አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ

ለእንጀራ፣ ለዳቦ እና ለተለያዩ የሸቀጥ እቃዎች መጠቅለያነት የሚውለውን የአንድ ብሩን ፕላስቲክ ይዞ መገኘት ከ2,000 እስከ 5,000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ጸደቀ፡

ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ፤ " ዜጎችን በማያውቁት ጉዳይ ለቅጣት የሚዳርግ ነው " የሚል ትችት ከምክር ቤት አባላት ቀርቦበታል፡፡

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ የጸደቀው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ፤ ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኝ ከ2,000 እስከ 5,000 ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፡፡

ያመረተ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ለገበያ ያቀረበ ወይም የሸጠ፣ ለንግድ ዓላማ ያከማቸ ወይም ይዞ የተገኘ ከ50,000 ብር በማያንስና ከ200,000 ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከ5 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት  እንዲቀጣ አዋጁ ያዝዛል፡፡

የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) የአዋጁን ይዘት በንባብ ከቀረቡ በኃላ የም/ቤት አባላት ጥያቄ አቅርበዋል።

የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) ህዝባችን በፕላስቲክ እቃ ይዞ ወደ ቤቱ ከገባ ይጣለው ? ወይስ መልሶ ለአካባቢ ጥበቃ ያስረክበው ? የሚል ጥያቄ ጠይቀዋል።

አክለው የምናመርተው የፕላስቲክ ውጤት ዳግም እንድንጠቀምበት የሚያደርግ ቢሆን አይሻልም ወይ ? ምክንያቱም 10 ጊዜ የምጠቀምበትን ፕላስቲክ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቀም ማለት ተገቢ አይደለም፣ አዋጁ ፕላስቲኩን ከተጠቀምኩበት ወዲያ የት ማስቀመጥ እንዳለበት አላስቀመጠም ብለዋል፡፡

አዋጁ ይዞ የተገኝ እንዲቀጣ ይደነግጋል ህዝባችን የዚህ ግንዛቤ ይኖረዋል ወይ ? የትኛው ፕላስቲክ እንደሆነ የመለየት ግንዛቤስ አለው ወይ ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ሌላ አንድ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው ማንኛውም ሰው ፕላስቲክ ይዞ ከተገኘ ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፤ ይህ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ ጋር  እንዴት ታየ ? በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ሊጠቀመው ስለሚችል ጫና አይፈጥርም ወይ ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ  አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ፌስታሎችን ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍልም ስለሚጠቀማቸው ቅጣቱ ያን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል፡፡

" ለምሳሌ አንዲት አሮጊት ወይም ሽማግሌ የሁለት ብር ዳቦ ወይም የአስር ብር ስኳር ገዝተው ሲሄዱ 5 ሺህ ብር ክፍሉ ቢባሉ ላይኖራቸው ስለሚችል ቅጣቱ ከ5 ሺህ ወደ 2 ሺህ ዝቅ እንዲል ተደርጓል ይህም የህብረተሰቡን የመክፈልም አቅም ከግንዛቤ ያስገባ ነው " ሲሉ አስረድተዋል፡፡

" የፕላስቲክ ከረጢቶች ከቅጣቱ በላይ ሀገርን የሚጎዱ ናቸው እስከ መቶ ዓመት ድረስም አይበሰብሱም " ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ " ከዚህ አንጻር ቅጣቱ ሃያም ሰላሰም ሺህ ቢሆን ሀገርን ለማትረፍ ነው " ብለዋል፡፡

ለህዝቡ ግንዛቤ ለመስጠትም ከመጪው ሃሙስ ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ይካሄዳል ሲሉ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

አዋጁ የፕላስቲክ ጫማዎችን፣ የውሃ ኮዳዎችን እና ወፍራም የፕላስቲክ ውጤቶችን አይጨምርም ተብሏል።

አዋጁ ማንኛውም ሰው ከመኖሪያ ቤቱ ድንበር አንስቶ ከሃያ ሜትር በላይ አካባቢውን የማጽዳት ግዴታንም ያስቀምጣል፡፡

አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

#ShegerFM101.2

@tikvahethiopia
" የተርሚናል አገልግሎት ክፍያው የሚፈጸመው ማህበራቱ በስኬት ባንክ በከፈቷቸው አካውንቶች በቴሌብር አማካኝነት ነው " - ማህበራቱ

ነባር ተራ እስከባሪዎችን በመተካት የተርሚናል አስተዳደር እና ቁጥጥር ስልጠና የወሰዱ ከ 80 በላይ በሚሆኑ ማህበራት(ኢንተርፕራይዝ) የተደራጁ ተራ አስከባሪ ወጣቶች ዛሬ ከሰአት ስራ ጀምረዋል።

ዛሬ ጠዋት የአዲስ አበባ ከተማ ስራ እና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ፣የአዲስ አበባ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ያብባል አዲስ በተገኙበት የተመረቁት 996 የታክሲ ተራ አስከባሪ ወጣቶች ከሰአት በኋላ ስራ መጀመራቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

ነባሮቹን ተራ አስከባሪ ወጣቶች በመተካት ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ የገቡት ወጣቶች በየወረዳው የተደራጁ ሲሆን በከተማዋ በሚገኙ 87 ተርሚናሎች ወደ ስራ ገብተዋል።

የተርሚናል አገልግሎት ክፍያው የሚፈጸመው ማህበራቱ በስኬት ባንክ በከፈቷቸው አካውንቶች በቴሌብር አማካኝነት መሆኑን ቲክቫህ ያነጋገራቸው የማህበራቱ አባላት ገልጸዋል።

ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ በሚል ከትላንት ጀምሮ የተበተነው እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው በራሪ ወረቀት የተቀመጠው የአገልግሎት ክፍያ በየትኛውም መነሻ እና መድረሻ ላይ 10 ብር መሆኑን በመግለጽ ክፍያውንም በዲጂታል መንገድ ብቻ እንዲፈጸም ይጠይቃል።

በተጨማሪም ከተቀመጠው የአገልግሎት ክፍያ በላይ የከፈለ አሽከርካሪም ሆነ ረዳት 4000 ብር እንደሚቀጡ ይገልጻል።

ነባር ተራ አስከባሪዎች በመረጡት የስራ ዘርፍ እንዲሰማሩ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረግላቸዋል ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
income_tax_amendment_proclamation-_amharic-_05282025.pdf
864.3 KB
#ለመረጃ፡ የገንዘብ ሚኒስቴር የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ የመጀመሪያ ረቂቅ አዘጋጅቷል! የረቂቁን የአማርኛ ቅጂ ማንበብ ለምትፈልጉ....
ከሰራተኛው ደሞዝ የሚነጥቀው አዋጅ ድንጋጌ ተሰረዘ!
በዚህ ጉዳይ ላይ ቀደም ሲል ረቂቅ አዋጁ ላይ ከሰራተኛ ደሞዝ መቀነስ ተገቢ እንዳሎነ እና ሰራተኛው ላይ ሌላ የመከራ ቀንበር መጫን እንደሆነ አንስቼ ይህ ድንጋጌ ከረቂቅ አዋጁ ላይ መውጣት እንዳለበት ከብዙወቻቹ ጋር መወያየታችን ይታወቃል፡፡ ምናልባትም ፓርላማው ከተሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ውድቅ ያደረገው ድንጋጌ ይመስለኛል፡፡ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ አሁንም ግን ኢትዮጵያ እያጸደቀቻቸው ያሉ ችኩልና ህዝብን ለበለጠ መከራ ሚዳርጉ አዋጆች በድጋሚ ሊጤኑ ይገባል።
በፊቃዱ ደሪባ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446 ኛው አመተ ሒጅራ የኢድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
EID MUBAREK🙏
Ethiopia’s Investment Board has issued Directive No. 1082/2025, replacing Directive No. 1001/2024. This significant update overhauls how foreign investors can participate in previously restricted export, import, wholesale, and retail trade sectors. The new policy shifts focus from specific financial thresholds and structural requirements towards verifying investor integrity and capacity.https://lawethiopiacomment.wordpress.com/2025/06/07/ethiopia-refines-foreign-trade-investment-rules-shifting-from-quantitative-hurdles-to-due-diligence/
#ለቲክቶከሮች እና #የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች #አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ!
ጤና ይስጥልኝ! ሚኪያስ መላክ ነኝ፣ ጠበቃ እና የህግ አማካሪ።
በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በቲክቶክ ላይ ንቁ ተሳትፎ ለምታደርጉ ሁሉ፣ አሁን የምሰጣችሁን ማስጠንቀቂያ በደንብ እንድትገነዘቡት እጠይቃለሁ። የቅርብ ጊዜዎቹ #ቲክቶከሮች #ጃኒ በትክክለኛው ስሟ ስመኝ ገብሩ እና የሌሎችን ቲክቶከር ጉዳዮችን ስንታዘብ ያየነው እና የተመለከትናቸው ዋነኛ ምሳሌዎች ናቸው። ሁሉም በፖሊስ ተይዘው ወደ ጣቢያ መወሰዳቸው፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሕግ ተጠያቂነትን በሚመለከት ሊገነዘቡት የሚገባ ትልቅ ትምህርት ነው። የእናንተ ተፅዕኖ ፈጣሪነት የራሱ የሆነ ኃላፊነት አለበት።
ጥንቃቄ አይለያችሁ!
አንድ ስኬታማ ሰው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚኖረው እንቅስቃሴ የሚያስከትለው ጉዳት የጎላ ነው። አንድ ተራ ሰው በሰራው ስህተት ጉዳዩ ተራ ሆኖ ሊቀር ቢችልም፣ እንደ ጃኒ ያሉ ብዙ ተከታይ እና አድማጭ ያላችሁ ሰዎች ግን የሚፈጠረው መዘዝ እጅግ ትልቅ ነው። ተጠንቀቁ!
በተለይ "የአፍ ወለምታ" እና መሰል ንግግሮች የሚያስከትሉትን የህግ ተጠያቂነት አቅልላችሁ እንዳትመለከቱ። ያላሰባችሁት ንግግር ከባድ የህግ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል።
የሕግ አማካሪ ወይም ቋሚ ጠበቃ ይኑራችሁ!
ይህ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ስራችሁን እና ንግግራችሁን ከህግ አንፃር ሳንሱር የሚያደርግ እና ከህዝብ ጋር ከመድረሱ በፊት አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ የህግ አማካሪ ያስፈልጋችኋል። ይህ ከብዙ ችግሮች ሊታደጋችሁ ይችላል። የጃኒ እና በእስር ላይ የሚገኙ ቲክቶከሮች እና ጉዳዮች ይህንን ፍላጎት በግልጽ ያሳያሉ።
#አላውቅም"፣ #ቀልድ ነው"፣ "#እድሜዬ አልደረሰም" - እነዚህ የህግ መከላከያ ሊሆኑ አይችሉም!
ምንም እንኳን ታሳቢ የሚደረጉ ሁኔታዎች ቢኖሩም በወንጀል ሕጉ መሰረት ጉዳዩ የሚታየው በህጉ ላይ በተመለከቱት መደበኛ ድንጋጌዎች መሰረት ነው። ስለዚህ፣ እድሜም ሆነ የትምህርት ደረጃ ለፈጸሙት ወንጀል መከለያ ሊሆን እንደማይችል ልብ ይበሉ።
ማህበረሰብን/ህዝብን/ብሄርን ማጥላላት ወንጀል ነው፣ ያስጠይቃልም!
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስትለጥፉ ወይም ስትናገሩ ዘርን፣ ሀይማኖትን፣ ብሄርን ወይም ማንኛውንም የማህበረሰብ ክፍል የሚያንቋሽሽ ወይም ጥላቻን የሚያነሳሳ ነገር ከመናገር ተቆጠቡ። ይህ በህግ የሚያስቀጣ ወንጀል መሆኑን አትርሱ።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምታደርጉትን እንቅስቃሴ በጥንቃቄ እንድታደርጉት አሳስባለሁ። ህጉን ማወቅ ከችግር ያድናል!
Mikias Melak AleHig
ጠበቃ እና የህግ አማካሪ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የፍትህ ሚኒስቴር እያከናወነ ላለው የዳሰሳ ጥናት መረጃ የማህበራችን አባላት ይህንን ፎርም እንዲሞሉ እናሳውቃለን::

