" ፈንድቃን ዳግም እንድገነባ መንግስት ፈቃድ ሰጥቶኛል "
#Ethiopia : ካዛንቺስ በተመሳሳይ ቦታ ፈንድቃን እንድገነባ መንግስት ፍቃድ ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ መላኩ በላይ ። የፈንድቃ ባለቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት ፣ ውድ የፈንድቃ ወዳጆችና ጏደኞቼ፣ ለፈንድቃ ያላችሁን ፍቅር እና ድጋፍ በጣም አከብራለሁ አመሰግናለሁ። መንፈሶቻችሁ ለጥበብ ያላቹ ክብር በልቤ ውስጥ ነው - በጣምም ያበረታኛል ብሏል ።
ካዛንቺስ በተመሳሳይ ቦታ ፈንድቃን እንድገነባ መንግስት ፍቃድ ስለሰጠኝ በጣም አመሰግናለሁ ያለው መላኩ ፣ አንድ ላይ ሆነን ለፈንድቃ የተሻለ የወደፊት ጊዜ እንዳለም አምናለሁ ሲል ገልጿል ።
አዲሱን ፈንድቃ ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ሁላችሁም የበኩላችሁን እንድታበረክቱ እጠይቃለሁ። የፈንድቃን ህልም አንድ ላይ በመሆን እንደምናሳካውም አውቃለሁ::
" በቅርቡ GoFundMe ዘመቻ እንጀምራለን ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በ fendika.org/support በዚህ መንገድ የገንዘብ ድጋፍ እንድታደርጉ አማራጮችን ይሰጥዎታል። ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል ።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #Fendika

"ለወደፊቱ ዘማሪ የመሆን እቅድ አለኝ" - ቬሮኒካ አዳነ
#Ethiopia | ሰላም የተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ የመዝናኛ መጽሔት አንባቢያን እንደሚታወቀው በአውደ ጥበብ ገፃችን በሀገራችን ኢትዮጵያ በኪነ፡ጥበብ ፣ በትምህርት ፣ በጤና ፣ በማህበራዊ ግልጋሎት ፣ በበጎ አድራጎት ፣ በስፖርትና በሌሎች የተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለሀገራቸው እና ለማህበረሰባቸው በርካታ ትሩፋትን ያበረከቱና ቅንነትን መለያቸው ፣ ምክንያታዊነትን የህይወት መርህ አድርገው በሀገር ፍቅር ከተቃኙ መካከል ለእናንተ ለአንባብያን በተለይም ለወጣቶችና ለሴቶች ከህይወታቸው ፣ ከስብዕናቸው ፣ ከስራ ውጣ ውረዳቸውና ከልምዳቸው ትማሩበታላችሁ ያልናቸውን ወደ እናንተ የምናደርስበት አምድ ነው፡፡ ታዲያ በዛሬው አውደ ጥበብ አምዳችን እንግዳችን ወጣቷ ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ ናት፣ ቬሮኒካ የህይወት ተሞክሮዋን እና ልምዷን ልታካፍለን ከመዝናኛ መጽሔት ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡ እንድትከታተሉን አስቀድመን በት ህትና እንጋብዛለን።
መዝናኛ:- በቅድሚያ በዚህ በተጣበበ ጊዜሽ የመዝናኛ መፅሔት እንግዳ ለመሆን ፈቃደኛ ስለሆንሽ በመፅሔት አንባቢያን ስም እጅግ በጣም እናመስግናለን። ወደ መዚቃው አለም እንዴት እንደገባሽ እና ማን ፈር ቀዳጅ እንደሆነልሽ ብትገልጭልን?

