የሀሳብና የተግባር አንድነትን በማቀናጀት ለሀገርና ሕዝብ የሚጠቅሙ ተግባራትን በላቀ ትጋት ማከናወን ይገባል- አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 7/2017(ኢዜአ):- የሀሳብና የተግባር አንድነትን በማቀናጀት ለሀገርና ሕዝብ የሚጠቅሙ ተግባራትን በላቀ ትጋት ማከናወን ይገባል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።
''የህልም ጉልበት ለእምርታዊ ዕድገት'' በሚል መሪ ሃሳብ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራሮችና አባላት የሥልጠና መድረክ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እየተካሄደ ነው።
የሥልጠናው ዓላማ በሀገራዊ ለውጡ የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠልና የሚያጋጥሙ ችግሮችን የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ለመፍትሔው ለመሥራት መሆኑ ተገልጿል።
#በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ በተጀመረው ስልጠና ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፤ የሀሳብና የተግባር አንድነትን በማቀናጀት ለሀገርና ሕዝብ የሚጠቅሙ ሥራዎችን በውጤታማነት ማከናወን ይገባል ብለዋል።
የምክር ቤት አባላት በለውጥ ወቅት የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በድል ለመሻገር የችግሩ መነሻ ላይ የጋራ መግባባት መያዝና ለመፍትሔውም መትጋት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያዊ አንድነትን ይበልጥ ለማጠንከር የወል ትርክትን በመገንባት ጊዜያዊ ፈተናዎችን መሻገርና ሀገራዊ ለውጡን ለማጽናት ዜጎች በጋራ ሊቆሙ ይገባልም ነው ያሉት።
የምክር ቤት አመራሮችና አባላት የሥልጠና መድረክም የሀሳብና የተግባር አንድነትን በማቀናጀት ለሀገርና ሕዝብ የሚጠቅሙ ተግባራትን በላቀ ትጋት ለማከናወን ይበልጥ መነሳሳትን ለመፍጠር ነው ብለዋል።

ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን በአግባቡ በመረዳት በሕገ-መንግሥቱ የተሰጣቸውን የሕዝብ አደራና ኃላፊነት በላቀ ብቃት ለመወጣት መሆኑንም አፈ-ጉባዔው አንስተዋል።
በምክር ቤቱ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፤ የሥልጠናው ዓላማ የምክር ቤት አባላት ሀገራዊ ህልሞችን ለማሳካት በተሄደበት እርቀት ልክ የተገኙ ድሎችና ያጋጠሙ ፈተናዎችን በአግባቡ እንዲገነዘቡ ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
በለውጡ ሂደት የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠል ለችግሮች ደግሞ የጋራ መፍትሔ እየሰጡ ለመቀጠል በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተሟላ ግንዛቤ መያዝ ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል።
የምክር ቤት አመራሮችና አባላት ሥልጠና በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ፣ በውጭ ግንኙነት፣ በተቋም ግንባታና የአመራር ብቃት ላይ በማተኮር #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ለዘጠኝ ቀናት የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል።

የምክር ቤት አባላት የሀገር ህልም እንዲሳካ ለማስቻል ከፍተኛ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል-#አቶ_አደም_ፋራህ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ ህልም እንዲሳካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ በመገኘት ገለፁ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች አመራሮች #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት ÷የምክር ቤት አባላት ካለባቸው ሕዝባዊ ኃላፊነት አኳያ የሀገር ህልም እንዲሳካ ከፍተኛ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እንዲሠሩ ያስፈልጋል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
ኢትዮጵያ ወደ ተሻለ ከፍታ የሚያደርሳትን እና ለትውልድ የሚሻገር ህልም ተልማለች፤ ይህ ህልም እውን ይሆን ዘንድም ምቹ ነባራዊ ሁኔታዎች አሏት ማለታቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
“ሀገሪቱ ያላት እምቅ የተፈጥሮ ሀብት፣ ከዓላማው ጎን የሚሰለፍ ሕዝብ እንዲሁም የተገነቡ ተቋማት የሀገራችንን ህልም ዕውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች ከሚባሉት ውስጥ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው” ብለዋል፡፡

