አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ወደ_ኢትዮጵያ_ሲመጡ_ከቀረጥ_ነጻ_የግል_መገልገያ.pdf
7.4 MB
ከቀረጥ ነጻ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የተፈቀዱ የግል መገልገያ እቃዎች ዝርዝር

#customs #lawyersamuel #Ethiopia #ህግ #samuelgirma #LegalService #Lawyer
🇪🇹
.
#ተግባር_ብቻ_የስኬት_ቁልፍ_ነው
∬≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡∬
📌 ማንኛውንም ውጤት ማስመዝገብ የሚቻለው በተግባር ብቻ ነው። #አለ_ህግ #Ale_Lawsocieties #Ale_Hig
የፈለግነውን ያህል ማለም፣ እቅድ ማውጣት፣ እራሳችንን ማዘጋጀት፣ ሊከሰቱ የሚችሉ ስህተቶችን መተንተን እና እነሱን ለማስወገድ ዘዴዎችን ማዘጋጀት እንችላለን ነገር ግን እርምጃ ካልወሰድን ወይም ተግባራዊ ካላደረግን ምንም አናገኝም! ምንም አናሳካም !

በተቃራኒው፣ ሳንዘጋጅ ወደ ተግባር ብንጣደፍ እንኳን ስኬታማ የመሆን እድል ይኖረናል! ትንሽ ቢሆንም, ግን እድል ይኖራል!ወደ ተግባር ካልገባ ግን ምንም አታገኝም !

ነገሮችን በጥልቀት ማሠብ እና በጥንቃቄ ማቀድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል ። ነገር ግን ሀሳብና ዕቅድ በተግባር ካልታጀበ ምንም ውጤት አይገኝም ።
🗝 ማንኛውም እቅዶች በውጤቱ ካልተተገበሩ ዋጋ ቢስ ናቸው !

🗝ተግባር ለሁሉም ድሎች ምክንያት ነው!
#መልካም_የተግባርና_የስኬት_ቀን_ይሁንላችሁ !

Via Bereket Bekele page

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
🟢🟡🔴 ክስን ስለማንሳት።።።።
ክስ ስለ ማንሳት ማለት ክስ ሂደት ላይ የነበረ ክስ በተለያዩ ምክንያቶች ክስ ሂደቱ እንዲቋረጥና መዝገቡ ለዘለቄታው ወይም ለጊዜው እንዲዘጋ የሚደረግበት ስርዓት ነው።

ክስ የሚነሳበት ምክንያት /ሁኔታ/ በወ/መ /ስ/ስ /ሕጋችን በአንቀፅ 122 ተደንግጎ ይገኛል።

የዚህ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ (1) እንደሚጠቁመው በድሮው የወ/መ/ ሕግ ቁ.522 (በአሁኑ የወ/ሕግ አንቀፅ 539) ወይም በቀድሞው የወ/መ/ሕግ ቁ.637 (በአሁኑ የወ/ሕግ አንቀፅ 671) መሰረት ከቀረበው ክስ በስተቀር ዓ/ሕጉ በተከሳሹ ላይ ያቀረበውን ማንኛውም ክስ በፍርድ ቤቱ ፈቃድ ከፍርድ በፊት ክሱ በሚሰማበት በማንኛውም ጊዜ ክሱን ለማንሳት ይችላል ማለት ነው።

ይህ ማለት፣
ሀ) ከከባድ የሰው ግድያ እና ከከባድ የወንብድና ተግባር ክሶች ውጭ ሌሎች ክሶች ሊነሱ እንደሚችሉ ፣ ለ) አቃቢ ሕጉ ክሱን ማንሳት የሚችለው በፍ/ቤቱ ፈቃድ መሆኑን ፣ እና ሐ) ክሱን ማንሳት የሚቻለው ከፍርድ በፊት በማንኛም ጊዜ መሆኑን ነው።

