጠብቁት አፍሪካዊ ሀብት ነው” ብለዋል።
“ታላቁ የህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያውያን ቢገነባም የነጻነት አዋጅ ምልክት ሆኖ የሚያገለግለው ለመላው አፍሪካውያን ጭምር ነው” የሚሉት አቶ ዛዲግ “የኢትዮጵያን ማንሰራራት ተከትሎ የፓን አፍሪካን ዕሳቤም እያንሰራራ መምጣቱን ግድቡ ያመላክታል። አፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነቷን ዳግም እያረጋገጠች መምጣቷን እና ዓለም አቀፍ ገጽታዋን እያደሰች እንዳለች ግድቡ ህያው ምስክርነት እየሰጠ ነው። ግድባችን አፍሪካ ከድህነት ጋር ታግላ በዝረራ እያሸነፈች ስለመሆኗ የሚያሳየን የመንገዳችን ኮምፓስ ነው። አፍሪካ በላቤ በድካሜ አርማዬን እተክላለሁ ብላ ለመነሳቷ ዋቢ ምስክሯ የህዳሴው ግድብ እንደሆነ አረጋግጣለች” ሲሉ ተናግረዋል።
ውሀን የተቆጣጠረ ሀይልን እንደሚቆጣጠር የሚጠቅሱት አቶ ዛዲግ አፍሪካ ባለቤት ሆና የሰራቸው የህዳሴ ግድበ የሀይል ሚዛንን እያስጠበቀ የመደራደር አቅምን እንደሚያሳድግም ተናግረዋል። የአፍሪካዊ እና የኢትዮጵያዊ ማንነት መገለጫ የሆነው የህዳሴ ግድብ አፍሪካውያን ከተባበሩ የመፈጸምና የማድረግ ሀይላቸው ምን ድረስ እንደሚዘልቅ ማሳያ እንደሆነም በስልጠናው ላይ ተጠቅሷል።
“ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከግድብ በላይ ነው ስንል በምክንያት ነው” የሚሉት አቶ ዛዲግ “ ግድቡ ጀምሮ የመፈጸም ሀገራዊ መሰረት የተጣለበት፤ ሀገራዊ ሽግግር ስጋ ለብሶ የተመለከትንበት፤የዳግም ማንሰራራት ትዕምርት ያኖርንበት፤ ጀምረን የመቋጨት ሰንኮፋችንን ወደ መቃብር ሰደን ጥንቅቅ አድርገን መጨረስን የተማርንበት፤ የመሰረተ ልማት ወንጌላችንን በቅጡ የጻፍንበት፤ ሀገራዊ ትርክታችንን ያደላደልንበት፤ የመንግስትን ቅቡልነት በተግባር ያየንበት፤ፉክክርን በትብብር የቀየርንበት፤ ቀጠናዊ ሀያልነታችንን ያስመሰከርንበት፤ ወዳጆቻችንን ያስደሰትንበት፤ ጠላቶቻችንን አፍ ያስዘጋንበት፤ ኢትዮጵያዊነትን የሚወልዱ እና የሚያዋልዱ መሪዎችን የፈጠርንበት፤ ዜጎችን ወደ ባለ ድርሻ አካልነት ያሸጋገርንበት፤ የብሔራዊ ማንነታችን እና ፍላጎታችንን አዋጅ ያስነገርንበት ነጋሪት ጋዜጣችን ነው” ብለዋል።
ህዳሴ ግድብ ባለመጨረስ የባህል ልምምድ ላይ የተሰነዘረ መዶሻ እንደሆነ ያስታወሱት አቶ ዛዲግ “ኢትዮጵያ የራሷን ወገብ እና አቅም የፈተሸችበት፤ በብድርም ሆነ በስጦታ ‘ቤሳቤስቲን’ ሳታገኝ ግድቧን ገንብታ ለሀይል ማመንጫ ብቻ ሳይሆን ለሉዓላዊነቷ ማረጋገጫ የተጠቀመችበት ነው” ብለዋል።
የግድብ ግንባታ በባህርይው ማቀድን፤ ማስተባበርን፤ ግብር መሰብሰብን እና የረጅም ጊዜ ርዕይን እንደሚጠይቅ የጠቆሙት አቶ ዛዲግ “በትንሹ የሚያስብ ግድብ አይገነባም፤ተሻጋሪ እና ምናባዊ ርዕይ ያለው መንግስት የመፈጸም አቅሙን አሳድጎ ህዝቡን በመሰረተ ልማት ያስተሳስራል። የተራራቁ ህዝቦችን ያቀራርባል። ህዝብን ለጋራ ተልዕኮ በአንድነት አሰልፎ ሀገራዊ አሻራን ያኖራል” ሲሉም ጠቅሰዋል።

