Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
84.2K subscribers
2.43K photos
92 videos
2 files
305 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
በቀደሙት ግዜያት ስንከተለው የነበረው “አፍሪካውያንን እርስ በርስ ማስተሳሰር” የተሰኘው መርሀችን ዛሬም በድምቀት ቀጥሎ ለ37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በአፍሪካዋ መዲና አዲስ አበባ የተገኙ 20 የአፍሪካ አገራት መሪዎችን በግዙፉ እና ዘመናዊው የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በክብር ተቀብለን አስተናግደናል። የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በአፍሪካ ከሚገኙ ትላልቅ ሆቴሎች አንዱ ሲሆን በውስጡም 1024 ክፍሎች አሉት። የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል እንደ አህጉራችን አፍሪካ ሁሉ በህብረ ቀለማት አሸብርቆ እንግዶቹን በክብር አስተናግዶ ሸኝቷል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያስካይላይትሆቴል #ፓንአፍሪካዊ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ አየር መንገዶች ማህበር (AFRAA) ጋር በጥምረት ያዘጋጀው 12ኛው የአፍሪካ አየር መንገዶች ማህበር ጉባዔ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል በድምቀት በመካሄድ ላይ ይገኛል። ይህ የሶስት ቀናት ጉባዔ 'የአፍሪካን አቪዬሽን ከማገናኘት ባሻገር' በሚል መሪ ቃል የኢንዱስትሪውን ቁልፍ ተዋናዮች ያሰባሰበ ነው። #12ኛውየአፍሪካአየርመንገዶችማህበር #የአፍሪካንአቪዬሽንከማገናኘትባሻገር #የኢትዮጵያስካይላይትሆቴል #የኢትዮጵያአየርመንገድ