አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ከዚህ በላይ በአንቀጽ 1000(1) እና (2) ላይ የተመለከቱት የጊዜ ገደቦች ከሌሎች የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች በተለይም 1ኛ) አንድ ወራሽ የሟች ኑዛዜ ተጠቃሚ መሆን የሚችለው ኑዛዜ በእጁ እንደሚገኝ ለውርስ አጣሪው አቅርቦ ውርስ አጣሪው ኑዛዜውን በሚነበብበት ሰዓት ራሱ ወይም ወኪሉ ካልነበረ ወራሹ ኑዛዜው ከፈሰሰበት ቀን አንስቶ በአስራ አምስት አመታት ውስጥ መቃወሚያ ካላቀረበ ከዚያ በኋላ ሊቀርብ እንደማይችል በፍ/ሕ/ቁ 974(2) የተመለከተው በፍ/ሕ/ቁ 1000(1) ካለው የጊዜ ገደብ ጋር እንዴት ተጣጥሞ ተግባራዊ ይሆናሉ ከሚለው ጋር ጥያቄ የሚያስነሳ ሲሆን በሌላ መልኩ በፍ/ሕ/ቁ 1000(1) እና (2) አተረጓጎምና አፈጻጸም እንዴት መሆን አለበት በሚል አልፎ አልፎ ጥያቄ ሲያስነሳ ይስተዋላል፡፡ ስለዚህ በእነዚህ የሕግ ማዕቀፎች ላይ የተጠቀሱት የጊዜ ገደቦች በተመለከተ መከተል የሚገባንን የሕግ ትርጓሜ እንደሚከተው ለማብራራት ተሞክሯል÷ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 974/2/ ተፈጻሚ የሚሆነው የሟች ውርስ የሚያጣራ ፤በሕግ በኑዛዜ ወይም በፍርድ ቤት የተሾመ የውርስ አጣሪ ፤ሟች አድርጎታል የተባለው ኑዛዜ አግኝቶ የኑዛዜውን ፎርምን የኑዛዜውን ዋጋ መኖር ፤የሟች ያለኑዛዜ ወራሾች ወይም አራት አካለመጠን ያደረሱ ሰዎች ባሉበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 968 በተመረመረበት ሁኔታ ነው፡፡ ሆኖም ግን ኑዛዜ ያለ መሆኑን ለውርስ አጣሪው ሳያሳውቅ ቀጥታ የኑዛዜ ወራሽ መሆኑ እንዲታወቅለት ለፍ/ቤት አመልክቶ የወራሽነት የምስክር ወረቀት በመውሰድ የሟች ንብረት በእጁ ያደረገ ሰው ወይም በሀሰት የሟች ያለኑዛዜ ወራሽ ነኝ ብሎ የሟችን ንብረት ከወሰደው ሰው ለማስመለስ አግባብ የሆነው የይርጋ ገደብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 968 የተጠቀሰው ሳይሆን በፍብ/ሕ/ቁ 1000/1/ የተመለከተው ተፈጻሚነት ሊኖረው ይገባል፡፡
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ እና 1000/2/ አስመልክቶ የተለያዩ አተረጓገሞች የሚስተዋሉ ሲሆን ለዚህ ጽሁፍ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 30158 ፤26422 እና 34011 በቅጽ 7/6/6/ እንዲሁም በቅጽ 11 በሰ/መ/ቁ 52407 የሰጠውን አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ለመዳሰስ ሞክሬያለው፡፡ በዚሁ አግባብ በፍ/ሕ/ቁ 1000/2/ ላይ ሟች ከሞተ አስራ አምስት አመት በላይ ወይም ተከሳሹ በመብቱ ሊሰራበት ከቻለበት ቀን አንስቶ አስራ አምስት ዓመት ውስጥ ክስ ካልቀረበ አስራ አምስት ዓመት ካለፈው በኋላ ክስ ሊያቀርብ የሚቻለው ከዘር የወረደ ርስት በሆነ ንብረት ላይ ነው፡፡