የወ/መ/ስ/ስ/ ሕጋችን የሁለቱ ከባድ ወንጀሎች ክስን በተመለከተ ማንሳት የከለከለበት ምክንያት ሁለት ነገሮችን ታሳቢ በማድረግ ሊሆን ይችላል ፡ በአንድ በኩል እንደዚህ የመሳሰሉትን ከባድ ወንጀሎች በህዝብ ላይ ስጋት የሚፈጥሩና ሰላምን የሚነሱ በመሆናቸው በእነዚህ ወንጀሎች የተከሰሱ ሰዎች ወንጀሉን መፈፀማቸው የሚያስረዳ ማስረጃ እስከ ቀረበ ድረስ ጥፋተኛ ሆነው ሊቀጡ እንደሚገባና የዚህ ወንጀል ሰለባ የሆኑ ሰዎችም ሕግ ከለላ የሰጣቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ሲሆን፤
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ተከሳሾች በተከሰሱበት ጉዳይ ቁርጣቸውን ኣውቀው እንዳያርፉ፤ አንዴ ክስ ተነስቶ መዝገብ እየተዘጋ ሌላ ጊዜ እየተንቀሳቀሰ ሰላም እንዳይነሳ ነው።

ከፍርድ ቤት ክስ እና ክርክር የራቀ ሰላም ሂይወት ለሁላችሁ።

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
የዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በፍርድ ቤቶች
*

https://vm.tiktok.com/ZMLQYdo9Y/
ACTION AGAINST HUNGER ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Position:-Gender and Protection Program

Manager-Re-advertisement
📚ትምህርትዓይነትእናደረጃ:-
University Master and or BA degree in social sciences, psychology, 🔴law, social work, international development, or other relevant field from a recognized institution.

🇪🇹 የስራ ቦታ ፡ Wollega- Gimbi, Oromia

🧭የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ ማያዚያ 07 /2014 ዓ.ም


🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://tikusjobs.com/job/gender-and-protection-program-manager-re-advertisement/

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
።።።።። አስፈላጊ አደራ ።።።
አንድ ሰው የራሱ ንብረት በሆኑት ዕቃዎች ላይ የማይታገድ እርግጠኛ አደጋ የሚደርስባቸው በሆነ ጊዜ እነዚህን ዕቃዎች ከቀረበው አደጋ ለማሸሽ ሲል ሌላ ሰው በአደራ ተቀብሎ እንዲያስቀምጥለት የሰጠ እንደሆነ ይህ አድራጎት አስፈሊጊ አደራ የማስቀመጥ ድርጊት ይባላል።
አስፈላጊ የአደራ ማስቀመጥ ጉዳይ ከማናቸውም የአሠራር ሥርዓት ነፃ እንደሆነ የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2802 ንዑስ አንቀፅ 1 የሚደነግግ ሲሆን አንድ ሰው አስፈላጊ አደራ ለሌላ ሰው የሰጠ መሆኑን በማናቸውም አይነት መንገድ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚችል የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2802 ንዑስ አንቀፅ 2 ይደነግጋል፡፡

