African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ #RIGHT_TO_PLAY ለተባለ ዓለምአቀፍ ድርጅት ሲሰጥ የነበረው የአመራር ልማት የአቅም ግንባታ መርሐ-ግብር ተጠናቀቀ።

የአቅም ግንባታ መርሐ-ግብሩ ለሁለት ቀናት የቆየ ሲሆን Concepts, Principles & Components of RBM, Results-Based Monitoring and Evaluation, Performance Indicators, Performance Management Framework እና Risks and Assumptions በሚሉ ዋና ዋና ርዕሶች ላይ ያተኮረ ነበር።

ስልጠናው በዘርፉ ሰፊ ልምድ እና አቅም ባላቸው የአመራር ልማት ባለሙያ ጥላዬ ካሳዬ (ዶ/ር) የተሰጠ ሲሆን ንድፈ ሀሳብን ከተግባራዊ ልምምድ ጋር ያጣመረ በመሆኑ ሰልጣኞች ችግር ፈች የሆነ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዳገኙ ተገልጿል።

#RIGHT_TO_PLAY የተሰኘው ዓለምአቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እ.ኤ.አ በ2000 የተቋቋመ ሲሆን ዋና መቀመጫውን #በካናዳ_ቶሮንቶ አድርጎ በአስራ አምስት ሀገራት ላይ ከህጻናት መብትና ትምህርት ጋር በተገናኘ የሚሰራ ተቋም ነው።