ስለሆነም በቀጣይ ምክር ቤቱም ሆነ የምክር ቤት አባላት ከስልጠናው የሚገኘውን ዕውቀት፣ ልምድና ተሞክሮ በመቅሰም፣ ከተቋማት ጋር በመቀናጀትና ተናቦ በመስራት፣ እንዲሁም የሚሰጡ ቀጣይ ሀገራዊ አቅጣጫዎችን በአግባቡ በመያዝ ሀገራችንን በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች በማጠናከር ወደተሻለ ከፍታና ብልጽግና የማሸጋገር ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅብናል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ‹‹የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት›› የሚለው አለማቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ጥቅል የሆነ ሀሳብን የያዘ በመሆኑ የነበራቸውን ግንዛቤ ይበልጥ እንዳሳደገላቸው ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም ዛሬ ላይ አደጉ የሚባሉት ሀገሮች የራሳቸውን ህልም አስቀምጠው እንዳሳኩ ሁሉ ሀገራችንም ወደ ብልፅግና የሚሻግራት ህልም ማስቀመጥ በመቻሏ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው ያገኙት ይህ ህልም ዕውን እንዲሆንም ለመራጭ ህዝባቸው በአግባቡ በማስገንዘብ ሀሳቡ እንዲሰርጽ ማድረግ እና በክትትልና ቁጥጥር ስራቸው ውስጥ በማካተት እንዲሰሩም ሰልጣኝ የምክር ቤት አባላቱ ተናግረዋል፡፡
የተሰጡንን ሀገራዊ ተልዕኮዎችን በአግባቡ በመወጣት፣ ከግጭት እና ከፅንፈኝነት አመላከት በመውጣት፣ ችግሮቻችንን በጋራ በመፍታት እንዲሁም ውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር ሀገራችንን ወደተሻለ ከፍታ ማሻገር ይጠበቅብናልም ነው ያሉት፡፡
በመጨረሻም ሰልጣኝ የምክር ቤት አባላት #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ በቀጣይም በሚሰጡ የስልጠና ርዕሶች ላይም በአግባቡ እንዲሳተፉና የተሻለ ዕውቀትና ግንዛቤ እንይዛለን ብለው እንደሚጠብቁም ገልጸዋል፡፡
(በኃይለሚካኤል አረጋኸኝ)

#በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ የሚሰጠው
ስልጠናው ምክር ቤቱ እና የምክር ቤት አባላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል ትልቅ አቅምን እንደሚፈጥር ተመላከተ
--------------------
(ዜና ፓርላማ)ጥቅምት 09 ቀን ፣ 2017 ዓ.ም፤ ሱሉልታ፤ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ለምክር ቤቱ አመራሮችና አባላት እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና ምክር ቤቱ እና የምክር ቤት አባላት የተጣለባቸውን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል ትልቅ አቅምን እንደሚፈጥር የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች አመላክተዋል፡፡
ስልጠናው ምክር ቤቱና የምክር ቤት አባላት ሀገራችንን ከወቅታዊ አለምዓቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማገናዘብ በህገ-መንግስቱ የተሰጠንን የህግ አወጣጥ፣ የክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም የህዝብ ውክልና ስራችንን በሙሉ አቅምና ብቃት ለመወጣት ያስችላል ብለዋል፡፡
የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች አክለውም ስልጠናው ሀገራችን በተጨባጭ እያስመዘገበች ያለውን እመርታ፣ ያጋጠሟትን ተግዳሮቶችን እና እነዚህን ተግዳሮቶች በአንድነት በመቆምና በትብብር መንፈስ በጋራ በመስራት መወጣት እንደሚቻል ያሳየም ነው ብለዋል፡፡
ከለውጡ ወዲህ በሀገራችን ብዙ ማሻሻያዎች ተደርገዋል፤ ሰፋፊ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እኛም እንደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና እንደ ምክር ቤት አባል ተሳትፏችን የጎላ ነበር ሲሉ አብራርተዋል፡፡

የሕዝብን ጥያቄዎች ለመመለስ የፖለቲካ እመርታን ማረጋገጥ ይገባል-አቶ አደም ፋራህ
****************
ሕዝብ የሚያነሳቸውን የዲሞክራሲ፣ የፍትህና የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ወቅቱን የዋጀ ህዝብን ሁለንተናዊ ጥያቄዎችን የሚመልስ የፖለቲካ እመርታን ማረጋገጥ እንደሚገባ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ገለፁ።
አቶ አደም ፋራህ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች አመራሮች " የፖለቲካ እመርታ፤ ከዲሞክራሲ መብት ወደ ሀገራዊ ኃላፊነት" በሚል ርዕስ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ገለፃ አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ ቀደም ባሉት ጊዜያት በነበሩ የመንግስት ስርዓቶች የህዝቡ ዲሞክራሲያዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ ያልተረጋገጠበት፣ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎች ምላሽ ያላገኙበት፣ ቁልፍ ፖለቲካዊ ተቃርኖዎችና ችግሮች ያልተፈቱበት እንደነበር አስታውሰዋል። እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የፖለቲካ ሪፎርም ማካሄድ ይገባል ብለዋል።
ይህ የፖለቲካ ሪፎርምም ተቃርኖዎችን ሊያስታርቅ የሚችል የመሀል ፖለቲካን የሚከተል፣ የህዝቦችን ሁለንተናዊ ጥያቄዎች የሚመልስ፣ የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ብልፅግናዋን ሊያረጋግጥ የሚችል መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ይህ ዕውን እንዲሆን ጠንካራ የዲሞክራሲ ስርዓትንና ተቋማትን መገንባት እንዲሁም ይህን መምራት የሚችል አመራር እንደሚያስፈልግ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ መግለፃቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓም

#ኢትዮጵያ በመጪዎቹ ዓመታት #የኢኮኖሚ_እመርታ እንደምታስመዘግብ ተገለፀ።
(ዜና ፓርላማ) ጥቅምት 11ቀን ፣2017 ዓ.ም፤ ሱሉልታ፤ ኢትዮጵያ በመጪዎቹ አራት አስርተ አመታት ከፍተኛ የኢኮኖሚ እመርታ እንደምታስመዘግብ የፕላንና ልማት ሚንስትር ክብርት ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ በሚሰጠው ስልጠና ላይ ገለፁ።
የትንበያ ጥናቱ ከሀገራችን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ባሻገር የውጭ ሀገራት ባለሙያዎችም ያረጋገጡት ነው ብለዋል።
ክብርት ዶ/ር ፍፁም ይህን የተናገሩት "እመርታ ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ተሟላ ብልፅግና" በሚል ርዕስ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽህፈት ቤቶች አመራሮች እየተሰጠ ባለው ሥልጠና ላይ ባቀረቡት ገለፃ ነው።
ሀገራት ባላቸው የነፍስ ወከፍ ገቢ፣ ከሚያመርቱት ምርትና ከሚጠቀሙት ቴክኖሎጂ አንፃር ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ተብለው በሶስት እንደሚከፈሉ አብራርተዋል።
ክብርት ዶ/ር ፍፁም ሀገራችን አሁን ላይ በአፍሪካ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ካስመዘገቡ ሀገራት በ5ኛ ደረጃ፣ ከሰሃራ በታች ካሉት ሀገራት በ3ኛ እና ከምስራቅ አፍሪካ ደግም ቀዳሚውን ደረጃ መያዟን አስገንዝበዋል።
በአለም ባንክ በተደረጉ ጥናቶች ኢትዮጵያ በ2021 እና በ2022 ዓ.ም. በአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ዕድገት ከሚያስመዘግቡ ሀገራት 2ኛ ደረጃን እንደምትይዝ መጠቆሙን አብራርተዋል።
ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሁን ላይ ኢትዮጵያ ካላት የተፈጥሮ ሀብት፣ የሰው ሀይል፣ ይሄንን ማስፈፀም የሚችል መንግስት አኳያ ህልሟን እውን የማታደርግበት አንዳች ምክንያት እንደማይኖርም ነው ያስረዱት።
ስልጠናው ዛሬም #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ለ5ኛ ቀን ቀጥሏል።

#የኢኮኖሚ_ሪፎርሙ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን የምክር ቤቱ ድጋፍ ከፍተኛ መሆን እንዳለበት ተገለፀ::
በኢትዮጵያ የተጀመረው የኢኮኖሚ ሪፎርም የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን የምክር ቤቱ ድጋፍ ከፍተኛ መሆን እንዳለበት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር ክቡር #ካሣሁን_ጎፌ (ዶ/ር) #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ በሚሰጠው ስልጠና ላይ ገለጹ።
ክቡር #ካሣሁን (ዶ/ር) የኢኮኖሚ አምርታ ለማምጣት ሰፊ ሥራዎች በመንግሥት እየተሠሩ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ይህንንም ከዳር እንዲደርስ ምክር ቤቱ በሕግ አወጣጥ፣ በክትትልና ቁጥጥር፣ ፖሊሲዎች እንዲወጡና ተፈፃሚ እንዲሆኑ ድጋፍ በማድረግ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል ።

ክቡር ዶ/ር ካሣሁን ጎፌ ይህን የገለፁት "እመርታ ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ተሟላ ብልፅግና" በሚል ርዕስ የፕላንና ልማት ሚንስትር በሆኑት በክብርት #ፍፁም_አሰፋ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች አመራሮች የቀረበ ገለጻን አስመልክቶ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ ከተሳታፊዎች ለቀረቡት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት መድረክ ላይ ነው።
ክቡር ዶ/ር ካሣሁን ከኢኮኖሚ ዕድገቱ፣ ከዋጋ ግሽበትና ከኑሮ ውድነት እንዲሁም ከንግድ ሥርዓቱ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ሲሰጡ ከለውጥ ወዲህ ባሉት ስድስት አመታት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ማሳየቷ ጥርጥር የሌለው፣ የሚታይና የሚጨበጥ መሆኑን አስገንዝበዋል ።
ይህን የኢኮኖሚ ዕድገት የአለም ባንክና የገንዘብ ተቋማት ሁሉ የመሰከሩለት ነው ያሉት ክቡር ዶ/ር ካሣሁን፤ የዕድገቱ መነሻዎች የለውጡ መንግሥት ያሳየው ቁርጠኝነት እና የፖሊሲ ለውጦች መሆናቸውን በዋናነት ጠቅሰዋል።
አያይዘውም አሁን ላይ የተጀመሩ የኢኮኖሚ፣ የንግድ፣ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት በተለይ በስንዴ፣ በሩዝና ሌሎች ምርቶች ከፍተኛ የማምረት አቅም፣ የመደበኛና ትይዩ ንግድ ላይ የነበረውን ሰፊ ልዩነት በማጥበብ እና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያዎች በመንግሥት ማድረግ በመቻሉ በአጭር ጊዜ በሀገራችን ኢኮኖሚ ላይ እያሳዩት ያለው ውጤት እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በ2025 ዓ.ም. ኢትዮጵያ በዓለም ኢኮኖሚያቸው በከፍተኛ ደረጃ ካደጉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ትገባለች፤ ከአፍሪካ ደግሞ በቀዳሚነት ተርታ ትሰለፋለች ሲሉ አብራርተዋል።
የኢኮኖሚ ዕድገቱ እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም ዜጎች የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ተፅእኖ እንዳለባቸው ክቡር ዶ/ር ካሣሁን ጠቁመው፤ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ደሞዝ ተከፋይ ለሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች ያለውን ጫና በመረዳት የደመወዝ ጭማሪ በማድረግ እና በሌሎች ልዩ ልዩ ድጎማዎች እንዲሁም እንደአጠቃላይ የሕዝብን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ምርትን በከፍተኛ ደረጃ በማምረት የገበያውን ሁኔታ በማስተካከል ኑሮን ለማቃለል መንግሥት እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
በቀጣይም መንግሥት ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ዜጎች በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ እየቀየሰ እንደሚሰራም ነው የገለፁት።
ከንግድ ሥርዓቱ ጋር በተያያዘ በርካታ ማነቆዎች መኖራቸውን ጠቁመው፤ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት መንግሥት ነፃ የንግድ ቀጠናን ጨምሮ በርካታ ማሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑንም ክቡር ዶ/ር ካሣሁን አመላክተዋል።

የዓለምን ነባራዊ ሁኔታዎች እና ጫናዎችን በመረዳት #የውጭ_ግንኙነት_እምርታ ማምጣት የግድ አንደሚል ተገለጸ።
የዓለምን ነባራዊ ሁኔታዎችና ጫናዎችን በመረዳት #የኢትዮጵያን_የውጭ_ግንኙነት_እምርታ ማምጣት የግድ አንደሚል ተገለፀ።
የዓለምን እጅግ ውስብስብ ሁኔታና የሁኔታዎችን በፍጥነት መለዋወጥ በመረዳት ሀገሪቷ የውጭ ግንኙነት ሥራዎቿን ማጠናከር እንዳለባት በአፅንዖት ተገልጿል።
ይህ የተገለፀው "የውጭ ግንኙነት እምርታ፤ ከገፅታ ግንባታ ወደ ተፅእኖ ፈጣሪነት" በሚል ርዕስ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም #ለሕዝብ_ተወካዮች እና #ለፌዴሬሽን_ምክር_ቤት ጽሕፈት ቤቶች አመራሮች ለ6ኛ ቀን እየተሰጠ ባለው ሥልጠና በክቡር #ፕሬዝዳንት_አምባሳደር_ታዬ_አጽቀ_ሥላሴ እና #በቀድሞ_ጠቅላይ_ሚንስትር ክቡር አቶ #ኃይለማሪያም_ደሳለኝ በቀረበ ገለፃ ነው።

አሁን ላይ በዓለም በተፈጠረው ዘርፈ ብዙ የእርስ በርስ ትስስር፣ የተፈጥሮ ሀብትን በከፍተኛ ደረጃ መጠቀም እና ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ዕድገትና ጥቅም ላይ መዋል ዓለም በፉክክርና እና በውጥረት ላይ እንድትጠመድ ማድረጉም ተመላክቷል።
በቅርቡ #በራሺያና #በዩክሬን መካከል በተፈጠረው ጦርነት ታዳጊ ሀገራት የምግብ ግብአቶችን እና ማዳበሪያን ወደ ሀገራቸው እንዳያስገቡ በማድረጉ የኢኮኖሚ ጫና መፍጠሩ ተገልጿል።
#ኢትዮጵያም በተፈጠሩ ዓለም አቀፍ ጫናዎች ውስጣዊ አቅሟን በማጠናከር በተለይ ስንዴንና ሌሎች የሀገር ውስጥ ምርቶችን በከፍተኛ ደረጃ በማምረት መቋቋም የተቻለ ቢሆንም በቀጣይም በቀጠናው በተለይ በቀይ ባህር አካባቢ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተገቢው መንገድ በመረዳት ከጊዜው ጋር የሚመጥን የራሷን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚኖርባትም ነው #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ የተብራራው።
አሁን ላይ በኢኮኖሚው እና በውጭ ግንኙነት ረገድ የተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኙት እንደ #ቻይና፣ #ሕንድ፣ #ቱርክና ሌሎች ቀደምት ሥልጣኔ ያላቸው ሀገራት መሆኑ ተጠቁሟል።
ከዚህ አኳያ #ኢትዮጵያም_ቀደምት_የስልጣኔ_ሀገር ከመሆኗም ባሻገር #በቅኝ_ያልተገዛች፣ #በኢኮኖሚ_እያደገች የመጣችና #የብሪክስ_ሀገራት አባል መሆን የቻለች፣ #ከአፍሪካ ትልቅ ሕዝብና የመልማት አቅም ያላት፣ በቀጠናው ተቀባይነት ያላትና ተፅእኖ ፈጣሪ የሆነች እንዲሁም ከፍተኛና ጥብቅ ማህበራዊ ትስስር ያላት ሕዝብ ባለቤት እንዲሁም #በአፍሪካ_አንድነት_ጉልህ_ድርሻ ያላት በመሆኗ በዓለም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር የመሆን ዕድሏ ሰፊ መሆኑ ተብራርቷል።
ስለሆነም #ኢትዮጵያ በውስጥ ያሉባትን ትንንሽ አለመግባባቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት በመፍታት #ገጽታዋን_መገንባት እና #የውጭ_ግንኙነት_እመርታዋን_ማረጋገጥ እንደሚኖርባት #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ እየቀረበ ካለው ገለፃ ለመረዳት ተችሏል ።

#ኢትዮጵያ የፀጥታ እና የደህንነት ተቋማትን እምርታ በማረጋገጥ ላይ መሆኗ ተመለከተ::
#ኢትዮጵያ የፀጥታ እና የደህንነት ተቋማትን እምርታ በማምጣት ላይ መሆኗን ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ #ተመስገን_ጥሩነህ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ በሚሰጠው ስልጠና ላይ አመላከቱ።
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ የፀጥታ እና የደህንነት ተቋማትን በመገንባት ረገድ የረጅም ጊዜ ባለ ታሪክ መሆኗንም ገልፀዋል።
የዛሬው የሥልጠና ርዕሰ ጉዳይ "የፀጥታና ደህንነት እመርታ" የሚል ሲሆን በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለኢፌድሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የጽህፈት ቤቶች አመራሮች የሥልጠናው ገለፃ በክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ ቀርቧል።
ክቡር ም/ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ባቀረቡት ገለፃ ሀገራችን የፀጥታና የደህንነት ተቋማትን በመገንባት ረጅም አመታትን ማስቆጠር ብቻ ሳይሆን እነዚህ ተቋማት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ አልፈው እንደ ኮሪያ፣ ኮንጎ እና በሌሎች ሀገራት በመሰማራት ሰላም የማስከበር ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን መወጣት የቻሉ ናቸው ብለዋል።
ተቋማቱ የየራሳቸው ጥንካሬ ቢኖራቸውም የነበረባቸው ክፍተት ሊያርም በሚችል መልኩ አሁን ላይ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ አነሳሽነት ወቅቱን በሚመጥን ደረጃ የሪፎርም ሥራ በመሠራቱ ከፍተኛ አቅም ለመፍጠር ተችሏል ሲሉ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ በሚሰጠው ስልጠና ላይ ተናግረዋል።

