አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
አሜሪካ የDV-2025 አመልካቾችን መቀበል ጀመረች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመታዊውን የዲይቨርሲቲ ቪዛ (#ዲቪ) ፕሮግራም / " ግሪን ካርድ ሎተሪ " በመባል የሚታወቀውን በአሜሪካ ለመኖር እና ለመስራት ለሚፈልጉ አመልካቾች ዛሬ ክፍት አድርጓል።

እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ መርሃ ግብሩ ዛሬ ሩቡዕ ጥቅምት 4 ተጀምሮ ማክሰኞ ህዳር 7 ቀን 2023 ይጠናቀቃል።

አሜሪካ አሁን ባለው ፕሮግራም 55000 ለሚደርሱ የውጭ ዜጎች የግሪን ካርድ እድል ትሰጣለች።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲቪ ፕሮግራም ለመመዝገብ / ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ እንደሌለው አሳውቋል።

ነገር ግን ወደፊት ለቃለ መጠይቅ ቀጠሮ የተያዙ ተመራጮች መደበኛ የቪዛ ማመልከቻ ከማቅረባቸው በፊት የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ። እነዚህ ተመራጮች በቆንስላ ኦፊሰር አማካኝነት ለቪዛ ብቁ መሆን አለመሆናቸውን የሚወሰንላቸው ናቸው።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዲቪ ለመሙላት ብቁ ከሆኑ በርካታ ሀገራት 55,000 አመልካቾች በዘፈቀደ በውስጥ ስርዓት ይመረጣሉ።

አስፈላጊ #መመሪያዎችን ፣ መስፈርቶችን እንዲሁም ለማመልከት ይህን ትክክለኛ ድረገፅ ይከተሉ፦ https://dvprogram.state.gov/

አመልካቾች ዲቪ ለማመልከት #ክፍያ_የማያስፈልግ ስለሆነ ከአጨባርባሪዎች እንዲጠነቀቁ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
👍9
በስምምነት የተደረገ የውርስ ኃብት ድርሻ ክፍፍል በሕግ ፊት ስለሚኖረው ውጤት፡፡ 

ወራሾች ራሳቸው ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከፍርድ ቤት ውጪ የውርስ ኃብት ክፍፍል ያደረጉ ከሆነ ይህ ስምምነት ፍርድ ቤት ቀርቦ ባይጸድቅም የሚጸና ነው፡፡ ማንኛውም ወገን ስምምነቱ በፍርድ ቤት ቀርቦ አልጸደቀም ስለዚህ ሊጸና አይገባም የሚል መከራከሪያ ቢያቀርብ የሕግ መሰረት የለውም፡፡ ( የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1079(1) እና 1080(1)
via #ethiolawtips
👍5
Legal vacancy:
1
በሥነምግባር ግድፈት የተከሰሱ 24 ጠበቆች ተቀጡ

*******

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መስከረም 22/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፍትህ ሚኒስቴር የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሥነምግባር ኮሚቴ በሥነምግባር ግድፈት ክስ የቀረበባቸው 24 ጠበቆችን መርምሮ ጥፋተኛ በማለት ቅጣት ጥሎባቸዋል።

ከ24ቱ ተከሳሾች መካከል 18ቱ የጥብቅና ፍቃዳቸውን በወቅቱ ባለማደስ የተከሰሱ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ግን በባለጉዳይ በቀረበባቸው የሥነምግባር ግድፈት ክስ ነው ጥፋተኛ ተብለው ቅጣት የተጣለባቸው፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር የጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥ አስተዳደርና የነጻ ህግ ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ደምሴ ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በሥነምግባር ግድፈት ክስ የቀረበባቸው 46 ጠበቆች ነበሩ።

ክስ ከቀረበባቸው ጠበቆች መካከል 24ቱ የቀረበባቸው ክስ ተመርምሮ ጥፋተኛ በመባላቸው ቅጣት እንደተጣለባቸው ገልጸው፥ ቀሪዎቹ ነጻ ተብለዋል።

ጥፋተኛ ከተባሉት 24 ጠበቆች ውስጥ ደግሞ 18ቱ በወቅቱ የጥብቅና ፍቃዳቸውን ባለማደስ በሥነምግባር ግድፈት የተከሰሱት በገንዘብ እንዲቀጡ ተወስኗል።

በተመሳሳይ በባለጉዳይ የሥነምግባር ግድፈት ክስ የቀረበባቸው አራት ጠበቆች በገንዘብ እንዲቀጡ የተወሰነ ሲሆን፥ አንድ ጠበቃ ደግሞ ለ3 ወራት ከጥብቅና ሙያው እንዲታገድ ተወስኗል። እንዲሆም ሌላኛው አንድ ጠበቃ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ኃላፊው ገልፀዋል።

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያ ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የጥቆማ ሶፍትዌር፡- https://epfs.gov.et
የጥቆማ ኢሜል፡- CorruptionReportEthiopia@feacc.gov.et
👍94
Lion Insurance New Job Vacancies Oct 2023👈👈

Lion Insurance Company invites interested and qualified candidates for the following positions.

Position 1: Legal Officer III
Educational background: LLB in Law
Relevant Work Experience: Four (4) Years, at list 2 years in insurance company
Additional skill: Excellent written and verbal communication, Basic computer skill ,Knowledge of all applicable laws, rules and regulations, High attention to detail, Strong negotiation  skills, Ability to prepare complex  legal  documents

Required Number: 2
Place of work: Addis Ababa

Position 2: Senior Legal Officer
Educational background: LLB in Law
Relevant Work Experience: Six (6) Years, at list 2 years in insurance company
Additional skill: Excellent written and verbal communication, Basic computer skill ,Knowledge of all applicable laws, rules and regulations, High attention to detail, Strong negotiation  skills, Ability to prepare complex  legal  documents

Place of work: Addis Ababa
Deadline: October 10, 2023


How to Apply:👈👈👈👈
Interested applicants, who full fill the aforementioned requirements can submit non-returnable application latter, CV & copies of testimonials accompanied by original documents in person within 10 (TEN) consecutive days from the date of this announcement in the Reporter news paper to:-
Lion insurance Company (S.C) Head office, located at Haile G/slassie Avenue, Lion Insurance Building HR& Facility Management Department 4th floor;Tell: – 0116187000/0116352285 –
Addis Ababa-Ethiopia.
https://t.me/lawsocieties
#share 👈👈👈👈👈👈👈
👍7😁1
🌿🌿Baga ayyaana Irreechaa   nagayaan isin ga'e jechaa
Qnash Ayyaana gaarii akka isiniif ta'uuf hawwiisaa isa guddaadha.

እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
👍106🤬3👎2
ሰ/መ/ቁጥር 241073 ሀምሌ 27 ቀን 2015 ዓ/ም #ውርስ_ህግ #ኑዛዜ
አመልካች፡- አቶ ዳዊት አበራ አቶ ዳዊት አበራ- ሞግዚት ፀሐይነሽ ተሾመ 
ተጠሪ፡- ወ/ሮ አለምነሽ ከፈለኝ-
በሁኔታ ላይ የተመሰረተ (conditional legaty) ወይም በገደብ የተደረገ ኑዛዜ

በ#ወራሽ የገቢ ማጣት እና በጤና ሁኔታ ችግር የተነሳ ኑዛዜ ሊሻሻል ወይም ቀሪ ሊሆን ስለሚችልበት ሁኔታ
#ፍ/ሕ/ቁጥር 879/1 እና #ፍ/ሕ/ቁጥር 872

በዚህ መዝገብ አመልካች የሟች ልጅ ሲሆኑ ተጠሪ ሟች ኋላ ላይ (ከአመልካች እናት በኋላ) ያገቧት ሚስት ናት። ሟች ለልጆቻቸው ንብረታቸውን እንዲወርሱ ኑዛዜ የተዉ ቢሆንም በኑዛዜው ተጠሪ በህይወት እስካሉ የመጠቀም መብት የተሰጣቸው በመሆኑ ኑዛዜው ተፈጻሚነት የሚያገኘው ተጠሪ ከሞቱ በኋላ ነው።
የአመልካች ጥያቄ ሟች ለተጠሪ በውርስ ሐብት በህይወት እስካሉ እንዲጠቀሙ ኑዛዜ ማድረጋቸው አመልካች ያለብኝን የአይምሮ ጤና እና የኑሮ ችግር ለመወጣት እንዳልችል የሚያደርገኝ ስለሆነ (በተጨማሪም ኑዛዜው በዝምታ የነቀለኝ ስለሆነ የሚል መከራከሪያም አቅርበዋል።) ኑዛዜው ሊፈርስ ይገባል የሚል ነው።

የ#ሰበር ችሎቱ የተያዘውን ጉዳይ አስመልክቶ የሰጠው ውሳኔ እና የሐተታው ክፍል ከዚህ በታች ይነበባል

አመልካች ባለባቸው ጤና ችግር ምክንያት ስራዎችን በመስራት ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት የራሳቸውን ገቢ ማግኘት እና ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎችን መሸፈን የማይችሉ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ሟች ለክርክሩ መሰረት በሆነው ኑዛዜ ለተጠሪ በህይወት እስካሉ በውርስ ሀብቱ የመጠቀም መብት ባያስተላልፉ ኖሮ አመልካች የውርስ ድርሻውን በማግኘት ለኑሮ እና ለጤና አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎችን ለመሸፈን ያስችላቸዋል፡፡ የሟችን ፍላጎት ለማስጠበቅ ሲባል ብቻ የአመልካች የከፋ ችግር እየታወቀ በኑዛዜ የተቀመጠው ገደብ መቀጠል አለበት የሚባል ከሆነ የአመልካችን በህይወት የመኖር መብት አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ለሞራል ተቃራኒ ይሆናል፡፡ ተጠሪ በሰጡት መልስ የአመልካች ብቻ ሳይሆን የተጠሪም የጤና ችግር ከግምት ሊገባ ይገባል በሚል የሚከራከሩ ቢሆንም ተጠሪ ለክርክር መሰረት ከሆነው ንብረት ላይ 50% የሚስትነት ድርሻ ያላቸው ከመሆኑ አንጻር በኑዛዜው ላይ የተቀመጠው ገደብ አመልካችን በተመለከተ ብቻ ተፈጻሚነቱ ቢቀር በተጠሪ ላይ የሚደርስባቸው ጉዳት ከፍተኛ ወይም ለሞራል ተቃራኒ ነው ሊባል አይችልም፡፡

