አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ድሬ ድዋ የነበረው የ consortium ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ
ሁሉም የህግ ት/ቤት deans እና heads ወደ የመጡበት በመመለስ ላይ ናቸው።
#ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ #የህግ ት/ቤትን ከልብ እናመሰግናለን።
ግሩም አቀባበል እና መስተግዶ አድርገው የስብሰባውን አላማ ግብ እንዲመታ ላደረጉት ጥረት እና መልካም አስተዋፅኦ
እናመሰግናለን።
ማሳሰቢያ አለ_ህግ #law #societies
ሁሉንም የ #አለ_ህግ አባላት የሚያሳትፍ ቀጠሮ፣ ሁሌም እሁድ እሁድ የቀጥታ (Live stream) የድምፅ ውይይት ይኖረናል።
#የህግ ጉዳይ የመወያያ እርዕስ አስቀድማችሁ እንዳትመርጡ እናሳስባለን።
ምክንያቱም፣ ከወዲሁ ተዘጋጅተው ለውይይቱ እንዲመጡና ፍሬአማ ሀሳቦችን እንድናገኝ ይረዳናል።
1. የመወያያ አጀንዳ ይምረጡ
2. ተዘጋጅተው የውይይቱ ተሳታፊ ይሁኑ
3. Share and add ማድረግን አትርሱ
#Ale_Lawsocieties
#አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties

@lawsocieties
አለሕግAleHig ️
ማሳሰቢያ ከ አለ_ህግ #law #societies ሁሉንም የ #አለ_ህግ አባላት የሚያሳትፍ ቀጠሮ፣ ሁሌም እሁድ እሁድ የቀጥታ (Live stream) የድምፅ ውይይት ይኖረናል። #የህግ ጉዳይ የመወያያ እርዕስ አስቀድማችሁ እንዳትመርጡ እናሳስባለን። ምክንያቱም፣ ከወዲሁ ተዘጋጅተው ለውይይቱ እንዲመጡና ፍሬአማ ሀሳቦችን እንድናገኝ ይረዳናል። 1. የመወያያ አጀንዳ ይምረጡ 2. ተዘጋጅተው የውይይቱ ተሳታፊ ይሁኑ…
ማስታወቂያ ከ አለ_ህግ #law #societies
እሁድ የ #አለ_ህግ አባላት የሚያሳትፍ ቀጠሮ፣ ሁሌም እሁድ እሁድ የቀጥታ (Live stream) የድምፅ ውይይት
...... ከምሽቱ 3:00 ስዓት ጀምሮ ይኖረናል።

#የህግ ጉዳይ የመወያያ አጀንዳ፣

የሰብአዊ መብቶች እና የሕግ ጥሰት ከመከሰቱ በፊት እንዴት መከላከል ይቻላል?
ከማን ምን ይጠበቃል?



ተዘጋጅተው የውይይቱ ተሳታፊ ይሁኑ
Share and add ማድረግን አትርሱ
#Ale_Lawsocieties
#አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties

@lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
ማስታወቂያ ከ አለ_ህግ #law #societies
እሁድ የ #አለ_ህግ አባላት የሚያሳትፍ ቀጠሮ፣ ሁሌም እሁድ እሁድ የቀጥታ (Live stream) የድምፅ ውይይት
...... ከምሽቱ 3:00 ስዓት ጀምሮ ይኖረናል።

#የህግ ጉዳይ የመወያያ አጀንዳ፣

የሰብአዊ መብቶች እና የሕግ ጥሰት ከመከሰቱ በፊት እንዴት መከላከል ይቻላል?
ከማን ምን ይጠበቃል?



ተዘጋጅተው የውይይቱ ተሳታፊ ይሁኑ
Share and add ማድረግን አትርሱ
#Ale_Lawsocieties
#አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties

@lawsocieties
ቀጠሮ ሳናከብር በመቅረታችን ይቅርታ እንጠይቃለን❗️❗️🙏🙏

ውድ የ አለ_ህግ ቤተሰቦች
@lawsocieties
ሁሉንም የ #አለ_ህግ አባላትን በሚያሳትፍ መልኩ በወቅታዊ ጉዳይ ስለ ህጎች፣ ሁሌም እሁድ እሁድ የቀጥታ (Live stream) የድምፅ ውይይት መጀመራችን ይታወቃል።
ሆኖም፣
#የህግ ጉዳይ የመወያያ እርዕስ አስቀድማችሁ እንድትመረጡ አሳሰብን ነበር፣
ምክንያቱም፣ ከወዲሁ ተዘጋጅተው ለውይይቱ እንዲመጡና ጠቃሚና ፍሬአማ ሀሳቦችን እንድንለዋወጥ ይረዳናል።
1. የመወያያ አጀንዳ ይምረጡ
2. ተዘጋጅተው የውይይቱ ተሳታፊ ይሁኑ
3. Share and add ማድረግን አትርሱ
#Ale_Lawsocieties
#አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
#የጠበቆች_የሙያ_ስነ_ምግባር_መርሆዎች
==========================

