Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
«መሀሙድ መዝፈን አልነበረበትም፤የሙዚቃው ድግስም ዓላማውን ስቷል» የጣዕም ልኬት አዘጋጆች

የሙዚቃ ባለሙያዎቹን ሰርፀ ፍሬ ስብሃት እና ምዕራፍ ተክሌን ያጣመረው በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 6 እስከ 8 ሰዓት የሚቀርበው "የጣዕም ልኬት" መሰናዶ በጥር 17 / 2017ዓ.ም ቆይታው ሳምንታዊ ዳሰሳውን ያደረገው ለአንጋፋው ድምፃዊ መሀሙድ አህመድ የተዘጋጀውን የሙዚቃ ድግስ በተመለከተ ነው።

የሙዚቃ መርሃ ግብሩ በቀረበበት ሳምንት በከተራና ጥምቀት በዓል ልዩ ዝግጅት ምክንያት በወቅቱስለ ኮንሰርቱ ማንሳት እንዳልተቻለ አዘጋጆቹ ጠቁመዋል።
አዘጋጆቹ 'የሳምንቱ የሙዚቃ አምባ' ላይ ዳሰሳ ባደረጉበት የአንጋፋው ድምፃዊ መሀሙድ አህመድ የሙዚቃ ዝግጅት መልካም ጎኖች ቢኖሩትም ሊስተካከሉ ይገባቸው የነበሩ መሰረታዊ ነጥቦችን አስቀምጠዋል።
ድምፃዊ መሀሙድ አህመድ የኢትዮጵያ የሙዚቃ መልክ ተደርጎ የሚቆጠር እና የሚወደስ ታላቅ ድምፃዊ ከመሆኑ አንፃር እርሱን አክብሮ የተሰናዳ ዝግጅት መሆኑ ከመርሃ ግብሩ ጀርባ ያሉትን እንደሚያስመሰግን አዘጋጆቹ ገልፀው ከድምፃዊው የቀደሙና ዛሬ ላይ በህይወት ያጣናቸው ታላላቅ ሥራን የሰሩ ድምፃውያንን እንዲህ ባለ መልኩ ሳናከብራቸው እንደማለፋቸው ይህ ዝግጅት ትልቅ ቦታ እንደሚሰጠውም አንስተዋል።

መሀሙድ አህመድ በሙዚቃ ሕይወቱ የደረሰበት ደረጃ እና ከፍታ «ለዚህ ክብር የሚመጥን የጥበበ ሰው እንዲሆን ያደርገዋል» ያሉት አዘጋጆቹ ከእሱ በተጨማሪ በሥራቸው የላቀ ከፍታ ላይ ደርሰው ልክ እንደ እሱ አክብረን ላልሸኘናቸው ሁሉ 'የመንፈስ ውክልናን የሚወስድ ነው።" ሲሉ ገልፀዋል።
ከዚህ አንፃር ለመርሃ ግብሩ መሳካት ከውጥን ጀምሮ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ የደከሙት በጠቅላላ ምስጋና እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ያም ሆኖ ግን  ከታለመለት አላማ አንፃር ሲታይ ትልቅ ክፍተት የነበረበት ከመሆኑ ባለፈ በታሰበው ልክ መሬት ላይ ወርዷል ማለት እንደሚያዳግት የጣዕም ልኬት አዘጋጆች አንስተዋል።

ክፍተቱ የሚጀምረው መርሃ ግብሩ "የስንብት" የሚለውን ቃል መጠሪያ ከማድረጉ እንደሆነ አንስተዋል። መጠሪያው ትልቅ ክፍተት የሚፈጥር እና ከሥነ ልቦና አንፃር ሲታይ አሉታዊ ተፅዕኖው እንደሚያጋድል አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

ከዚያ ይልቅ ማክበር እንደመሆኑ መጠን ስያሜው ያንን ተንተርሶ ሊሰጥ ይገባው እንደነበር በማንሳት መድረኩ ግቡን መቷል የሚል አመኔታ እንደሌላቸው ተናግረዋል። በጣዕም ልኬት አዘጋጆች ዕይታ በሙዚቃ ድግሱ ላይ የታዩ ክፍተቶች እንደሚከተለው ተቀምጠዋል።