ሟች ለተጠሪ በህይወት እስካሉ የውርስ ድርሻቸውን የመጠቀም መብት በኑዛዜ አስተላልፈዋል፡፡ በኑዛዜው መሰረት የሟች ወራሾች ድርሻቸውን ማግኘት የሚችሉት ተጠሪ ከዚህ አለም በሞት ሲለዩ ብቻ ነው፡፡ ይህም ሟች ለወራሾቻቸው ያረጉት ኑዛዜ በሁኔታ ላይ የተመሰረተ (conditional legaty) ወይም በገደብ የተደረገ ኑዛዜ መሆኑን ያሳያል፡፡ በኑዛዜ የተጠቀሰው ሁኔታ ወይም በወራሾች ላይ በኑዛዜ የተደረገው ገደብ እንዳልተደረገ ሊቆጠር የሚችለው ግዴታው የማይቻል ወይም ለህግ ወይም ለመልካም ጠባይ ወይም ለሞራል ተቃራኒ ሆኖ ሲገኝ መሆኑን በፍ/ሕ/ቁጥር 879/1 ስር ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም በፍ/ሕ/ቁጥር 872 ስር ሟቹ በፊት ካደረገው ጋብቻ የተገኙ ተወላጆች ያሉት ከሆነ ለኋላኛው ባል ወይም ሚስት ጥቅም የተደረገ የኑዛዜ ቃል በዳኞች ሊቀነስ ወይም ሊሻር እንደሚችል ተመልከልቷል፡፡

እነዚህ ሁለት ድንጋጌዎች ሟች ከቀድሞ ትዳር የተፈሩ ልጆች እያሉ ለኋላኛው ሚስት ወይም ባል የተደረገ ኑዛዜ ከቀድሞ ትዳር የተወለዱትን ልጆች ጥቅም የሚጎዳ ከሆነ በተወላጆቹ ጠያቂነት ዳኞች ኑዛዜውን ለማሻሻል ወይም ሙሉ ለሙሉ ቀሪ ሊያደርጉ እንደሚችሉ፤ በተለይም ኑዛዜው በግዴታ ላይ የተመሰረተ ከሆነ እና ግዴታው ለህግ፣ ለሞራል ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ ከሆነ በኑዛዜው የተመለከተው ገደብ ወይም ግዴታ በኑዛዜው እንዳልተጻፈ ይቆጠራል፡፡ በእርግጥ እነዚህ ድንጋጌዎች ተግባራዊ ሲደረጉ በጥንቃቄ ሊሆን ይገባል፡፡ ምክንያቱም ኑዛዜ የተናዛዙን ፍላጎት መግለጫ እና ሟች ንብረቱን ለሚፈልገው ሰው የማስተላለፍበት አንዱ መንገድ በመሆኑ ኑዛዜው ሲቀነስ ወይም ሲሻሻል ወይም በኑዛዜ የተቀመጠው ገደብ እና ግዴታ ቀሪ ሲደረግ የተናዛዙን ፍላጎት እንዳይቃረን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ በሌላ በኩል ኑዛዜው ላይ የተገለጸው ግዴታ ለመፈጸም የማይቻል ወይም ለህግ ወይም ለሞራል ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ መሆኑ በጥንቃቄ በዳኞች ተመርምሮ ግዴታው ሊፈጸም የማይችል ወይም ለህግ ወይም ለሞራል ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ ሆኖ ከተገኘ በኑዛዜ ላይ የተመለከተው ገደብ ወይም ግዴታ ቀሪ ሊሆን ይገባል፡፡
👍153👎2
ሰራተኛን ያለማስጠንቂያ ስለ ማሰናበት ያልታተመ የሰበረ ውሳኔ
👍2
Fresh Graduate- People in Need(PIN) would like to invite qualified and competent applicants to apply for the following vacant post.

Position: HR intern

Minimum BA degree in Management, Human Resource Management, Law other related social science fields of study from a recognized higher education institution.