ርስት የሚለው ቃል በፍ/ሕ/ቁ 1130 እና ስለ ንብረቶች በሚናገረው የፍ/ብሔር የህጉ ክፍል መሬት የሚያመለክት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ በኢትዮጲያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል የተዘጋጀው የአማርኛ መዝገበ ቃላት ርዕስት የሚለው መሬትን የሚመለከት መሆኑን ጠቅሶ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ በዚሁ አግባብ ከዘር የወረደ ርዕስት የሚለው ቤትን አያጠቃልልም የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ በርዕስት የሚተላለፍ መሬት ብቻ ማለት ሰለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/2/ መሰረት ለተወላጆች የሚተላለፍ መሬት ብቻ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡
በኢፌድሪ ህገ መንግስት መሰረት መሬት የመንግስትና የህዝብ ሀብት በመሆኑ ከዘር የወረደ ርዕስት ካልሆነ በስተቀር በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/2/ ላይ የተገለጸው የተሻረ እና ተፈጻሚነት የሌለው ነው በማለት አስገዳጅ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ አፈጻጸምን በተመለከተ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 32407 በቅጽ 11 ላይ ትርጓሜ የሰጠ ሲሆን በዚህም መሰረት በወራሾች መካከል የሚነሳ የውርስ ንብረት ክርክር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ በተደነገገው አግባብ በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ያለበት ሲሆን ወራሽ በሆነ እና ወራሽ ባልሆነ ተከራካሪ ወገን መካከል የሚቀርበው የውርስ ንብረት ይገባኛል ጥያቄ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1677 እና 1845 መሰረት በአስር አመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ መብቱ በይርጋ የሚታገድ ይሆናል፡፡
//////
የክፍፍል ጥያቄ በይርጋ የማይታገድ ስለመሆኑ
/////🇪🇹
ወራሾች ተለይተው የውርስ ሀብቱ ድርሻ ታውቆ ግን ክፍፍል ሳይደረግ የቆየ የውርስ ሀብት ያለ እንደሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1062 በተገለጸው መሰረት እያንዳንዱ የጋራ ወራሾች ውርሱን እንከፋፈል በማለት በማንኛውም ጊዜ ለመጠየቅ የሚችሉ በመሆኑ የክፍፍል ጥያቄ በይርጋ የማይታገድ ይሆናል፡፡
//////
መደምደሚያ
///////
በአጠቃላይ አንድ ሰው ከዚህ አለም በሞት የተለየ እንደሆነ የውርስ ጉዳዩን በተመለከተ ወራሽ የሆነ ወገን ኑዛዜን ሚቃወምበት፤የወራሽነት ጥያቄ ሚያቀርብበትና ክፍፍል የሚጠይቅባቸው የጊዜ ገደቦች ከዚህ በላይ በተገለጸው አግባብ ተፈጻሚ ሚሆኑ ሲሆን ባለመብት የሆነ ወገን ጥያቄውን በህጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያላቀረበ እንደሆነ ውጤቱ መብቱን እስከማጣት የሚደረስ ይሆናል፡፡
#like #shareshare ያድርጉ።