የሰው ልጆች ሁሉ በሰብዓዊ ፍጡርነታቸው የተቸሩትን መብቶችና መሰረታዊ ነፃነቶች እንዲጎናፀፉ ለማድረግ ብቃት ያለው የህግ ምክር አገልግሎት የሚያገኙበት መንገድ ማመቻቸት አስፈላጊ እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት የህግ ሙያተኞችን ሚና ለመወሰን በደነገገው መሰረታዊ መርሆዎች ላይ በሚገባ ተመልክቷል፡፡
A) #የዜጎች መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች በተለይም ግልጽና ፍትሃዊ የሆነ ዳኝነትን የማግኘት መብት በተለያዩ የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችና መግለጫዎች ላይ የሰፈረ ከመሆኑም ባሻገር በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙና፣ የተከሰሱ እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች በተቻለ መጠን ተገቢ የህግ ምክር አገልግሎት ማግኘት የሚገባቸው መሆኑንና ከጠበቆቻቸውም ጋር የመገናኘትና የመወያየት፣ የውይይቱ ሚስጥራዊነትም እንዲጠበቅላቸው ሙሉ ነፃነት ያላቸው መሆኑ ተደንግጓል፡፡ በአንድ የፍትህ ስርዓት ውስጥ የዜጎች እኩልነት ተከብሮ፣ ፍትህና ርቱዕ የተሞላበት ዳኝነት እንዲያገኙ ከተፈለገ ሁሉም ዜጎች በተቻለው አቅም ሁሉ የህግ አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል ለፍትሃዊ የህግ ስርዓት መጎልበትና ለሰብአዊ መብቶች መከበር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ በፍትህ ስርዓቱና በህግ የበላይነት ላይም ሰፊው ህብረተሰብ ፅኑ እምነት እንዲያሳድርና የሁሉም ሰው መብት ህግ ባስቀመጠው ወሰንና አግባብ እንዲከበር ጠንካራ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ሊኖር የሚገባው ሲሆን ከፍተኛ ስነ ምግባር የተላበሱ የህግ ሙያተኞችና ጠበቆችም እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆናቸውን እንገነዘባለን፡፡
እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1990 ዓ.ም የወጣው የተባበሩት መንግስታት የህግ ሙያተኞች ሚና መሰረታዊ መርሆዎች ከሚደነግጉት ሁኔታዎች መካከል አንዱና ዋንኛው ሁሉም ሰዎች በወንጀል የፍርድ ሂደት መሰረታዊ መብቶቻቸውን በሚገባ ለማስጠበቅና ራሳቸውን ለመላከል ተደራሽነት ያለው የህግ ምክር አገልግሎትና የህግ አማካሪዎችን ወይም ጠበቆችን በቀላሉ ማግኘት እንደሚገባቸውና መንግስታትም በዚህ ረገድ ያለ አንዳች አይነት አድሎአዊ ልዩነት ሁሉም ዜጎች ይህንን አገልግሎት የሚያገኙበት ውጤታማ ስልቶችና ስነስርዓቶች መቀየስ ይጠበቅባቸዋል፡፡
B) #ከዚህ አኳያ መንግስታት የተለየ ኃላፊነት እንዳለባቸውና ይህ ኃላፊነትም በቂ ገንዘብ በመመደብ ድሆችና ሌሎችም የተገፉ የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የህግ ምክር አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግን ይጨምራል፡፡
C) #የህግ ባለሙያዎች ማህበራትና ጠበቆችም በዚህ ረገድ ከመንግሰታት ጋር በመተባበር ነፃ የህግ አገልግሎት ለመግዛት የኢኮኖሚ አቅማቸው ለማይፈቅድ ዜጎች እንዲመቻች ለማድረግ የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ አላባቸው፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ሁሉም የህብረተሰቡ ክፍል በህግ ስለተረጋገጠላቸው መሰረታዊ መብቶችና ግዴታዎቻቸው እንዲያውቁ ለማድረግ መንግስትና ጠበቆች እንዲሁም የህግ ሙያተኞች ማህበራት በጋራ መረባረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ መልኩ በወንጀል የፍርድ ሂደት ውስጥ የተያዙና የተከሰሱ ሰዎች መሰረታዊ መብቶቻቸውና ነፃነቶቻቸው እንዲጠበቁ የማድረግ ኃላፊነት የመንግስት እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ከዚህ አንፃር መንግስት በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች እንደተያዙ ወዲያውኑ በሚመለከታቸው የፍትህ አካላት በሁሉም የወንጀለ ፍትህ አስተዳደር ሂደቶች በፈለጉት ወይም በመረጡት የህግ አማካሪ የመወከልና ተገቢውን የምክር አገልግሎት የማግኘት መብት እንዳላቸው እንዲያዉቁ መደረጉን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

D) #በተለይም የመክፈል አቅምን በማጣት ምክንያት የህግ ምክር አገልግሎት ማግኘት ያልቻሉ ግለሰቦች በቂ ልምድና ብቃት ያለው የህግ አማካሪ በመንግስት ወጪ እንዲያገኙ መደረግ አለበት፡፡
E) #በመንግስት የሚመደብላቸውም የህግ አማካሪ ከተከሰሱበት ጉዳይ ውስብስብነት ጋር በሚመጣጠን መልኩ በቂ ልምድና ችሎታ ያላቸው መሆን ይገባዋል፡፡ ችሎታቸውና ልማዳቸው እምብዛም ያልሆነ የህግ አማካሪዎችን መመደብ በዚህ ረገድ በመንግስት ላይ የተጣለውን ኃላፊነት መንግስት በሚገባ እንዳልተወጣው ነው የሚያስቆጥረው፡፡ በርግጥ በአብዛኛው በወንጀል ጉዳዮች ላይ ነው የመክፈል አቅም ለሌላቸው ግለሰቦች በመንግስት ወጪ ጠበቃን ማቆም የሚገባው፡፡ ይሁን እንጂ ከወንጀል ጉዳይ ዉጪ በሆነ መልኩ ለተያዙ ግለሰቦች በመንግስት በነፃ ጠበቃ የማቆም ግዴታ እንዳለበት ነው ተደንግጎ የሚገኘው፡፡
F) #በአለም አቀፍ መርሆዎች የተደነገገው ደረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ በተለይም የተያዙ ሰዎች ጠበቃ የማቆም አቅም በማይኖራቸው ጊዜ መንግስት በተቻለው አቅም ሁሉ ከተያዙበት ጊዜ አንስቶ በ48 ሰዓታት ውስጥ ነው ነፃ የህግ አገልግሎት የሚሰጣቸውን የህግ አማካሪ ሊመደብላቸው የሚገባው፡፡ ከዚህ የምንረዳው በሁሉም የፍርድ ሂደቶች ዜጎች በህግ አማካሪ ሳይወከሉ በፍርድ ሂደት እንዳያልፉ የሚደረግ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር አቅም ያጡ ግለሰቦች በድህነታቸው ምክንያት ብቻ የህግ ምክር ሳያገኙ በማንኛውም የፍርድ ሂደት እንዲሳተፉ ወይም ለፍርድ እንዲቀርቡ ከተደረገ የሁሉም ሰዎች ፍትሃዊ፣ሚዛናዊ ግልፅ የሆነ ዳኝነት የማግኘት መብት ተከብሯል ለማለት አያስደፍርንም፡፡
የተያዙ ሰዎች በእስር ወቅት በመንግስት ከተመደበላቸው የህግ አማካሪ ጋር የሚገናኙበትና በነፃነት የሚወያዩበት በቂ እድል ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ እነዚህ ሰዎች ከህግ አማካሪዎቻቸው ወይም ጠበቆቻቸው ጋር የሚያደርጉት ምክክርና ውይይት በየትኛውም መልኩ በህግ አስከባሪ ባለስልጣናት ሊደመጥና ይዘቱም ቅድመ ምርመራ ሊደረግበት አይገባም፡፡
G) #ጥብቅና ከፍተኛ ኃላፊነት የሚያስከትልና በፍትህ አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው ሙያ በመሆኑ ከጠበቆች ከፍ ያለ ስነ ምግባር ነው የሚጠበቀው፡፡ ከዚህም የተነሳ ጠበቆች በግል ህይወታቸውም ጭምር የሙያውን ክብርና ዝና ከሚያጎድፉ ባህሪያት ራሳቸውን ማግለልና በሚገባ መጠበቅ አለባቸው፡፡ ከዚህም አልፍው የሙያ ባልደረቦቻቸው የስነ ምግባር ጉድለት እንዳያሳዩ የመምከርና የስነ ምግባር ጉድለት ፈፅመው ሲገኙ ደግሞ ለተገቢው አካል የመጠቆም ኃላፊነት አለባቸው፡፡

ለዚህ ነው ጠበቆች ሁሌም ቢሆን የሙያቸውን ክብርና ዝና በመጠበቅ የፍትህ አስተዳደሩ ዋልታ መሆን ይገባቸዋል የሚባለው፡፡
H) #አንድ ጠበቃ የሙያውን ክብርና ዝና ለመጠበቅ የሚከተሉትን እሴቶች ማክበር፣ በተግባርም ማሳየት ይኖርበታል፡፡

