አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በአዲስ አበባ ይደረጋል የተባለው የነዳጅ ድጎማ የትኞቹን ተሸከርካሪዎች ይመለከታል?

በአዲስ አበባ ለሚገኙ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከሀምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ድጎማ ሊደረግላቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለአል ዐይን በላከው መግለጫ አሰረታውቋል።

በዚህም መሰረት በመዲናዋ የህዝብ የትራንስፓርት አገልግሎት የሚሠጡ የመንግሥትና የግል አውቶቡሶች፣ የሳሎን ታክሲዎችን ሳይጨምር በከተማ ውስጥና በከተሞች መካከል የህዝብ የትራንስፓርት አገልግሎት የሚሠጡ ኮድ 1 እና ኮድ 3 ሚኒባስ (አዲስ አበባ ውስጥ የተመዘገቡ) ተሽከረካሪዎችን እንደሚያካትት ቢሮው አስታውቋል።

በድጎማ ስርዓቱ የተመዘገቡ ተሸከርካሪዎች እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜ ውስጥ GPS መግጠም አስገዳጅ ነው ተብቧል።
https://am.al-ain.com/article/addis-ababa-to-subsidize-oil-price-for-public-transport

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያ የሆነዉን የጥብቅና ድርጅት (Law Firm) ፈቃድ ሰጠ🟢🟡🔴
#አለ_ህግ #Ale_Lawsocieties
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያ የሆነዉን የጥብቅና ድርጅት (Law Firm) ፈቃድ ሰጠ
#አለ_ህግ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መንግስት የሕግ አገልግሎት ዘርፍን ለማሻሻል የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አዲስ የፌዴራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 ማዉጧቱ የታወሳል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቅርቡ የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር መመስረቱና አመራሮች በጠበቆች ጠቅላላ ጉባኤ ተመርጠዉ ሥራ መጀመራቸዉ ይታወቃል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴርም ከአዲሱ የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማህበር እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አዋጁን በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ ዝርዝር የአሰራር መመሪያዎችና ዉስጠ ደንብ መቅረጽን ጨምሮ አደራጃጀቶችን በመፍጠርና መነሻ የሚሆን የሰዉ ሃይል እና ግብዓት በመመደብ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአዲሱ የጠበቆች አዋጅ አንቀጽ 37 መሰረት የፀና የጥብቅና ፈቃድ ያላቸው ቢያንስ ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠበቆች አንድ ላይ በመሆን የጥብቅና ድርጅት ማቋቋም እንደሚችሉ የተደነገገ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር መስፈርቱን ለሚያሟሉ አመልካቾች የጥብቅና ድርጅቶች ፈቃድ መስጠት የጀመረ ሲሆን በትናንትናዉ ዕለት የመጀመሪያዉን የጥብቅና ድርጅት ፈቃድ ሰጥቷል፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የመንግስት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዓለምአንተ አግደዉ ፈቃዱን በሰጡበት ወቅት በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የጥብቅና አገልግሎት በድርጅት መስጠት የሚያስችል ሕግ መዉጣቱና ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ለዜጎች የተሻለና ጥራት ያለዉ የሕግ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለዉና በደንበኞችና ጠበቆች መካከል ሊኖር የሚገባዉን መተማመን የሚያጎለበት ከመሆኑም ባሻገር የተሻለ ዋስትና የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በአዋጁ ላይ በተመለከተዉ መሰረት የጥብቅና ድርጅት ለመመስረት ወይም የሽርክና ማህበር ለማቋቋም የሚቀርብ ጥያቄ የሚመለከቱትን ዝርዝሮች መያዝ እንዳለበት ለማሳታወስ እንወዳለን፡-
1. ማህበሩን ለመመስረት በተስማሙ አባላት የተፈረመ የፈቃድ ይሰጠኝ ማመልከቻ፣
2. ከማመልከቻው ጋር በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የተረጋገጠና በሁሉም አባላት የተፈረመ የመመስረቻ ጽሁፍ፣
3. “የጥብቅና አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር" በሚል ስያሜ የጥብቅና ድርጅት ለማቋቋም በአባላት የተፈረመ ቃለ ጉባዔ፣
4. በአባላት የተፈረመ የሸሪኮች የሽርክና ስምምነት፣
5. አመልከቾች ጠበቆች ስለመሆናቸዉ እና የታደሰ የጥብቅና ፍቃድ ያላቸው መሆናቸውን የሚገልጽ ፈቃድ ኮፒ፣
6. ማህበሩ የመድህን ዋስትና ስለመግባቱ የሚያረጋግጥ የመድህን ዋስትና ሰነድ በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

