Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ታዋቂ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች እና ቲክቶከሮች በእግር ኳስ ሜዳ ላይ ይፋለማሉ

#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከቅዳሜ ሚዲያ እና አድሽርታይዚንግ ጋር በመተባበር ልዩ የሆነ የታዋቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫል ሊያካሂዱ መሆኑ ተገለጸ።

በዚህ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ታዋቂ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ድምፃውያን እና ቲክቶከሮች የሚሳተፉበት የእግር ኳስ ውድድር የፊታችን ሚያዚያ 23 እና ሚያዚያ 26 በልደታ በሚገኘው ብሪሞ ሜዳ ይካሄዳል።

የቅዳሜ ሚዲያ እና አድሽርታይዚንግ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ አዳረ ረጋሳ ይህንን መርሃ ግብር አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንደገለጹት " ከዚህ ቀደም መሰል ውድድሮች በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነት የነበራቸው ሲሆን ዘንድሮም ይህንን የአብሮነት እና የመዝናኛ ጊዜ ለመፍጠር ታስቧል።

አክለውም በቅርብ ጊዜያት ህዝቡ በቤተሰቡ ልጆቹን ይዞ ወደ መዝናኛ እና ስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች በስፋት እየሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ በእነዚህ ቦታዎች ላይ አዝናኝ ፕሮግራሞች ቢዘጋጁ ህዝቡ በሰፊው እንደሚታደም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ይህ የታዋቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫልም በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ በመሆኑ ብዙዎች በጉጉት እንደሚጠብቁት "ተናግረዋል።

በመግለጫው ላይ እንደተገለጸው ሚያዚያ 23 የዋንጫ ማለፍ ጨዋታ የሚደረግ ሲሆን የፍጻሜው የዋንጫ ጨዋታ ደግሞ ሚያዚያ 26 ይካሄዳል። ከዚህ የትኬት ሽያጭ የሚገኘው ሙሉ ገቢ ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ ይውላል።

@waliyaentmt
@waliyaemtmt
@waliyaentmt
እኔንም ስሙኝ ብሏል :-

እኔ አድናናን እባላለው ባለትዳር እና የሴት ልጅ አባት ነኝ::

ዳግማዊ ደቡብ አፍሪካ በነበርኩ ግዜ ጏደኛዬ ነበረች የባሏ ቤተሰቦች እና የባሏ የድሮ ፍቅረኛ የሚያደርጏትን ጭምር ታጫውተኝ ነበር:: ከዛ ለረዥም ግዜ ተለያይተን በድጋሚ ፃፍኩላት ይሄ ዛቻ ከሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ እኔ ለቀልድ ነው ያልኳት እንጂ ለሌላ ነገር አይደለም እኔ የምኖረው ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም::

አድናን ነኝ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #dagimawittsehaye #adnan
የሳምንቱ ምርጥ 10 ሙዚቃዎች

1. ዓይዋ
467,009 Views | + 467,009 Views

2. አሞራው ካሞራ – አስቻለው ፈጠነ
9,741,769 Views | + 430,788 Views

3. Sona Takele – WARRA BOOLEE
19,533,830 Views | + 422,378 Views

4, ማህሌት ወንድሞ - ዝም
4,313,400 Views | + 412,976 Views

5, Amanuel Yemane - Niskila
7,946,782 Views - +355,971 Views

6, ቬሮኒካ አዳነ - እናነይ
25,243,113 Views | + 319,082 Views

7, ያሬድ ነጉ - አለምድም
4,613,587 Views | + 288,143 views

8, አንዷለም ጎሳ - ማሬ
2,028,385 Views | + 253,180 Views

9, Ibiddo Galaan - Dammee
480,030 Views | + 237,409 views

10, ኤደን ገብረስላሴ - ይኹን
8,894,539 Views | + 237,306 Views

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #top10
"በሙዚቃ ዝግጅቴ አምስትም ሆነ አስር ሰው ቢመጣ ታዳሚዬን አከብራለሁ":- ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ

ወጣቱ ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ከመጀመሪያ አልበሙ በኃላ በአዲስ አበባ ያዘጋጀው ሁለተኛ የሙዚቃ ዝግጅቱን በዛሬው ዕለት ያካሂዳል::

ልዑል ከወራት አስቀድሞ መድረኩን የሚመጥን ዝግጅት ማድረጉን ይገልፃል::

"በእርግጥ ይህ በአዲስ አበባ የሚኖረኝ ሁለተኛ ዝግጅቴ ነው። አሁንም በመድረክ እንይህ የሚሉ ጥያቄዎች ስለነበሩ እኔም ጥያቄውን ተቀብዬ ተዘጋጅቻለሁ" ሲል ይናገራል::

ልዑል ባለፈው ከነበረው የሙዚቃ ኮንሰርቱ በርካታ ጠቃሚ ልምድን ማግኝቱን ገልፆ ከራሱ ስራዎች ባለፈ የተለያዩ ድምፃዊያንን ስራም አብሮ እንደሚጫወት ገልፆል::

የኮንሰርት የመጨረሻው ሰዓታ ጥንቃቄ ይፈልጋል ከዚህ አንፃር ምን ልምድ አለህ? ያልነው ልዑል

"ብዙ ጊዜ ከቤት አልወጣም ድብቅ ለማለት እፈልጋለሁ። በአመጋገብ አትክልት በመጠጥ ውሃን አዘወትራለሁ" ብሏል::

ልዑል የሙዚቃ ዝግጅቱን በሚያቀርብበት ተመሳሳይ ሰአት ሌሎች ዝግጅቶም በአዲስ አበባ ይካሄዳሉ። ስለሁኔታው የተጠየቀው ድምፃዊው

"የእኛ ቀደም ብሎ የተደረገ ነው በዕለቱ አድማጭ ሊሻማ ቢችልም ሁላችንም የራሳችን ተከታይ እንዳለን መዘንጋት የለበትም። በግሌ አምስትም ሆነ አስር አድማጭ ቢመጣ ታዳሚዬን አክብሬ እጫወታለሁ" ብሏል::

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #leul_sisay
በሽርጉድ ኮንሰርት ላይ ያለፈው ቅዳሜ ዝግጅታቸውን ያቀረቡት አርቲስቶቹ ስንት እንደተከፈላቸው ታወቀ።

ሶስት የሙዚቃ ትውልዶችን በአንድ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ያገናኘው ሽርጉድ ኮንሰርት ያለፈው ቅዳሜ እለት በሚሊኒየም አዳራሽ መካሄዱ ይታወቃል። በዝግጅቱም ላይ በርከት ያሉ ታዳሚዎች የተገኙም ሲሆን ድምፃዊያኖችም በአሪፍ የመድረክ አቀራረብ ገነው ታይተዋል።

በሙዚቃ ዝግጅቱ ላይ አርቲስቶቹ ስራየውን ለማቅረብ ከሽርጉድ ኢንተርቴይመንት ጋር የተፈራረሙ ሲሆን ዋልያ ኢንተርቴይመንት ከአንዳንድ የውስጥ ታማኝ ምንጮች እንዳጣራው ኤፍሬም ታምሩ በዝግጅቱ ላይ 10 ስራዎችን እንዲያቀርብ ለሱም 3 ሚሊዮን ብር ሊከፈለው ጎሳዬ ተስፋዬ እና አለማየሁ ሂርጶም የተለያዩ የሙዚቃ ስራቸውን ሊያቀርቡ ለእነሱም ለእያንዳንዳቸው 3 ሚሊዮን ብር ሊከፈላቸው ተስማምተው እንደነበር ዋልያ ኢንተርቴይመንት መረጃ ደርሶታል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #shirgoodconcert #ephremtamru #gossayetesfaye #alemayehuhirpo
"ደጃዝማች " የተሰኘው የድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ስምንተኛ አልበሟ የፊታችን አርብ ሚያዚያ 24 ይለቀቃል

ታላላቅ ገጣሚዎችና የዜማ ደራሲያን የሙዚቃ አቀናባሪዎች የተሳተፉበት "ደጃዝማች " የተሰኘው የድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ስምንተኛ አልበሟ የፊታችን አርብ ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በእራሷ በኩኩ ሰብስቤ የዩቲዮብ ቻናል እና በሁሉም የዲጂታል መተግበሪያዎች ለአድማጭ እንደሚደርስ ተገልጿል ።

ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ለሰባት ዓመታት በደከመችበት "ደጃዝማች " በተሰኘው አዲስ የሙዚቃ አልበም ላይ አስራ ሶስት /13/ ዘፈኖችን የያዘ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ከእነዚህ አስራ ሶስት ዘፈኖች ውስጥ የስምንቱ ዘፈኖች ግጥምና ዜማ የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ / ሲሆኑ ሌሎቹን ሙዚቃዎች ደግሞ በግጥም ገጣሚ ይልማ ገብረአብ ፡ ገጣሚ መሰለ አስማማው ፡ ገጣሚ ናትናኤል ግርማቸው የሰሩ ሲሆኑ ሞገስ ተካ እና ምስክር አወል በግጥምና ዜማ በመስራት በአልበሙ ላይ ተሳትፈዋል

ከተቀሩት ስራዎች ውስጥ "ወለላዬ" የተሰኝው ሙዚቃ ደግሞ የኩኩ የድሮ ስራ ሲሆን ቴዲ ማክ እንደገና ሪአሬንጅ /Re Arrange/ አድርጎ የሰራው ሙዚቃ ነው ተብሏል። የድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ " ደጃዝማች " በተሰኘው አዲስ አልበም ላይ ስመጥር የሆኑ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉበት ሲሆን የሙዚቃ አቀናባሪው አቤል ጳውሎስ ዘጠኙን ሙዚቃዎች በማቀናበር እንዲሁም አስራ አንዱን ሙዚቃዎች ሚክስ በማድረግ እንደተሳተፈ ተነግሯል ።

ሁለቱን ሙዚቃዎች አሬንጅ ያደረገው ማሩ ዓለማየሁ ሲሆን ሙዚቀኛ ያሬድ ተፈራ ፡ ሙዚቀኛ አክሊሉ ወ/ዩሐንስ (ጆኒ ሳክስ) እና ሙዚቀኛ ዘሪሁን በለጠ በሳክስፎን ፡ ግሩም መዝሙር እና ሳሙኤል አሰፋ በጊታር ተሳትፈዋል ።

@waliyaentmt
@waliyaentmt
@waliyaentmt
ዘቢባ ግርማ ለግንቦት 1 ቀጠሮ ሰጥታለች ።

ከ5.7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሆነበት የዘቢባ ግርማ "እንደምንም" የሙዚቃ አልበም መውጫው ቀን ይፋ ሆኗል!

ይህ "እንደምንም የተሰኘው አልበም በግጥም ይልማ ገብረአብ፣ ሞገስ ተካ፣ አለምጸሀይ ወዳጆ፣ መስለ ጌታሁን፣ ናትናኤል ግርማቸው፣ ወንደሰን ይሁብ፣ ፍሬዘር አበበወርቅ፣ እልፍአግድ እምሻው፤ ኒና ግርማ፤ ገዳ ሀምዳ በግጥም የተሳተፉ ሲሆን

በዜማ ደግሞ አበበ ብርሃኔ ፣ ሞገስ ተካ፣ ኢንጅነር ፋንታ ወጨፎ፣ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፤ አንተነህ ወራሽ፣ ምህረትአብ ደስታ፤ ካሙዙ ካሳ፣ ዳንኤል ዘውዱ (ዳኒ ቀዮ)፣ አብዲ ያሲን

በመዚቃ ቅንብር አቤል ጳውሎስ፣ ታምሩ አማረ፣ ሸካሙዙ ካሳ፣ ፋኑ ጊዳቦ፣ አዲስ ፍቃዱ ማስተሪንግ ክሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል፡፡

"እንደምንም" የተሰኘው አልበም የፊታችን አርብ ግንቦት አንድ በዘቢባ ግርማ ዩቲዩብ ቻናል እና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች አማካኝነት ይገኛል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #zebibagirma
ቬሮኒካ በአውሮፓ የሙዚቃ ዝግጅቶቿን ልትጀምር ነው

"Europe ለምትገኙ ለመላው ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ቤተሰቦቼ ጊዜው ደርሶ የመጀመርያውን መጠሪያዬ ቱር ከእናንተ ውድ ቤተሰቦቼ ጋር ላሳልፍ ስለሆነ የተሰማኝን ደስታ እየገለፅኩ; ቀኖቹን እንዳሳውቃችሁ በጠየቃችሁኝ መሰረት ቀኖቹን ይዤላችሁ መጥቻለሁ፤ ይሄ ቱር በተለያዩ አዳዲስ ነገሮች ብቅ የምልበትም ስለሆነ በዚህ የህይወቴ ታሪክ ውስጥ እንድትሳተፉልኝ በትህትና እገልፃለሁ ; እወዳችዋለሁ፤

ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን 🙏🏽 " - ቬሮኒካ አዳነ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Veronica_adane