#የአመራር_የሥነ_ምግባር_እመርታ በሀገረ መንግሥት ግንባታ ውስጥ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ::
የአመራር መልካም ሥነ-ምግባር እመርታ በሀገረ መንግሥት ግንባታ ውስጥ አስፈላጊ በመሆኑ የአመራሩ ሥነ-ምግባር መላበስ ወሳኝ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክቡር #ጌዲዮን_ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ በሚሰጠው ስልጠና ላይ አሳሰቡ።

የአመራሩ የሥነ-ምግባር ጉድለት የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል በመገንዘብ ተገቢውን ሥራ መሥራት ይገባል ብለዋል።
ክቡር #ዶ/ር_ጌዲዮን "የስነ-ምግባራዊ እመርታ፤ ከሞራል ብልሹነት ወደ ግብረገባዊ አርኣያነት" በሚል የሥልጠና ርዕስ ላይ ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የጽህፈት ቤቶች አመራሮች ገለፃ አቅርበዋል።
ክቡር ሚንስትሩ ሰለ #ሥነ-ምግባር፣ #ግብረገብ ፣ #ሞራል፣ #ዲሲፒሊን ልዩነትን እና አንድነትን በተመለከተ ፍልስፍናዊ ዳራዎችንና አብነቶችን በመጥቀስ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ በሚሰጠው ስልጠና ላይ አብራርተዋል።
የሥነ-ምግባር ዋነኛ መገለጫዎችን በዝርዝር ያነሱት ክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ሥነ-ምግባር #በግለሰብ፣ #በቤተሰብ፣ #በቡድን፣ #በተቋም ደረጃ እንደሚገለፅ ጠቁመዋል።
በተቃራኒው የአመራሩ የሥነ-ምግባር ብልሹነት #የግል_ጥቅምን_ብቻ_መመልከትን፣ #በዘር_መከፋፈልንና_ፅንፈኝነትን፣ #ሙስናንና_ብልሹ_አሰራርን የሚያስፋፋ ከሆነ እና የመልካም አስተዳደር እጦት የሚኖር ከሆነ #በሕዝብና_በመንግሥት_መካከል_አሉታዊ_ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት እንደሚሆን አስገንዝበዋል።
ለዚህም እንደ ሊባኖስ ያሉ ሀገሮች ከውጭ ሀገሮች ጣልቃገብነት ይልቅ በሀገራቸው የተንሰራፋው ሙስናና በስልጣንን አለ አግባብ መጠቀም 80 በመቶ የሚሆነውን ሕዝብ ለከፋ ድህነት እና ሀገሪቱን ለአደጋ ማጋለጡን በአብነት አንስተዋል። በመሆኑም በአመራሩ ሥነ-ምግባር ላይ ብዙ መሥራት ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም ክቡር ሚንስትር #ጌዲዮን_ጢሞቲዎስ ኢ- ሥነምግባራዊ በሆኑ መንገዶች የሚገኝ ጥቅምም ሆነ ማንኛውም ነገር ዘላቂነት እንደሌለው አስገንዝበው አመራሩ #መልካም_ሥነ-ምግባርን_በመላበስ እና #መርህን_በመከተል ሕዝቡንና ሀገሩን በማገልገል ኢትዮጵያን የማበልጸግ አደራ አለበት ብለዋል።
#በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ዛሬም ለ7ኛ ቀን ቀጥሏል።

"ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመታገል ረገድ የምክር ቤት አባላት ሚና ከፍተኛ ነው"
---- የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ----
የሀገራችንን ህልም እውን ለማድረግ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመታገል ረገድ የምክር ቤት አባላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ በሚሰጠው ስልጠና ላይ አሳሰቡ።

የምክር ቤት አባላት በሀገራችን የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እንዳይቀለበስ እና ዳር እንዲደርስ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ከመታገል ባሻገር በዕውቀትና በሥነ-ምግባር የታነፀ ዜጋ በማፍራት ለሀገራቸው ብልፅግና አሻራቸውን እንዲያስቀምጡም ጥሪ አቅርበዋል።
የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ይህን ያሉት "የሥነ-ምግባራዊ እመርታ፤ ከሞራል ብልሹነት ወደ ግብረገባዊ አርኣያነት" እና "ሰብአዊ ዕመርታ" በሚሉ ርዕሶች ለኢፌድሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የጽህፈት ቤቶች አመራሮች በተሰጠው ሥልጠና ዙሪያ ከሠልጣኞች ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ነው።
የተከበሩ አፈ-ጉባኤ ለለውጡ መምጣት ገፊ ከሆኑት ምክንያቶች ውስጥ የሥነ-ምግባርና ብልሹ አሰራሮችን ተከትለው የመጡ የፍትሕ፣ የፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ችግሮች እንዲሁም የመልካም አስተዳደር እጦት ተጠቃሽ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ከለውጡ በፊት የልማት ባንክን እና የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶ ለሙስናና ምዝበራ ተጋልጠው እንደነበረ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ በሚሰጠው ስልጠና ላይ አስታውሰዋል።
አሁን ላይ መንግስት እነዚህን ተቋማት መልሶ በማደራጀት ከኪሳራ እየታደጋቸው መሆኑንም ነው የተናገሩት። ይህ ሲባል ግን በለውጡ መንግሥት ምንም አይነት የሥነ-ምግባር እና የሙስና ችግር የለም ማለት እንዳልሆነ እና አልፎ አልፎ በአንዳንድ ግለሰቦች፣ በውስን አመራሮችና በተቋማት የሚታዩ ትንንሽ ችግሮች የሉም ለማለት አይቻልም ብለዋል።
ይሁን እንጂ እዚህም እዛም የሚታዩ ትንንሽ ችግሮች ስጋት እንዳይሆኑ የምክር ቤት አባላት በሚያደርጉት የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች ብልሹ አሠራሮች እንዲስተካከሉ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።
"እኛም የምክር ቤት አባላት" አሉ የተከበሩ አፈ-ጉባኤ ሙስናንና ኢፍትሐዊ አሠራርን ለመታገል መንግሥት ቁርጠኛ በመሆኑ እንደ አባልና እንደ አመራር በቁርጠኝነት ልንታገል ይገባል ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል ።
ስለዚህም ጥቃቅን ችግርችም ቢሆኑ በእንጭጭነታቸው መቀጨት እንዳለባቸው መንግሥት ስለሚያምንና ቁርጠኛም በመሆኑ በሺህ የሚቆጠሩ ኃላፊዎች ላይ እርምጃ የመውሰድ፣ የሀብት ምዝገባ እና ሙስናን የመከላከል ስትራቴጂ ተቀርፆ ወደ ሥራ መገባቱንም ነው በምላሻቸው ያስገነዘቡት።
በመጨረሻም የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ይህ የመንግሥት ዕቅድ እንዲሳካ የምክር ቤት አባላት በሕግ ማዕቀፍ፣ በክትትልና ቁጥጥር ሥራቸው ውስጥ በማካተትና በትኩረት በመስራት ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ በሚሰጠው ስልጠና ላይ አሳስበዋል።

ሚዲያዎች ኢትዮጵያዊያንን አንድ በሚያደርጉ ትርክቶች ላይ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ ይገባል ተባለ፡፡
*********************
“የሚዲያ ሚና ለትርክትና ሀገረ መንግሥት ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዘጋጅነት ለሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና ዛሬ ጥቅምት 18/2017 ዓ/ም #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥተጀምራል፡፡
"ሚዲያ ለብሔራዊ ትርክትና ሀገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል ርዕስ ላይ ገለጻ ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስተሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሚዲያዎች ኢትዮጵያዊያንን አንድ በሚያደርጉን ትርክቶች ላይ ትኩረት አድርገው መሥራት እንደሚጠበቅባቸውና ሃገር የሚገነባው በአዎንታዊ ትርክቶች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሥራ ትርክትን እንደሚቀይር የተናገሩት አማካሪ ሚኒስትሩ ባዶ ትርክት እንደማይጸናና ተግባራዊ ሥራ ሲሰራ ትርክቶች ይለወጣሉ ብለዋል። ትላንት የነበረው የአባይ ውሃ ዛሬ ህዳሴ ግድብን ሰርተን ስናጠናቅቅ ትርክቱ ተቀይሯል በማለት ሥራ ተግባርን እንደሚቀር አመላክተዋል፡፡
ትርክቶች አካታች መሆን እንዳለባቸው ፣ልሂቃን የሚገቡ ትርክቶች መቃናት እንዳለባቸው ያነሱት አማካሪ ሚኒስትሩ ትርክት ለነገ ሲባል የትላንቱን የሚተወውን ትተን፣ የዛሬንም ይቅር ብለን ነገን የምንገነባበት ሊሆን ይገባል ብለዋል በገለፃቸው፡፡
ትርክት የአብሮነት ታሪካዊ መሰረት እንደሆነ፣ ሰዎች ከየት ተነስተው እና ወደየት እንደሚሄዱ እና የት እንደሚደርሱ የሚመለከቱበት መሆኑንም ዲያቆን ዳንኤል አክለዋል፡፡
ለመገናኛ ብዙሃን "ሚዲያ ለብሔራዊ ትክርክትና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ስልጠና ለሶስት ቀናት #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ይቀጥላል፡፡