“የራስህ ፣ የተቋምህ እና የሀገርህ የትርክት ባለቤት ካልሆንክ የሌሎች የትርክት ጭሰኛ ትሆናለህ” ዛዲግ አብርሃ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም (አፍሌክስ):- ግለሰቦች ፣ ተቋማት እና ሀገራት በአግባቡ ቀርፀው ከትውልድ ወደ ትውልድ ካላሸጋገሩ በተጠለፈ ትርክት ውስጥ እንደሚዳክሩ እና የትርክት ጭሰኛ እንደሚሆኑ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናገሩ::
"መርዛማ ትርክትን አፍርሶ ገንቢ ትርክትን መትከል ለሀገር ሉዓላዊነት የሚከፈል መስዋዕትነት ነው" የሚሉት አቶ ዛዲግ "የሀገርን ትርጉም የተረዳ ህዝብ የራሱን አሰባሳቢ ትርክት እየገነባ የጋራ ዕድል-ፈንታውን ይወስናል:: ታላቁ የህዳሴ ግድብ የራሱን ትርክት ራሱ ያነፀ ቢሆንም የላቀ ገንቢ ትርክት ተሰናድቶ በዓለም ሊናኝ ይገባል" ብለዋል::
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለዘመናት አብረውን ላረጁ ስብራቶቻችን ወጌሻ ሆኖ በዓለም ህዝብ እና ታሪክ ፊት ቀና እንድንል ያስቻለ ድንቅ በትራችን እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ዛዲግ "በእያንዳንዱ ቤት የነበረው የጨለማ ስልጣን ተገፍፎ በብርሀን ፀዳል እንዲተካ ያስቻለ ፣ የጀመርነው የብልጽግና ጉዞ ከዳር እንዲደርስ ጉልበትና ሀይል የሆነ ፣ ኢትዮጵያ ካለልኳ የተሰፋላትን የቅኝ ግዛት ህግና መመሪያ አሽቀንጥራ እንድትጥል ምክንያት የሆነ ፣ በብሄራዊ ብቻ ሳንወሰን ድንበር ተሻግረን ቀጠናዊ እና ዓለምአቀፋዊ ትርክትን እንድንቀርፅ መንገድ የከፈተልን የዚህ ዘመን ገንቢ ትርክታችን ነው" ብለዋል::

👍8
ታላቁ የህዳሴ ግድብ የዚህ ዘመን ትውልዶች በደማቸው እና በላባቸው የፃፉት ደብዳቤ እንደሆነ ያስታወሱት አቶ ዛዲግ "የትልልቅ ፕሮጀክቶች እስትንፋስ ትርክት ነው:: ትርክት ፕሮጀክቶችን ያድናልም:: ይገድላልም:: የታላቁን ህዳሴ ክብር የሚመጥንና ትውልድን ተሻግሮ የሚነገር ቋሚ ትርክት መቅረጽ ፣ ማደራጀት እና ማስረፅ ቀጣዩ ቁልፍ ተግባር ነው:: ይህን ሳናደርግ ከቀረን ገንቢ ትርክታችን በጠላት መዳፍ ውስጥ ወድቆ አንድም ይሸረሸራል አሊያም ይጠለፋል" በማለት ቋሚ ትርክት መገንባት ላይ ሰፊ ሀሳብ አቅርበዋል::
የትርክት ሀውልት ሆነው በዓለም መድረክ ምስክርነት ከሚቆሙ ኢትዮጵያዊ ማህተሞች መካከል ታላቁ የህዳሴ ግድብ እንደሆነ ያነሱት አቶ ዛዲግ የትርክት መሰረቶች ላይም ትንታኔ ሰጥተዋል:: "የህዳሴ ግድብ ከጣለልን የትርክት መሰረቶች ውስጥ ቀዳሚው ወድቆ አለመቅረትን ነው:: የውድቀታችን እና ያለመቻላችን ማሳያ የነበረው የአባይ ወንዝ ታሪክ የተቀየረበት ነው:: ጀምሮ ካለመጨረስ ደዌ የተፈወስንበት ነው:: ሁለተኛው የትርክት መሰረት የሉዓላዊነት እና የአልገዛም ባይነት ነው:: የማንም ፈቃድም ሆነ ይሁንታ ሳያስፈልገን ፍርሃት እና ስጋትን ቁልቁል ያየንበት የትርክት መሰረትን ከግድባችን አግኝተናል" ብለዋል::
"በግድባችን ነፃነትን ገንብተናል:: ከግድቡ ብረት እና ኮንክሪት ጀርባ በወርቅ ቀለም የተፃፈ ነፃነት አለ:: ሁሉንም በአንድነት ያሰለፈ ፣ ጥልቅ ብዝሀነታችን ጉልበታችን እንደሆነ ያስመሰከረ ፣ የጥል ግድግዳን ያፈረሰ ፣ የባይተዋርነት ሰንሰለትን የበጣጠሰ የትርክት መሰረትም አለው:: ህዳሴ የዚህ ትውልድ አድዋ ነው:: እንደገና የመወለድ ትርክትን ያላበሰን ሀቃችን ነው:: ህዝቡን የሀገር ባለቤት ያደረገ ፣ የክብርና የወንድማማችነት ማሳያ ትርክትን ሰጥቶናል" ብለዋል አቶ ዛዲግ::
ህዳሴ ግድብ ለሀገር ግንባታ ቀጣይነት ሲባል የተዋደቅንበት የጦርነት አውድማ እንደሆነና ይህም የትርክት መሰረት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ዛዲግ ወደ ፊት መገስገስ እና አዲስ የአካታችነት ዘመን መበሰሩን የሚያመላክት የትርክት መሰረት እንዳለንም ለህዳሴ ግድብ ምክር ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች በሰጡት ስልጠና ላይ አመላክተዋል::

“ይህ ትውልድ በጨለማ ዘመን ተወልዶ ለማያውቀው ብርሀን ታጋይ ሆኖ ህዳሴ ግድብን አዋልዷል” ዛዲግ አብርሃ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም (አፍሌክስ):- ይህ ትውልድ ብርሀን ባልነበረበት ዘመን ተወልዶ ሲናፍቀው ለነበረው ብርሀን ታግሎ ዋስትናውን እያረጋገጠ የሚገኝ ልዩ ትውልድ መሆኑን የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናገሩ::
"ፅልመትን ተዋግቶ ብርሀንን ነፃ ያወጣ ትውልድ አካል መሆን መታደል ነው" ያሉት አቶ ዛዲግ "ረጅሙን ምናብ ተጠቅሞ ለእሱ ሳይሆን ለትውልድ ተሻጋሪ ተጨባጭ እውነታን ያወረሰ ትውልድ በታሪክ አይረሳም:: የአባይ ምንጭ የነበርነውን ሰዎች ወደ ብርሀን ምንጭነት እንድንሸጋገር ምክንያት በሆነ የትውልድ ዘመን ላይ ተገኝተን ሪቫን ለመቁረጥ መዘጋጀታችን በኩራት መደላድል ላይ አዋጅ እያወጅን ለመሆናችን ምስክር ነው" ብለዋል::
በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አማካይነት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አላማውን አምኖ ያለውን ብቻ ሳይሆን ከጉድለቱ ላይ ቦንድ የገዛውና ገንዘብ የለገሰው ህዝብ በወቅቱ ይታየው የነበረው የመሰረት ድንጋይ ሳይሆን የመነጨ የኤሌክትሪክ ሀይል እና ብርሀን ነበር የሚሉት አቶ ዛዲግ ከግድቡ ግንባታ ጀምሮ የተገኙ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞች ተንትነዋል::

ግድቡ ከውሀ ፖለቲካ አንፃር የተለየ መልክ እንዳለው የሚጠቅሱት አቶ ዛዲግ "ድንበር ተሻጋሪ የሆነ ግድብ ሲገነባ በአወንታዊ እና በአሉታዊ መልኩ የቀጠናውን ፖለቲካ የመዘወር እድሉ ሰፊ ነው:: የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት እኛ የውሀው መነሻ ነን በሚል ውሀ የማይቋጥር ሀሳብ ያነሳሉ:: የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በበኩላቸው ኢትዮጵያ የውሀ መጠናችንን ቀንሳ ብቻዋን ልትበለፅግ ነው በሚል ኢፍትሀዊ አጀንዳቸውን ያራግባሉ" ብለዋል::