👉« የመድረኩ ይዘት የተቃኘበት መንገድ ትልቅ ስህተት ነበረው፤ይህንን ያለ ይሉኝታ ማስቀመጥ ይገባል።» ብለዋል

👉ከሰዓት አከባበር ጋር በተገናኘ ትልቅ ክፍተት መፈጠሩን ተከትሎ በርካቶች ዝግጅቱን አቋርጠው ለመውጣት ከመገደዳቸው ባለፈ ጥቂት ታዳሚያን ብቻ መሀሙድ ሥራውን ሲያቀርብ መመልከታቸው  ቀዳሚው ክፍተት እንደነበር ተጠቅሷል።

👉«መሀሙድን ለማክበር የተገኙት ድምፃውያን የራሳቸውን የቀደሙ ሥራዎች እና በየምሽት ክበቡ የሚቀርቡ ሙዚቃዎችን ደግመው ማቅረባቸው ከመድረኩ አላማ ጋር የሚጋጭ ነበር። በተጨማሪም የመድረኩ ዝግጅት ላይ ምን አይነት ሥራ ይቅረብ በሚለው ዙሪያ ምንም ግንዛቤ አልነበራቸውም።»

« ከዚያ ይልቅ በእለቱ ተዋጣላቸውም አልተዋጣላቸውም ከሁሉም ድምፃውያን አንደበት የመሀሙድን ስራ ልናደምጥ ይገባ ነበር» ሲሉ አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

👉 «መሀሙድ በወቅቱ ከነበረበት የጤና እክል አንፃር አዘጋጆቹ ብቻ ሳይሆኑ ሙዚቀኞችም ጭምር  እንዲዘፍን ፈፅሞ ማድረግ አልነበረባቸውም።»
ከእዚያ ይልቅ በመድረኩ የክብር ሥፍራ ላይ ሆኖ ቢከታተል መልካም እንደነበር አንስተዋል።

👉 የዝግጅቱ "እጥር ምጥን" ማለት አለመቻሉ ክፍተት መፍጠሩን ያነሱት የጣዕም ልኬቶች መርሃ ግብሩ ሚሊኒየም አዳራሽ የግድ እንዲሆን ከማድረግ ይልቅ ሌላ ስፍራ በመምረጥ የሙያ ምስክርነት፣ ዘጋቢ ፊልሞች፣ ስጦታዎችና ሌሎችም ጉዳዮች በተናበበ መልኩ ማድረግ ይቻል ነበር ሲሉ አንስተዋል። የምሽት ክለብ የመሰለ መርሃ ግብር መሆኑን ተከትሎ አዘጋጆቹ ሳይቀሩ ለመቆጣጠር ተቸግረው እንደነበር ገልፀዋል።

👉«ፕሮግራሙ ኮንሰርት የሚሰሩ ሰዎች እጅ ላይ መውደቁ ክፍተት ፈጥሯል ያሉት አዘጋጆቹ ኮንሰርት መሆኑ እና ገንዘብ ላይ ማተኮሩ የቀረቡት ድምፃውያን ከመሀሙድ አርቋቸዋል። » ሲሉ ሁኔታውን የገለፁ ሲሆን የመሀሙድን ስራ በተደጋጋሚ የተጫወቱ እንዲሁም የመሀሙድ ሙዚቃ ዘመን ተጋሪ ሆነው የሰሩ ባለሙያዎች ቢመረጡ መልካም ነበር ሲሉ ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል።

ከእዚህ እና ከሌሎች ክፍተቶች እንፃር ዝግጅቱ ሀሳቡ እና መነሻው ትልቅ ተግባር ግን  አጨራረሱ  ዝቅተኛ እንደሆነ አንስተዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #mehamud_ahmed
«የተፈሪ ህልፈት የኢትዮጵያ የሙዚቃ ዕድገት ላይ ስብራት ይፈጥራል» እዮኤል መንግስቱ( የሙዚቃ ባለሞያ)

ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ባለሙያ ተፈሪ አሰፋ ባሳለፈነዉ ሳምንት ህይወቱ አልፏል።

ሙዚቀኛዉ የኢትዮጵያ ሙዚቃን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለሚገኙ ታዳሚዎች በማስተዋወቅ፤በምርምር፣ በማስተማር እንዲሁም በሀገረሰብ የሙዚቃ ስራዎቹ ይታወቃል፡፡