የገንዘብ ሚንስቴር #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ
#የገንዘብ_ሚንስቴር አመራሮች እና ባለሙያዎች በተቀናጀ የሪፖርት አፃፃፍና አቀራረብ፣ ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ሳይንሳዊ እና ችግር ፈች ምክር እና አስተያየት መስጠት የሚያስችል ፣ በተቋም ግንባታ እና ማጠናከሪያ እንዲሁም በለውጥ አመራር እና አስተዳደር ዙሪያ የአመራር ልማት ፕሮግራም ላይ እየተሳተፉ ነው።

የማኅበረሰብ ሚዲያዉ ብሔራዊ ጥቅሞችን ማስገንዘብ እና የወል ትርክትን ማስረጽ ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባዉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ በሰጠው ስልጠና ላይ አስገነዘበ፡፡
************************
የማኅበረሰብ ሚዲያዉ አካባቢያዊና ሀገራዊ አጀንዳዎችን በማስተሳሰር ብሔራዊ ጥቅሞችን በማስገንዘብ እና የወል ትርክትን በማስረጽ ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባዉ የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስገንዝቧል፡፡
አገልግሎቱ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ጋር በመተባበር ለተከታታይ ዐራት ቀናት #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የሰጠዉ ሥልጠና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ በሥልጠናዉ ማብቂያ ላይ በሰጡት ማጠቃለያ የማኅበረሰብ ሚዲያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞችን ተገንዝቦ በማስገንዘብ፤ ከማኅበረሰቡ እሴቶች እና ፍላጎቶች ላይ ተመሥርቶ የወል ትርክትን በማስረጽና አካባቢያዊ ተሞክሮዎችን በማካፈል የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው የማህበረሰብ ሚዲያዎች አካባቢያ ተልዕኮዎቻቸውን ከሀገራዊ አቅጣጫዎችና ግቦች ጋር በማስተሳሰር በሀገረ መንግስት ግንባታው ሂደት የበኩላቸውን ሚና መጫወት እንዳለባቸው #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ በተሰጠው ስልጠና ላይ አሳስበዋል፡፡
የማኅበረሰብ ሚዲያ መሠረታዊ ተልእኮ አካባቢያዊ የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ልምዶችን፣ ጥያቄዎችን እና ጸጋዎችን በማጉላት በሀገር ደረጃ ጭምር እንዲደመጡ እና ትኩረት እንዲሰጣቸው ማድረግ በውጤቱም የጋራ ሀገር እና ብሔራዊ ትርክት መገንባት እንደኾነም አቶ ከበደ

በመጪው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ ለመገንባት የተቀናጀ የኮሚኒኬሽን ሥራ ያስፈልጋል-ክቡር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ !
ከወራት በኋላ በአዲስ አበባ በሚካሄደው 38ኛው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ ለመገንባት የተቀናጀ የኮሚኒኬሽን ሥራ እንደሚያስፈልግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ በሚሰጠው ስልጠና ላይ ገልፀዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን የገለፁት በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለሚሳተፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነባር ዲፕሎማቶችና በጎ ፍቃደኛ ካዴቶች #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ተገኝተው በውጤታማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ላይ ያተኮረ ስልጠና በሰጡበት ወቅት ነው።
በስልጠናው የተቀናጀ፣ የተደራጀ፣ ስትራቴጅክ እና አጀንዳ ሰጪ የኮሙኒኬሽን ስልትን በመከተል ውጤታማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን እንዲኖር ሁሉም ዜጎች በብሄራዊ ስሜትና አገራዊ ሀላፊነት እንዲሰሩ ሚኒስትር ዴኤታው አበክረው ተናግረዋል።
በመጪው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ኢትዮጵያን በሚገባ ለማስተዋወቅ ምቹ አጋጣሚ መሆኑን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታው ሰልጣኞቹ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በተገቢው በመረዳት በሁሉም ዘርፍ እየታዩ ያሉ እምርታዎችን ለእንግዶቹ በማስገንዘብ አገራዊ ሀላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል።