African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የምክር ቤት አባላት የሀገር ህልም እንዲሳካ ለማስቻል ከፍተኛ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል-#አቶ_አደም_ፋራህ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ ህልም እንዲሳካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ በመገኘት ገለፁ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች አመራሮች #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት ÷የምክር ቤት አባላት ካለባቸው ሕዝባዊ ኃላፊነት አኳያ የሀገር ህልም እንዲሳካ ከፍተኛ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እንዲሠሩ ያስፈልጋል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
ኢትዮጵያ ወደ ተሻለ ከፍታ የሚያደርሳትን እና ለትውልድ የሚሻገር ህልም ተልማለች፤ ይህ ህልም እውን ይሆን ዘንድም ምቹ ነባራዊ ሁኔታዎች አሏት ማለታቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
“ሀገሪቱ ያላት እምቅ የተፈጥሮ ሀብት፣ ከዓላማው ጎን የሚሰለፍ ሕዝብ እንዲሁም የተገነቡ ተቋማት የሀገራችንን ህልም ዕውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች ከሚባሉት ውስጥ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው” ብለዋል፡፡