የታላቁ ህዳሴ ግድብን ከተለያዩ ሙያዊ መስኮች አንፃር የተነተኑት አቶ ዛዲግ "ግድቡን በፖለቲካ ሳይንስ መነፅር ስንመለከተው የመንግስትን እና የተቋማትን ፕሮጀክት ጀምሮ የመፈፀም አቅም ያመላክታል:: የቀጠናዊ ትብብርን ቅርፅ ይወስናል:: በሶሽዎሎጂ እይታ ደግሞ ግድቡ ከፍትሀዊ ልማት ጋር ተያይዞ በመስዋዕትነት የጋራ ማንነትን የመገንባት ሀይሉ ከፍተኛ ነው:: ከኢኮኖሚክስ በኩል ግድቡ ከወጣበት ገንዘብ አንፃር የሚያመነጨውን ሀይል በገንዘብ ይተምናል:: ግድባችንን ከስነ-ልቦና ሙያ አንፃር ብንመለከተውም ህዝብን ከተስፋ ጋር አቆራኝቶ የጀመርነውን መጨረስ ካልቻልን ተስፋችን እንደሚሞት ካጠናቀቅነው ግን የለመለም ተስፋ ባለቤቶች እንሆናለን" ሲሉ ግድቡን ከተለያዩ ሳይንሳዊ መሰረቶች አንፃር ትንታኔ አቅርበዋል::
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለሀገራችን ህዝቦች የጋራ ኩራትን እና ተስፋን እንዳጎናፀፈም ለህዳሴ ግድብ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች በሰጡት ስልጠና ላይ አቶ ዛዲግ ገልፀዋል::

👍9
"ያጋጠሙንን ችግሮች የተሻገርናቸው 'ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ እንሆናለን' የሚለውን ትርክት ተመርኩዘን ነው" ዛዲግ አብርሃ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም (አፍሌክስ):- ሀገራት እና መሪዎች በብሄረ መንግስት ግንባታም ሆነ በብልፅግና መንገዳቸው ችግር ሲያጋጥማቸው የሚሻገሩበት አሰባሳቢ ትርክትን እንደ ምርኩዝ እንደሚጠቀሙ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናገሩ::
ፕሬዚደንቱ ለህዳሴ ግድብ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች በሰጡት ስልጠና ላይ እንደገለፁት በህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት ላይ ያጋጠሙንን የቴክኒክ እና የዲፕሎማሲ ጫናዎች የተሻገርናቸው የአሰባሳቢ ትርክት መሰረት የሆነውን የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 'ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ እንሆናለን' የሚለውን ቃል ምርኩዝ አድርገን እንደሆነ ተናግረዋል::

👍6
"የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሰባሳቢ ትርክት ኮንክሪት እና ብረት ወደ እምነት እንዲቀየር አድርጏል" የሚሉት አቶ ዛዲግ "ግድቡን ጀምረው ያስረከቡንን አመስግነን ፣ የነበሩበትን ችግሮች በሳይንሳዊ መንገድ ለይተን ፣ ያለንን እምቅ የመሪነት አቅም በተግባር መንዝረን ፣ የተጏደለውን አሟልተን በሙሉ አቅም የኤሌትሪክ ሀይል ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ግለት ማስጠበቂያ ሚዛን አድርገነዋል" ብለዋል::
