Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ሕጻናት ላይ ወሲባዊ ጥቃት የሚያደርሱ ወደ ቢዮንሴ ኮንሰርት እንዳይገቡ ፍተሻ መደረጉ ተገለጸ

የሰዎችን ምሥል በማየት ማንነታቸውን የሚገልጸውን የፌሻል ሪኮግኒሽን በመጠቀም ወደ ቢዮንሴ ኮንሰርት የሚገቡ ሰዎች ሕጻናት ላይ ወሲባዊ ጥቃት የሚፈጽሙ ወይም አሸባሪ መሆናቸው እየተለየ እንደነበር ተገለጸ።

ኮንሰርቱ የተካሄደው በዌልስ በሚገኘው ካርዲፍ ከተማ ነበር።

እአአ በ2017 በማንችስተር አሬና ከደረሰው የቦንብ ፍንዳታ በኋላ አሸባሪዎችን በኮንሰርቶች ወይም ሌሎች ሰው የሚሰበሰብባቸው ቦታዎች መፈለግ እየተለመደ መምጣቱን የደቡብ ዌልስ የፖሊስ ኮሚሽነር አሉን ማይክል ተናግረዋል።
ኮንሰርቱን የሚታደሙ በርካታ ሴት ሕጻናት ስላሉ ሕጻናት ላይ ወሲባዊ ጥቃት የሚያደርሱ ሰዎችን ለመለየት እንደሞከሩም አክለዋል።

ኮሚሽነሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ካሜራ ተጠቅሞ በአርቴፍሻል ኢንተለጀንስ ሰዎችን መለየት ያለውን አስፈላጊነት ገልጸዋል።
ቢዮንሴ በካርዲፍ ኮንሰርት ባዘጋጀችበት ወቅት የሰዎች ምሥል እየታየ በወንጀል ተፈላጊ የሆኑ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ስማቸው ካለ እየተነጻጸረ ነበር።

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaent
Facebok: https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaent
Telegram - https://www.t.me/waliyaent

#waliya_entertainment #Beyonce
ቢዮንሴ በግራሚ ሽልማት የክፍለ ዘመኑ የመጀመሪያዋ ጥቁር ምርጥ የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበም አሸናፊ ሆነች

#Ethiopia | አሜሪካዊቷ አቀንቃኝ ቢዮንሴ ጂሴል ኖልስ በግራሚ ሽልማት የ21ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዋ ጥቁር ምርጥ የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበም አሸናፊ ሆናለች።

ቢዮንሴ በ67ኛው ግራሚ ሽልማት በምርጥ የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበም ዘርፍ አሸናፊ መሆን ችላለች።

በዚህም ከ1975 በኋላ በክፍለ ዘመኑ የመጀመሪያዋ ጥቁር የዘርፉ አሸናፊ ለመሆን በመብቃት ታሪክ ሰርታለች።

አቀንቃኟ “ካው ቦይ ካርተር“ በሚለው የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበሟ ነው አሸናፊ መሆን የቻለችው።

በግራሚ በርካታ ሽልማቶችን ያሸነፈችው አቀንቃኟ ከዚህ ቀደም 4 ጊዜ ያህል የዓመቱ ምርጥ አልበም ዘርፍ ላይ ብትታጭም ሳታሸንፍ ቀርታለች።

ቢዮንሴ 35 የግራሚ ሽልማቶችን የተቀዳጀች ሲሆን ከማንኛውም የሙዚቃ ባለሙያ በበለጠ በግራሚ 99 ጊዜ በመታጨት ክብረ ወሰን መያዝ የቻለች አቀንቃኝ ነች።

ለምርጥ የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበም ሽልማቱ ከ100 በላይ ድምጻዊያን ተፎካክረዋል፡፡

የ2025 የግራሚ የሽልማት ሥነ-ሥርዓትን ሚልዮኖች ተከታትለውታል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Beyonce