አሁን ላይ በዓለም በተፈጠረው ዘርፈ ብዙ የእርስ በርስ ትስስር፣ የተፈጥሮ ሀብትን በከፍተኛ ደረጃ መጠቀም እና ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ዕድገትና ጥቅም ላይ መዋል ዓለም በፉክክርና እና በውጥረት ላይ እንድትጠመድ ማድረጉም ተመላክቷል።
በቅርቡ #በራሺያና #በዩክሬን መካከል በተፈጠረው ጦርነት ታዳጊ ሀገራት የምግብ ግብአቶችን እና ማዳበሪያን ወደ ሀገራቸው እንዳያስገቡ በማድረጉ የኢኮኖሚ ጫና መፍጠሩ ተገልጿል።
#ኢትዮጵያም በተፈጠሩ ዓለም አቀፍ ጫናዎች ውስጣዊ አቅሟን በማጠናከር በተለይ ስንዴንና ሌሎች የሀገር ውስጥ ምርቶችን በከፍተኛ ደረጃ በማምረት መቋቋም የተቻለ ቢሆንም በቀጣይም በቀጠናው በተለይ በቀይ ባህር አካባቢ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተገቢው መንገድ በመረዳት ከጊዜው ጋር የሚመጥን የራሷን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚኖርባትም ነው #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ የተብራራው።
አሁን ላይ በኢኮኖሚው እና በውጭ ግንኙነት ረገድ የተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኙት እንደ #ቻይና፣ #ሕንድ፣ #ቱርክና ሌሎች ቀደምት ሥልጣኔ ያላቸው ሀገራት መሆኑ ተጠቁሟል።
ከዚህ አኳያ #ኢትዮጵያም_ቀደምት_የስልጣኔ_ሀገር ከመሆኗም ባሻገር #በቅኝ_ያልተገዛች፣ #በኢኮኖሚ_እያደገች የመጣችና #የብሪክስ_ሀገራት አባል መሆን የቻለች፣ #ከአፍሪካ ትልቅ ሕዝብና የመልማት አቅም ያላት፣ በቀጠናው ተቀባይነት ያላትና ተፅእኖ ፈጣሪ የሆነች እንዲሁም ከፍተኛና ጥብቅ ማህበራዊ ትስስር ያላት ሕዝብ ባለቤት እንዲሁም #በአፍሪካ_አንድነት_ጉልህ_ድርሻ ያላት በመሆኗ በዓለም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር የመሆን ዕድሏ ሰፊ መሆኑ ተብራርቷል።
ስለሆነም #ኢትዮጵያ በውስጥ ያሉባትን ትንንሽ አለመግባባቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት በመፍታት #ገጽታዋን_መገንባት እና #የውጭ_ግንኙነት_እመርታዋን_ማረጋገጥ እንደሚኖርባት #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ እየቀረበ ካለው ገለፃ ለመረዳት ተችሏል ።
(በኃይለሚካኤል አረጋኸኝ)