ሰ/መ/ቁ. 64887 ቅጽ 14 ፤ ፍ/ህ/ቁ. 2800፤ 2802

ማስታወሻ

በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 2800 አስፈላጊ አደራ አለ የሚባለው በንብረት ላይ እርግጠኛ አደጋ የሚደርስ በሆነ ጊዜ እንጂ አስቀማጩ አደጋ ይደርሳል ብሎ ባሰበ ወይም በሰጋ ጊዜ አይደለም። የድንጋጌው ተፈጻሚነት አንድም አደጋው እየደረሰ እያለ ወይም መድረሱ የማይቀር ስለመሆኑ እርግጠኛ የሆነ ሁኔታ ሲከሰት ብቻ ነው።
በሰ/መ/ቁ. 64887 አመልካች በመንገድ ስራ ምክንያት የተከፈለውን ካሳ ወደሚኖርበት ገጠራማ ቦታ ቢወስደው ደህንነቱን ጠብቆ ለማቆየት የማይችል በአንጻሩ ገንዘቡን ለመዝረፍ ሰዎች ሊገድሉት እንደሚችሉ በማስረዳት ሰባ ሺ ብር በአደራ እንዲያስቀምጥለት ለተጠሪ እንደሰጠ በፍሬ ነገር ደረጃ በምስክር እንደተረጋገጠ ተዘግቧል። ፍሬ ነገሩ የአመልካች ከፍ ያለ ስጋት እንጂ የደረሰ አደጋ ሆነ ሊደርስ ያለ እርግጠኛ አደጋ ስለመኖሩ አልተረጋገጠም። ከዚህ አንጻር የችሎቱ የህግ ትርጓሜ በተሳሳተ የፍሬ ነገር መነሻ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ የተሳሳተ ነው።
አብርሃም ዮሐንስ
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
HR6600 እና S3199 ረቂቅ ሕጎች ሕግ ሆነው ከመውጣት እንዲዘገዩ የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለፀ
*********************

የአሜሪካ ኮንግረስ HR6600 እና S3199 ረቂቅ ሕጎች ሕግ ሆነው ከመውጣት እንዲዘገዩ የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱን የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በትዊተር ገጹ አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያውያን ረቂቅ ሕጎቹ እንዳይፀድቅ እያደረጉት ያለው የዲፕሎማሲ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ካውንስሉ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነትና ጫና በመቃወምና ዳያስፖራ ማህበረሰቡን ጭምር በማስተባበር ከፍተኛ የህዝብ ዲፕሎማሲ ስራ በመስራት ላይ ያለ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገ ተቋም ነው።

ETV
የሽያጭ ውልን የተመለከቱ አንዳንድ ነጥቦች ከሰበር ውሳኔ ጋር ተገናዝቦ የቀረበ
በ፡ ሙሉቀን ሰዒድ ሐሰን
በዚህ ጽሑፍ የሽያጭ ውል ምንነት፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት የገዛ ሰው ስላለው መብትና ገዥው ስለሚኖርበት ግዴታ፣ የሽያጭ ውልን መሰረት አድርገው የሚቀርቡ ክርክሮች ይዘታቸው እና የይርጋ ገደባቸው ምን እንደሚመስል እንዲሁም የማይንቀሳቀስ ንብረት የገዛ ሰው ንብረቱን ሊለቅ የሚችልባቸው የሕግ አግባብ ምን ምን እንደሆኑ ከፍትሐብሔር ሕግ እና ከሰበር ውሳኔዎች አንጻር ዳሰሳ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡
መልካም ንባብ!
https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2028-contract-of-sale-in-ethiopia
#ተገጣጣሚ_ቤቶች
ከተማ አስተዳደሩ በስምንት ቢሊዮን ብር ሊያስገነባቸው የነበሩ ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ በፍርድ ቤት ታገደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስምንት ቢሊዮን ብር በጀት ያስጀመረውና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ወርቁ ሠፈር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ሊያከናውነው የነበረው የአምስት ሺሕ ተገጣጣሚ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ሕንፃዎች ግንባታ፣ በፍርድ ቤት ዕግድ እንዲቆም መደረጉ ተገለጸ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በ21.8 ሔክታር መሬት ላይ የተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ለማስጀመር ጥር 4 ቀን 2014 ዓ.ም. መሠረተ ድንጋይ ቢያስቀምጥም፣ መሬቱ የባለቤትነት ጥያቄ ተነስቶበት ፍርድ ቤት ዕግድ በማውጣቱ ግንባታው እንዲቆም መደረጉን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮና የቤቶቹን ግንባታ የሚያካሂደው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታውቀዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምርያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥንፉ ሙጬ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ግንባታው ይፋ ከተደረ በኋላ ኮርፖሬሽኑ 291 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የተገጣጣሚ ሕንፃ አካላት ኮንክሪትና ሌሎች ተያያዥ ምርቶችን ወደ ቦታው አስገብቷል፡፡ በግንባታ ቦታው ላይ አሥር ሚሊዮን ብር የሚያወጣ አፈር ጠረጋና ምንጣሮ ሥራ መካሄዱንም አስረድተዋል፡፡