How to Apply               
   👇👇👇                    
https://shegerjobs.net/people-in-need-vacancy-announcement/

Deadline: Oct  16, 2023
👍1
ስለ ጋብቻ
***
በራህዋ ተስፋዬ ቸርነት (LL B, LL M, የህግ አማካሪ እና ጠበቃ) ( ነገሩን ፍጁት)

ውድ አንባብያን ዛሬም በዚሀ ጽሁፍ ዳግም ለመናኘት ስለበቃን ደስ ብሎኛል። ዞሮ ዞሮ ከቤት፤ ኑሮ ኑሮ ከመሬት አይቀርምና የሞት መልአክ በራችንን ከማንኳኳቱ በፊት ቃላችንን በኑዛዜ እንዴት በተግቢው ማስፈር እንዳለብን ባለፈው ተነጋግረን ነበር። አሁን ደግሞ የህይወታችንን ታላቁን ስምምነት፤ ትዳርን፤ እንዴት ህጋዊ በሆነ መንገድ አስጀምረን፣ በሀገራችን የፍትህ ማእቀፍ መደላደል እንችላለን የሚለውን ጥያቄ በከፊሉ የምትመልስ አንዲት አጭር ጽሁፍ ይዤ ቀርቤያለሁ። የትዳር ጅምሩን ጋብቻን ትዳስሳለች። መልካም ንባብ።
ለመጋባት ወሰናችሁ እንበል። በመጀመሪያ እንኳን ለዚህ ማዕረግ ፈጣሪ አበቃችሁ። ለሶስት ጉልቻ፣ ለስራና ለክብሩ ደርሳችኋል። የፍቅር የትብብር ያርገው። ወይም ውዶችህ/ውዶችሽ እዚህ ስለደረሱ ምን ማድረግ ይኖረባቸው ይሆን ብላችሁ ያሰባችሁ ደግሞ የናንተ ቢጤ ጠባቂ ይቆያችሁ። ስለ ጋብቻ ህጉ ይህን እንደሚል እነግራችኋለሁ።
፩. በመጀመሪያ ለመጋባት ህጉ ብቁ ናቸው የሚለው እነማንን እንደሆነ እንመልከት። ቤተሰብ ማህበረሰቡ የሚደራጅበት መሰረታዊ መገንቢያ ጡብ በመሆኑ ህጉ ጥበቃ እና ክትትል ያደርግለታል። ይህም ጋብቻው ከተፍፀመ በኋላ ብቻ አይደለም፤ ጋብቻው ከመከወኑ በፊት ከሚከሰቱ እና እንዳይፀና ህልውናውን ሊፈታተኑት ከሚችሉ ግድፈቶችም ጭምር ነው። ስለዚህ ወደ ጋብቻ ሊገቡ ያሰቡ ጥንዶች ራሳቸውንም ትዳራቸውንም ለመጠበቅ በእነዚህ መስፈርቶች መመራት ግዴታቸው ነው። ከምንም ነገር በፊት ጋብቻ እንዲጸና ተጋቢዎች ያልተገደበ፣ ሙሉ ፈቃዳቸውን መስጠት አለባቸው። ይህ በመሆኑ በሀይል የተደረገ ጋብቻ ህጋዊ መሰረት እንደማይኖረው ግልፅ ነው። መሰረታዊ ስህተት ተሳስተው የፈፀሙት ጋብቻም ቢሆን እንደሁኔታው ፈራሽ ይሆናል። ቢሆንም የትኛውም ስህተት ትዳር አያፈርስም፤ በህጉ ስር መሰረታዊ ስህተት የሚባሉትም የሚክተሉት ናቸው፡ የሚያገባው ሰው ማንነት አግቢው ከጠበቀው ሌላ ሲሆን፤ ያገባው ሰው ሊድን የማይችል ወይም ወደ ሌሎች ሊተላልፍ የሚችል ከባድ በሽታ ኖሮበት ይህንን ሳያውቅ አግቢው ካገባው፤ ሌላኛው ግለሰብ ግብረስጋ ግንኙነት መፈጸም የማይችል ከሆነና አግቢው ይህን ሳያውቅ ትዳር ከመሰረተ፤ ወይም ተጋቢው ግብረ ሰዶማዊ ግንኙነት የሚፈጽም መሆኑን ሳያውቅ የትዳር አጋሩ ካደረገው ናቸው። እዚህ ላይ አንድ ህጉ በተዘዋዋሪ የሚናገረው ነገር  ስላለ ልብ ሳትሉ እንዳታልፉ ልጠቁማችሁ።  አንድ ሰው ከላይ እንደተገለጸው አይነት ከባድ በሽታ ኖሮበት ወይም ግንኙነት መፈጸም የማይችል ግለሰብ ሆኖ ለተጋቢው ከመጋባታቸው በፊት ካሳወቀው እና ተጋቢው በጋብቻው ለመቀጠል ከወሰነ ጥንዶቹ የመጋባት ሙሉ ህጋዊ መብት አላቸው። ጋብቻ የፍቅር እና የመተጋገዝ ስምምነት ነው። መታመም እና ወሲባዊ ድክመት ይህንን እውነታ ስለማያስቀሩ ተቻችለው አብረው ለመሆን ለቆረጡ ህጉ ጥበቃ አይከለክልም።  
በግለሰቦች ማንነት እና/ወይም ሀጋዊ ሁኔታ ምክንያት የሚሰጡ ከልከላዎችም አሉ። እነዚህም በዘመዳሞች (በወላጆችና ተወላጆች፣ ወንድም እና እህት፣ በአክስቶች እና አጎቶች ወደታች ከሚቆጠሩ ዘመዶቻቸው፣ በትዳር በተፈጠር ዝምደናም፣ ዝምድናው ያልተረጋገጠ ግን በማህበረሰቡ በሰፊው የሚገመት ከሆነ እንኳን) መካክል ጋብቻን መፈጸም፤ በህግ የተከለከለን ሰው ማግባት እና/ወይም ፍቺ ከፈጸመች 180 ቀን ያልሞላትን ሴት ማግባት ህጉ አይፈቅድም። ከፈታች 180 ቀን ያለፋት ሴት ግን በዚህ ጊዜ ውስጥ ከወለደች ከማግባት አትከለከልም።
