Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
74.8K subscribers
1.87K photos
84 videos
2 files
275 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቻይና ጓንዡ ተጨማሪ ሶስት ሳምንታዊ በረራዎችን በማከል ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ አስር ከፍ እንደሚያደርግ ለመግለፅ ይወዳል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ።#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የብሩንዲ ትልቋ እና የኢኮኖሚ ማዕከል ወደሆነችው ቡጁምቡራ ከተማ የምናደርገው ሳምንታዊ መደበኛ በረራ ላይ ተጨማሪ 4 ሳምንታዊ በረራዎችን በማከል ከ ጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ከተማዋ የሚደረገውን የመንገደኞች በረራ ቁጥር 11 ማድረሳችንን ስንገልፅ በደስታ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከህዳር 15 ቀን 2023 ዓ.ም ጀምሮ ወደ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ ባንጉይ ሶስት ሳምንታዊ የመንገደኞች በረራ አገልግሎት እንደሚጀምር ሲገልጽ በደስታ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሲንጋፖር “ማሪና ቤይ ሳንድስ”በተዘጋጀው የ 2023 የኢስያ ቡና እና ሻይ ኤግዚቢሽን ላይ በመሳተፍ በአለም ተመራጭ እና ልዩ የሆነውን የኢትዮጵያን ቡና አስተዋወቀ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የአቪዬሽን የስልጠና ዘርፎች በትርፍ ሰዓታቸው የሚያስተምሩ ብቁ መምህራንን በጊዜያዊነት ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ፋላጎቱ እና ብቃቱ ያላችሁ ባለሙያዎች በዩኒቨርስቲው ድረገጽ እስከ መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንድታመለክቱ ይጋብዛል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ
(https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies).
መልካም የእረፍት ቀናት ይሁንልዎ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አስደናቂ እና ውብ መልከዓምድር ፤ የብዝሀሕይወት እና የዓለም ቅርሶች መገኛ ኢትዮጵያ!
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይብረሩ! ኢትዮጵያን ይጎብኙ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ምድረቀደምት #ውብኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ለንደን ከተማ ከሚያደርገው 7 ሳምንታዊ በረራ በተጨማሪ ከሕዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ 3 ሳምንታዊ በረራዎችን ወደ ጋትዊክ ኤርፖርት በመጀመር ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን የበረራ አድማስ ማስፋቱን ሲገልፅ በደስታ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
አዲሱን ሳምንት ስንቀበል ወዳሰቡበት የጉዞ መዳረሻዎ ልናደርስዎ ዝግጁ ሆነን ነው፡፡
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ጅቡቲ ተጨማሪ ሶስት ሳምንታዊ የምሽት በረራዎችን በማከል ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ አስራ ሰባት ከፍ እንደሚያደርግ ለመግለፅ ይወዳል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