Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
90.5K subscribers
3.78K photos
142 videos
2 files
413 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
ወዳጅነት በተሞላው ልባዊ መስተንግዶአችን ልንቀበልዎ ዝግጁ ነን። ከእኛ ጋር በምቾት ይብረሩ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፍረው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ፈገግታን በተላበሰ መስተንግዶ ወዳሻዎት ቦታ ይጓዙ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮቪድ-19ን ወረርሽኝ ለመከላከል እና ለመግታት በተደረገው ዓለም አቀፍ ርብርብ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅዖ በቶሮንቶ ካናዳ በተካሄደ የመጀመሪያው ድህረ ኮቪድ ኮንፈረንስ የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት።
ሽልማቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በአፍሪካ እና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የሚገኙ አገራት ወረርሽኙን ለመከላከል ጥቅም ላይ ያዋሉዋቸውን የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶች በቀልጣፋ አገልግሎቱ በማጓጓዝ የበርካቶችን ህይወት ለመታደግ በተደረገው ጥረት ለነበረው የጎላ ሚና የተሰጠ ነው።
ኮንፈረንሱ የተዘጋጀው በDevelopment International Initiatives (LDII) ፣በምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት(ኢጋድ) እና የተለያዩ ወረርሽኞችን በጋራ መከላከል ላይ አተኩረው በሚሰሩ የስራ አጋሮች ትብብር ነው።
ለበለጠ መረጃ: https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-receives-global-recognition-and-appreciation-award-for-outstanding-role-in-covid-19-response
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጉዘው ሊያዩት የሚሹት መዳረሻ የት ነው?

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን አቤል መንግስቱ ናቸው፤ እናመሰግናለን! እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበርሩ ያነሷቸውን ምስሎች ይላኩልን፤ መልሰን እናጋራዎታለን።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለክቡራን መንገደኞቹ የሚሰጣቸው ዓለም አቀፍ የበረራ ቲኬት ሽያጭ አገልግሎቶች በሙሉ በውጪ ምንዛሪ (hard currency) ብቻ እንደሚሆን ተደርጎ በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ አውታሮች ሲዘዋወር ተመልክቶታል።

ይሁን እንጂ የጉዳዩ ትክክለኛ መረጃ በቅርቡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም መመርያ ማውጣቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ ቀደም ከሀገር ውጪ ተነስተው ወደ ሀገራችን ለሚደረጉ ጉዞዎች በሀገር ውስጥ መገበያያ ገንዘብ ሲሰጥ የነበረውን የበረራ ቲኬት ሽያጭ አሰራር ከሐምሌ 02 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በከፊል የተከለከለ መሆኑን እና በውጪ ምንዛሪ አገልግሎቱን የሚያገኙ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።

ይኸውም ሀገር ውስጥ በሚንቀሳቀሱ በሁሉም አየር መንገዶች ተግባራዊ እንዲደረግ የወረደ መመርያ መሆኑን እያሳሰብን ኢትዮጵያዊያን እና ህጋዊ ሰነድ ያላቸው (የመኖርያ ፈቃድ፣ ቢጫ ካርድ፣ የሥራ ፈቃድ፣ የዲፕሎማቲክ ፈቃድ ወዘተ) የውጪ ሀገር ዜጎች በሙሉ ከሀገር ውስጥ ወደ ውጪ ሀገራት ለሚደረጉ በረራዎች የቲኬት ሽያጭ አገልግሎታችንን ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር መሰረት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። ነገር ግን ትኬታቸውን በኢትዮጵያ የሚገዙ የውጭ ሀገር ዜጎች በውጭ ምንዛሬ መክፈል ይኖርባቸዋል።

ለበለጠ መረጃ
https://www.ethiopianairlines.com/aa/services/help-and-contact/Global-Customer-Interaction-Centre-numbers

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የስታር አሊያንስ አባል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች እ.ኤ.አ. በ1977 ዓ.ም. በልዩ የአቪዮኒክስ ሥልጠና ላይ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ትውስታ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን ዘርፉ ስኬት ቁልፍ ሚና ካላቸው ባለድርሻ አካላት አንዱ ለሆነው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አቪዬሽን ፖሊስ መምሪያ ያስገነባውን መኖሪያ ካምፕ አስመርቆ ለአገልግሎት አበቃ።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ክቡር ደመላሽ ገሚካኤል ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ስኬታማ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አቪዬሽን ፖሊስ መምሪያ አይተኬ ሙያዊ አስተዋፅዖ እያበረከተ እንደሆነ ገልፀዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ሞምባሳ የ“አንድ ትኬት ይግዙ፤ አንድ በነፃ ይሸለሙ” ልዩ የጉዞ ጥቅል አዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል። ትኬትዎን እስከ ሐምሌ 18 ቀን 2016 ዓ. ም በ ET323/324 ላይ ብቻ ይግዙ፤ ጉዞዎን እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ. ም ያድርጉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