#ተከሳሽ_በሌለበት_የወንጀል_ክስን_ማየት፣
በመርህ ደረጃ ክስ መሠማት ያለበት ተከሳሽ ባለበት ነው፡፡ በወንጀል ተጠርጥሮ የተከሰሰ ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱ ደርሶትና ተረድቶት የመሰማት ሕገ መንግሥታዊ መብት እንዳለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንሥግሥት አንቀጽ 2ዐ ደንግጓል፡፡ ይህ ማለት ግን የወንጀል ክስ ሁሉ ተከሳሽ ፍርድ ቤት ካልቀረበ ታይቶ አይወሰንም ማለት አይደለም፡፡
በሕግ ተለይተው በተመለከቱ ወንጀሎች ላይ ተከሳሽ በሌለበትም ክሱን መርምሮ መወሰን ይቻላል፡፡ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ አራተኛ መድሐፍ አንቀጽ 2 ልዩ ሥነ ሥርዓት በሚለው በምዕራፍ አንድ ቁጥር 160/2/ ሥር ነገሩ ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን ተከሳሽ ካልቀረበ ወይም ለመቅረቱ በቂ ምክንያት የሚሰጥለት እንደራሴ ካልቀረበ እንዲያዝ ትዕዛዝ ፍ/ቤት እንደሚሰጥ ይደነግጋል፡፡ በዚህ ትዕዛዝ መሠረት መፈፀም ካልተቻለ ተከሳሹ በሌለበት ነገሩን ለመስማት ፍ/ቤቱ እንደሚያስብበት የዚሁ ቁ. 160/3/ ያስቀምጣል፡፡ ከዚህ መርህ ሁለት ነጥቦችን እናያለን፡፡ ተከሳሽ ሲቀር የመጀመሪያው የፍ/ቤቱ ተግባር እንዲያዝ ማዘዝ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሌለበት ጉዳዩን ለማየት ማሰብ ናቸው፡፡
አንድን የወንጀል ክስ ተከሳሽ በሌለበት መስማትና መወሰን የሚቻለው በቁ. 161/2/ መሠረት ከ12 ዓመት በማያንስ ጽኑ እሥራት የሚያሳስር ወንጀል የሠራ ወይም በቀድሞ ወ/መ/ሕግ ቁ. 354-365 በአዲሱ የወንጀል ሕግ ቁ. 343 እስከ 354 ድረስ ያሉ ወንጀሎች ፈጽሞ ጽኑ እሥራት ወይም ከ5ዐዐዐ ብር በላይ በሚያስቀጣ ወንጀል የተከሰሰ ሲሆን እና እንዲሁም በውጭ ሀገር ጥገኛ ሆኖ ጥገኛ ያደረገው ሀገር አሳልፎ ያልሰጠው እንደሆነ ነው ቁ. (161/3/) ተከሳሹ በቁ. 160/2/ ካልቀረበ ወይም ለመቅረቱ በቂ ምክንያት ካልተሰጠና ወንጀሉ በቁ. 161/2/ እና /3/ የተመለከተው ከሆነ ክሱ በሌለበት እንዲሰማ ይታዘዛል፡፡ በቁ. 162 መሠረት ፍ/ቤት በጋዜጣ ማስታወቂያ ተከሳሽ እንዲጠራ የሚያዘው ነገሩ እንዲሰማ ቀጠሮ በተሰጠበት ቀን ባይቀርብ በሌለበት ጉዳይ እንዲታይ በታዘዘው መሠረት ቀጥሎ እንደሚታይ ለማስታወቅ ነው፡፡ ከጋዜጣ በተሻለ በሌላ መንገድ መጥሪያው ለተከሳሽ ሊደርስ ይችላል ከተባለም አማራጩ ለፍ/ቤት የተተወ ነው፡፡
በተግባር የሚታየው አሠራር የተለየ ሊመስል ይችላል በቁ. 161 የተመለከቱት ሁኔታዎች በተሟሉበትም ቢሆን ፍ/ቤት የተከሳሽን ጉዳይ በሌለበት ለማየት የሚወሰነው በጋዜጣ ማስታወቂያ ጥሪ ካደረገ በኋላ ነው ምናልባትም ይህ አሠራር የተከሳሹን መብት በተሻለ መንገድ ይጠብቅለታል ከሚል የመነጨ ይመስላል፡፡ ነገር ግን ፍ/ቤቱ ተከሳሹ የቀረው ያለበቂ ምክንያት መሆኑን ካረጋገጠ በጋዜጣ ጥሪ የሚያደርግበት አግባብ የለም፡፡
በዚህ ሁኔታ በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ የተፈረደበት ሰው ፍርዱ ውድቅ እንዲደረግለት ፍርዱን ባወቀ በ3ዐ ቀን ውስጥ ለፈረደው ፍ/ቤት ማመልከት ይችላል (ቁ. 164,197,198) ማመልከቻውም ተቀባይነት የሚያገኘው ተከሳሹ ፍ/ቤት ያልቀረበው መጥሪያው ስላልደረሰው ወይም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የቀረ መሆኑን ማስረዳት ከቻለ ብቻ ነው፡፡ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ምንድነው የሚለውን የመወሰን ኃላፊነት የፍርድ ቤቱ ነው፡፡ ማመልከቻው ተቀባይነት አግኝቶ ፍ/ቤቱ በሌለበት የሰጠውን ውሣኔ ውድቅ ካደረገው ጉዳዩ/ ክሱ እንደገና በሌላ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት እንዲታይ ይታዘዛል ቁ. 202፡፡
በሌለበት የተፈረደበት ፍርድ እንዲነሳለት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ የተደረገበት ተከሳሽ ይግባኝ ማለት የሚችለው በቅጣቱ ላይ ብቻ ነው፡፡
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/