ለፈጠራ ራሱን አሳልፎ የሰጠ እና የኢትዮጵያን ሙዚቃን ለማስተዋወቅ ዕድሜ ልኩን የሠራ እንደሆነም ይነገርለታል፡፡

የተፈሪ የቅርብ ወዳጅ የሙዚቃ ባለሙያው እዮኤል መንግስቱ «የተፈሪ ህልፈት የኢትዮጵያ የሙዚቃ ዕድገት ላይ ስብራት ይፈጥራል» ብሏል።

👉 «የተፈሪ አሰፋን ህልፈት መስማት እጅግ ከባድ ሀዘን ነው።ልብም ይሰብራል አጋጣሚ እኔ የኢሜል መልዕክት ከፍራንሲስ ፋልሴቶ ደረሰኝ፤ፍራንሲስ ከ30 በላይ የኢትዮፒክስ የሙዚቃ ዕትም፤ በኢትዮ ሶኒክ ተከታታይነት ያላቸዉ ሙዚቃዎችን አሳትሟል። በዚህ እትም ከነጋሪት ባንድ ጋር ተፈሪ የሰራዉ ሙዚቃ የመጨረሻ መሆኑን ተፈሪን ማጣትም ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ኪሳራ እንደሆነም በላከልኝ መልዕክቱ ገልፇል፡፡»

👉« አጋጣሚ የሙዚቃ ስራችንን ለማቅረብ ፈረንሳይ ሀገር ነበር የምንገኘው።ህልፈቱን በሰማሁ ሰአት ከክፍሌ በድንጋጤ ወጣሁ አብረውኝ የነበሩ ሙዚቀኞችም ተረብሸዉ እየተላቀሱ ደረስኩኝ ተፈሪ በሰዓቱ ለነበርነው ለሁሉም ሙዚቀኞች በስራ፤በመምህርነት ቅርብ ነበር እና ስሜቱ ከባድ ነበር፡፡»
👉« ለህክምና ወደ አሜሪካ ከመጓዙ በፊት ከተፈሪ ጋር በስልክ ተገናኝተን ነበር። አሜሪካም ሆኖ ተደዋውለናል።ለህክምና ቀጠሮ እንደያዘ ነግሮኝ ነበር።ለመጨረሻ ጊዜ ስንገናኝ ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሰህ መልዕክት ተለዋውጠናል፡፡»

👉 «ተፈሪን ድራመር ብቻ አድርጎ መውሰድ እሱን ማሳነስ ይሆናል።ተፈሪ እጅግ ሩህሩህ ደግ ለሰው አዛኝ ነው። ይህ በተለምዶ ሰዎች ሲያልፉ የሚባል ሳይሆን የእውነት የኖረበት ስለሆነም ነው፡፡»

👉 «ተፈሪ የሙዚቃ ተመራማሪ፤መምህር፤የሙዚቃ ደራሲ ሲሆን በምርምሩ ረገድ ኢትዮጵያን ከጫፍ ጫፍ ዞሮ ምርምር ያደረገ ሲሆን ውጤቱን ለህዝብ ለማድረስ በተዘጋጀበት ጊዜ ህይወቱ ማለፉ ያስቆጫል፡፡»

👉 «በርግጥም  በተቋማት ደረጃ መሰራት የሚገባውን የባህል እሴትን ማጥናት ብሎም መሰነድን ብቻውን ሲያደርግ የነበረ ታላቅ ሰው ነበር፡፡»

👉« ባለፈው ዓመት በወጣው የየማ እና የኔ አልበም ላይ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ  ተሳትፎ ነበረው።አልበሙ ላይ የመጀመሪያውን ሳንፕል አሰምቼው ወዶታል።በተለይ ሀገረሰብ የሆኑ ስራዎችን መውደዱ እገዛውን ከፍ አድርጎልን ነበር።ከደጋ ሰው አልበምም ሾንቢቴ ለተሰኘው ሙዚቃ ፍቅር ነበረው። ከወጣ በኃላም ''ታዋቂ አደረጋችሁኝ አይደል? " ዕያለ ይቀልድብኝ ነበር»

👉«ተፈሪ በቅርብ ካሳተመው ኦርጂንስ አልበሙ በተጨማሪ በእጁ ብዙ አርካይቮች አሉት።
የሰበሰባቸው ያጠናቸው ብዙ ስራዎች ነበሩት።በቅጂ ደረጃም የጨረሰውን አልበም አንድ ላይ ሰምተነዋል።
ወደፊት ብዙ የሚሰጠን ስራዎች ነበሩ አንድም ህልፈቱ የሚያስቆጨው ይህ በመሆኑ ነው፡፡»

👉 «ድራም ተጫዋቹ፤መምህሩ፤ተመራማሪውን ተፈሪ  በቀጥታ በስራም ይሁን በተዘዋዋሪ ስለሚገናኘው፤ ስለሚያውቀው ህልፈቱ ለኢትዮጵያ የሙዚቃ እድገት ስብራት መሆኑን ተረድቶታል። ይህ በሌሎች ማህበረሰቦች ዘንድ ተመሳሳይ ነው ከተባለ አይደለም። ነገር ግን ተፈሪን ወደፊት የሚረዱ፤ስራዉ ላይ ምርምር የሚደርጉ ሰዎች በቀጣይ ይፈጠራሉ።»

ሲል የሙዚቃ ባለሙያው እዮኤል መንግስቱ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 መሰንበቻ ፕሮግራም ጋር የነበረዉን ቆይታ አጠቃሏል።

ተፈሪ አሰፋ በላስታ ሳውንድ፣ ውዳሴ፣ ኢትዮ-ጃዝ እና ነጋሪት ባንድ በሠራቸው ሥራዎቹ ባህላዊ የኢትዮጵያን ሙዚቃዎች የኢትዮ-ጃዝ መንፈስን በማላበስ በሙዚቃ ዓለም ላይ የማይሻር አሻራ አሳርፏል፡፡

በስቱዲዮም ዘመን አይሽሬ የሙዚቃ ሥራዎችን የሠራ ሲሆን፣ በ2011 ዓ.ም በተካሄደው አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል ከቃየን ጋር፣ በ2015 ዓ.ም በተካሄደው አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል ደግሞ ከኢትዮጵያን ሪከርድስ ጋር በመሳተፍ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከፍ አድርጓል፡፡

ሀገር በቀል ሙዚቃዎች ላይ በትኩረት በመሥራት እና የጃዝ የሙዚቃ ስልትን በመጫወት የሚታወቀው ተፈሪ በፖላንድ ሀገር በተለያዩ የሙዚቃ ስልቶች እስከ ሁለተኛ ድግሪ ተምሯል፡፡ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀም በሩሲያ፣ በካዛኪስታን፣ በቤላሩስ እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ሲሠራ ቆይቶ፣ ወደ አሜሪካ በማቅናት አካውንቲንግ በመማር የሙዚቃ ሥራ እስከሚያገኝ ድረስ አካውንታትን ሆኖ ሠርቷል፡፡

በአሜሪካ እያለም ላስታ ሳውንድ የተባለን ባንድ በማቋቋም የመጀመሪያ መድረኩን ከጥላሁን ገሰሰ ጋር የሠራ ሲሆን፣ አልበምም አሳትሟል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #teferi #eyuel_mengistu
አርቲስት ይሁኔ በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

አርቲስት ይሁኔ በላይ በፍኖተሰላም ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 67 አረጋዊያን 1መቶ ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ ዓመታዊ የህክምና ወጭ ሸፍኗል።

ኑሮውን በሀገር አሜሪካ ያደረገውና በህዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሆነው አርቲስት ይሁኔ በላይ አንድ መቶ ሺህ ብር ድጋፍ ያደረጉት ወጣት ይኸነው አንዷለምና የአርስቲስቱ ቤተሰቦች ችግሩን በማስረዳት ባደረጉት መልካም ጥረት ነው።