#ሙያዊ ነፃነትን፣ ገለልተኝነትን ቅንነትን በስራው ላይ በተጨባጭ ማሳየት፣
#የባለጉዳዩን ምርጫ ፣ፍላጎትን ጥቅም በማስቀደም በርሱ ፍላጎት መሰረት የጥብቅናውን ስራ ማከናወን፣
#የባለጉዳዩን ጥቅም በተቻለ መጠን ሁሉ ለማስጠበቅ ትጋት ማሳየትና ተገቢውን ጥረት ማድረግ፣
#የሙያውን ወይም የራሱን ክብና ዝና በሚያስጠብቅ መልኩ የግል ህይወቱን መምራት፣
#የጥብቅና ስራ የሚጠይቀውን ሙያዊ ኃላፊነትና የስራ ደረጃ አሟልቶ መገኘት፣
#በክርክር ሂደት ለዳኝነት አገልግሎቱ ውጤታማነት ሲባል ፍ/ቤቶች ከፍትሃዊ ውሳኔ እንዲደርሱ ያለበትን ግዴታና ኃላፊነት መወጣት ናቸው፡፡
#ETA

" ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም "

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፤ ባዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወይም የስልጠና ተቋማት በሁሉም መርሃ ግብሮች #የሕግ እና #የመምህርነት ትምህርት ዘርፎችን #አሁንም ማስተማር እንደማይችሉ ተገልጿል።

ከዚህ በፊትም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁሉም መርሃግብሮች የሕግ እንዲሁም የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ የተደረገ ሲሆን አሁንም በአዲሱ መመሪያ የሕግ እና የመምህርነት ትምህርት መስጠት አይችሉም ተብሏል።

ሌሎች በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ #ረቂቅ መመሪያ ላይ ምን ተካቷል ?

- ማንኛውም ተቋም አዲስ ፕሮግራም ለመከፈት ወይም ነባሩን ፕሮግራም ለማስቀጠል የፍላጎት ዳሰሳ፣ የገበያ ጥናት እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውደ ጥናት ማካሄድ ይኖርበታል፡፡

- ለማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፕሮግራም ፈቃድ የሚሰጠው ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን መስፈርቶች አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል፡፡

- የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከፍቷቸው ፕሮግራሞች ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን የመመዘኛ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

- ለማንኛውም ተቋም የሚሰጥ ፈቃድ የሚያገለግለው በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ተገምግሞ ለተፈቀደለት ካምፓስና የትምህርት መስክ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም ተቋም የጤና የትምህርት መስኮችን መስጠት የሚችለው በመደበኛ መርሃ ግብር ብቻ ይሆናል፡፡

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በርቀት ትምህርት መርሃ ግብር ማስተማር የሚችለው ከድንበር ተሻጋሪ ወጪ በመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም፡፡

- ማንኛውም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም የትኛውንም ስልጠና በርቀት መርሃ ግብር ለማሰልጠን የሚቀርብ የፈቃድ ጥያቄ የማይስተናግድ ይሆናል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም #በህክምና_ዶክትሬት እና #በስፔሻሊቲ ትምህርት ፈቃድ ለማግኘት ተቋሙ #የህክምና_ሆስፒታል ሊኖረው ይገባል።

- በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ ጊዜው ሳያበቃ የስርዓተ ትምህርት ወይም የዲግሪ ስያሜ ለውጥ ካለባለስልጣኑ ፈቃድ ወጪ ማድረግ አይችልም።

- በሀገር ደረጃ በትምህርት ፖሊሲ ስርዓተ ትምህርቱ እስካልተቀየረ ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ወይም በካምፓስ ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ/ፈቃድ እድሳት ጊዜው እስካላበቃ ድረስ በሌሎች ካምፓሶች መተግበር ወይም መጠቀም ይችላል።

- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በበየነ መረብ ወይም በርቀት ትምህርት መርሃ-ግብር ፈቃድ ሲጠይቁ በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ስርዓተ-ትምህርቱ ቀድሞ መገምገም እና ተገቢ ማስተካከያ ተደርጎ መፅደቅ ይኖርበታል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በብሎክ ኮርስ ትምህርት ለመስጠት ያለው አመቺነትና ተገቢነት እንዲሁም የትምህርት ጥራት ላይ የሚኖረውን ተፅህኖ ከግምት በማስገባት ስርዓተ ትምህርቱ ከጸደቀ በኃላ ሊተገብር ይችላል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያገኘው ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን መሪ አስፈፃሚ ሕይወት አሰፋ ነው።

@tikvahethiopia