የአመራሩ የሥነ-ምግባር ጉድለት የሀገርን ህልውና አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል በመገንዘብ ተገቢውን ሥራ መሥራት ይገባል ብለዋል።
ክቡር #ዶ/ር_ጌዲዮን "የስነ-ምግባራዊ እመርታ፤ ከሞራል ብልሹነት ወደ ግብረገባዊ አርኣያነት" በሚል የሥልጠና ርዕስ ላይ ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የጽህፈት ቤቶች አመራሮች ገለፃ አቅርበዋል።
ክቡር ሚንስትሩ ሰለ #ሥነ-ምግባር፣ #ግብረገብ ፣ #ሞራል፣ #ዲሲፒሊን ልዩነትን እና አንድነትን በተመለከተ ፍልስፍናዊ ዳራዎችንና አብነቶችን በመጥቀስ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ በሚሰጠው ስልጠና ላይ አብራርተዋል።
የሥነ-ምግባር ዋነኛ መገለጫዎችን በዝርዝር ያነሱት ክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ሥነ-ምግባር #በግለሰብ፣ #በቤተሰብ፣ #በቡድን፣ #በተቋም ደረጃ እንደሚገለፅ ጠቁመዋል።
በተቃራኒው የአመራሩ የሥነ-ምግባር ብልሹነት #የግል_ጥቅምን_ብቻ_መመልከትን፣ #በዘር_መከፋፈልንና_ፅንፈኝነትን፣ #ሙስናንና_ብልሹ_አሰራርን የሚያስፋፋ ከሆነ እና የመልካም አስተዳደር እጦት የሚኖር ከሆነ #በሕዝብና_በመንግሥት_መካከል_አሉታዊ_ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት እንደሚሆን አስገንዝበዋል።
ለዚህም እንደ ሊባኖስ ያሉ ሀገሮች ከውጭ ሀገሮች ጣልቃገብነት ይልቅ በሀገራቸው የተንሰራፋው ሙስናና በስልጣንን አለ አግባብ መጠቀም 80 በመቶ የሚሆነውን ሕዝብ ለከፋ ድህነት እና ሀገሪቱን ለአደጋ ማጋለጡን በአብነት አንስተዋል። በመሆኑም በአመራሩ ሥነ-ምግባር ላይ ብዙ መሥራት ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም ክቡር ሚንስትር #ጌዲዮን_ጢሞቲዎስ ኢ- ሥነምግባራዊ በሆኑ መንገዶች የሚገኝ ጥቅምም ሆነ ማንኛውም ነገር ዘላቂነት እንደሌለው አስገንዝበው አመራሩ #መልካም_ሥነ-ምግባርን_በመላበስ እና #መርህን_በመከተል ሕዝቡንና ሀገሩን በማገልገል ኢትዮጵያን የማበልጸግ አደራ አለበት ብለዋል።
#በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ዛሬም ለ7ኛ ቀን ቀጥሏል።

ከልዑካን ቡድኑ አባላት መካክል የሻላ ዌልነስ ሴንተር መስራች #ዶ/ር_ዳዊት_መንግስቱ በጤና እና በውጤታማ አመራር መካከል ያለውን ግንኙነት አጽንዖት በመስጠት "በደንብ መስራት የሚችሉ ጤናማ መሪዎች ያስፈልጉናል ለዚህም በመሪዎች አቅም ግንባታ ላይ ከሚሰራው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በትብብር መስራት ወሳኝ ነው።" ብለዋል።
የዛሬው ጉብኝት አፍሌክስ እና ፖላር ፕላስ ኤክሰለንስ ሃብ ከቀናት በፊት አጋርነትን ለመፍጠር በማሰብ ያደረጉትን የመጀመሪያ ውይይት ተከትሎ የተካሄደ ሲሆን ትብብሩ ከሁለቱ ተቋማት እና አጋሮቻቸው የተወጣጡ ሃብት እና እውቀትን በማዋሃድ የአመራር አቅምን የሚያጎለብቱ ስራዎችን ለመስራት ያለመ ነው።
አፍሌክስ የትብብር አድማሱን በማስፋት ከመንግስት፣ ከግሉ ዘርፍ፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርቶች እንዲሁም ከአለም አቀፍ እና አህጉራዊ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ይታወቃል።