African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
በሱሉልታ የአመራር ማዕከል ውስጥ ከሚገኙ የቀድሞ ህንጻዎች መካከል የአስተዳደር ህንጻውን በማደስ ለቢሮ አገልግሎት እንዲውል ስራ መጀመሩ ተገለጸ።
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ #ለውጥ_Reform #ማስፋት_Scaling_Up እና #ሽግግር_Transformation ስራዎች መካከል አንዱ ሱሉልታ ውስጥ የሚገኙትን የቀድሞ ህንጻዎች በአዲስ መልክ በማደስ ወደ ስራ ማስገባት መሆኑም ተጠቅሷል።
ለአስተዳደር ቢሮው እድሳት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን (ERA) ወጭውን የሚሸፍን ሲሆን ህንጻውን ለማደስ ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ECC) ውል መግባቱንና ስራ መጀመሩ ተገልጿል።
የአስተዳደር ቢሮው እድሳት ከአምስት እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የተገለጸ ሲሆን; አጠቃላይ ወጭውም ወደ 200 ሚሊየን ብር እንደሚሆን ተነግሯል።
የህንጻው እድሳት እንደተጠናቀቀም የአካዳሚው ሰራተኞች ወደ አዲሱ ህንጻ ተዛውረው ስራ እንደሚጀምሩ የተጠቀሰ ሲሆን፤ ይህም አካዳሚው ለቢሮ ኪራይ የሚያወጣውን ገንዘብ ከማስቀረቱም በላይ የአመራር ልማት ስራውን በቅርበት ሆኖ ለማገዝ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።