ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከምስረታው ጀምሮ ባካሄዳቸው የተለያዩ የሩጫ መርሓግብሮች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሰጠው ያልተቋረጠ ድጋፍ እና ለሩጫ መርሐግብሮቹ ስኬታማነት ላበረከተው አስተዋፅዖ ‘የወርቅ ደረጃ’ የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት። ሽልማቱን ያበረከቱት ጀግኖች አትሌቶቻችን ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ እና ገዛኸኝ አበራ ሲሆኑ በሽልማት አሰጣጥ ስነስርዐቱ ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ናሲሴ ጫሊን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ታላቁሩጫበኢትዮጵያ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ታላቁሩጫበኢትዮጵያ
አዲስ በረራ በባህር ዳር እና ደሴ ኮምቦልቻ ፤ በመቐለ እና ሽረ መካከል!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐምሌ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሳምንት ሥስት ቀን ማክሰኞ፣ ሐሙስ እና ቅዳሜ ከባህርዳር ወደ ደሴ ኮምቦልቻ እንዲሁም ሰኞ፣ ረቡዕ እና ዓርብ ከመቐለ ወደ ሽረ ቀጥታ በረራ የጀመረ መሆኑን ለክቡራን መንገደኞቹ በደስታ ይገልጻል። ጉዞዎን ያቅዱ በተቀላጠፈ አገልግሎታችን ይረካሉ። በምቾት ይጓዙ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ

የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ውበት እና ኩራት ጋር ከፍ ብለን እንብረር! #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የማይረሳ እና አስደሳች ጉዞ ከእኛ ጋር ያድርጉ!
የበረራ ምዝገባዎን በዚህ ያድርጉ፡
https://www.ethiopianairlines.com/et
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የበረራ ምዝገባዎን በዚህ ያድርጉ፡
https://www.ethiopianairlines.com/et
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጎርጎራ ሪዞርትን በኢትዮጵያ ስካላይት ሆቴል ስር የማስተዳደር ኃላፊነትን ዛሬ በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በተደረገ የስምምነት ስነስርዐት ተረከበ። በስነ ስርዐቱ ላይ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አረጋ ከበደ፣ ከፍተኛ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ሥራ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ እና ሌሎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት የተገነቡትን ሀላላ ኬላ ሪዞርት፣ የወንጪ ኢኮ ሎጅ እንዲሁም የጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅን የማስተዳደር ኃላፊነትን በቅርቡ ወስዶ ወደ ስራ በመግባት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ኢንደስትሪ ዕድገት የራሱን ድርሻ ለመወጣት ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያስካይላይትሆቴል #ገበታለሀገር
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #የኢትዮጵያስካይላይትሆቴል #ገበታለሀገር
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የተከሰተው ድንገተኛ የመሬት ናዳ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ባደረሰው ከፍተኛ ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለተጎጂ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ይመኛል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥገና ክፍል እና አውሮፕላኖች አምራች የሆነው ATR አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ፈጸሙ። በስምምነቱ መሰረት በአፍሪካ ትልቁ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥገና ክፍል በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የATR ስሪት አውሮፕላኖችን የመጠገን አቅሙን የሚያዳብር ይሆናል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
ውድ መንገደኞቻችን
የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እ.ኤ.አ. 21 ጁላይ 2024 ለአየር መንገዳችን በላከው ደብዳቤ እ.ኤ.አ. ከሴፕቴምበር 30 ቀን 2024 ዓ.ም. ጀምሮ አየር መንገዳችን ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን ሁሉንም በረራ ማገዱን አሳውቆናል።
ደብዳቤው ለክልከላ ውሳኔ ያደረሱ ምክንቶችን አልጠቀሰም። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳዩን አስመልክቶ የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝና ጉዳዩም በበጎ መልኩ እልባት እንደሚያገኝ ያለውን ዕምነት ይገልጻል።
በዚሁ አጋጣሚ አየር መንገዱ ተጨማሪ መረጃዎች እንደተገኙ ለውድ ደንበኞቹ እንደሚያሳውቅ ለመግለፅ ይወዳል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አልያንስ አባል

አዲስ በረራ በጋምቤላ እና አሶሳ መካከል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በጋምቤላና በአሶሳ መካከል ቀጥታ በረራ የጀመረ መሆኑን ለክቡራን መንገደኞቹ በደስታ ይገልጻል። ጉዞዎን ያቅዱ በተቀላጠፈ አገልግሎታችን በምቾት ይጓዙ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በጋምቤላና በአሶሳ መካከል ቀጥታ በረራ የጀመረ መሆኑን ለክቡራን መንገደኞቹ በደስታ ይገልጻል። ጉዞዎን ያቅዱ በተቀላጠፈ አገልግሎታችን በምቾት ይጓዙ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፓሪስ የ2024 ኦሎምፒክ ሀገራችን ኢትዮጵያን ወክሎ ለሚሳተፈው የኦሎምፒክ ቡድን መልካም ምኞቱን ይገልፃል። ድል ለኢትዮጵያ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓሪስ2024
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ፓሪስ2024