ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከምስረታው ጀምሮ ባካሄዳቸው የተለያዩ የሩጫ መርሓግብሮች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሰጠው ያልተቋረጠ ድጋፍ እና ለሩጫ መርሐግብሮቹ ስኬታማነት ላበረከተው አስተዋፅዖ ‘የወርቅ ደረጃ’ የዕውቅና ሽልማት ተበረከተለት። ሽልማቱን ያበረከቱት ጀግኖች አትሌቶቻችን ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ እና ገዛኸኝ አበራ ሲሆኑ በሽልማት አሰጣጥ ስነስርዐቱ ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ናሲሴ ጫሊን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ታላቁሩጫበኢትዮጵያ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ታላቁሩጫበኢትዮጵያ