Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
"ዳታን" ሊለቀቅ ነው

የያሬድ ነጉ የመጀመርያ የሆነው ዳታ የሙዚቃ አልበም ሊለቀቅ ነው።

#Ethiopia | ድምጻዊ ያሬድ ነጉ "ዳታን" የተሰኘው የመጀመሪያ አልበሙ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

ይህ "ዳታን" የተሰኘው አልበም በግጥም ወንደሰን ይሁብ፣ ፍሬዘር አበበወርቅ፣እዩቤል ብርሃኑ፣ ሃ/ማርያም መንግስቴ ፣ ጃሉድ አወል፣ሄኖክ ክብሩ(ጎፈር)መልእቲ ኪሮስ እና ፈለቀ ማሩ በዜማ ፋኑ ጊዳቦ ፣ ፀጋው ተክሉ (ቹቹ) ፣ኤሊያስ ግዛቸው ፣ጃሉድ አወል፣ሙሉአለም ታከለ እና ዩሃና ሲሆን በመዚቃ ቅንብር ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ፣ስማገኘው ሳሙኤል፣ፋኑ ጊዳቦ፣ ጊልዶ ካሣ፣ሱራፌል የሺጥላ እና ሃይፐር በሚክሲንግ ይትባረክ ክፍሌ ማስተሪንግ ክሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል፡፡

ከነዚህም መካከል:- ከዳይመንድ፣ ያሚ አላዲ፣ሪቫኒ እና ሃርመናይዝ ጋር ሙዚቃን በብቃት መጨወት ችሏል፡፡

ድምጻዊ ያሬድ ነጉ ከሀገራች በርካታ ወጣት ድምጻዊያን ጋር ሙዚቃን አብሮ በመስራት በህዝብ ዘንድ እውቅናን ተወዳጅነትነ አግኝቷል፡፡

ዳታን አልበም 11 track ያሉት ሲሆን አርቲስቱ የአለቀ አልበም አፍርሶ እንደ አዲስ የሰራው አልበም ነው ፡፡

ዳታን አልበምን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 3 ዓመት እና ከፍተኛ በጅት ፈጅቷል።

አልበሙ ላይ ሦስት የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ተሰርቶ የተጠናቀቁ ሲሆን ይህ አልበም ሙሉ በሙሉ ወጪ በድምጻዊ ያሬድ ነጉ ፕሮዲዩስ ተደርጓል፡፡

ይህ "ዳታን” አልበም ብዙ የተደከመበት እና የተለፋበት አልበም_ስለ ፍቅር፣ስለመለያየት እና ስለሀገር የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ይዳስሳል።

"ዳታን" የተሰኘው አልበም የፊታችን አርብ ጥር 09 በያሬድ ነጉ ዩቲዩብ ቻናል እና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በዞጃክ ወርልድ አማካኝነት ይገኛል፡፡

@waliyaentmt
@waliyaentmt
@waliyaentmt
ተወዳጁ አርቲስት አለማየሁ እሸቴ ተሸላሚ ሆነ

ተማር ልጄ! የመጀመሪያው ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት 2017 ልዩ ተሸላሚ Special Recognition Award አንጋፋው አርቲስት አለማየሁ እሸቴ ተሸላሚ ሆኖአል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #alemayehu_eshete
እንኳን ለብርሐነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ እያልን ዋልያ ኢንተርቴይመንት ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በመተባበር በሚያዘጋጀው "ዋልያ ስቴጅ" ፕሮግራማችን ላይ ከልኡል ሲሳይ ጋር የነበረንን ቆይታ በተወዳጁ የቴሌቪዥን ጣቢያ "አርትስ ቲቪ" ላይ ዛሬ ማታ 2:00 ላይ በቀጥታ መከታተል እንደምትችሉ ለማሳወቅ እንወዳለን።

መልካም በአል!!!!
#waliyaentertainment #waliyastage #artstv #BritishCouncil #leulsisay Leul Sisay
አንጋፋው የድራም የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቹ ተፈሪ አሰፋ ከዚህ አለም በሞት ተለየ🖤

በኢትዬጲያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በግንባር ቀደም ከሚጠቀሱት ውስጥ የሚጠራው የያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት የድራም አስተማሪው ለብዙዎች ሙዚቀኞች አርአያ በመሆን የሚታወቅ ሲሆን ለህክምና ክትትል ወደአሜሪካ ከሄደ በዃላ በህክምና ላይ ባለበት ሰአት ከዚህ አለም በሞት እንደተለየ ዋልያ ኢንተርቴይመንት ከቅርብ ሰዎች በደረሰው መረጃ አውቋል።

ዋልያ ኢንተርቴይመንት ለተፈሪ አሰፋ ቤተሰቦቹ እና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #teferi_assefa #yared_music_school
አልጣሽ አልበም ዛሬ ማታ

የፋና ላምሮት የድምፃዊያን ውድድር አሸናፊው ተወዳጁ ድምፃዊ አህመድ ሁሴን (ማንጁስ) የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበም ስራው የሆነው አልጣሽ ዛሬ ጥር 16 ምሽት በናሆም ሪከርድስ ይለቀቃል!!

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Manjus #Altash_Album
የመሃሙድ አህመድ የስንብት ፕሮግራም አርቲስቱን ከማስከበር ይልቅ ለገንዘብ የተሰራ ነው ሲሉ የተለያዩ አድናቂዎቹ ተናገሩ።

የመሃሙድ አህመድ የስንብት ፕሮግራም በቅርቡ በሚሊኒየም አዳራሽ በ ጆርካ ኢቨንት እና በዳኒ ዴቪስ አማካኝነት መዘጋጀቱ ይታወቃል። ምንም እንኳን አርቲስቱን ለማክበር የተዘጋጀ ፕሮግራም ቢሆንም ነገር ግን በቦታው ላይ የተገኙት አድናቂዎቹ በጣም የወረደ ዝግጅት እንደሆነ ከድምፅ ጥራት ጀምሮ በሰአቱ አለመጀመር እንዲሁም ከተጋበዙት ትላልቅ ድምፃዊያኖቹ ውስጥ የመሃሙድ ስራን የተጫወተው አንድ ሙዚቀኛ ብቻ መሆኑ እንዲሁም የ vip ትኬት የገዙት ሰዎች ልዩ ምግብ እና መጠጥ እንደሚዘጋጅላቸው ቢተዋወቅም ነገር ግን በጣም ውድ የሆኑ መጠጦችን በገንዘባቸው እንዲገዙ ዝቅ ያሉ መጠጦች እንደ ቢራ አይነቶቹ ጭራሽ እንዳይኖሩ መደረጋቸው ታዳሚዎች የተጭበረበሩ እንደመሰላቸው አዘጋጆቹ ለመሃሙድ አህመድ የማይረሳ ምሽትን ከመፍጠር ይልቅ ለራሳቸው ገንዘብ ማካበትን እንደፈለጉ ያስታውቃሉ ሲሉ የፕሮግራሙ ታዳሚዎች ቅሬታቸውን ገልፀዋል።

የፕሮግራሙ አዘጋጆች ከኢትዬፒካሊንክ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስም ለዝግጅቱ ከ42 ሚሊየን ብር በላይ ከራሳቸው ማውጣታቸውን የገለፁ ሲሆን የተለያዩ ችግሮች ቢያጋጥሟቸውም ችግሮችን በተገቢ ሁኔታ በመፍታት ሁሌም የሚኮሩበትን ዝግጅት በብቃት ማዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Mehamud_ahmed #jorkaevent
በአንድ ሳምንት ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዕይታ ያገኘው የአስቻለው ፈጠነ አሞራው ካሞራ ሰንጠረዡን እየመራ ይገኛል።

📈 ከጥር 9 እስከ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

1️⃣የድምፃዊ አስቻለዉ ፈጠነ - አሞራዉ ካሞራ
በሳምንቱ ውስጥ የጨመረው የተመልካች ብዛት: 2,176,375

2️⃣የድምፃዊ አማኑኤል የማነ - ንስክላ
በሳምንቱ ውስጥ የጨመረው የተመልካች ብዛት: 1,109,004

3️⃣የድምፃዊት ሰብለ ካሳይ - አብለኒ
በሳምንቱ ውስጥ የጨመረው የተመልካች ብዛት: 631,004

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #aschalewufetene
ታዋቂው ራፐር ኬንያ ዌስት የሃብት መጠኑ 2.77 ቢሊየን ዶላር ደረሰ።

በአለም አቀፍ መድረክ ላይ ተወዳጅነህን ካተረፉ ራፐሮች ውስጥ አንዱ የሆነው ከንያ ዌስት በኢቶን ቬንቸር ዘገባ መሰረት በ2025 የሃብት መጠኑ ከ2.77 ቢሊየን ዶላር በላይ መሆኑን አሳውቋል ይሄም ማለት 348 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር ማለት ነው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #kanyawest
ተወዳጁ የሙዚቃ አርቲስት ሮፍናን ኑሪ የምስራቅ አፍሪካ ምርጥ አርቲስት በሚለው ዘርፍ ታጭቷል።

በኢትዬጲያ ውስጥ በጣም ተወዳጅነትን ካተረፉት አርቲስቶች መካከል አንዱ የሆነው ሮፍናን ኑሪ በታንዛንያ, ዛንዚባር በሚካሄደው ትሬስ ሽልማት ላይ ምርጡ የምስራቅ አፍሪካ እጩ በሚለው ውስጥ ታጭቷል።

ሮፍናን በታጨበት በዚህ ዘርፍ ውስጥ ከአፍሪካ አልፈው አለም ላይ ተፅኖ መፍጠር የቻሉትም እነ ዳይመንድን ጨምሮ ማሪዬ፣ሃርመናይዝ ሌሎችም ይገኙበታል።

ድምፆትን ለሮፍናን ለመስጠት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ👇👇
www.traceawards.plus

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #rophnan
ድምፃዊ አለማየሁ ሂርጶ አዲስ ሙዚቃ !!

ተወዳጁ ድምፃዊ አለማየሁ ሂርጶ አዲስ ሙዚቃ ስራ ይዞ እየመጣ ይገኛል፡፡ ከአስራ ዘጠኝ አመት በኃላ ወደ አገሩ የተመለሰው ድምፃዊ አለማየሁ ሂርጶ ሰኞ ጥር 20/2017 ሁለት ነጠላ ሙዚቃዎችን ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኢትጵያ እናቶች እና ደስ ይላል የተሰኙ ርዕሶች የያዘ ሲሆን በአለማየሁ ሂርጶ የዩትዮብ ቻናል በኩል ይለቀቃል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Alemayehu_hirpo
«ኤልያስ መልካ ሀሳቡን የገለፀባቸውን ግጥሞች ብዘፍን ደስ ይለኝ ነበር»

ድምፃዊ አብርሀም በላይነህ (ሻላዬ)

ከሰሞኑ "ቀን በቀን" ሲል የሰየመውን ዓዲስ የሙዚቃ አልበም ለአድማጭ ያቀረበው ድምፃዊ አብርሀም በላይነህ(ሻላዬ) ስለአዲሱ አልበሙ፤በውስጡ ስለተነሱት ሀሳቦች እንዲሁም ሙያዊ ህይወቱን የተመለከቱ ጉዳዮችን አንስቷል፡፡

✍️«በሙዚቃ ጅማሮዬ አድማጭ ጋር ያደረስኩት እና የምታወቀው በተለያዩ ነጠላ ዜማዎች ነው።
ከአሊ ቢራ ጋር ከሰራሁት ከመጨረሻው "ዳርም የለው" ጀምሮ ቢታይ ስራዎቼን እየቆየሁ ነበር ለአድማጭ የማደርሰው አሁን ከሶስት አመት በኃላ በሙሉ አዲስ አልበም መጥቻለሁ፡፡»

✍️«በመጀመሪያ አልበሜ የሚያኮራኝ ነገር አለ ብዬ አላምንም።እንደሌሎቹ ታላላቅ የሙያ ጓደኞቼ 15፣ 20ም አልበም እንዲኖረኝ ነዉ ምኞቴ ያኔ ኩራት ካለው ብጠየቅ ምመልሰዉ ይኖራል።አሁን ግን ጀማሪ ነኝ»
✍️«"ቀን በቀን" ከሚለው የአልበም መጠሪያዬ በፊት ብዙ ስም አስበን ነበር።ካወጣናቸዉ ርዕስ ውስጥ ይህን ወደድነው፤ያወጣንበት ቀን ደግሞ እኔ ከተወለደኩበት ቀን ጋር ገጠመ»

✍️«በዚህ አልበም ውስጥ ከኤልያስ መልካ ጋር የሰራናቸዉ በቅንበር ብቻ የተሳተፈበት 5 ዘፈኖች ተካተዋል።እንደሌሎች ድምፃውያን ኤልያስ ሀሳቦቹን የገለፀበትን ግጥሞች ባዜም ደስ ይለኝ ነበር ይህ ግን አልሆነም፡፡»

✍️«ከኤልያስ ጋር መስራት ውጤት ሳይመጣልህ ዩኒቨርስቲ እንደመግባት ነው።ኤሊያስ በተሰጠዉ ሙያ እሱ ጋር ተቀምጦ መስራትን መግለፅ ከባድ ነው።ለሁሉም ሰው የሚሰጠዉ ክብር፤ ሰዋዊ ምላሽ የሚደነቅ ነዉ፡፡»

✍️«ሻላዬ የሚለዉ ሙዚቃዬ ላይ ብዙ ትዉስታ አለኝ።ጀማሪ ነኝ ጉጉት ነበረኝ። ቢሆንም ፈጣሪ ፈቅዶ ጥሩ ተሰማ ከዛውጪ ሻላዬ ቅፅል ስሜ
ሆኖ እንድጠራበትም ሆኗል። ካዛ ባባ ፋዮ እያለ እቴ አባይ፤አሜን፤ዳርም የለው መዚቃዎቼ ጥሩ ተቀባይነት አግኝተዋል፡፡»

✍️«"እቴ አባይ" ላይ ግን ከወንደሰን ይሁብ እና አንተነህ ወራሽ ጋር በጣም የለፋንበት ስራ ነበር፤በጊዜውም አፍሪማ የሙዚቃ ሽልማት አግኝተንበት የልፋታችንን የከፈለ ሙዚቃ ሆኖ አልፏል፡፡»

✍️«ከአሊ ቢራ ጋር የሰራሁት ዳርም የለው መዚቃ፤ በእንድ ወቅት በስራ ተገናኝተን ወዳጅነታችንንም  አጠንክረን የሰራነው ሙዚቃ ሲሆን አንድ ጓደኛዬም ሀሳቡን አመነጨ።ለአሊ የሚመጥን ግጥምና ዜማ ለመምረጥ በነበረው ሂደት ግን ብዙ ጊዜ አፍርሰን ገንብተን በመጨረሻም የሰማችሁት ሙዚቃ ተስርቷል።ከአሊ ጋር መስራት ክብርም ዕድለኝነትም ነው፡፡»

✍️«ሲቲና የሚለዉ ሙዚቃ ግጥሙን ወንደሰን ይሁብ፤ዜማውን አንተነህ ወራሽ ሰርተውታል።ሲቲና ካራክተር ናት። ከተሰራ ሰባት አመት ቆይቷል።እኔም የምወደው ሙዚቃ ነው፤ሚኪ ጃኖም ጥሩ አድርጎ አቀናብሮታል፡፡»

ፈጣን ጥያቄዎች

- ከኤሊያስ የግጥም ስራዎች የኔ በሆነ ያልከው?

አብርሀም _« የእዮብ መኮንን ነቅቻለሁ»

- የሚያስደስትህ ነገር?

አብርሀም_« ሙዚቃ እና ሙዚቃ »

- ሰምተህ የወደድካቸው  ሶስት አልበሞች?

አብርሀም_« የጌቴ አንለይ መልክሽ አይበልጥሽም።የእዮብ መኮንን አንድ ቃል፤ቴዲ አፍሮ ጃ ያሰተሰርያል፡፡»

-  ኤልያስ ካቀናበራቸው  አልበሞች ውስጥ ከቤሪ እና ከዘሪቱ ምረጥ? 

አብርሀም_« የዘሪቱ»

- ከራስህ ስራዎች ከእቴ አባይ እና ሲቲና?

አብርሀም_« ሲቲና»

- ከግጥም እና ዜማ ደራሲ ፀጋዬ ደቦጭ እና ከአበበ መለሰ?

አብርሀም_« አበበ መለሰ»

- ከግጥም እና ዜማ ደራሲ ወንደሰን ይሁብ እና እንተነህ ወራሽ?

አብርሀም «ወንደሰን ይሁብ»

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #abrhambelayneh #yasitina