ይሁንና የመሬቱ ባለቤትነት ይገባኛል ያለ ግለሰብ ጥያቄ በማንሳቱ፣ ኮርፖሬሽኑ ሥራ በጀመረ በቀናት ውስጥ ዕግድ ወጥቶበታል፡፡ ኮርፖሬሽኑ እግዱ ቢወጣም የግንባታ ሥራውን እንደቀጠለ ያስረዱት አቶ ጥንፉ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ዕግድ ከመጣ በኋላ ግን መሬቱ ላይ ያለው ሥራ እንዲቆም መደረጉን ተናግረዋል፡፡......... ይቀጥላል....
#አለ_ህግ
#አለ_Share....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
........የቀጠለ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስምንት ቢሊዮን ብር በጀት ያስጀመረውና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ወርቁ ሠፈር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ሊያከናውነው የነበረው የአምስት ሺሕ ተገጣጣሚ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ሕንፃዎች ግንባታ፣ በፍርድ ቤት ዕግድ እንዲቆም መደረጉ ተገለጸ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በ21.8 ሔክታር መሬት ላይ የተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ለማስጀመር ጥር 4 ቀን 2014 ዓ.ም. መሠረተ ድንጋይ ቢያስቀምጥም፣ መሬቱ የባለቤትነት ጥያቄ ተነስቶበት ፍርድ ቤት ዕግድ በማውጣቱ ግንባታው እንዲቆም መደረጉን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮና የቤቶቹን ግንባታ የሚያካሂደው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታውቀዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምርያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥንፉ ሙጬ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ግንባታው ይፋ ከተደረ በኋላ ኮርፖሬሽኑ 291 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የተገጣጣሚ ሕንፃ አካላት ኮንክሪትና ሌሎች ተያያዥ ምርቶችን ወደ ቦታው አስገብቷል፡፡ በግንባታ ቦታው ላይ አሥር ሚሊዮን ብር የሚያወጣ አፈር ጠረጋና ምንጣሮ ሥራ መካሄዱንም አስረድተዋል፡፡

ይሁንና የመሬቱ ባለቤትነት ይገባኛል ያለ ግለሰብ ጥያቄ በማንሳቱ፣ ኮርፖሬሽኑ ሥራ በጀመረ በቀናት ውስጥ ዕግድ ወጥቶበታል፡፡ ኮርፖሬሽኑ እግዱ ቢወጣም የግንባታ ሥራውን እንደቀጠለ ያስረዱት አቶ ጥንፉ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ዕግድ ከመጣ በኋላ ግን መሬቱ ላይ ያለው ሥራ እንዲቆም መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ሊያስገነባቸው ያቀደው ከ90 በላይ ባለ አራትና ዘጠኝ ፎቅ የተገጣጣሚ ቤት ብሎኮች ግንባታቸው የሚያርፍበት መሬት፣ በሕገወጥነት ተይዞ የነበረና ወደ መሬት ባንክ የገባ መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤት ልማት ትግበራና የሥራ ዕድል ፈጠራ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ኪያ በሬቻ (ኢንጂነር)፣ ቢሮው ከከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ መሬቱን በሊዝ ተረክቦ ካርታ መቀበሉን ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክተሩ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ መሬቱን በሊዝ ሊወስድ የሚችለው፣ ይዞት የነበረው ተቋም የሊዝ ውል ሲቋረጥ ወይም ሲመክን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ይሁንና መሬቱ ከዚህ ቀደም የነበረበትን ሁኔታ መግለጽ የሚችለው የከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በመሆኑ፣ የክርክር ሒደቱ አካል የሆነውም ይኸው ቢሮ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ዕጣ ወጥቶባቸው ለዕድለኞች ካልተላለፉት ከ50 ሺሕ በላይ ቤቶች ባሻገር፣ ሁለት ጊዜ በተደረገው ምዝገባ ተካተው ቤት ያልወጣላቸው 700 ሺህ ሰዎች ይገኛሉ፡፡ የቤት የፈላጊዎችን ጥያቄ በተለያዩ አማራጮች ለመፍታት እየሞከረ ያለው የከተማ አስተዳደሩ፣ ግንባታቸውን በቶሎ ለማጠናቀቅ ይቻላል የተባለላቸውን የተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ከሦስት ወራት ገደማ በፊት አስጀምሯል፡፡