ደግሞ አንዳንድ ሁኔታዎች ሲሟሉ ስለሚቀሩ ክልከላዎች እናውራ። በፌደራል ህጉ መሰረት የማግቢያ ትንሹ አመት 18 ነው። ነገር ግን እንደክልሉ ህግ ይህ እድሜ ሊበልጥ ወይም ሊያንስ ይችላል። በፌደራል ህግ ራሱ እድሜው ያልደረሰ አንድ ልጅ ነፃ ወጥቶ ራሱን መቻል ይችላል። ይህ ልጅ ላግባ ቢል አይከለከልም። በተጨማሪም ለፍርድ ቤቶች በሚገባ አቤቱታ ይህንን የእድሜ መስፈርት ከሁለት አመት ላላነሰ ጊዜ ማስቀነስም ይቻላል። ሌላው ክልከላ አስቀድሞ ያገባን ይመለከታል። ዋናው መስፈርት ለአንድ ሰው አንድ አጋር ብቻ ቢሆንም በባህል እና በሃይማኖት በሃገራችን ውስጥ ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት እንደሚቻል ይታወቃል። ይህ በህጉ እውቅና ተሰጥቶታል። በመጨረሻም በመርህ ደረጃ ጋብቻን በወኪል ወይም እንደራሴ መፈፀም አይቻልም። ተጋቢዎቹ በአካል ቃላቸውን ለመስጠት መገኘት አለባቸው። ነገር ግን ተጋቢዎች በሁኔታዎች የሚገደዱ ከሆነ እና ወካዩም ተጋቢ ፈቃዱን በማያሻማ ሁኔታ ካሳወቀ ጋብቻ በውክልና መፈጸም ይቻላል።  
፱. ስለዚህ እነዚህ ጉድለቶች እንዳሉ እየታወቀ ጋብቻ ቢፈጸም ምን ይፈጠራል? በመሰረቱ ግድፈት አለበት የተባለ ትዳር እንዲፈርስ ነው የሚደረገው። ይህ ቢሆንም ግን የሚፈርስበት ሁኔታ በግድፈቱ ይወሰናል። በዘመዳሞች መካከል የሚደረግ ጋብቻ በማንኛውም ጊዜ ይህ ለህግ አስፈጻሚ አካላት ግልፅ የተደረገ እንደሆነ አንዲፈርስ ይደረጋል። በአንጻሩ እድሜያቸው ያልደረሰ ስዎች የሚፈጽሙት ጋብቻ፤ ባለ ጋብቻ ላይ የተፈፀመ ጋብቻ፤ በፍርድ የተከለከለ ሰው የሚፈፅመው፤ በሃይል እና/ወይም በስህተት የተፈፀሙ ጋብቻዎች ፈራሽ ቢሆኑም እንኳ ተጋቢዎቹ ወይም በህግ ይህንን አሳውቀው ማስፈርስ የሚችሉ ሁሉ በተወሰነ ጊዜ ግድፈት መኖሩን ካላሳወቁ ቀሪ መሆን የሚችሉት በፍቺ ብቻ ይሆናል ማለት ነው። ህጉ ይህንን የጊዜ ወሰን በስድስት ወር ቢበዛም በሁለት አመት ይወስነዋል። ለምን እነዚህ ግድፈቶች ስለኖሩ ብቻ ጋብቻው ቀሪ አይሆንም ብለን እንጠይቅ ይሆናል። መልሱ ቀላል ነው። ግድፈት አለበት ሰለተባለ ብቻ ጋብቻን የሚያህል ነገር ማስቀረት ተገቢ አይደለም ብሎ ህጉ ስለሚያምን። ለምሳሌ በህግ የተከለከለው ሰው ወንጀል ሰርቶ ይሆናል። ስለዚህ ወንጀለኛ ማፍቀር ማግባት የለበትም? ወይም ሶስት አመት በሰላም ከኖሩ በኋላ አስገድዶ ስላገባት ትዳር የለም ብሎ የሚመጣ ሰው ፍትሃዊ ጥያቄ አነሳ ማለትስ? እዚህ ጋር በምንም መልኩ የህጉ ሚዛን ሳያዘነብል ቆመ እያልኩ አይደለም። ግን በአብዛኛው ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች ጋር ተጋቢዎች መኖር ከቻሉ ህጉ ስለእነርሱ ለመወሰን እንደማይፈልግ እየገለጸ ነው እያልኩ እንጂ።
በሌላ ጎኑ ግድፈት ሳይሆኑ ናቸው ተብለው ስለሚታመኑ ጥያቄ የሚፈጥሩ ጉዳዮች አሉ። ስለዚህ ህጉ በግልጹ ይህን ያስቀምጣል፡  የፈታች ሴት ብቻዋን መኖር ባለባት ጊዜ ካገባች፤ የመዝገብ ሹም የተባለ ሰው ስልጣን ሳይኖረው ጋብቻን ካስፈፀመ፤ እና የጋብቻ የፎርም ወይም የይዘት ጉድለት ትዳርን የሚያህል ነገርን የማስቀርት ብቃት የላቸውም።  
፭. አሁን ወደ ገደለው እንዙር። እንዴት መጋባት እንችላለን? ከአንድ በላይ አማራጭ አለላችሁ። በሃይማኖታዊ እና በባህላዊ ስርዓት ወይም አስተዳደራዊ አካል ፊት መጋባት ይቻላል።  ብትሉ በቤተክርስትያን ወይም በሼሁ ፊት ፈጣሪያችሁን እያከበራችሁ፤ በባህላዊ ጭፈራ እና ወግ ደምቃችሁ፤ ሲያሻችሁ ደግሞ ቀለል ባለ መልኩ እናነተ እና ምስክሮቻችሁን ክቡር መዝገብ ፊት አቅርባችሁ በማክሰኞ ከሰዓት እንጋባ ብትሉ የሚገባው ትዳር እኩል ነው። ህጉም ጥበቃ ያደርግለታል። ከኢትዮጵያ ውጭ ተጋብታችሁ መጣችሁ? ችግር የሚባል እንደሌለበት የሚጠፋው ያለ አይመስለኝም።
👍9
፮. የቤተሰብ ህጉ የክብር ሹም ብሎ የሚጠራው፣ በፌደራል ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የውሳኝ ኩነት ኤጅንሲ ቢሮዎች ውስጥ የሚደረግ ጋብቻ ከተጋቢዎቹ አንዱ ሳያቋርጥ ቢያንስ ለስድስት ወር በኖረበት ቀበሌ ውስጥ ባለ ወኪል ቢሮ መፈጸም ይችላል። ተጋቢዎች ለክቡር መዝገቡ ለመጋባት ያላቸውን ፍላጎት ሲያሳውቁ ይሄው ቢሮ እንዳላገቡ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ሊጠይቃቸው ይችላል። በዚህ ጊዜ ወይም የስርጋቸው ቀን ተጋቢዎች ጉርድ ፎቶ ይዘው እንዲመጡም ይታዘዛሉ። ማስረጃውን ከያዘ በኋላ ካመለከቱበት ቀን ቢያንስ አንድ ወር የሚቆይ ቀን ቆርጦ ያሰናብታቸዋል። በቀኑ ተጋቢዎች ብቻቸውን መቅረብ የለባችሁም። ሁለታችሁም ሁለት ሁለት ምስክሮች ይዛችሁ ካልመጣችሁ ሂደቱ መቀጠል አይችልም። ይህ ሲሟላ ግን ተጋቢዎች ጋብቻ ለመፈጸም ብቁ እንደሆናችሁ ለክብር መዝገብ ሹሙ በቃለ መሃላ ታሳውቃላችሁ። ለመጋባት ፈቃደኛ እንደሆናችሁ ትገልጻላችሁ። መዝገብ ሹሙ ደግሞ የምትሰጡት ቃል የሚያስከትለውን ውጤት ያስረዳችኋል። ይህን አውቃችሁ ስትቀጥሉ እናንተ እና ምስክሮቻችሁ በሚቀርብላችሁ (ትልቅና ወፍራም) መዝገብ ላይ ትፈርሙና ጋብቻችሁን ትፈፅማላችሁ ማለት ነው። ከዚያ በኋላ ክቡር መዝገቡ አስፈላጊውን መረጃ የያዘውን የጋብቻ ሰርቲፊኬታችሁን ያስረክባችሁና ጨርሳችሁ ትወጣላችሁ ማለት ነው።
፯. በባህል እና በሃይማኖት የሚፈጸሙ ጋብቻዎች እንደሃይማኖቱ ወይም ባህሉ እንደሚወስኑ ግልጽ ቢሆንም ከላይ የተገለጸውን የፈቃድ እና የችሎታ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል። በባህላዊ እና ሀይማኖታዊ ተቋማትም ለከወኑት ጋብቻ ሰርቲፊኬት ስለሚሰጡ መጠየቅ ቸል አትበሉ። በተጨማሪም የተፈጸመው ጋብቻ በወሳኝ ኩነቶች መመዝገብ የሚጸናው ከተፈጸመበት ቀን እንጂ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ እንዳልሆነ አንባቢ ያስተውል።  
፰. ለተጋቢዎች የሚሰጥ ሰርቲፊኬት ምን መርጃዎችን ይይዛል? የተጋቢዎቹ ሙሉ ስም እና የተወለዱበትን ቀን፤ ጋብቻው የተፈጸመበትን ቦታ (ከፍለ ከተማ እና ወረዳ)፤ ጋብቻው የተፈጸመበትን ቀን፣ ወር እና አመተ ምህረት፤ ጋብቻው ሲደረጉ የነበሩ ምስክሮችን ሙሉ ስሞች፤ የተጋቢዎቹ እና የምስክሮቻቸው ፊርማ፤ ሰርቲፊኬቱን ያወጣው ባለስልጣን ስም፤ ሰርቲፊኬቱ የወጣበት ቀን እና የተጋቢዎቹ ፎቶዎች ናቸው። ውሳኝ ኩነቶች ኤጅንሲ የተጋቢዎች መዝገብ የመያዝ ሀላፊነት በህጉ ተጥሎበታል። ይህ በመሆኑ የተጋቢዎች ሰርቲፊኬት በማንኛውም አጋጣሚ ቢበላሽ ወይም በጠፋ ግልባጭ ማውጣት ይቻላል።
፱. ጋብቻ ሊፈፅሙ ያሰቡ ግለሰቦች በትንሹ ከላይ የተዘረዘሩትን ማወቅ ይጠቅማቸዋል አላለሁ። መብትን ማወቅ የመፍትሄ ምንጭ ነውና ስለህጉ ማወቅ ጠቃሚ እንደሆነ እናገራለሁ። ግን ምን አንባቢ ብንሆንም በጉግል ስርች ብቃታችን ሀኪም ሆንን ብለን ከሆስፒታል እንደማንቀረው ሁሉ ከችግር ጋር ስንጋፈጥ የህግ ባለሙያ ጥበቃን እንጠቀምበት። ጠበቃ እና ነገረፍጅ አማክሩ። ይህንን የምታነቡ ግለሰቦች የትዳር ውጤት እና ማግባት ህይወታችን ላይ የሚኖረውን መሰረታዊ እና ዘርፈ ብዙ ውጤት በተገቢው ለመጠቀም ሁለገብ የህግ እውቀት ያለውን ባለሙያ እንደታካትቱበት እመክራችኋለሁ። ይችንም እንደ አንድ ተጨማሪ አውቀት ያዟት።

2015። የፀሃፊዋ መብት በህግ የተጠበቀ ነው።
የህግ ጥያቄዎች አሏችሁ? የህግ ምክር ለማግኘትም ሆነ ጉዳያችሁን እንደራሱ የሚጨርስ ባለሙያ ባስፈለጋችሁ ጊዜ ቫርኒሮ አደባባይ ደንድር ህንፃ በሚገኘው ቢሯችን ብቅ ይበሉ።
Via lawyer Daniel Fikadu
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
አለ_ህግ🔵Ale_Hig:
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ
#Share #ሼር
#አለ_ህግ #Alehig
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ 
👍72
ማስታወቂያ

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ  ቤት የጥብቅና ፍቃድ ለማግኘት ይቻል ዘንድ ፈተናው ጥቅምት 03 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥና ፈተናው የሚሰጥበት ቦታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በቀጣይ  ማስታወቂያ የሚገለፅ ስለመሆኑ በ23/01/2016 ዓ.ም በማስታወቂያ መነገሩ ይታወቃል፡፡ 

  በዚሁ መሰረት የፈተና ኮድ የሚሰጠው ጥቅምት 01 እና 02 ቀን 2016 ዓ.ም በፍትህ ሚኒስቴር ሲሆን ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ ደግሞ ፒያሳ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን  ከፍ ብሎ በሚገኘው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አዳራሽ በመሆኑ ፈተናው ከሚጀመርበት ከጥዋቱ 3.00 በፊት በፈተናው ቦታ እንድትገኙና ከህግ ኮዶች በስተቀር ምንም አይነት ፅሁፍ ይዞ መገኘትም የተከለከለ መሆኑን እንድታውቁ  በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

መረጃውን #share #like በማድረግ ላልደረሳቸው እንድታሳውቁ እንጠይቃለን::

መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ የፌስ ቡክ ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ::


#ethiopianfederalbarassociation

የኢትዮዽያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር

መስከረም 29 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤
👍5
ለፍትህ አሰጣጥ ተገቢ ሆኖ ሲገኝ ክርክሩ በማናቸውም ደረጃ በሚገኝበት ጊዜ ቀድሞ መስክረው የነበሩትን ምስክሮች ፍ/ቤቱ እንደገና አስጠርቶ ማናቸውንም ተገቢ መስሎ የታየውን ጥያቄ ሊጠይቃቸው ይችላል (ቁ. 266)።

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ
#Share #ሼር
#አለ_ህግ #Alehig
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ 
👍31
ውድ የ2015 ትምህርት ዘመን ተፈታኞች በሙሉ

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ በ29/01/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ተፈታኞች የሚከተሉትን ሶስት አማራጭ አድራሻዎችን ብቻ በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ፡፡
• በዌብ ሳይት፡- eaes.et
• በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፡- 6284
• ቴሌግራም አድራሻ፡- @eaesbot

ጥብቅ ማሳሰቢያ፡-

ከላይ ከተገለጹት የውጤት መግለጫ አማራጮች ውጪ ሌላ የውጤት መግለጫ መንገዶች የሌሉ መሆኑን እያሳወቅን በማመሳሰል ውጤት እንገልጻለን ከሚሉ ከማንኛውም አጭበርባሪዎች እራስዎን ይጠብቁ። በተጨማሪም ተቋሙ ውጤት ለማሳየት ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑን ይወቁ።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

አጠቃቀም
በዌብ ሳይት ለማየት

1. eaes.et ብለው ብሮውዘር ላይ ይጻፉ
2. በመቀጠልም በሚመጣው ገጽ ላይ የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) እና የመጀመሪያ ስም ይጻፉ
3. Check Result የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማግኘት ይችላሉ
በአጭር የጽሁፍ መልዕክት
6284 የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር ) ብቻ ጽፎ አንዴ ብቻ በማላክ መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ
በቴሌግራም ቦት
1. @eaesbot ይፈልጉ
2. የሚመጡ አማራጮችን በመከተል የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ያስገቡ በመቀጠልም መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ።
👍4😁1
የከርታታው መምህር መልእክት!
*
#ዩኒቨርስቲ_ገነት_አይደለም‼️

ከስር ያያዝኩት የ#Masters_Degreeዬ ውጤት ነው ፤ የዚህ ልጥፍ ዓለማ ራስን ማንቆለጳጰስ ምናምን ሳይሆን ልፋቴ እና የሚከፈለኝ አለመገናኘቱ ሲቀጥል ዩኒቨርስቲ መግባት እና ትምህርት መስቀል ትርጉም አልባነቱን እንዲሁም 12ኛ ክፍል ውጤት ላልመጣላቸው መጽናኛ እንዲሆናቸው ነው።

በአንድ የመንግስት ዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ፤ከህይወቴ 17 ዓመት ለመጀመሪያ ድግሪ ሁለት ዓመት ደግሞ ለMasters ድግሪ በአጠቃላይ 19 ዓመታትን ያጠፋሁበት በትምህርት ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም Highschool እና መሰናዶ ጓደኛቼ የነበሩ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ እና በተለያዩ የሙያ የንግድ እና የመሳሰሉ ነገሮች ላይ የተሰማሩ በአሁኑ ሰዓት የቤት አከራዮቼ ናቸው ፤ ባለመኪና ባለሆቴል ጽድት ያለ ቡቲክ ብቻ ምን አለፋህ በአጠቃላይ ከእኔ እጅግ በጣም በተሻለ የኑሮ ሁኔታ ነው የሚገኙት!😭

በአሁኑ ሰዓት በመንግስት ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ድግሪ የያዘ የዩኒቨርስቲ መምህር የሚከፈለው ደመውዝ ግብር ሳይቀነስ 12,579 ብር ነው ፤ 35% ግብር እንዲሁ የጡረታ ሲወጣ ኪሴ የሚገባው 9956(ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ስድስት)ብር ነው።

እንግዲህ በትምህርት ደረጃዬ ሲወራልኝ የዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ ፤ ሶስተኛ ድግሪዬን ብሰራ እና ዶ/ር አበባየሁ ጌታ ብባል ወደ 16,000 ብር ከታክስ በፊት እና ወደ 13,000 ብር ገደማ ከታክስ በኋላ እጄ ላይ ይደርሳል።

እና ለምንህ ነው ዩኒቨርስቲ ቀረብኝ ብለህ የምትጨነቀው?

ወዳጄ/ወንድሜ/እህቴ 12 ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት አልመጣልህም?

እሰይ እንኳንም አልመጣልህም! ራስህን ለመቀየር ታትር ፣ አጫጭር ኮርሶችን ከዩቲዩቭ አውርድ ፣ተማር ፣ቪዲዮ ቱቶሪያል ተከታተል ፣ ግራፊክስ እና የመሳሰሉ ገንዘብ ልትሰራ የምትችልባቸው ከምርጥ ኮንተንት ጋር ከመጣህ የዩቲዩብ ስራዎች ብቻ ብዙ ብዙ አማራጮች አሉህ፣ ተስፋ አትቁረጥ! በበሰበሰ ስረዓተ ትምህርት ብዙ ባለድርሻ አካላት ሀላፊነቱን ባልወሰዱበት ከስር ተጀምሮ ባልተሰራ ስራ እና ሰረዓት ተምረህ መጥተህ መጨረሻ ላይ ብትወድቅ(የመስዋዕት በግ ብትሆን) ብቻህን ተጠያቂ አይደለህም! ራስህን ብቻ አትውቀስ! እልፍ በል! ታገል! እመነኝ ታመሰግነኛለህ!

በተመዘገበው ውጤት ልቡ የደማው የአንተው ከርታታው መምህር ወዳጅህ!
#አበባየሁጌታ
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ
#Share #ሼር
#አለ_ህግ #Alehig
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ 
👍122👎2🔥2