አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#የጠበቆች_የሙያ_ስነ_ምግባር_መርሆዎች
==========================

የሰው ልጆች ሁሉ በሰብዓዊ ፍጡርነታቸው የተቸሩትን መብቶችና መሰረታዊ ነፃነቶች እንዲጎናፀፉ ለማድረግ ብቃት ያለው የህግ ምክር አገልግሎት የሚያገኙበት መንገድ ማመቻቸት አስፈላጊ እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት የህግ ሙያተኞችን ሚና ለመወሰን በደነገገው መሰረታዊ መርሆዎች ላይ በሚገባ ተመልክቷል፡፡
A) #የዜጎች መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች በተለይም ግልጽና ፍትሃዊ የሆነ ዳኝነትን የማግኘት መብት በተለያዩ የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችና መግለጫዎች ላይ የሰፈረ ከመሆኑም ባሻገር በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙና፣ የተከሰሱ እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች በተቻለ መጠን ተገቢ የህግ ምክር አገልግሎት ማግኘት የሚገባቸው መሆኑንና ከጠበቆቻቸውም ጋር የመገናኘትና የመወያየት፣ የውይይቱ ሚስጥራዊነትም እንዲጠበቅላቸው ሙሉ ነፃነት ያላቸው መሆኑ ተደንግጓል፡፡ በአንድ የፍትህ ስርዓት ውስጥ የዜጎች እኩልነት ተከብሮ፣ ፍትህና ርቱዕ የተሞላበት ዳኝነት እንዲያገኙ ከተፈለገ ሁሉም ዜጎች በተቻለው አቅም ሁሉ የህግ አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል ለፍትሃዊ የህግ ስርዓት መጎልበትና ለሰብአዊ መብቶች መከበር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ በፍትህ ስርዓቱና በህግ የበላይነት ላይም ሰፊው ህብረተሰብ ፅኑ እምነት እንዲያሳድርና የሁሉም ሰው መብት ህግ ባስቀመጠው ወሰንና አግባብ እንዲከበር ጠንካራ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ሊኖር የሚገባው ሲሆን ከፍተኛ ስነ ምግባር የተላበሱ የህግ ሙያተኞችና ጠበቆችም እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆናቸውን እንገነዘባለን፡፡
እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1990 ዓ.ም የወጣው የተባበሩት መንግስታት የህግ ሙያተኞች ሚና መሰረታዊ መርሆዎች ከሚደነግጉት ሁኔታዎች መካከል አንዱና ዋንኛው ሁሉም ሰዎች በወንጀል የፍርድ ሂደት መሰረታዊ መብቶቻቸውን በሚገባ ለማስጠበቅና ራሳቸውን ለመላከል ተደራሽነት ያለው የህግ ምክር አገልግሎትና የህግ አማካሪዎችን ወይም ጠበቆችን በቀላሉ ማግኘት እንደሚገባቸውና መንግስታትም በዚህ ረገድ ያለ አንዳች አይነት አድሎአዊ ልዩነት ሁሉም ዜጎች ይህንን አገልግሎት የሚያገኙበት ውጤታማ ስልቶችና ስነስርዓቶች መቀየስ ይጠበቅባቸዋል፡፡
B) #ከዚህ አኳያ መንግስታት የተለየ ኃላፊነት እንዳለባቸውና ይህ ኃላፊነትም በቂ ገንዘብ በመመደብ ድሆችና ሌሎችም የተገፉ የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የህግ ምክር አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግን ይጨምራል፡፡
C) #የህግ ባለሙያዎች ማህበራትና ጠበቆችም በዚህ ረገድ ከመንግሰታት ጋር በመተባበር ነፃ የህግ አገልግሎት ለመግዛት የኢኮኖሚ አቅማቸው ለማይፈቅድ ዜጎች እንዲመቻች ለማድረግ የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ አላባቸው፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ሁሉም የህብረተሰቡ ክፍል በህግ ስለተረጋገጠላቸው መሰረታዊ መብቶችና ግዴታዎቻቸው እንዲያውቁ ለማድረግ መንግስትና ጠበቆች እንዲሁም የህግ ሙያተኞች ማህበራት በጋራ መረባረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ መልኩ በወንጀል የፍርድ ሂደት ውስጥ የተያዙና የተከሰሱ ሰዎች መሰረታዊ መብቶቻቸውና ነፃነቶቻቸው እንዲጠበቁ የማድረግ ኃላፊነት የመንግስት እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ከዚህ አንፃር መንግስት በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች እንደተያዙ ወዲያውኑ በሚመለከታቸው የፍትህ አካላት በሁሉም የወንጀለ ፍትህ አስተዳደር ሂደቶች በፈለጉት ወይም በመረጡት የህግ አማካሪ የመወከልና ተገቢውን የምክር አገልግሎት የማግኘት መብት እንዳላቸው እንዲያዉቁ መደረጉን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

D) #በተለይም የመክፈል አቅምን በማጣት ምክንያት የህግ ምክር አገልግሎት ማግኘት ያልቻሉ ግለሰቦች በቂ ልምድና ብቃት ያለው የህግ አማካሪ በመንግስት ወጪ እንዲያገኙ መደረግ አለበት፡፡
E) #በመንግስት የሚመደብላቸውም የህግ አማካሪ ከተከሰሱበት ጉዳይ ውስብስብነት ጋር በሚመጣጠን መልኩ በቂ ልምድና ችሎታ ያላቸው መሆን ይገባዋል፡፡ ችሎታቸውና ልማዳቸው እምብዛም ያልሆነ የህግ አማካሪዎችን መመደብ በዚህ ረገድ በመንግስት ላይ የተጣለውን ኃላፊነት መንግስት በሚገባ እንዳልተወጣው ነው የሚያስቆጥረው፡፡ በርግጥ በአብዛኛው በወንጀል ጉዳዮች ላይ ነው የመክፈል አቅም ለሌላቸው ግለሰቦች በመንግስት ወጪ ጠበቃን ማቆም የሚገባው፡፡ ይሁን እንጂ ከወንጀል ጉዳይ ዉጪ በሆነ መልኩ ለተያዙ ግለሰቦች በመንግስት በነፃ ጠበቃ የማቆም ግዴታ እንዳለበት ነው ተደንግጎ የሚገኘው፡፡
F) #በአለም አቀፍ መርሆዎች የተደነገገው ደረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ በተለይም የተያዙ ሰዎች ጠበቃ የማቆም አቅም በማይኖራቸው ጊዜ መንግስት በተቻለው አቅም ሁሉ ከተያዙበት ጊዜ አንስቶ በ48 ሰዓታት ውስጥ ነው ነፃ የህግ አገልግሎት የሚሰጣቸውን የህግ አማካሪ ሊመደብላቸው የሚገባው፡፡ ከዚህ የምንረዳው በሁሉም የፍርድ ሂደቶች ዜጎች በህግ አማካሪ ሳይወከሉ በፍርድ ሂደት እንዳያልፉ የሚደረግ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር አቅም ያጡ ግለሰቦች በድህነታቸው ምክንያት ብቻ የህግ ምክር ሳያገኙ በማንኛውም የፍርድ ሂደት እንዲሳተፉ ወይም ለፍርድ እንዲቀርቡ ከተደረገ የሁሉም ሰዎች ፍትሃዊ፣ሚዛናዊ ግልፅ የሆነ ዳኝነት የማግኘት መብት ተከብሯል ለማለት አያስደፍርንም፡፡
የተያዙ ሰዎች በእስር ወቅት በመንግስት ከተመደበላቸው የህግ አማካሪ ጋር የሚገናኙበትና በነፃነት የሚወያዩበት በቂ እድል ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ እነዚህ ሰዎች ከህግ አማካሪዎቻቸው ወይም ጠበቆቻቸው ጋር የሚያደርጉት ምክክርና ውይይት በየትኛውም መልኩ በህግ አስከባሪ ባለስልጣናት ሊደመጥና ይዘቱም ቅድመ ምርመራ ሊደረግበት አይገባም፡፡
G) #ጥብቅና ከፍተኛ ኃላፊነት የሚያስከትልና በፍትህ አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው ሙያ በመሆኑ ከጠበቆች ከፍ ያለ ስነ ምግባር ነው የሚጠበቀው፡፡ ከዚህም የተነሳ ጠበቆች በግል ህይወታቸውም ጭምር የሙያውን ክብርና ዝና ከሚያጎድፉ ባህሪያት ራሳቸውን ማግለልና በሚገባ መጠበቅ አለባቸው፡፡ ከዚህም አልፍው የሙያ ባልደረቦቻቸው የስነ ምግባር ጉድለት እንዳያሳዩ የመምከርና የስነ ምግባር ጉድለት ፈፅመው ሲገኙ ደግሞ ለተገቢው አካል የመጠቆም ኃላፊነት አለባቸው፡፡