የቤቶቹን ግንባታ የማከናወን ኃላፊነት የተሰጠው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን፣ ለሕንፃ ግንባታው የሚውሉትን የተገጣጣሚ አካላት ቃሊቲ በሚገኘው ፋብሪካው የሚያመርት ሲሆን፣ አምስት ሺሕ ቤቶችን በአንድ ዓመት ውስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ይዟል፡፡ የኮርፖሬሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምርያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥንፉ፣ ዕግዱ ባይመጣ ኖሮ ኮርፖሬሽኑ፣ ውል ከተወሰደበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን በርካታ ቤቶችን የመሥራት ዕቅድ ነበረ ብለዋል፡፡ ክረምት ከመግባቱ በፊት ከ90 በላይ የሚሆኑትን ብሎኮች ኮንክሪታቸውን ከአፈር በላይ አውጥቶ የማጠናቀቅ ዕቅድ እንደነበረም ተናግረዋል፡፡

ፍርድ ቤት የግንባታ መሬቱ ላይ ዕግድ ቢጥልም፣ ኮርፖሬሽኑም ሆነ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣ እግዱ ለፕሮጀክቱ እክል ይሆናል የሚል ሐሳብ የላቸውም፡፡ ኮርፖሬሽኑ መሬቱ ላይ ያለው ሥራ ቢታገድም አሁንም ድረስ የተገጣጣሚ አካላትን፣ እንዲሁም በርና መስኮቶችን እያመረተ መሆኑን አቶ ጥንፉ ተናግረዋል፡፡ ሁለቱም አካላት ተገጣጣሚ አካላቱ ከተመረቱ መገጣጠሙ ብዙም ጊዜ እንደማይወስድ ገልጸዋል፡፡

ይሁንና ኮርፖሬሽኑ የግንባታ ሥራውን መቀጠል የሚችለው የፕሮጀክቱ ባለቤት የሆነው የከተማ አስተዳደሩ መሬቱን ነፃ ሲያደርግለት መሆኑን አስታውቋል፡፡ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ ቢሆንም የከተማ አስተደዳሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግሮ ቦታውን ያስለቅቃል የሚል እምነት እንዳለው አቶ ጥንፉ አስረድተዋል፡፡

የቤት ልማት ትግበራና የሥራ ዕድል ፈጠራ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተሩ ኪያ (ኢንጂነር) በበኩላቸው፣ ከፕሮጀክቱ ባህሪ አንፃር መገጣጠሙ ትንንሽ ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ የመሬት ሥራው መቆሙ ሥጋት እንደማይሆን ገልጸው፣ ግንባታው ቢቆምም ለተወሰነ ጊዜ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በ1997 ዓ.ም. የተጀመረው የመንግሥት የጋራ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት 17 ዓመታት ቢያስቆጥርም፣ እስካሁን የመጀመሪያ ተመዝጋቢዎችን በሙሉ ማዳረስ አልቻለም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩን የ54 ቢሊዮን ብር ዕዳ ባለቤት አድርጎታል፡፡ የተገጣጣሚ ቤቶቹ ግንባታ ይፋ በተደረገበት ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ ለቤቶቹ ግንባታ በተወሰደው ብድርና በተገነቡት ቤቶች ቁጥር መካከል ልዩነት እንዳለ ተናግረው ነበር፡፡

የከተማ አስተዳደሩ እንደሚገልጸው፣ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ክፍተት ይታይባቸዋል፡፡ በተለይ ከ2006 ዓ.ም. እስከ 2010 ዓ.ም. በአገሪቱ ውስጥ ከነበረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ጋር ተይይዞ ኮንትራክተሮች ክትትል ሳይደረግባቸው ሥራቸው ‹‹ልቅ›› የነበረ በመሆኑ፣ ፕሮጀክቶቹ ለሌብነትና ለዝርክር አሠራር እንደተጋለጡ ወ/ሮ አዳነች በየካቲት ወር መጀመሪያ ላይ በተካሄደው የከተማዋ ምክር ቤት አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ጉባዔ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ሪፖርተር
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
አለሕግAleHig ️
ማሳሰቢያ ከ አለ_ህግ #law #societies ሁሉንም የ #አለ_ህግ አባላት የሚያሳትፍ ቀጠሮ፣ ሁሌም እሁድ እሁድ የቀጥታ (Live stream) የድምፅ ውይይት ይኖረናል። #የህግ ጉዳይ የመወያያ እርዕስ አስቀድማችሁ እንዳትመርጡ እናሳስባለን። ምክንያቱም፣ ከወዲሁ ተዘጋጅተው ለውይይቱ እንዲመጡና ፍሬአማ ሀሳቦችን እንድናገኝ ይረዳናል። 1. የመወያያ አጀንዳ ይምረጡ 2. ተዘጋጅተው የውይይቱ ተሳታፊ ይሁኑ…
ማስታወቂያ ከ አለ_ህግ #law #societies
እሁድ የ #አለ_ህግ አባላት የሚያሳትፍ ቀጠሮ፣ ሁሌም እሁድ እሁድ የቀጥታ (Live stream) የድምፅ ውይይት
...... ከምሽቱ 3:00 ስዓት ጀምሮ ይኖረናል።

#የህግ ጉዳይ የመወያያ አጀንዳ፣

የሰብአዊ መብቶች እና የሕግ ጥሰት ከመከሰቱ በፊት እንዴት መከላከል ይቻላል?
ከማን ምን ይጠበቃል?



ተዘጋጅተው የውይይቱ ተሳታፊ ይሁኑ
Share and add ማድረግን አትርሱ
#Ale_Lawsocieties
#አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties

@lawsocieties
Ethiopian chamber of commerce. ምክር ቤቱ ያዘጋጀውን ዘመናዊ የዲጂታል አገልግሎት በይፋ አስጀመረ

የኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከአይርላንድ መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ (Trade Mark East Africa) የቴክኒክ እገዛ አማካኝነት ያዘጋጀውን ዘመናዊ የዲጂታል አገልግሎት መጋቢት 28 ቀን 2014ዓ.ም በራዲሰን ብሉ ሆቴል በደማቅ ሁኔታ በይፋ አስጀመረ፡፡
የኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ተ/ዋና ፀሀፊ አቶ ውቤ መንግስቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን ሲያስተላልፉ በምክር ቤቱ ቀደም ሲል በነበረው አሰራር በአብዛኛው የንግድ ማሳለጫ ስራዎች(trade facilitation operations) ማንዋል የነበሩ በመሆኑ ነጋዴዎች በምክር ቤቱ በአካል ተገኝተው ፎርሞችን ለመግዛትና ለመሙላት ይገደዱ ነበር ብለዋል፡፡ አሁን በተዘጋጀው ዘመናዊ የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ ግን የንግዱ ማህበረሰብ ከየትኛውም የዓለም ክፍል እና ቦታ ሆኖ አገልግሎቱን ማገኘትና መጠቀም እንደሚቻል ተ/ዋና ፀሀፊው አክለው ተናግረዋል።
የዲጂታል አገልግሎቱን በይፋ ያስጀመሩት የኢፌዲሪ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ እንዳለው መኮንን እንደተናገሩት ምክር ቤቱ አገልግሎት አሰጣጡን ከማኑዋል ወደ ዲጂታል በማሸጋገር አባላቱ እና የንግዱ ማህበረሰብ በተመቻቸው ጊዜና ቦታ አገልግሎት ማግኘት የሚችችሉበትን አዲስ የዲጂታል ፕሮጀክት በማዘጋጀቱ ትግበራ መጀመሩ ትልቅ አድናቆት ይገበዋል፤ ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱም በሚፈለግበት ሁሉ እገዛ ያደርጋል።
በትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብነት በቀለ በበኩላቸው የንግዱን ምህዳር ምቹ ለማድረግ ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ በለጋሾች በኩል የኢትዮጵያን መንግስት ለመደገፍ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከሚያስተባብራቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ የምክር ቤቱ የዲጂታል አገልግሎት ፕሮጀክት አንዱ መሆኑን በመጥቀስ፤ ጊዜ እና የግብይት ወጪዎችን ቆጣቢ የሆነውን የዚህን ፕሮጀክት አጠቃቀም ለንግዱ ማህበረሰብ ሙሉ በሙሉ ለማስተዋውቅ ወደፊት ቀጣዩ ደረጃ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ምክር ቤቱ እስካሁን ሲሰጣቸው የነበሩትን አገልግሎቶች በኦንላይን ለመስጠት በዋነኛነት አባላትን ለመመዝገብ የሚያስችል የአባላቶች የመረጃ ቋት፣ የአቻ ለአቻ የቢዝነስ ትስስር (B2B) መፍጠር፣ ለአባላት አቅም ግንባታ ሥልጠናዎች፣ የግልግል ዳኝነት እና ኤክስፖርትን ለማስፋፋት እንዲሁም የንግድ ነክ መረጃን ያካተተውን አዲሱን የምክር ቤቱን የዲጂታል ሲስተም (Ethiopian Chamber Digital System) አስመልክቶ በ Africom Technologies & iDaptive Data Fusion System ባለሙያዎች ገለፃ ተድርጓል።
የመዝጊያ ንግግር የደረጉት የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ኢ/ር መለአኩ እዘዘው በበኩላቸው አዲሱን የዲጂታል ሲስተም አተገባበር ምክር ቤቱ አቅሙን ገንብቶ በራሱ ሙሉ በሙሉ እስከ ሚያስተዳድረው ድረስ ሲፍትዌሩን ያዘጋጀው ድርጅት በቀጣይ ለሁለት አመት የቴክኒክ እገዛ እንደሚያደርግና በኤሌክትሮኒክ የአንድ መስኮት አገልግሎትን(Electronic Single Window Service) አስመልክቶ ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋርም በመተባበር በመስራት የንግዱን ማህበረሰብ በበቃት እንደሚያገለግሉ ገለፀዋል፡፡ በመጨረሻም በእለቱ ትግበራውን በይፋ የጀመረውን የምክር ቤቱን የዲጂታል ሲስተም እውን እንዲሆን በገንዘብና በቴክኒክ የረዱትን የአይርላንድ መንግስት፣ የትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ እና Africom Technologies & iDaptive Data Fusion System ድርጅትን አመስግነዋል፡፡
በዚህ የዲጂታል አገልግሎት ይፋ የማስጀመር ስነ-ስርዓት ላይ የኢፌዲሪ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መሰሪያ ቤትን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሀላፊዎች እና የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Position:- Partnership Officer

📚ትምህርትዓይነትእናደረጃ:-
MA/BA Degree in 🔴Law or Social Science;

🇪🇹 የስራ ቦታ ፡ አዲስ አበባ

🧭የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ ማያዚያ 11 /2014 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://jobs.amazonethiopia.com/job/partnership-officer/

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties