Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
86K subscribers
2.75K photos
99 videos
2 files
336 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጎርጎራ ሪዞርትን በኢትዮጵያ ስካላይት ሆቴል ስር የማስተዳደር ኃላፊነትን ዛሬ በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በተደረገ የስምምነት ስነስርዐት ተረከበ። በስነ ስርዐቱ ላይ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አረጋ ከበደ፣ ከፍተኛ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ሥራ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ እና ሌሎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት የተገነቡትን ሀላላ ኬላ ሪዞርት፣ የወንጪ ኢኮ ሎጅ እንዲሁም የጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅን የማስተዳደር ኃላፊነትን በቅርቡ ወስዶ ወደ ስራ በመግባት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ኢንደስትሪ ዕድገት የራሱን ድርሻ ለመወጣት ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያስካይላይትሆቴል #ገበታለሀገር
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የተከሰተው ድንገተኛ የመሬት ናዳ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ባደረሰው ከፍተኛ ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለተጎጂ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ይመኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥገና ክፍል እና አውሮፕላኖች አምራች የሆነው ATR አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ፈጸሙ። በስምምነቱ መሰረት በአፍሪካ ትልቁ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥገና ክፍል በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የATR ስሪት አውሮፕላኖችን የመጠገን አቅሙን የሚያዳብር ይሆናል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
ውድ መንገደኞቻችን
የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እ.ኤ.አ. 21 ጁላይ 2024 ለአየር መንገዳችን በላከው ደብዳቤ እ.ኤ.አ. ከሴፕቴምበር 30 ቀን 2024 ዓ.ም. ጀምሮ አየር መንገዳችን ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን ሁሉንም በረራ ማገዱን አሳውቆናል።
ደብዳቤው ለክልከላ ውሳኔ ያደረሱ ምክንቶችን አልጠቀሰም። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳዩን አስመልክቶ የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝና ጉዳዩም በበጎ መልኩ እልባት እንደሚያገኝ ያለውን ዕምነት ይገልጻል።
በዚሁ አጋጣሚ አየር መንገዱ ተጨማሪ መረጃዎች እንደተገኙ ለውድ ደንበኞቹ እንደሚያሳውቅ ለመግለፅ ይወዳል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አልያንስ አባል
ምርጫዎን ያማካለ ልዩ መስተንግዶ ከደማቅ ፈገግታ ጋር ማቅረብ የአገልግሎታችን ስኬት ምንጭ ነው!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አዲስ በረራ በጋምቤላ እና አሶሳ መካከል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በጋምቤላና በአሶሳ መካከል ቀጥታ በረራ የጀመረ መሆኑን ለክቡራን መንገደኞቹ በደስታ ይገልጻል። ጉዞዎን ያቅዱ በተቀላጠፈ አገልግሎታችን በምቾት ይጓዙ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፓሪስ የ2024 ኦሎምፒክ ሀገራችን ኢትዮጵያን ወክሎ ለሚሳተፈው የኦሎምፒክ ቡድን መልካም ምኞቱን ይገልፃል። ድል ለኢትዮጵያ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓሪስ2024
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ20% ቅናሽ ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ በሚደረጉ በረራዎች ላይ አድርጓል። ልብ ይበሉ ፤ ይህ ልዩ ቅናሽ እስከ ነሐሴ 25 2016 ድረስ የሚቆይ ሲሆን ጉዞዎን ከጳጉሜ 1 ፣ 2016 እስከ መስከረም 2 ፣ 2017 ዓ.ም ያድርጉ። ይፍጠኑ ይህ አስደናቂ ቅናሽ እንዳያመልጥዎ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከአዲስ አበባ መቐለ እንዲሁም ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ የምሽት በረራ የሚጀምር መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቹ ይገልፃል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ከጉዞዎ መጀመሪያ እስከ መዳረሻዎ ድረስ እየተንከባከብን ካሰቡበት እናደርስዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ወዳሰቡት መዳረሻ ልናደርስዎ ሁልጊዜ ዝግጁ ነን!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በላቀ ተከታታይ የስኬት ጎዳና!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ስኬት
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ! ምድረ ቀደምት!
በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ የሚረከበው የኤርባስ A350-1000 የመጨረሻ የቀለም ቅብ እና መለያ ሲደረግለት የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል እነሆ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ኢትዮጵያ #ምድረቀደምት
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን @Zelalem Alemenew ናቸው፤ እናመሰግናለን! እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበርሩ ያነሷቸውን ምስሎች ይላኩልን፤ መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ልዩ ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ እና ልብ የሚያሞቅ ፈገግታ በጉዞዎ ሁሉ ይጠብቅዎታል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአሜሪካ የትራንስፖርት ደህንነት አስተዳደር (TSA) የተቀላጠፈ የኤርፖርት ውስጥ የደህንነት ፍተሻ (TSA PreCheck®) ፕሮግራም አባል ሆነ። የዚህ ፕሮግራም አባልነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሚበርባቸው በአሜሪካ ከሚገኙ ኤርፖርቶች የሚነሱ መንገደኞች የተቀላጠፈ፣ ይበልጥ ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የቅድመ በረራ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። ለበለጠ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።
https://rb.gy/59mf4r
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮችና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ተሳትፏቸውን በመቀጠል በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶው አየር መንገድ ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ የአካባቢ ጥበቃን እንደ አንድ ማህበራዊ ሀላፊነት ይዞ እየሰራ መሆኑን አስታውቀው ከችግኝ ተከላ በተጨማሪም ለአካባቢ ምቹ እና ተስማሚ የሆኑ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ በማዋል የራሱን አስተዋፅዖ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል። አዳዲስ እና ዘመናዊ አውሮፕላኖችን የበረራ አገልግሎት ላይ በማዋል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ በአየር መንገዶች በሚደረገው ርብርብ አካል በመሆን የካርበን ልቀትን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንሰውን ዘላቂ የአቪዬሽን ነዳጅ (Sustainable Aviation Fuel) በመጠቀም እንዲሁም ቁሳቁሶችን መልሶ በመጠቀም (Recycling) ለአካባቢ ደህንነት መጠበቅ የራሱን ጉልህ ድርሻ እየተወጣ መሆኑን አስታውሰዋል።


40 ሄክታር በሚሆን ስፍራ ላይ 16 አይነት ሀገር በቀል የሆኑ 50 ሺህ ችግኞች ለመትከል ዕቅድ የተያዘ ሲሆን እስካሁን 27 ሺህ ያህል ችግኞች ተተክለዋል። ። የተቋሙ ሰራተኞች የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡና በቀጣይም የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አረንጓዴአሻራ