"ግድቡ የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን እውነታ በዓለም አደባባይ የሰበከ ሀዋርያ ነው" የሚሉት አቶ ዛዲግ "የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሰባሳቢ ትርክት በትውልዶች መካከል ስለ ሀገር የሚከፈል መስዋዕትነት እንንዲቀጥል አድርጎ መፃኢው ጊዜ የእኛ እንደሚሆን ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነበር" ሲሉም አቶ ዛዲግ አክለዋል::
ታላቁ የህዳሴ ግድብ የዚህ ትውልድ አድዋ እንደሆነ የጠቀሱት አቶ ዛዲግ "በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሰባሳቢ ትርክት ውስጥ ግድቡ ኢትዮጵያ የቀደምት ስልጣኔ መነሻ መሆኗን ይጠቅሳል:: በመውደቅ መነሳት ውስጥ አልፋ ፣ በምታስመዘግባቸው ትናንሽ ድሎች ሳትዝናና እና ሳትዘናጋ ፣ ወደ ድሏ ጫፍ ተጉዛ ፣ የማንሰራራት ዘመኗን እያወጀች ትገኛለች" ብለዋል::

👍12👎1
የትምህርት ኃይል እና የመጪው ጊዜ ዕድል-ፈንታው
በዛዲግ አብርሃ
ዛሬ ምሽት
በአፍሌከስ የፌስቡክ እና የዩቲዩብ ገጾች👇
Facebook: https://web.facebook.com/aflexacademy.gov.et
YouTube: https://www.youtube.com/@AfricanLeadershipExcellenceAca
ትምህርት እውቀትና ወረቀት ከማግኘት በላይ ማንነታችንን የሚቀርጽ፣ የምናደርገውን፣ የምንኖርበትን መንገድ እና ወደፊታችንን የሚወስን ነገር ነው❗️
የሚያስፈልገን ምን እንደምናስብ ሳይሆን እንዴት እንደምናስብ የሚያስረዳን ትምህርት ነው!
📚ትምህርት ከትናንት እስከ ነገ
👨🔬የመምህራን ሚና፡ ከግለሰብ እስከ ማህበረሰብ
በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት አስፈላጊነቱ ጥያቄ ውስጥ በገባበት በዚህ ዘመን የትምህርትን ሃይል አጉልቶ የሚያሳይ፣ ምን አይነት ትምህርት እንደሚያስፈልገን የሚያስረዳ ስልጠና!

👍4
“በዚህ ዘመን ዓለም የሚድነው ጦር በታጠቀ መሪ ሳይሆን ርዕይ በሰነቀ መሪ ነው" ዛዲግ አብርሃ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)፡- ይህ ዘመን የሚጠይቀው እና የሚያስፈልገው ጦር ይዞ የሚወረውር ጋሻ ይዞ የሚመክት መሪ ሳይሆን ርዕይን የሰነቀ እና የራቀውን በምናብ አቅርቦ የረቀቀውን አጉልቶ ዕሴቱን የሚያጋራ አመራርን እንደሆነ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናግረዋል::