አመልካቾች የመመስረቻ ጽሁፋቸው በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት በኩል ከመረጋገጡ በፊት በፍትሕ ሚኒስቴር የጥብቅና ፈቃድ አስተዳደርና ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በኩል የመመስረቻ ጽሁፉ የአዋጅ ቁጥር 1249/2013 እና የንግድ ሕጉ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 ላይ የተመለከቱትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ መሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም አመልካቾች በሰየሙት የጥብቅና ድርጅት ስም የተመዘገበ ሌላ የጥብቅና ድርጅት የሌለ ስለመሆኑ የማረጋገጥ ሥራ ይሰራል፡፡

ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተዉ ሲገኝ ለኢንሹራንስ ሰጭዎችና ለሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ የትብብር ደብዳቤ በፍትህ ሚኒስቴር ከተጻፈ በኋላ ሁሉም መመዘኛዎች መሟላታቸዉ ሲረጋገጥ የጥብቅና ድርጅት ሰርተፊኬት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ማስታወሻ፡- የፈቃድ ይሰጠኝ ማመልከቻው በቀጥታ ባምቢስ በሚገኘው የፍትሕ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ለጠበቆች ፍቃድ አስተዳደርና ነጻ የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ይቀርባል፡፡

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚከተሉት የስራ መደቦች ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
Position:-
1 – Technician (Sky Techno Req.# 2 )
2 – Legal Attorney

📚ትምህርትዓይነትእናደረጃ:-
Grade 10 and a Diploma in General Mechanics, LLB/LLM Degree in Law from recognized higher education institution & a license from the concerned gov’t office.
🇪🇹 የስራ ቦታ ፡Ethiopian Airlines Head Quarter, Ethiopian, Addis Ababa
🧭የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ ማያዚያ 01 /2014 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://jobs.amazonethiopia.com/job/ethiopian-airlines-4/

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
Forwarded from Bea .T
በአብክመ ፍትህ ብሮ የዞን አቃቢያን ህግ የውስጥ የደረጃ እድገት የወጡ ጥያቄዎች ያላችሁ ብታጋሩኝ በቅድሚያ አመሰግናለሁ🙏
የውጪ ሀገር ገንዘብ ትርጓሜና የወንጀል ኃላፊነቱ፡ ሕግና ትግበራ አጭር ዳሰሳ

በ፡ ዳግም አሠፋ

ወዳጄ! በኪስህ እንደ ልማድም (hobby) እንደ ቅንጦትም በዋሌትህ ወይም በእጅሽ ቦርሳ የያዝሻት 1(አንድ የአሜሪካን ዶላር) እስከ 10 (አስር ዓመታት) ሊያሳስርህ እና እስከ ብር 50,000 (ሀምሳ ሺ) ሊያስቀጣህ እንደሚችል ብነግርህ ምላሽህ/ሽ ምን ይሆን? ነገሩ ወዲህ ነው-

መልካም ንባብ!

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/2029-the-definition-of-foreign-currency-and-its-criminal-liability

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
በሰው መነገድ ወንጀል ምንነት
በሰው መነገድ ወንጀል ምንነት❗️
#አለ_ህግ
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን ተከታታዮች አሁን አሁን በሰዎች የመነገድ ወንጀል በሀገራችን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳትን እያደረሰ የሚገኝ ወንጀል ሲሆን፤ በተለይም በወጣቱ ወይም በአምራቹ ኃይል ላይ ሞትን እንዲሁም አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳትን እያስከተለ ይገኛል፡፡ ሰዎች የህይወትን ውጣ ውረድ ለማሸነፍ የተሻለ ስራ ፍለጋ በህገ-ወጥ ደላላዎች አማካኝነት የጎረቤት ሀገራትን ድንበር በህገ-ወጥ መንገድ በማቋረጥ ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚሄዱ መሆኑ ደግሞ ለዚሁ ጉዳት መጋለጫ ምክንያት ነው፡፡

ለመሆኑ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወይም በሰው መነገድ ወንጀል ሲባል ምን ማለት ነው? ከሀገራችን የህግ ማዕቀፎች አኳያ ወንጀሎቹ በምን መልኩ ተደንግገዋል? በሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ በፍትህ ሚኒስቴር የብሄራዊ የትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ዐቃቤ ህግ ከሆኑት አቶ ዮሐንስ ሲሳይ ጋር ቆይታ አድርገን ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተውናል እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

 በሰዎች የመነገድ ወንጀል ምንነትን እና የአፈጻጸም ሁኔታን በተመለከተ ላቀርብንላቸው ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተውናል

በሰው መነገድ ድርጊት በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም የወንጀል ድርጊት ሲሆን በሀገራችንም ይሁን በመላው አለም ስልቱን እና መልኩን በመቀያየር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ የሚገኝ አስከፊ ወንጀል ነው ሲሉ አቶ ዮሐንስ ማብራሪያቸውን ይጀምራሉ፤ ለችግሩ መስፋፋት በርካታ ምክንያቶችን ማንሳት የሚቻል ቢሆንም በዋናነት ግን ድህነትና ሥራ አጥነት፣ የአመለካከት ወይም የግንዛቤ ችግር፤ የተሻለ ሥራና ገቢ ፍለጋ፤ የቤተሰብና የጓደኛ ግፊት ተጠቃሾች ስለመሆናቸው በጉዳዩ ዙሪያ የተከናወኑ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመላክቱም ዐቃቤ ህጉ ይናገራሉ፡፡ ወንጀሉ በአብዛኛው አምራች ኃይል የሆኑ ወጣቶች፣ ሴቶችና እንዲሁም ህፃናትን ሰለባ በማድረግ እስከ ሞት ለሚያደርስ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚዳርግ መሆኑ ችግሩን የበለጠ አሳሳቢ ያደርገዋል ያሉት ዐቃቤ ህጉ አስከትለውም ወንጀሉ በሰው ልጆች መብቶችና ክብር ላይ የሚፈጸም እና የሁሉም ሀገራት ችግር መሆኑን ይናገራሉ፡፡ እንዲሁም በየለቱ የሚፈጸም ውስብስብና አስቸጋሪ ገጽታ ያለው መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

አያይዘውም አቶ ዮሐንስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለወንጀሉ ትኩረት መሰጠት የጀመረው በ20ኛ ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ጀምሮ መሆኑን አንስተው ሁሉንም ዓይነት በሰው የመነገድ ድርጊቶች ያካተተ የህግ ትረጉም የተሰጠው ግን እ.ኤ.አ በ2000 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በወጣው በሰዎች በተለይም በሴቶችና ሕፃናት መነገድን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የወንጀሉን ፈፃሚዎች ለመቅጣት በወጣው ፕሮቶኮል ነው፡፡ በዚህም መሠረት በፕሮቶኮሉ አንቀጽ 3(ሀ) ላይ በሰው የመነገድ ወንጀል ማለት “ለብዝበዛ ዓለማ ሲባል ሰዎችን በዛቻ ፣ ኃይል በመጠቀም፣ በማገት፣ በመጥለፍ፣ በማስፈራራት ወይም ሌላ የማስገደጃ ዘዴ በመጠቀም፣ በተንኮል፣ በማታለል ወይም የተስፋ ቃል በመስጠት፣ ስልጣንንን አላግባብ በመጠቀም ፣የሰዎችን ለጥቃት ተጋላጭነት በመጠቀም ወይም ስለሌላው ሰው ኃላፊነት ያለበትን ሰው ፈቃድ ለማግኘት መደለያ ወይም ጥቅም በመስጠት ሰዎችን መመልመል ፣ማጓጓዝ፣ ማዘዋወር፣ ማስጠለል ወይም መቀበል ነው” የሚል ትርጉም ተሰጥቶታል ሲሉ ስለጉዳዩ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጠውናል፡፡

በዚህም መሠረት በሰው የመነገድ ወንጀል ድርጊት ተፈጽሟል ለመባል ሦስት መሠረታዊ ነገሮች መሟላት እንዳለባቸው ዐቃቤ ህጉ ያነሱ ሲሆን እነዚህም በወንጀል ፈጻሚዎቹ የሚፈጻመው ግዙፋዊ ድርጊት ማለትም መመልመል ፣ማጓጓዝ፣ ማዘዋወር፣ ማስጠለል ወይም መቀበል፣ድርጊቱን ለመፈጸም ጥቅም ላይ የዋለ ዘዴ ይህ ሲባል ዛቻ፣ ኃይል መጠቀም፣ ማገት፣ መጥለፍ ማስፈራራት ወይም ሌላ የማስገደጃ ዘዴ መጠቀም፣ ተንኮል፣ ማታለል ወይም የተስፋ ቃል መስጠት፣ ስልጣንንን አላግባብ መጠቀም ፣ሰዎችን ለጥቃት ተጋላጭነት መጠቀም ወይም ስለሌላው ሰው ኃላፊነት ያለበትን ሰው ፈቃድ ለማግኘት መደለያ ወይም ጥቅም መስጠት እና በዝበዛ ናቸው ሲሉ ያነሳሉ፡፡ ነገር ግን ይላሉ አቶ ዮሐንስ የወንጀል ድርጊቱ በህጻናት ላይ በሚፈጸም ጊዜ ህጻናት ከሚገኙበት ልዩ የተጋላጭነት ሁኔታ ነገሮችን ከማመዛዘን እና የውጭ ጫናን ከመቋቋም አንጻር ያለባቸውን ውስንነት ግምት ውስጥ በማስገባት ግዙፋዊ ድርጊቱ እና ድርጊቱን የተፈጸመው ለብዝበዛ ዓላማ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ አጥፊው ድርጊቱን ለመፈጸም የተጠቀመው ልዩ ዘዴ ባይኖርም ወንጀሉን ግን እንደሚያሟላ ገልጸዋል፡፡

 ከወንጀሉ ማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮች መካከል አንዱ ዓላማ ነው ብለውናል፡፡ በሰው የመነገድ ወንጀል መሠረታዊ መገለጫው እና ይህው ዓላማስ ምንድን ነው ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ፡-
በሰው የመነገድ ወንጀል መሠረታዊ መገለጫው እና ዓላማው ተጎጂዎችን መበዝበዝ ሲሆን ለአብነት ያህል ሴቶችን ለዝሙት አዳሪነት ማቅረብ፣ በሴቶች የዝሙት አዳሪነት መጠቀም ፣ ሰውን ለግዳጅ ስራ ወይም አገልግሎት ማሠማራት፣ በባርነት ወይም ባርነት መሰል ተግባር መያዝ፣ አገልጋይ ማድረግ ወይም በዕዳ መያዣነት መያዝ ወይም ማቅረብ፣ የሰውን ልጅ አካል ማውጣትና መወስድ፣ ሰውን ለልመና ወይም ለወንጀል ተግባር ማሰማራት፣ ሰውን ለግዳጅ ጋብቻ ወይም የማህጸን ኪራይ ማሰማራት ከብዘብዛ ዓይነቶች ውስጥ ተጠቃሾች መሆናቸውን የገለጹት ዐቃቡ ህጉ ብዝበዛው አንዴ ብቻ ተፈጽሞ የሚያቆም ሳይሆን ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚፈጸም ነው ብለዋል፡፡

ከተል አድርገውም ለዚህም ዓላማ ተጎጂዎችን በቁጥጥር ሥር ማድረጊያ መነገዶችም መካከል
• የተጎጂውን ፓስፖርት መያዝ (መቀማት)
• ከሥር ቦታ ወይም ከመኖሪያ ቤት እንዳይወጡ መከልከል
• ቤተሰብ ላይ ጉዳት አደርሳለሁ ብሎ ማስፈራራት ወይም ቤተሰብን ማስፈራራት
• ደመወዝን መያዝ (መከልከል)
• ህጋዊ የጉዞ እና የመኖሪያ ፈቃድ ሰነድ የሌላቸውን ተጎጂዎችን ለፖሊስ ወይም ለባለስልጣናት አሳውቅብሀለው/አሳውቅብሻለሁ ማለት
• ሌላ ሥራ እንዳታገኝ/ እንዳያገኝ ማድረግ…ወዘተ ተጠቃሾ ናቸው ሲሉ ያነሳሉ፡፡

 ከሀገራችን የህግ ማዕቀፍ እና ከሚያስከትለው የቅጣት ውሳኔ አኳያ ላነሳንላቸው ጥያቄ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጠውናል፡-
ሀገራችንም ከላይ የተገለጸውን ስምምነት ፈራሚ እንደመሆኗ ስምምነቱን በአዋጅ ቁጥር 737/2004 በማጽደቅ ከዚህ በፊት አዋጅ ቁጥር 909/2007 በማውጣት ስትተገበር የቆየች ሲሆን አዋጁ በነበሩበት አንዳንድ ክፍቶች ምክንያት በ2012 ዓ.ም በአዲስ አዋጅ በአዋጅ ቁጥር 1178/2012 እንዲተካ መደረጉን ማብራሪያቸው ላይ አንስተዋል፡፡

በአዋጁ ቁጥር 1178/2012 መሠረትም ማንኛውም በሰው የመነገድ ወንጀል ፈጽሞ የተገኘ ሰው ከሰባት ዓመት እስከ አስራ ሁለት ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና ከአርባ ሺህ እስከ አንድ መቶ ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ እንደሚቀጣ በአንቀጽ 3/2 ( በማረሚያ ቁጥር 11/2013 እንደተስተካከለው) ተደግንግጓል ያሉት አቶ ዮሐንስ ወንጀሉ በህጻናት፣ በአዕምሮ ህመምተኞች ወይም በአካል ጉዳተኞች ላይ ከተፈጸመ፣ አደንዛዥ መድሀኒት፣ የጦር መሳርያ በመጠቀም ከተፈጸመ ወይም ኃላፊነቱን መከታ በማድረግ በባለስልጣን ወይም በመንግስት ሠራተኛ ከተፈጸመ እንዲሁም ፈቃዱን ሽፋን በማድረግ በውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ፈቃድ ባለው ሰው የተፈጸመ ከሆነ ከ10 እስከ 20 ዓመት.........
በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከ30, 000 እሰከ 100, 000 ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ ይሆናል ብለዋል፡፡በተጨማሪም ወንጀሉ የተደራጀ የወንጀል ቡድን አባል በመሆን ከተፈጸመ ወይም በተጎጂው ላይ የማይድን በሽታ ካስከተለ ወይም የተጎጂውን ደህንነት አደጋ ላይ የጣለ ከሆነ በተጎጂው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ያስከተለ ከሆነ ወይም ተጎጂው ለኢሰብዓዊ አያያዝ የተዳረገ ከሆነ ቅጣቱ ከ15 እስከ 25 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከ50,000 እስከ 150,000 ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ መሆኑን አቶ ዮሐንስ አንስተዋል፡፡ ነገር ግን ይላሉ አቶ ዮሐንስ ወንጀሉ በተጎጂው ላይ ሞትን አስከትሎ ከሆነ ደግሞ ቅጣቱ እንደ ወንጀሉ አፈጻጸም ሁኔታ እስከ እድሜ ልክ ጽኑ እስራት ወይም የሞት ቅጣት የሚያስቀጣ ይሆናል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ማንኛውም በሰው የመነገድ ወንጀልን የመደግፍ፣ በሰው የመነገድ ወንጀልን መፈጹሙን ወይም እየተፈጸመ መሆኑን ወይም ሊፈጸም መሆኑን እያወቀ ለሚመለከተው ህግ አስከባሪ አካል ወዲያውኑ አለማሳወቅ፣ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት ያለውን ንብረትን መሰወር፣ ማስረጃን በማጥፋት እና ተጠርጣሪን እንዳይከሰስ በመርዳት ፍትህን ማስተጓጎል በአዋጁ መሠረት በወንጀል የሚያስጠይቁ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

አዋጅ ቁጥር 1178/2012 ከዓለም አቀፉ የህግ ማዕቀፍ ልዩ የሚያደረግ በአንቀጽ 3(1) እንተመለከተው የብዝበዛ ተግባር መፈጸሙ እስከተረጋገጠ ድረስ ሌሎች በሰው የመነገድ ወንጀልን የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮች ማለትም ድርጊትና ዘዴ ባይኖሩም አጥፊውን በሰው የመነገድ ወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የሚቻል መሆኑ ነው ሲሉም አዋጅ ቁጥር 1178/2012 ከዓለም አቀፉ የህግ ማዕቀፍ የሚለይበትን ሁኔታ የገለጹት ፡፡

በመጨረሻም ይላሉ አቶ ዮሐንስ ወንጀሉን በመከላከል፣ አጥፊዎችን ለህግ በማቅረብ እና የተጎጂዎችን መብት መጠበቅና በመንከባከብ ረገድ በፌዴራልና በክልል ደረጃ ሰፊ ሥራዎች በመሠራት ላይ የሚገኙ ሲሆን የታሰበውን ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የህበረተሰቡ ተሳትፎ እና የባለርሻ አካላት ትብብርና ቅንጅታዊ ሥራ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም ለወንጀሉ ተጋላጭ የሆኑ ወጣቶችም ማንኛውንም የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት መንግስት በዘረጋው ሥርዓት መሠረት ቢሰማሩ ተጋላጭ ሳይሆኑ ሰብዓዊ መብታቸው እና ከብራቸው ተጠብቆ ያሳቡትን ማሳካት ይችላሉ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አቶ ዮሐንስ ከእኛ ጋር ለነበራቸው ቆይታ እያመሰገንን በቀጣይ በህገ ወጥ መንገድ ሰዎችን ድንበር የማሻገር ወንጀል እና ፈቃድ ሳይኖር ሰዎችን ለስራ ወደ ውጭ መላክ ወንጀሎች ምንነትን በተመለከተ ጥንቅር ይዘን እንቀርባለን፡፡ ሰላም!
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
አለ_ህግ Ale Hig, Ale Law Societies #አለ_ህግባለሙያ፣ ነፃ የህግ ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ የውልና የክስ ቅፆች (ፎርሞች) ፤ የህግ ጉዳዮችን 🔴ሁሉንም ሕጎች በአንድ ላይ ያገኙበታል 🔴 All in one, for All. #አለ_ህግ መሰረታዊ የህግ መረጃና እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው።
ይህን ሊንክ በመጫን በቴሌግራም ተቀላቀሉን https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
email us: lawsocieties@gmail.com
contact us via telegram Bot @LawsocietiesBot

follow us on Facebook page
https://www.facebook.com/lawsocieties/
Vacancy at Wasasa Microfinance S.C

🔰 The Wasasa Micro finance Institution S.C is invites job seekers for an appointment the below Position.

1: Head, Legal Services 🔴

2: Teller I
3: Branch I Manager
4: Junior Savings and Credit Officer

📌ሰለ ሰራው ሙሉ መረጃ ለማየት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ👇👇
👉 Read Detail:- https://bit.ly/3v7xWPI
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
መልካም ዜና!

ገንዘብ ሚኒስቴር መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ በቀጥታ እንዲገቡ ወሰነ!!

የገንዘብ ሚኒስቴር መሰረታዊ የምግብ ሽቀጦች የሆኑት ዘይት፣ስንዴ፣ስኳር፣የህጻናት ወተት እና ሩዝ ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፍቃድ (በፍራንኮ ቫሉታ) በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል በቀጥታ እንዲገቡ ወሰነ፡፡

መንግስት በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት እንዲቻል እና በርካታ የውጭ ሀገር የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን ሚና መጫወት እንዲችሉ የፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲፈቀድላቸው ጥያቄ እያቀረቡ በመሆኑ ነው፡፡

ቀርጥና ታክሱ በሚመለከት በገንዘብ ሚኒስቴር በ22/3/2013 ዓ.ም በቁጥር ማአ.30/7/51 በተጻፈው ደብዳቤ መሰረት እንዲፈጸም ፤ አፈጻጸሙን በተመለከተ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት በኩል ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግበት ተወስኗል፡
Via ethio mereja
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties
#WHO Internship Programme 2022#

▪️Organization: WHO
▪️Duration: 6 to 24 Weeks
▪️For: Undergraduate/Graduate/PhD
▪️Financial Coverage: Fully Funded
▪️Deadline: Varies (Open Now)
▪️Find More Details here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3qc4mqO
በምሥረታ ላይ የሚገኘው የጃኖ ባንክ አመራሮች ቢሮ ዘግተው መጥፋታቸውን ባለድርሻዎች ገለጹ

በምሥረታ ላይ የሚገኘው የጃኖ ባንክ አመራሮችና ሠራተኞች፣ የባንኩ ባለድርሻዎች የገዙትን አክሲዮን ገንዘብ ሳይመልሱ ተከራይተውት የነበረውን ቢሮ ለቀው እንደጠፉና ስልካቸውንም እንዳጠፉባቸው አክሲዎን የገዙ ሰዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደሚሉት፣ ጃኖ ባንክን ለመመስረት ከሁለት ዓመት በፊት አክሲዮን መሸጥ የተጀመረ ሲሆን፣ የተወሰነ ከተሸጠ በኋላ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የሚመሠረቱ ባንኮች የመነሻ ካፒታላቸው አምስት ቢሊዮን ብር ማድረስ እንዳለባቸው መመሪያ ማውጣቱን ተክትሎ በምሥረታ ላይ የነበረው ባንክ ይህንን ማሟላት ባለመቻሉ ወደ ማይክሮ ፋይናንስ እንዲወርድ ተወስኖ ነበር።

ነገር ግን፣ በምሥረታ ላይ የነበረው ጃኖ ባንክ ይህን ለማድረግ መሥራቾችን እንዲያስፍርም ከብሔራዊ ባንክ ትዕዛዝ ቢሰጠውም፣ አብዛኛዎቹ መሥራቾች የባንኩ ምስረታ ወደ ማይክሮ ፋይናንስ በመቀየሩ ላይ አለመስማማታቸው ተሠምቷል።
በዚህም፣ መሥራቾቹ ብሔራዊ ባንክ የገባው ሰነድ ፈርሶ ገንዘባቸው እንዲመለስ ቢፈልጉም አመራሮቹን ማግኘት እንዳልቻሉ ጠቅሰው መፍትሔ ይሰጠን እያሉ ነው።

https://bit.ly/3jjW2RS
____________________
አዲስ ማለዳ
The Danish Refugee Council (DRC) ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
Position :- Programme Officer – Information Hub.
የትምህርትዓይነትእናደረጃ:-
Bachelor’s degree in social sciences, law, social work, international development, or other relevant fields from a recognized institution.
🇪🇹 የስራ ቦታ:-Addiss Ababa
🧭የምዝገባ ጊዜ /Deadline/: እስከ ሚያዚያ 13/2014 ዓ.ም
🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
//https://jobs.amazonethiopia.com/job/programme-officer-information-hub/

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share.....
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
................ @Lawsocieties