የአንጋፋው የክራር ሙዚቃ መሳሪያ ተጨዋች መሰለ አስማማው የቀብር ሥነሥርዓት ዛሬ ተፈፀመ!
(ይትባረክ ዋለልኝ)
#Ethiopia | የአንጋፋው የክራር ሙዚቃ መሳሪያ ተጨዋች የነበረው መሰለ አስማማው የቀብር ሥነ ሥርዓቱም ዛሬ ረቡዕ ሕዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በየካ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቹ ዘመዶቹ ጓደኞቹ የሙዚቃ ባለሙያዎች እና ጥቂት ድምፃዊያን ጋዜጠኞች በተገኙበት ተፈፀሟል ፡፡
የመሰለ አስማማው የቀብር ስነስርዓት በየካ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቀሳውስትና ዲያቆናት በሙያው ብዙ ለሐገሩ ለሰራና ለደከመ ለአንድ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሐይማኖት ተከታይ የሚደረገውን ስርዓት በማድረግ ቤተክርስቲያኒቱ በክብር ሽኝት በማድረግ ስርዓተ ቀቡሩም እንዲፈፀም አድርጋለች::
በቀብር ስነስርዓቱ ላይ በነበረው ፕሮግራም የመሰለ አስማማው የህይወት ታሪክ ከመቅረቡ ውጪ አንድ ሙዚቃ ባለሙያ ሲያርፍ ሁልጊዜ በየቀብሩ እንደምናየው አይነት የሐዘን መግለጫ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማህበርም ሆነ መሰል ተቋሞችና ታዋቂ ግለሰቦችም በሽኝቱ ፕሮግራም ላይ ምንም አላሉም::
ሌላው የሙዚቀኛ መሰለ አስማማውን በሙዚቃ መሳሪያዎችና በክራር የተቀነባበሩ የሙዚቃ ስራዎቹን በፈለጉት ሰዓት ላሻቸው ጉዳይ የሚጠቀሙበት የሐገራችን ሚዲያዎች ዛሬ የዚህን ሰው የቀብር ፕሮግራም ለመዘገብ ቸግሯቸዋል::
በመሰለ የቀብር ፕሮግራም ላይ ከአንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ እና ከእኔ /ትርታ ኤፍ ኤም/ ውጪ የተገኝ ሚዲያ አልነበረም ::
ይህ ጉዳይ እጅግ ያሳዝናልም እንደሐገርም የሚያሳፍር ተግባርም ነው:: ይህን ያህል ህዝብ እንዲመጣ የሆነውም በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት የተሰራው ዘገባ እንጂ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አንድም ሥራ የለም::
@waliyaentmt

"የደጋ ሰው"
የየማ የመጀመሪያ አልበም በፈረንሳይ 🇫🇷 ሀገር በሲዲ ታተመ
#Ethiopia | "የደጋ ሰው" የተሰኘው የየማ የመጀመሪያ አልበም በተለያዩ መተግበሪያዎች ከተለቀቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንሳይ ሀገር በሲዲ ታተመ።
“በዲጂታል ዘመን ሙዚቃዎቼ ታትመው በእጄ ሳገኛቸው ስሜቱ የተለየ ነው። “ ስትል በማህበራዊ ገፇ የማ አስፍራለች።
በቅርቡ በዩኤስቢ እና በሽክላ የሚታተም ይሆናል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #yema #eyuel_mengistu #yedegasew

ቀላቲ ቢውቲ ድምጻዊ ቬሮኒካ አዳነን የብራንድ አምባሳደር ሆነች
#Ethiopia | ተወዳጅዋ ድምፃዊ ቬሮኒካ አዳነ ለቀላቲ ቢዉቲ ለቀጣይ ሁለት ዓመት የክብር አምባሳደር በመሆን ለቴሌቪዥን ፤ ለቢል ቦርድ እና ለማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያዎች ለመስራት የብራንድ አምባሳደር በመሆን ተፈራርማለች።
በ2008 ዓ.ም በአቶ ሮቤል ቀላቴ የተመሠረተው ዋና መቀመጫውም በአዲስ አበባ ያደረገው ቀላቲ ቢዉቲ የተለያዩ የውበት መጠበቂያ ምርቶችን በኦን ላይን በማዘዝ ለደንበኞች ባሉበት ስፍራ ለማድረስ የተመሠረተ ተቋም ነው።
ተወዳጅዋ ድምፃዊ ቬሮኒካ ቀላቲ ቢውቲ ጋር ለመስራት እድሉን በማግኘቷ የተሰማትን ክብር በፊርማ መርሐግብሩ ላይ ገልጻለች።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #veronica_adane

እንኳን ደስ ያላችሁ !!
#Ethiopia: እንኳን ደስ ያላችሁ - ድምፃዊት ቤቲ ጂ እና ወንድማችን ጋዜጠኛ ኤልያስ ወንድሙ!

#Waliya_Entertainemnt #Music #bettyg

"ዳታን" ሊለቀቅ ነው
የያሬድ ነጉ የመጀመርያ የሆነው ዳታ የሙዚቃ አልበም ሊለቀቅ ነው።
#Ethiopia | ድምጻዊ ያሬድ ነጉ "ዳታን" የተሰኘው የመጀመሪያ አልበሙ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
ይህ "ዳታን" የተሰኘው አልበም በግጥም ወንደሰን ይሁብ፣ ፍሬዘር አበበወርቅ፣እዩቤል ብርሃኑ፣ ሃ/ማርያም መንግስቴ ፣ ጃሉድ አወል፣ሄኖክ ክብሩ(ጎፈር)መልእቲ ኪሮስ እና ፈለቀ ማሩ በዜማ ፋኑ ጊዳቦ ፣ ፀጋው ተክሉ (ቹቹ) ፣ኤሊያስ ግዛቸው ፣ጃሉድ አወል፣ሙሉአለም ታከለ እና ዩሃና ሲሆን በመዚቃ ቅንብር ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ፣ስማገኘው ሳሙኤል፣ፋኑ ጊዳቦ፣ ጊልዶ ካሣ፣ሱራፌል የሺጥላ እና ሃይፐር በሚክሲንግ ይትባረክ ክፍሌ ማስተሪንግ ክሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል፡፡
ከነዚህም መካከል:- ከዳይመንድ፣ ያሚ አላዲ፣ሪቫኒ እና ሃርመናይዝ ጋር ሙዚቃን በብቃት መጨወት ችሏል፡፡
ድምጻዊ ያሬድ ነጉ ከሀገራች በርካታ ወጣት ድምጻዊያን ጋር ሙዚቃን አብሮ በመስራት በህዝብ ዘንድ እውቅናን ተወዳጅነትነ አግኝቷል፡፡
ዳታን አልበም 11 track ያሉት ሲሆን አርቲስቱ የአለቀ አልበም አፍርሶ እንደ አዲስ የሰራው አልበም ነው ፡፡
ዳታን አልበምን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 3 ዓመት እና ከፍተኛ በጅት ፈጅቷል።
አልበሙ ላይ ሦስት የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ተሰርቶ የተጠናቀቁ ሲሆን ይህ አልበም ሙሉ በሙሉ ወጪ በድምጻዊ ያሬድ ነጉ ፕሮዲዩስ ተደርጓል፡፡
ይህ "ዳታን” አልበም ብዙ የተደከመበት እና የተለፋበት አልበም_ስለ ፍቅር፣ስለመለያየት እና ስለሀገር የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ይዳስሳል።
"ዳታን" የተሰኘው አልበም የፊታችን አርብ ጥር 09 በያሬድ ነጉ ዩቲዩብ ቻናል እና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በዞጃክ ወርልድ አማካኝነት ይገኛል፡፡

ድምፃዊ ተስፋዬ ታዬ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ተሸለመ
#Ethiopia | (African Book of Records) የምስከር ወረቀት የተሰጠው በአፍሪካ ጃዝ መንደር በተዘጋጀ ዝግጅት ነው፡፡
ድምፃዊ ተስፋዬ ታዬ በሀገራችን ከሚገኙ ከ45 በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች የሙዚቃ ስራዎችን ለአድማጮች አቅርቧል፡፡ በነዚህ ስራዎቹም የሀገራችንን ህዝቦች ባህል፣ ቋንቋ አጠቃላይ ማንነት ማስተዋወቅ ችሏል፡፡ በዚህም ምክንያት የአፍሪካ የድንቃድንቆች መዝገብ የክብር የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡
ተስፋዬ ታዬ ሙዚቃን የጀመረው በዳግማዊ ምንልክ ትምህርት ቤት ሲሆን ትምህርቱንም እዳጠናቀቀ ወደ ራስ ቴአትር በመግባት ለ አምስት አመታት ካገለገለ በኋላ የሚያስባቸውን ስራ ለመሰራት ስራውን በመልቀቅ በተለያዮ አካባቢዎች በመዞር ስራውን በግሉ መስራት ጀመረ።
የአልበም ስራም በመስራት 2 አልበሞችን ለአድማጭ አብቅቷል።
በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በመዞር በርካታ ስራዎችን ሰርቷል። አሁንም በመሰራት ላይ ይገኛል። በስራ ሂይወቱም ከ 30 አመት በላይ አገልግሏል፤ እያገለገለም ይገኛል።
እንኳን ደስ አለህ !
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #tesfaye_taye #africanbookrecords

« ለቅኔ ለዜማ ቤት ዝቅ ማለት ተገቢ ነው።እንደዛ ካልሆነ ዜማውን አታገኝም።»
አበበ ብርሃኔ(የግጥም እና የዜማ ደራሲ)
#Ethiopia | ከ300 በላይ የሙዚቃ አልበሞች ላይ የተሳተፈው ፤ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ እያስቆጠረ ባለዉ የሙዚቃ ህይወት ጉዞው ለበርካታ አንጋፋ እና ወጣት ድምፃውያን ግጥም እና ዜማዎችን የሰጠው አበበ ብርሃኔ የዜማ አሻራውን በብዛት ያሳረፈበትን የወጣቱ ድምፃዊ አህመድ ማንጁስ «አልጣሽ» አልበምን መነሻ በማድረግ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 መሰንበቻ ፕሮግራም ጋር ቆይታ አድርጓል።
👉« አልበም ላይ አንድም፤ስድስትም፤አስርም ዜማ መስራቴ ለእኔ እኩል ነው።ዋናው ነገር ለተዘጋጀው አልበም የምሰራው ስራ ውበት አለው ወይ? የሚለው ላይ ነው ትኩረት የማደርገው ፡፡»
👉« ከአህመድ ማንጁስ ጋር ግንኙነታችን የጀመረዉ እሱ የተስጥኦ ውድድርን አሸንፎ በንጋታው እኔ ቤት መጣ።ቁጭ አለ የሆነ ረሀብ፤ጉጉት ያለው ስሜትን ይዞ ነበር የመጣው። እንደ መጀመሪያ ልቤ አቃተዉ የሚለውን ነጠላ ዜማን ሰራን፡፡»

ቢዮንሴ በግራሚ ሽልማት የክፍለ ዘመኑ የመጀመሪያዋ ጥቁር ምርጥ የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበም አሸናፊ ሆነች
#Ethiopia | አሜሪካዊቷ አቀንቃኝ ቢዮንሴ ጂሴል ኖልስ በግራሚ ሽልማት የ21ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዋ ጥቁር ምርጥ የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበም አሸናፊ ሆናለች።
ቢዮንሴ በ67ኛው ግራሚ ሽልማት በምርጥ የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበም ዘርፍ አሸናፊ መሆን ችላለች።
በዚህም ከ1975 በኋላ በክፍለ ዘመኑ የመጀመሪያዋ ጥቁር የዘርፉ አሸናፊ ለመሆን በመብቃት ታሪክ ሰርታለች።
አቀንቃኟ “ካው ቦይ ካርተር“ በሚለው የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበሟ ነው አሸናፊ መሆን የቻለችው።
በግራሚ በርካታ ሽልማቶችን ያሸነፈችው አቀንቃኟ ከዚህ ቀደም 4 ጊዜ ያህል የዓመቱ ምርጥ አልበም ዘርፍ ላይ ብትታጭም ሳታሸንፍ ቀርታለች።
ቢዮንሴ 35 የግራሚ ሽልማቶችን የተቀዳጀች ሲሆን ከማንኛውም የሙዚቃ ባለሙያ በበለጠ በግራሚ 99 ጊዜ በመታጨት ክብረ ወሰን መያዝ የቻለች አቀንቃኝ ነች።
ለምርጥ የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበም ሽልማቱ ከ100 በላይ ድምጻዊያን ተፎካክረዋል፡፡
የ2025 የግራሚ የሽልማት ሥነ-ሥርዓትን ሚልዮኖች ተከታትለውታል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #Beyonce

በወርቅ ቀለበቶች የተጌጠ ከዘራ
#Ethiopia | ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ትናንት ምሽት በትዝታው ንጉሥ ማህሙድ አህመድ መኖሪያ ቤት ከባለቤቱና ከወዳጆቹ ጋር በመገኘት፣ በወርቅ የተጻፈ የማህሙድ የስሙ የመጀምሪያ ፌደል (M) ያለበትና መተጣጠፊያዎቹ ላይ በወርቅ ቀለበቶች የተጌጠ ከዘራ እንዳበረከተለት ምንጮች ገልጸዋል።

#Waliya_Entertainemnt #Music #teddy_afro

የተወዳጁ ሙዚቀኛ ተፈሪ አሰፋ አስከሬን ዛሬ ሀገሩ ይገባል !!
#Ethiopia : ተወዳጁ ሙዚቀኛ ተፈሪ አሰፋ* በሀገረ አሜሪካ በሕክምና ላይ እንዳለ በድንገት ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።
አስከሬኑ ዛሬ ረቡዕ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ወደ ሀገሩ ይመጣል ። በነገው ዕለት ሐሙስ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ የክብር ስንብት መርኀ ግብር ይከናወናል።
ከክብር ስንብቱ መርኀ ግብር በኋላ፣ ከቀኑ 6:30 ላይ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ይፈጸማል።
በክብር ስንብት እና በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ በመገኘት ተወዳጁን ጥበበኛ ተፈሪ አሰፋን እንድንሰናበተው ኮሚቴው የአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል። የሥነ ሥርዓቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #teferi

"የፒያሳ ቆሌዎች" የተሰኘ የቱርጉም መጽሐፍ ተመረቀ
#Ethiopia | በኢትዮጵያ ሙዚቃ ጥናት የታወቁት ጃፓናዊው አንትሮፖሎጂስት ፕሮፌሰር ኢትሱሺ ካዋሴ የጻፉት "የፒያሳ ቆሌዎች" የተሰኘው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ትናንት ማምሻውን በሀያት ሬጀንሲ ሆቴል በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ተመርቋል።
ፕሮፌሰር ኢትሱሺ ካዋሴ ላለፉት 25 ዓመታት የኢትዮጵያን ሙዚቃ ሲያጠኑ የቆዩ ሲሆን፣ መጽሐፉም በጥናታቸው ወቅት የገጠማቸውን ማህበራዊ ገጠመኞች ላይ የተመሠረተ እንደሆነ በምረቃው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።
"የፒያሳ ቆሌዎች" የተሰኘው መጽሐፍ በፕሮፌሰር ኢትሱሺ ካዋሴ በጃፓንኛ ቋንቋ የተጻፈ ሲሆን፣ "Mischief of the Gods" በሚል ርዕስ በጄፍሪ ጆንሰን ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመ ሲሆን፣ በአማርኛ ደግሞ ያዕቆብ ብርሃኑ እና ዓለማየሁ ታዬ ተርጉመውቷል።
በምረቃው መርሐ ግብሩ ላይ የተለያዩ ዝግጅቶች የቀረቡ ሲሆን ከመጽሐፉ ላይ ንባብ፣ አጠር ያለ ዳሰሳና ከተርጓሚዎቹ ጋር ጥያቄና መልስ ሌሎች የአዝማሪ ጨዋታዎች ተከናውነዋል።
መጽሐፉ በኢትዮጵያ ሙዚቃ እና ባህል ላይ ያተኮረ ሲሆን፣
17 የተለያዩ ታሪኮች ፣ 149 ገጾች ያሉት ሲሆን በ350 የኢትዮጵያ ብር ለገቢያ ቀርቧል።
"የፒያሳ ቆሌዎች" ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ጥናት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ አባላት፣ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

አንጋፋው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ በልዩ ስጦታ በወዳጅ ዘመዶቹ ተሸለመ
#Ethiopia | የትዝታው ንጉስ ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ ለሀገራችን የሙዚቃ ዘርፍ ላደረገው አስተዋፅዖ ያላቸውን አድናቆት ለመግለጽ በመኖሪያ ቤቱ በመገኘት ከወዳጅ እና ቤተሰቦቹ ከልብ የመነጨ አድናቆትን አግኝቷል።
በፕሮግራሙ ላይ ለታዋቂው ድምፃዊ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ለበርካታ አመታት ላበረከቱት ትሩፋት ያላቸውን ጥልቅ አክብሮት እና ምስጋና የሚገልጽ የወርቅ ሃብል ተበርክቶለታል።
ድምፃዊዉ ዘመን እና ጊዜ የማይሽራቸውን ስራዎችን በመስራትየሚታወቀው ማህሙድ አህመድ የሀገሪቱን የባህልና የሙዚቃ ገጽታ ለዓለም በማስተዋወቅ በኩል ትልቅ ሚና ተጫውቷል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #mehamu_ahmed

ሩብ ሚሊየን (250,000) ብር
#Ethiopia | ተወዳጁ ድምፃዊ ሸዋንዳኝ ሃይሉ ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል 2 ህንፃዎች ግንባታ ማጠናቀቂያ ይሆን ዘንድ የሩብ ሚሊየን (250,000) ብር ድጋፍ አደረገ ።
ያስጀመረን ያስፈፅመናል!!!
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #shewanday_hailu

የአይቤክስ ባንድ ስቴሪዮ በመሳሪያ የቀነባበረ ሙዚቃ ከ49 አመት በኋል በድጋሚ ለአድማጮች ሊቀርብ ነው ⵑⵑ
#Ethiopia | ከ1968 ዓ.ምቱ የአይቤክስ ባንድ አልበም የሆነውን ስቴሪዮ በመሳሪያ የቀነባበረ ሙዚቃ በሚል የተሰየመውን አልበም በድጋሚ ከ49 አመት በኋላ በድጋሚ ለአድማጮች እንደሚደርስ ሙዚቃዊ አስታውቋል ፡፡
የጆቫኒ ሪኮ እና ሰላም ወልደማርያም ልዩ ስራዎች የሚደመጡበት ይህ አልበም ከሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የዲጂታል መተግበሪያዎች አማካኝነት ለህዝብ ተደራሽ እንደሚሆን ቅዳሜ ገበያ ያገኘችው መረጃ ያሳያል ።
የሙዚቃ አልበሙ ከምድላዬይ፤ መለያየት ሞት ነው ፤ ዘራፌዋ ፤ ሸሞንሟናዬ፤ የዘመድ የባዳ፤ ሀኪም ዘሞሴ፤ የኔ ፍቅር ፤ ስቃይሲ ይካአልዩ ፤ ቱሩምቡሌ ፤ አይ ውበት ፤ አሳ አበላሻለሁ ፤ የኑሮ መጠንሽን የሚሉ ሙዚቃዎች የያዘ እንደሆነ ቅዳሜ ገበያ ካገኘችው መረጃ ተረድታለች ፡፡
Follow us
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #ibex

ኢትዮጵያ የባህል ዕሴቿን እና ኪናዊ ፀጋዎቿን ለብሪክስ አባል ሀገራት ልታስተዋውቅ ነው
#Ethiopia | “የኢትዮጵያ የባህል ድልድይ ህዝብ ለህዝብ ትስስር” በሚል መሪ ቃል ኢትዩጵያ ላይ ያሉ ቱባ ባህላዊ ዕሴቶችን፣ ኪናዊ ፀጋዎችን እንዲሁም የፈጠራ ምርቶችን በመጠቀም ከኢትዩጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች በተውጣጡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለብሪክስ አባል ሀገራት ለማቅረብ ዝግጅት ጀምራለች፡፡
ኢትዩጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በዲፕሎማሲው መስክ ከምትሰራቸው ስራዎች አንዱ የባህልና የኪነ ጥበብ ዲፕሎማሲ እንደመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዚህ ልክ አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡
ይህንን ዝግጂት ለማቅረብም የሚያስችል የውል ስምምነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሻኩራ ፕሮዳክሽን ጋር ተፈራርሟል፡፡
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #kamuzukassa

ሙዚቀኛው ሞቶ ተገኘ!
#Ethiopia | የቀድሞ ሮሀ ባንድ ሳክስፎኒስቱ በመኖሪያ ቤቱ ሞቶ ተገኘ
ከቀደምት ሮሀ ባንድ አባላት መካከል ተጠቃሹ አርቲስት ስምኦን ሊባኖስ በመኖሪያ ቤቱ ሕይወቱ አልፎ እንደተገኘ ጋዜጠኛ ግርማ ፍስሃ የአርቲስቱን የቀድሞ ስራ ባልደረባና ጓደኛ ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
" ከደቂቃዎች በፊት ጋሽ ዳዊት ይፍሩ እንዲህ አለኝ.. "እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ነን። የዛን ዘመን የሮሃ ባንድ ሳክስፎኒስት የቀድሞ የስራ ባልደረባዬና ጓደኛዬ የነበረው አርቲስት ስሞኦን ሊባኖስ ( ዮናስ ደገፉ) ዛሬ ህንድ ኢንባሲ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤት ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።
ለምርመራው የአዲስ አበባ ፖሊስ አስክሬኑን ወስዷል"አለኝ።
ግን ሌላው የሚያሳዝነው ቤተሰቦቹን ማግኘት አልተቻለም ። እና ቤተሰቡ ወይም ወዳጆቹ አዲስ አበባ ፖሊስ መጠየቅ ትችላላችሁ። " ሲል መረጃውን አጋርቷል።

#Waliya_Entertainemnt #Music

የድምፃዊ የሺ ደመላሽ አዲስ አልበም የመውጫው ቀን ተቆረጠለት…
#Ethiopia | ድምፃዊት የሺ ደመላሽ ብዙጊዜ የተለፋበትን አልበም ውብ ሰው የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ሚያዚያ 12/2017 አመተ ምህረት እንደ ሚወጣ ጠቁማለች፡፡
ድምፃዊ የሺ ደመላሽ "ውብ ሰው" የሙዚቃ አልበም በራስዋ ዩትዮብ ቻናል እና በሌሎች የሙዚቃ መተግበርያ ወደ ህዝብ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ድምፃዊ የሺ ደመላሽ የመጀመርያ አልበምዋ "ቅኔ" አልበም ማድረሷ ይታወሳል በውስጡ 12 የሙዚቃ ክር ሲኖረው ቅኔ ፣ፋኖ፣ትኩስ እና በራድ ፣ኮከብ፣ዛሬ፣መልካም እና ክፊ እና የመሳሰሉት ሲካተቱ በርካታ ከያኒያን ተሳትፈዋል በግጥም ዜማ አብዛኛውን ድምፃዊት የሺደም ደመላሽ ስትሆን ቀሪውን ሰለሞን ሙሄ እና አንድዋለም አባተ ሰርተውታል፡፡
ቅንብር ፡ሮቤል ዳኜ(10) ትራክ፣እዮብ ፋንታሁን(2) ቀሪው ትራክ ሰርተውታል ሬጌ ሮክ፣ ሬጌ ስልተምት እና ሌሎችም ስልተ ምት ተካተዋል፡፡
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #yeshi_demelash

ታዋቂ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች እና ቲክቶከሮች በእግር ኳስ ሜዳ ላይ ይፋለማሉ
#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከቅዳሜ ሚዲያ እና አድሽርታይዚንግ ጋር በመተባበር ልዩ የሆነ የታዋቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫል ሊያካሂዱ መሆኑ ተገለጸ።
በዚህ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ታዋቂ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ድምፃውያን እና ቲክቶከሮች የሚሳተፉበት የእግር ኳስ ውድድር የፊታችን ሚያዚያ 23 እና ሚያዚያ 26 በልደታ በሚገኘው ብሪሞ ሜዳ ይካሄዳል።
የቅዳሜ ሚዲያ እና አድሽርታይዚንግ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ አዳረ ረጋሳ ይህንን መርሃ ግብር አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንደገለጹት " ከዚህ ቀደም መሰል ውድድሮች በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነት የነበራቸው ሲሆን ዘንድሮም ይህንን የአብሮነት እና የመዝናኛ ጊዜ ለመፍጠር ታስቧል።
አክለውም በቅርብ ጊዜያት ህዝቡ በቤተሰቡ ልጆቹን ይዞ ወደ መዝናኛ እና ስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች በስፋት እየሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ በእነዚህ ቦታዎች ላይ አዝናኝ ፕሮግራሞች ቢዘጋጁ ህዝቡ በሰፊው እንደሚታደም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ይህ የታዋቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫልም በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ በመሆኑ ብዙዎች በጉጉት እንደሚጠብቁት "ተናግረዋል።
በመግለጫው ላይ እንደተገለጸው ሚያዚያ 23 የዋንጫ ማለፍ ጨዋታ የሚደረግ ሲሆን የፍጻሜው የዋንጫ ጨዋታ ደግሞ ሚያዚያ 26 ይካሄዳል። ከዚህ የትኬት ሽያጭ የሚገኘው ሙሉ ገቢ ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ ይውላል።
@waliyaentmt
@waliyaemtmt