"አባቶቻችን ከጠላቶቻችን ጋር በኃላ ቀር መሳሪያ ተዋግተው ያቆዩልንን ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ የምናሻግረው ጦር በመምዘዝ ሳይሆን ዕሴት ላይ የተመሰረተ ወኔ እና ድፍረትን የተላበሱ አመራር እያፈራን ስንሄድ ነው" የሚሉት አቶ ዛዲግ ፣ "የቀጣዩን ትውልድ መሪዎች ዛሬ ላይ ካልሰራን የምናወርሰው ጥጋብን ሳይሆን ችጋርን ነው" ብለዋል::
ቀደም ባሉት አመታት የነበረውን የመሪነት ሚና ከዘመኑ ጋር እያነፃፀሩ ያቀረቡት አቶ ዛዲግ "ድሮ መሪ የሚያስፈልገው ድንበርን ከጠላት ለመከላከል ፣ ትእዛዝ ሰጥቶ አስተባብሮ ለመምራት ፣ ጠላትን ለመማረክ ፣ የሀብትን እጥረት ለማስተዳደር ፣ የሚታወቀውን ለማወቅ ነበር" የሚሉት አቶ ዛዲግ የዚህ ዘመን መሪ ሚና የሚለይባቸውን ተግባራትም ጠቅሰዋል:: "የዚህ ዘመን መሪ ውስብስቡን ዓለም ተረድቶ የሚያቀል ፣ ትእዛዝን ሳይሆን ጥበብን የሚያስቀድም ፣ የራቀውን የሚያቀርብ ፣ የተበታተነውን አንድ የሚያደርግ ፣ ሞልቶ የተረፈውን ሀብት የሚያስተዳድር ፣ የማይታወቀውን ለማወቅ በርዕይ የሚሰራ ነው" ሲሉም አክለዋል::
ህሊናን ለህዝብ ጥቅም ያሳደሩ መሪዎች ከሌሉ ዴሞክራሲ የውሸት ይሆናል ያሉት አቶ ዛዲግ ፣ በአሁኑ ወቅት በአመራር ላይ የሚስተዋሉ ፈተናዎች እና የሚያስፈልጉ ለውጦች ላይ ለከፍተኛ ለአመራሮች ስልጠና ሰጥተዋል።

ፕሬዝደንቱ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች በሰጡት ስልጠና፣ በተለያዩ ዘመናትና ስልጣኔዎች የተለያዩ የአመራር ፍልስፍናዎች እንደነበሩ ጠቅሰዋል። በአሁኑ “ድህረ-እውነት” አለም ውስጥ፣ ሁሉም እውነት በጥያቄ ምልክት ውስጥ በመግባቱ፣ አመራር ከምንጊዜውም በላይ ብዙ ፈተናዎች እንደሚገጥሙት ገልጸዋል።
“እኛ ሰዎች ራሳችንን ለመሪነት ብቁ ማድረግ ካልቻልን፣ እኛው የፈጠርነው አልጎሪዝም ይመራናል” ሲሉ ተናግረው፣ “ነባር ነገሮች ሁሉ ፈርሰው አዳዲስ ነገሮች በፍጥነት እየተጀመሩ ባለበት በዚህ አለም፣ ረጋ ብሎ የወደፊቱን ጊዜ ለመወሰን የሚቻለው በመሪነት ብቻ ነው” ብለዋል።
ለዘመናችን የሚያስፈልገው መሪ ደፋር ብቻ ሳይሆን፣ ድፍረትንና ወኔን ከጥበብ ጋር የሚያስተሳስር አመራር መሆኑን ፕሬዝደንቱ አጽንኦት ሰጥተዋል።
“ባለአደራ መሪ” የምንለው አመራር የተሰበረን የሚጠግን፣ መቀጠል ያለበትን የሚያስቀጥል፣ አላስፈላጊውን ቆርጦ የሚጥል፣ ነገን የሚተነብይ፣ አዲሱን ነገር ተቀብሎና አጎልብቶ ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፍ አቅም ያለው መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ዛዲግ በአሁኑ ወቅት ያሉ ወጣቶች የሚቆጣጠራቸውን ሳይሆን የሚያሳትፋቸውን ስርዓት እንደሚፈልጉ ጠቅሰው፣ መሪዎች ስርዓትን መሰረት አድርጎ ከመስራት ባሻገር ከስርዓት ውጪም ማሰብ እንዳለባቸው አስረድተዋል።
ከቴክኒካዊ አመራር ይልቅ፣ ራሱን ከጊዜና ሁኔታዎች ጋር የሚያላምድ እና ችግሮችን በዘላቂነት የመፍታት አቅም ያለው አመራር እንደሚያስፈልግም አቶ ዛዲግ ገልጸዋል።
ስልጠናው በቀጣይ ቀናት ውሎው በአቶ ዛዲግ ከሚሰጠው ማብራርያ በተጨማሪ አሳታፊ ውይይቶች እንደሚኖሩት ተገልጿል።

👍32