https://docs.google.com/forms/d/1QPTURT6BE6ij3zLpc2t6u3vLQ69tZCNK_RDumfK5Tow/edit?usp=sharing_eil_se_dm&ts=6842988b
"ፀዴ ናቸው"

የ21 ዓመቷ ጃኒ ገብሩ በአፍ ወለምታ ሸቤ ገብታ ችሎት ስታፍታታ ውላለች።

ችሎት ፊት ቀርባ "የድሬዳዋ ሰዎች ፀዴ ናቸው"ብላ ስትናገር ሙሉ ችሎቱ በሳቅ ወድቋል። እውነተኛ ስሟ 'ስመኝ ገብሩ' ነው ቢባልም ትክክለኛው የመታወቂያ ስሟም ሆነ የሚዲያ ስሟ 'ጃኒ' መሆኑ ተረጋግጧል። ...ችሎቱን ሲከታተል በነበረው ጠበቃ ዮሀንስ ዘውዱ አንደበት ከአፍ የወደቀች ጥሬ የምታክል ሚጢጢ ናት ተብላ የተገለፀችው ጃኒ "በቀጣይ ስመጣ ሺቲ ለብሼ ነው የምመጣው" ብላ ችሎቱን ፈገግ አሰኝታዋለች። ጃኒ 1ሳምንት ተጨምሮባት ጉዳዩ እንደሚጣራ ተነግሯታል። ቀላሉን ያድርግላት። መሳሳቷ  ለትምህርት ይሁን🙏
ፀሀፊ ፦ ኪዳ የገጠር ልጅ_ቅዱስ

ዋስትና ተከልክሎ ለሰኔ 09/2017 ተቀጠረች።
ሊሰረዙ የሚችሉ የስራ መደቦች‼️
እንደ ፎርብስ መፅሄት ትንበያ እ.ኤ.አ. በ2030 ሙሉ ለሙሉ ሊሰረዙ የሚችሉ 21 የስራ አይነቶችን አስቀምጧል‼️
በዚህም ወደ 92 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰራተኞች በ 2030 ሙሉ በሙሉ ስራቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም በ 2025 የወደፊት የስራ ሪፖርት ላይ ትንበያ አስቀምጧል።
ለእነዚህ የስራ መደቦች መጥፋት እንደ ዋነኛ ምክንያት የተጠቀሰው የእነዚህ የስራ መደብ ሰራተኞች በ Artificial intelligence system እና በ robot ሊተኩ ይችላሉ በሚል ነው።
በ2030 ሊጠፉ ይችላሉ የተባሉት የስራ መደቦች ዝርዝር;-👇👇
🎯የፖስታ አገልግሎት ጸሐፊዎች
🎯የባንክ ከፋዮች/tellers/ እና ተዛማጅ ጸሐፊዎች
🎯የችርቻሮ ገንዘብ ተቀባዮች እና የቲኬት ፀሐፊዎች
🎯የአስተዳደር ረዳቶች እና ዋና ጸሐፊዎች
🎯የኅትመትና ተዛማጅ ሠራተኞች
🎯የሂሳብ አያያዝ፣የመፅሐፍ አዟሪዎች እና የደመወዝ ፔሮል ሰራተኞች
🎯የመጓጓዣ አስተናጋጆች እና መሪዎች
🎯ቤት ለቤት የሚሸጡ ሰራተኞች፣ የዜና እና የመንገድ አቅራቢዎችና ተዛማጅ ሰራተኞች
🎯ግራፊክ ዲዛይነሮች
🎯ቅሬታ ሰሚዎች፣ፈታኞች እና መርማሪዎች
🎯የህግ ባለስልጣናት
🎯የሕግ ጸሐፊዎች
🎯ቴሌማርኬተሮች
🎯መሰረታዊ የአይቲ ድጋፍ ሚናዎች
🎯የማሽን ኦፕሬተሮች
🎯የመጋዘን ሰራተኞችን መምረጥ እና አያያዝ
🎯የኢንሹራንስ አዘጋጆች
🎯የጉዞ ወኪሎች ናቸው።
አሁን ላይ የ Artificial intelligence system እንዲሁም Robot በዓለም ላይ የሰዎችን ስራ በመተካት እየሰሩ ይገኛሉ። ከላይ ያቀረብነው ትንበያ በተለይ በአውሮፓ ሀገራት እንዲሁም በአሜሪካ እውን ሊሆን እንደሚችል እና ቀስ በቀስ ወደ ሌሎች ሀገራት ሊዛመት እንደሚችል መረጃዎች ያመላክታሉ(አዩዘሀበሻ)።
#የፍርድ_ቤቱን_ውሳኔ_አጥብቄ_የምቃወም_ቢሆንም_እቀበላለሁ ፣ የዚህን ውጤት የመጨረሻነት ተቀብያለሁ ፤ እንደ ህዝብ ለአንድነታችን እና ለዲሞክራሲያችን ጥንካሬ ስል እሺ እላለሁ።"
ይህን ታሪካዊ ንግግር ያደረገው ለ43ኛ የአሜሪካን ሀገር ፕሬዚዳንትነት ከ ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ ጋር የተወዳደረው እና በጠቅላይ ፍርድ ቤት ብይን 5 -4 በሆነ ድምጽ የተወሰነበት #አል_ጎር ነበር!

ጉዳዩን እንበልጥጠው!

ፍሎሪዳ በአሜሪካ ካሉ ግዛቶች ውሰጥ የምትገኝ እና በፕሬዝዳንትነት ምርጫ ላይ ሁነኛ ሚና ከሚጫወቱ እና ወሳኝ ከሚባሉ ግዛቶች አንዷ ናት ።
ግዛቷ ውስጥ አንድ ሕግ አለ በከባድ ወንጀል የተፈረደበት እና መሰየም ያልተደረገለት ሰው የመምረጥ መብት ይነፈጋል ።

በምርጫው ጊዜ ከዚህ በፊት ወንጀል ሰርተዋል ተብሎ በ Database ተመዝግቦ የሚገኙ ሰዎች ስም ከሌሎች ወንጀል ካልሰሩ ሰዎች ፤ እንዲሁም ወንጀል ቢሰሩም የመምረጥ መብትን ከማያስከለክሉ ቀላል የወንጀል ዓይነት ከሰሩ ሰዎች ጋር የስም መመሳሰል በመፈጠሩ በግዛቲቱ ወደ 91,000 ሰዎች እንዳይመርጡ ተደርገዋል ።

እነዚህ የስም መመሳሰሎች ደግሞ ጥቁር አሜሪካዊያን እና አል ጎርን ይመርጣሉ ተብሎ የሚጠበቁ ሰዎች እንደሆኑም ይገለጻል ፤ ይህ ውጤት አጠቃላይ የምርጫ ውጤትም ላይ ጥላ አጥልቶ ነበር ፤ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ በኋላ በመካከላቸው የነበረውን ልዩነት እንመልከት

ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ 2,912,790
አል ጎር 2,912,253
ልዩነት 537 ድምጽ ብቻ
91,000 ሰው በስም መመሳሰል ባይወገድ እና አል ጎርን ቢመርጥ ወይም አብዛኛው አል ጎርን ቢመርጥ በአሜሪካን ታሪክ አል ጎር 43ኛ ፕሬዚዳንት ይሆን ነበር ።

የስም መመሳሰልን ጉዳይ እናፍታታው ።

በፍሎሪዳ ግዛት ውስጥ ወንጀል ከሰራህ ስምህ ዳታቤዝ ላይ ይመዘገባል ፤ በተለይም ከባድ የሚባሉ ወንጀሎቹን ከሰራህ የመምረጥ መብትህ ይነፈጋል ዳታ ቤዝ ላይ Flagged 🛑 ይደረጋል ።

ለምሳሌ 1.Alex L.Smith (ከባድ ወንጀል የሰራ)
2.Allex A.Smith (ወንጀል ያልሰራ) ግን በስም መመሳሰል ከምርጫ የተወገደ

እንግዲህ በዚህ መልክ ሀቁን ያጣው አል ጎር ፤ ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ "ምንም ጥርጥር አይኑር፣ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አጥብቄ ባልስማማም እቀበላለሁ" በማለቱ ይህ ንግግሩ ለፍርድ ቤቱ የሰጠው ቦታን በማመልከት ታሪካዊ ንግግር ሊባል ችሏል ፤ ከግል ምኞቱ በላይ የሀገሪቱን መረጋጋት በማስቀደም ሕገ መንግሥታዊ ቀውስ እንዳይፈጠር ረድቷል ተብሎም ተንቆለጳጵሷል ።

#ወደ_መልዕክቴ_ልምጣ👇

የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 79 ንዑስ አንቀጽ 2 እና 3 እንደሚከተለው ይነበባል ።

2. በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግሥት አካል፣ከማንኛውም ባለሥልጣን ሆነ ከማንኛውም ሌላ ተጽዕኖ ነጻ ነው፡፡
3. ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነጻነት ያከናውናሉ፡፡ ከሕግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም፡፡

ፍርድ ቤቶቻችን ላይ ችግር የለውም ካላችሁ 10 ገጽ የሚሆኑ ችግሮችን ልጽፍላችሁ እችላለሁ የ አስፈጻሚው አካል ጣልቃ ገበነት ፣ ሙስና ፣ የዳኞች ብቃት ማነስ ፣ የዳኞች ክፍያ ማነስ ለስራው ተነሳሽነት እንዲያጡ ማድረግ ፤ በቴክኖሎጂዎች አለመታገዝ..........

ግን ከእነዚህ ሁሉ ችግሮችም ጋር በቻልነው አቅም የፍርድ ቤቱን ገለልተኝነት እናክብር ፤ ፍርድ ቤቶችን ከአስፈጻሚው አካል ከጫና ነጻ እንዲሆኑ እንስራ ፤ በሕግ እና በሕግ ብቻ እንዲመሩ እናበረታታ ፤ ስነ ምግባር የጎደላቸውን ዳኞችን በሕጉ መሰረት እንቅጣ ፤ ፍርድ ቤት የሕዝብ አመኔታ የሚጣልበት ተቋም ስህተት ቢሰራም እንኳን ሕጉ ባስቀመጠው በራሱ ሰንሰለት የሚስተካከልበት ተቋም እንጂ የሕዝብ የጩኸት ምንጭ እንዳይሆን እንተባበር እንጂ የማንም አካል ጣልቃ ገብነትን አንሻት አንመኝ! ምክንያቱም ውጤቱ ከዚህም እጅግ የከፋ ነውና! አበቃሁ!
#ሰላም ✌️
Abebayehu Geta Enaro
መምህር ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ
Alternative legal enlightenment & Service
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
https://t.me/AleHig
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
#የሕግ_እውቀት alehig.com
#አለሕግ #ህግ #ሰበርመዝገብ #ሕግ_መረጃ #እግድ