ለዚህ ነው ጠበቆች ሁሌም ቢሆን የሙያቸውን ክብርና ዝና በመጠበቅ የፍትህ አስተዳደሩ ዋልታ መሆን ይገባቸዋል የሚባለው፡፡
H) #አንድ ጠበቃ የሙያውን ክብርና ዝና ለመጠበቅ የሚከተሉትን እሴቶች ማክበር፣ በተግባርም ማሳየት ይኖርበታል፡፡

#ሙያዊ ነፃነትን፣ ገለልተኝነትን ቅንነትን በስራው ላይ በተጨባጭ ማሳየት፣
#የባለጉዳዩን ምርጫ ፣ፍላጎትን ጥቅም በማስቀደም በርሱ ፍላጎት መሰረት የጥብቅናውን ስራ ማከናወን፣
#የባለጉዳዩን ጥቅም በተቻለ መጠን ሁሉ ለማስጠበቅ ትጋት ማሳየትና ተገቢውን ጥረት ማድረግ፣
#የሙያውን ወይም የራሱን ክብና ዝና በሚያስጠብቅ መልኩ የግል ህይወቱን መምራት፣
#የጥብቅና ስራ የሚጠይቀውን ሙያዊ ኃላፊነትና የስራ ደረጃ አሟልቶ መገኘት፣
#በክርክር ሂደት ለዳኝነት አገልግሎቱ ውጤታማነት ሲባል ፍ/ቤቶች ከፍትሃዊ ውሳኔ እንዲደርሱ ያለበትን ግዴታና ኃላፊነት መወጣት ናቸው፡፡
#የጥብቅና #ፈቃድ
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥብቅና ፈቃድ፣

ምዝገባ እና ፈተና መቼ እንደሆነ እስከ አሁን የታወቀ ነገር የለም።
አዲስ ነገር ሲኖር የምናሳውቅ ይሆናል።
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #ህግ #Lawsocieties #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
#የፌዴራል #የማናቸውም #ፍርድ_ቤት #የጥብቅና #ፈቃድ መግቢያ #ፈተና መውሰድ የሚፈልግ ሰው ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟላ መመዝገብ የሚችል መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀፅ 6፣13፣16/2/ እና 21/3/ በተደነገገው መሰረት እንገልፃለን::
Stay Connected with AleHig!
https://linktr.ee/alehig
alehig.com
Follow us for real-time updates and empower yourself with knowledge to navigate the legal landscape in Ethiopia!
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE #የሕግአማካሪ
Telegram
https://t.me/AleHig

Telegram_Group
https://t.me/AleHig_Group

Facebook Page
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

LinkedIn
https://www.linkedin.com/company/alehig/

YouTube
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

TikTok
https://www.tiktok.com/@alehigofficial

Instagram https://www.instagram.com/alehigofficial

Twitter /X
https://x.com/AlehigOfficial?t=yFRauAZ7v70Je2MEPIGGsQ&s=09

official website
https://www.alehig.com

#LegalAwareness #AleHig #LegalUpdates #AccessToJustice