በድጋፍ ርክክቡ ዕለት የፍኖተሰላም ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ማማሩ ሽመልስ እንዲሁም የአርቲስቱ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #yihune_belay
ለሀዘንትኞች
የወንድማችን የተፈሪ አሰፋ ህልፈትን ተከትሎ ቀብርን አስመላልክቶ የተሳሳተ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል፣ ስለሆነም ሀዘንተኛው ፣ ትክክለኛ መረጃ ያገኝ ዘንድ፣ የቀብር ስነ-ስርዓቱ ተወልዶ ባደገበት በእዚሁ በአዲስ አበባ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤ/ክ ለማድረግ በሂደት ላይ መሆኑን እየገለፅን፣ ስለ አጠቃላይ የቀብሩ ስነ ስርዓት አካሄድ እና አፈፃፀም ይፋዊ መረጃ እስከሚሰጥ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ መግለፅ እንወዳለን።

አክሊሉ ወልደዮሃንስ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Teferiassefa
Job Title: Marketing Manager

Job Type: On-site - Permanent (Full-time)

Work Location: Addis Ababa, Ethiopia

Applicants Needed: Female

Salary/Compensation: Monthly

Key Responsibilities:
- Develop and execute integrated marketing strategies.
- Identify and secure sponsorship.
- Proactively seek new clients for Waliya’s services.
- Lead digital campaigns (social media, email, SEO/SEM, content marketing) and traditional channels. 
- Collaborate with other teams to align messaging and maximize impact. 
- Negotiate sponsorship agreements and client contracts, ensuring mutually beneficial terms and deliverables. 
- Analyze campaign performance using metrics (ROI, engagement, conversion) to refine tactics. 
- Manage budgets, timelines, and vendor relationships to ensure cost-effective delivery. 
- Stay ahead of industry trends and leverage insights to innovate campaigns. 
- Cultivate partnerships with influencers, media, and industry stakeholders. 
- Uphold brand consistency across all touchpoints and markets. 

Qualifications:
- Education: Bachelor’s degree in Marketing, Business, Communications, or related field. 
- Experience: 1+ years in marketing.

Send your cv
@bekibami

#waliya_Entertainment #music #jobpost #marketing_manager
Waliya Entertainment pinned «Job Title: Marketing Manager Job Type: On-site - Permanent (Full-time) Work Location: Addis Ababa, Ethiopia Applicants Needed: Female Salary/Compensation: Monthly Key Responsibilities: - Develop and execute integrated marketing strategies. - Identify…»
6 አመት የፈጀው «እንደ ጊዜው» የተሰኘው የድምፃዊ ማሚላ ሉቃስ አዲስ አልበም ሊወጣ ነው!!

የድምፃዊ ማሚላ ሉቃስ «እንደ ጊዜው» የሙዚቃ አልበም የስድስት አመት ስራው ተጠናቆ የፊታችን ጥር 30/2017 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

አስራ ሶስት ትራኮችን የያዘው “እንደ ግዜዉ" አልበም አንጋፋ እና ወጣት ባለሞያዎች ተሳትፈዉበታል በግጥምና ዜማ ይልማ ገ/አብ ፣ ናትናኤል ግርማቸዉ ፣ አለማየሁ ደመቀ እንዲሁም ራሱ ድምፃዊ ማሚላ ሉቃስን ጨምሮ ሌሎችም ባለሙያዎች አሻራቸዉን አሳርፈዉበታል፡፡

አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ ፣ ካሙዙ ካሳ ፣ ሚኪ ጃኖ ፣ ስማገኘዉ ሳሙኤል ፣ ፋኑ ጊዳቦ ፣ ሱራፌል የሺጥላ እና ጊልዶ ካሳ በሙዚቃ ቅንብሩ ተሳትፈዉበታል፡፡

አልበሙ የፊታችን ጥር 30 ጀምሮ በሰዋሰዉ አፕ እና በሰዋሰዉ የዩቲዩብ ገፅ ላይ ይለቀቃል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #mamila
«አዲስ አልበሜ ከፋሲካ በፊት ወይ በኃላ ይወጣል» ድምፃዊ አለማየሁ ሂርጶ

ዝነኛው ድምፃዊ አለማየሁ ሂርጶ ከ19 አመት በኃላ ወደ ሙዚቃዉ ተመልሷል፡፡

የ80 እና የ90ዎቹ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘመን ላይ አይረሴ ተወዳጅ ዜማዎችን ለአድማጭ ያቀረበዉ ድምፃዊ ወደ ሚወደው ሙያ ብቻ ሳይሆን በስደት ከኖረበት ኖርዌይ ወደ ሀገሩ ጠቅልሎ በመግባት በአዲስ አበባ ከተማ እየኖረ ነው፡፡

👉 «ወደ ሀገሬ ከመጣሁ በኃላ ዑመር መሀመድ የሚባል የምወደው ጓደኛዬ እንዳይደብረኝ፤ለስራዬም እንዲያግዘኝ ኪቦርድ ገዝቶ ሰጥቶኛል፤እሱ ብቻ ሳይሆን አሁን የምኖርበትን ቤት በነፃ ኑርበት አለኝ። እንዴት ደግ መሰለህ? አመሰግነዋለሁ፡፡»

👉« ከመጣሁ አራት ወር ሆኖኛል።አሁን ላይ ሙሉ አልበሜን በሶስት ወር ውስጥ ጨርሻለሁ።ወደ 14 የሚሆኑ ስራዎችን ጨርሼ ምርጫ እያደረግን ነው አለማየሁ ደመቀ፤ብስራት ሱራፌል፤ሽፈራዉ ከበደን የመሳሰሉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።»

👉 «የኢትዮጵያ እናቶች አዲሱ ስራ የተሰራበት አጋጣሚ ገጣሚ እዩኤል ብርሀኑ አንድ የእናት ግጥም አምጥቶ አሳየኝ፤በጣም የሚገርም ብቃት ያለው ልጅ ነው። አሌክስ ይህን ከፃፍኩ 13 አመት ይሆነዋል፤ምን አልባት አንተን እየጠበቀ ይሆናል የቆየው አለኝ፤ስንኙን ሲነግረኝ ተገረምኩ ከዛም ሰራሁት፡፡»

👉 «የኢትዮጵያ እናቶች ልጆቻቸውን የሚያሳድጉበት መንገድ እኮ አስገራሚ ነው። በ200 እና 300 ብር ደሞዝ ተመስገን እያሉ ከብልሀት ጋር ልጆቻቸውን
አሳድገዋል።ለእናቶች ሁሌ ቢዘፈን፤ቢለቀቅ ያንሳል፡፡»

👉« መኖር ደስ ይላል የሚለውን ሙዚቃ ደግሞ በስጦታነት ያበረከተልኝ አብዱ ኪያር ነው።የሚገርምህ ግጥም እና ዜማውን ብቻ ሳይሆን ለስቱዲዮ ለአቀናባሪ፤ለመሳሪያ ተጫዋች ለሙዚቀኞች ከፍሎ የራስህ አድርገዉ ይህ የኔ ስጦታ ነው ብሎ የሸለመኝ ሙዚቃ ነው፡፡»

@waliyaentmt
ድምፃዊ ተስፋዬ ታዬ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ተሸለመ

#Ethiopia | (African Book of Records) የምስከር ወረቀት የተሰጠው በአፍሪካ ጃዝ መንደር በተዘጋጀ ዝግጅት ነው፡፡

ድምፃዊ ተስፋዬ ታዬ በሀገራችን ከሚገኙ ከ45 በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች የሙዚቃ ስራዎችን ለአድማጮች አቅርቧል፡፡ በነዚህ ስራዎቹም የሀገራችንን ህዝቦች ባህል፣ ቋንቋ አጠቃላይ ማንነት ማስተዋወቅ ችሏል፡፡ በዚህም ምክንያት የአፍሪካ የድንቃድንቆች መዝገብ የክብር የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡

ተስፋዬ ታዬ ሙዚቃን የጀመረው በዳግማዊ ምንልክ ትምህርት ቤት ሲሆን ትምህርቱንም እዳጠናቀቀ ወደ ራስ ቴአትር በመግባት ለ አምስት አመታት ካገለገለ በኋላ የሚያስባቸውን ስራ ለመሰራት ስራውን በመልቀቅ በተለያዮ አካባቢዎች በመዞር ስራውን በግሉ መስራት ጀመረ።

የአልበም ስራም በመስራት 2 አልበሞችን ለአድማጭ አብቅቷል።

በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በመዞር በርካታ ስራዎችን ሰርቷል። አሁንም በመሰራት ላይ ይገኛል። በስራ ሂይወቱም ከ 30 አመት በላይ አገልግሏል፤ እያገለገለም ይገኛል።

እንኳን ደስ አለህ !

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #tesfaye_taye #africanbookrecords