(By Muluken Seid Hassen)
source Abyssinialaw.com
የክስ ምክንያት ምንድነው?🇪🇹
#Like #Comment #Share ያድርጉ

ለጥያቄው ምላሽ የሰበር ችሎት በ 6 መዝገቦች ላይ እንደሚከተለው የህግ ትርጓሜ ሰጥቷል።

1/ አንድ ሰው አንድን ነገር ከአንድ ሰው ላይ ለማግኘት ፍ/ቤቱ እንዲወስንለት ክስ ለማቅረብና ዳኝነት ለማግኘት የሚያስችለው የፍሬ ነገር ሁኔታ

ማንም ሰው በህግ ችሎታ ኖሮት በሌላ ሰው ላይ ማናቸውንም ክስ ለማቅረብ እንዲችል አስቀድሞ ለክሱ መነሻ በሆነው ነገር ወይም ክሱ በተመሠረተበት ነገር ላይ ጥቅም ወይም መብት ያለው መሆኑ መረጋገጥ እንደሚገባው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33 ይደነግጋል፡፡ በዚህም ከሣሽ ከተከሣሽ ላይ ሊፈፀም የሚችል መብት አለኝ ብሎ ለማለት አስቀድሞ ለመብቱ መገኘት መነሻ የሆነውን ነገር በማረጋገጥ የተጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ከሣሹ በሕግ መብት ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡
የክስ ምክንያት አለ ብሎ ለመወሰን የሚቻለው በክሱ ላይ የቀረበው ነገር ቢረጋገጥ ከሣሹ የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ሕግ ይፈቅድለታል ወይ? ለሚለው ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ሲቻል ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 16273 ቅጽ 2፣ ስለ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ የወጣ አዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 9፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 29፣ 80/2/፣ 224/2/፣ 23/1/ ሀ ፣ 224/2/፣ 23/1//ሀ/፣ 33፣ ሮበርት አለን ሴድለር በችሎቱ እንደተጠቀሰ

2/ ሻጭ ከሽያጭ ውሉ በሚመነጭ ግዴታ የተሸጠውን ነገር ስመ ሀብትነት በሚመለከተው ክፍል ቀርቦ ለማዛወር እንደገባው ግዴታ ይፈጽምልኝ የሚል ክስ የክስ ምክንያት አለው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 82234 ቅጽ 15

3/ አንድ ክስ ሊቀርብ የሚገባው የክስ ምክንያት ሲኖረው ሲሆን የክስ ምክንያትም ተከሣሽ ለከሣሽ ሊፈጽመው የሚገባው ግዴታ መኖሩ ጋር ተያይዞ ሊነሣ የሚችለውን ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት የሚቻልበት ሁኔታ ስለመኖሩ ሲረጋገጥ የሚታወቅ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 33945 ቅጽ 12፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 231(1) ሀ

4/ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መነሻ ምክንያት
በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 231 ላይ እንደተመለከተው ማንኛውም ፍርድ ቤት የክስ አቤቱታ ሲቀርብለት ተከሣሽ የሆነው ወገን ክሱን እንዲከላከል ከመጥራቱ በፊት ከሳሽ ክሱን ለማቅረብ የሚያስችል መነሻ ምክንያት ያለው ስለመሆኑና ፍ/ቤቱም አቤቱታውን ተቀብሎ ለማየት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ መመርመር ይኖርበታል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 32147 ቅጽ 6፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 231

5/ አንድ ሰው በተለያዩ ምክንያቶች በአባቱ ብቻ ሳይሆን በአሳዳጊው ስም ጭምር ሊጠራ የሚችልባቸው አጋጣሚዎች መኖራቸው የሚታወቅ ሲሆን እንዲህ ዓይነቱ ሰው ተገቢ ሆኖ ባገኘው ጊዜ በአሳዳጊው ስም ጭምር መጠራቱ ቀሪ ሆኖ በፍትሐብሔር ሕጉ መሰረት በአባቱ ስም ብቻ እንዲጠራ የመወሰን መብት ያለው በመሆኑ ይህንኑ መብቱን በፍርድ ለማረጋገጥ የሚያቀርበው የዳኝነት ጥያቄ የክስ ምክንያት የለውም የሚባልበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 95995 ቅጽ 15

6/ ከባዶ ቦታ ሽያጭ የመነጨ ግዴታ ለማስፈጸም የሚቀርብ አቤቱታ የክስ ምክንያት የለውም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 27739 ቅጽ 6
በአብርሐም ዮሐንስ
#LegalServices #lawsocieties #Ethipianlawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
ማስታወቂያ

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ  ቤት የጥብቅና ፍቃድ ለማግኘት ይቻል ዘንድ ፈተናው ጥቅምት 03 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥና ፈተናው የሚሰጥበት ቦታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በቀጣይ  ማስታወቂያ የሚገለፅ ስለመሆኑ በ23/01/2016 ዓ.ም በማስታወቂያ መነገሩ ይታወቃል፡፡ 

  በዚሁ መሰረት የፈተና ኮድ የሚሰጠው ጥቅምት 01 እና 02 ቀን 2016 ዓ.ም በፍትህ ሚኒስቴር ሲሆን ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ ደግሞ ፒያሳ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን  ከፍ ብሎ በሚገኘው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አዳራሽ በመሆኑ ፈተናው ከሚጀመርበት ከጥዋቱ 3.00 በፊት በፈተናው ቦታ እንድትገኙና ከህግ ኮዶች በስተቀር ምንም አይነት ፅሁፍ ይዞ መገኘትም የተከለከለ መሆኑን እንድታውቁ  በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

መረጃውን #share #like በማድረግ ላልደረሳቸው እንድታሳውቁ እንጠይቃለን::

መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ የፌስ ቡክ ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ::


#ethiopianfederalbarassociation

የኢትዮዽያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር

መስከረም 29 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤
የኢት/ ፌደራል ጠበቆች ማህበር አዘጋጅቶ የሚያሰራጨውን የስራ/አባልነት መታወቂያ የመረጃ ማደራጀት ተግባራትን አጠቃሎ ለፌደራል ጠበቆችና የህግ አማካሪዎች ማሰራጨቱን ቀጥሎአል
***

የኢት/ ፌደራል ጠበቆች
ማህበር እስከእሁን ድረስ ከ 2160(ሁለት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ) በላይ ለሚሆኑ የፌደራል ጠበቆችና የህግ አማካሪዎችን ከሁሉም ክልሎች መረጃዎቻቸውን በማሰባሰብና በማደራጀት ደረጃውን የጠበቀ መታወቂያ ማሰራጨቱ የሚታወስ ነው::

በዚህም አስቀድሞ ባሳወቀው መሰረት የመታወቂያ ህትመት በዝርዝሩ መሰረት ከፒያሳ ከፍ ብሎ አራዳ ከፍተኛ ፍ/ቤት የፍትህ አካላት ህንፃ 9ኛ ፎቅ በሚገኘው በማህበሩ ዋና መ/ቤት ቀርባችሁ እንድትወስዱ የተለጠፈ የስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው::

መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር

መጋቢት 26 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤
EFAA BYLAW FINAL PDF.pdf
480.3 KB
ረቂቅ የመተዳደሪያ ደንብ
*******

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆ
ች ማህበር በቅርቡ ለሚያካሂደው ጉባኤ ዝግጅቶችን እያደረገ ያለ መሆኑ ይታወቃል::

በዚሁ ጉባኤ ላይ ከሚቀርቡ ሰነዶች አንዱና ዋነኛው የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ነው:: በመሆኑም መላው የማህበሩ አባላት ይህ ሰነድ የማህበሩን ህጋዊ አቋም ፤ የአመራር አደረጃጀት እና አስራር የሚወስን ወሳኝ ሰነድ መሆኑን በመገንዘብ በአግባብ በማንበብ እና ሀሳባቸውን በማደራጀት መስጠት እንደሚገባቸው ታምኖበታል::

በመሆኑም የማህበሩ አባላት መተዳደሪያ ደንቡ የተሻለ እና ማህበሩን የሚያጠናክር ሆኖ እንዲወጣ የበኩላቸውን እንዲወጡ ማህበሩ ጥሪውን ያቀርባል::

መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን::

መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ ይፋዊ ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ::

ፌስቡክ- https://www.facebook.com/ethiopianbarassociation?mibextid=9R9pXO


የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ሚያዝያ 18 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ፤
Consoledated_Training_Manual_Final draft edited T + H.pdf
211.8 KB
በጠቅላላ ጉባኤ ቀርበው ከሚፀድቁ መመሪያዎች አንዱ የስልጠና መመሪያ ተለቋል::

መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን::

በሚከተለው መስፈንጠሪያ የስልጠና መመሪያውን ያንብቡ::

https://t.me/lawsocieties/9482

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ሚያዝያ 29 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤

አማራጭ የሕግ እውቀት
👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig