አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#ጥንቃቄ❗️

በመዲናዋ ስልክ እየደወሉ እና የተለያዩ የማጭበርበር ዘዴዎችን በመጠቀም  ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦች  በመኖራቸው ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል።

ግለሰቦቹ በተለያየ ስልክ በመደወል እንኳን ደስ አላችሁ ሎተሪ ደርሷችኋል ሲስተም እያስተካከልን ነው፣ የሞባይሎትን አቅም ከ4G ወደ 5G እየቀየርን ነው ፣ከሌሎች ባንኮች ጋር ኦንላይን ሲስተም እየጀመርን  ነው በሚሉ እና በሌሎች ማደናገሪያዎች በመጠቀም የተለያዩ የማጭበርበር ወንጀል እንደሚፈጽሙ ታውቋል።

አንዳንዶቹ የማጭበርበሪያ ስልቶች  ግለሰቦች እንዲያምኑ በኤቲም ገንዘብ ያወጡበት ትክክለኛ ቀን ተነግሯቸው የወንጀሉ ሰለባ እየሆኑ የሚገኙ ሲሆን የግለሰቦች የባንክ ሚስጥር የሚወጣበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ምርመራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ተብሏል።

ወንጀሉ በልዩ ልዩ የአፈፃፀም ስልቶች እየተፈፀመ ከመሆኑም ባሻገር ስልክ በመንጠቅና ቴክኒካል የሆኑ ዘዴዎችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ አካውንት ወደ ቴሌ ብር በማስተላለፍ ወንጀሉ እየተፈፀመ ይገኛል፡፡

ህብረተሰቡ የማያውቋቸው የስልክ ጥሪዎች እና የጹሁፍ መልዕክቶች ሲደርሷቸው ተገቢውን ማጣራት ማድረግ እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
#tikvahethmagazine
https://t.me/lawsocieties
ቤቶች ኮርፖሬሽን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ሊያደርግ ነው‼️👇👇👇👇

የመንግሥት ኃላፊዎችና ተቋማት የሚጠቀሙባቸውን ቤቶች ኪራይ እንዲከፍሉ ተጠይቀስ

አቶ ኃዴስ በርህን ዜማ የቤቶች ኮርፖረሽን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ በተያዘው በጀት ዓመት የነባር መኖሪያ ቤቶች የኪራይ ዋጋ ክለሳ በማድረግ፣ ጭማሪ ሊያደርግ መሆኑን የፌደራል ኮርፖሬሽን አስታውቀ

ቤቶች

የኪራይ ቤቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ ጥናት ማድረጉን የገለጹት የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይለ ብርሃን ዜና፣ ባለፉት ዓመታት በአገሪቱ ውስጥ በተከስቱ _ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ችግሮች ምክንያት ዕቅዱ መቆየቱን ተናግረዋል::

ኮርፖሬሽኑ ከጥቂት ዓመታት በፊት በንግድ ቤቶች ላይ ጭማሪ ባደረገበት ወቅት፣ ከተከራዮች በገጠመው ተቃውሞ ሳቢያ የፓርላማው ዕገዛ ትልቅ እንደነበር ያወሱት ምክትል ዋና አስፈጻሚው በተያዘው ዓመት ዕቅዱን ለማሳካት የምክር ቤቱን ዕገዛ እንደሚፈልግ ተናግረዋል::

ከ1967 ዓ.ም. ጀምሮ በመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ የማስተካከያ ጭማሪ ባለመደረጉ፣ በቀጣይ በሚካሄደው ጥናት ላይ ገልጸዋል:: ከቤት ባለቤቶችና ከሚመለከታው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበት በኮርፖሬሽኑ ሥራ አመራር ቦርድ ፀድቆ እንደሚተገበር ተነግሯል::............ይቀጥላል።👆👆👆https://t.me/lawsocieties
Forwarded from Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ
#እንድታውቁት

" ነገ እና እሁድ ከጥዋት እስከ ምሽት መታወቂያ ማሳደስ ትችላላችሁ "

#መታወቂያ_ለማሳደስ እየተጠባበቁ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ነገ #ቅዳሜ እና #እሁድ ከጥዋት እስከ ምሽት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ነገ ቅዳሜ እና እሁድ ማለትም ህዳር 3 እና 4 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋት እስከ ምሽት ድረስ በየአካባቢው ባሉ የወረዳ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ  ፅ/ቤቶች ይሰጣል።

ነዋሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በየአቅራቢያቸው ባሉ ፅ/ቤቶች ተገኝተው መስተናገድ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አሳውቋል።
#tikvahethiopia
95338.pdf
123.4 KB
ሰ-መ-ቁ 95338 (ያልታተመ)
የባልና ሚስት ንብረት ፍቺ ተከትሎ ተጣርቶ ውሳኔ ካላረፈበት አንደኛው ተፋቺ የጋራ ንብረት በሽያጭ ለሶስተኛ ወገን ካስተላለፈ ውሉ እንዲፈርስ ክስ ማቅረቢያው የይርጋ ጊዜ 10 /አስር ዓመት/ ነው።
እሁድ 2:30 ቀጥታ ስርጭት 👈

የመወያያ እርዕስ፣
በፍትህ ስርዓቱ ላይ የተደቀነው አደጋ👇
የዳኞችና የአቃቤ ህጎች ፍልሰትና  ውጤቱ፨

ከዳኛ ወደ 🔜ጠበቃ
ከአቃቤ ህግ ወደ🔜 ጠበቃ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Topic of the discussion
.
https://t.me/lawsocieties
እሁድ 👇👇👇👇👇👇
በዚህ ቴሌግራም ይጠብቁ

ሼር በማደረግ ሰዎቸን ይጋብዙ👆👆👆
https://t.me/lawsocieties
Live 🔘 Live on Telegram 👈👈
#አለ_ህግ #Ale_Hig

የእለቱ እንግዳ
"አቶ ወንድወሰን ዮሐንስ
በሀዋሳ ዪንቨርሲቲ የህግ መምህር
የህግ አማካሪና ጠበቃ
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ዳኛ እና በህግ ሙያ ከ15 አመት በላይ ልምድ ያላቸው
.......🙏

Live🔴on Telegram                   

🔵 Ale_Hig / አለ ህግ


Starting Time: 8:30PM -
[Sunday evening]

Join us: https://t.me/lawsocieties

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን        
  👉 https://t.me/lawsocieties

Subscribe our YouTube👇👇👇
https://www.youtube.com/@Lawsocieties
በፍትህ ስርዓቱ ላይ የተደቀነው አደጋ ነው🔜
የወራሽነት ማረጋገጫ፣ መቃወሚያ እና ልጅነት፡- ክፍተተ ወሕግ ወአሰራር እና መፍትሔዎቻቸው

በዚህ ጽሑፍ ወራሽ ለመሆን ወይም ልጅ መሆንን ለማረጋገጥ ስለሚሰጡ ማረጋገጫዎች እንዲሁም እነዚህን ማረጋገጫዎች ስለመቃወም የሚቀርቡ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ጸሐፊው በጽሑፍ በወራሽነት ማረጋገጫ፥ ልጅነት እና መቃወሚያ ያሉ የሕግ እና የአሠራር ክፍተቶችን በማሳያት የመፍትሔ ሐሳቦችን ይሰነዝራል።
ፈቃዱ ዳመነ - ጠበቃ
መልካም ንባብ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.abyssinialaw.com/blog/2022-11-11-16-44-28
በፍትህ ስርዓቱ ላይ የተደቀነው አደጋ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Join us for more‼️🙏
https://t.me/lawsocieties
የመወያያ ርዕስ

በፍትህ ስርዓቱ ላይ የተደቀነው አደጋየዳኞችና የአቃቤ ህጎች ፍልሰትና  ውጤቱ‼️


እሁድ 2:30 ቀጥታ ስርጭት
Live 🔘 Live on Telegram 👈👈
በዚህ ቴሌግራም ይጠብቁ
ሼር በማደረግ ሰዎቸን ይጋብዙ👆👆👆

የእለቱ እንግዳችን
"አቶ ወንድወሰን ዮሐንስ
በሀዋሳ ዪንቨርሲቲ የህግ መምህር
የህግ አማካሪና ጠበቃ
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ዳኛ እና በህግ ሙያ ከ15 አመት በላይ ልምድ ያላቸው
.......🙏

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን        
  👉 https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig
ፍልሰቱ ከላይ ጀምሮ ነዉ።
~~~
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
★ባህር ዳር ምድብ ችሎት ዳኞች የነበሩት፦
#አቶ አለሙ ዩሐንስ
#አቶ ዳውድ አሊ
የዳኝነት ሙያን ተሰናብተው የጥብቅና ሙያን ተቀላቅለዋል።

የሲያድርና ዋዩ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የፍትሐብሄር የስራ ሂደት አስተባባሪ የነበረው #አቶ ግርማ ላቀው በ2015 ዓ.ም የዳኝነት ሙያን ለቀው ወደ ጥብቅናውን አለም ተቀላቅለዋል።

በባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበረውና ረዥም ጊዜ በዳኝነት ያገለገለው ጠንካራዉ #ዳኛ አቶ መንግስቱ አዱኛ የዳኝነት ሙያቸውን ለቀው የጥብቅና ሙያን ተቀላቅለዋል።
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
የመወያያ ርዕስ

በፍትህ ስርዓቱ ላይ የተደቀነው አደጋየዳኞችና የአቃቤ ህጎች ፍልሰትና  ውጤቱ‼️


እሁድ 2:30 ቀጥታ ስርጭት
Live 🔘 Live on Telegram 👈👈
በዚህ ቴሌግራም ይጠብቁ
ሼር በማደረግ ሰዎቸን ይጋብዙ👆👆👆

የእለቱ እንግዳችን
"አቶ ወንድወሰን ዮሐንስ
በሀዋሳ ዪንቨርሲቲ የህግ መምህር
የህግ አማካሪና ጠበቃ
የቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ዳኛ እና በህግ ሙያ ከ15 አመት በላይ ልምድ ያላቸው
.......🙏

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን        
  👉 https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig
በሴት ዳኛ ላይ ድብደባ እና እስር፣
ፍትህ ለዳኛ ወ/ት መሰረት አርጋቸው
https://t.me/lawsocieties
our discussion will start soon.....👁‍🗨
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
መልስ ያላገኘው የ ህግ ት/ት መውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ጉዳይ፣

መመሪያውን ተከትላችሁ ቅሬታችሁን በዩኒቨርሲቲያችሁ አቅርቡ በተባልነው መሰረት መንግስትን አምነን ቅሬታችን በፎርሙ መሰረት በግልጽ አስገብተናል። ሆኖም ጥያቄያችንን መመሪያውን ተከትለን በላክነው አግባብ ታይቶ ምላሽ አልተሰጠም ይላሉ።
ድምፅ ለህግ ተማሪዎች
#Ale_Hig #አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties
የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በአውሮፓ ህብረት የወንጀል ፍትህ ስርዓት ማሻሻያ በኢትዮጵያ ፕሮጀክት ስር ከዚህ በታች ተያይዞ በቀረበው የጋዜጣ እትም ላይ በተጠቀሱት የስራ መስኮች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ሁሉ ማስታወቂያው ከወጣበት መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በመገናኛ ብዙሃን በቀረበ ዘገባ መልካም ሥሜና ክብሬ በሃሰት ወይም በአሉታዊ ጎኑ ተጎዳብኝ ያለ ሰው ምን መብት አለው?

በዛሬው “ከነጋሪት ገጾች” አምዳችን በአዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ውስጥ ከመገናኛ ብዙሃን መብቶች እና ግዴታዎች መካከል አንዱን ነቅሰን ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡

በዚሁም መሰረት በመገናኛ ብዙሃን በቀረበ ዘገባ መልካም ሥሙና ክብሩ በሃሰት ወይም በአሉታዊ ጎኑ ተጎዳብኝ ያለ ማንኛውም ሰው በተመሳሳይ ሚዲያ፣ በተመሳሳይ ጊዜ፣ በግልፅ እና ያለክፍያ እርማት የመጠየቅ መብት ያለው ሲሆን ዘገባው የቀረበው በቴሌቪዠን ወይም በሬዲዮ ፕሮግራም ላይ የነበረ ከሆነ እርማቱ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ባሉ 5 ቀናት ውስጥ መተላለፍ አለበት። ይህ ካልሆነ የእርማት መብቱን የተነፈገ ማንኛውም ሰው የፕሮግራሙ አዘጋጅ ተገዶ መልሱን እንዲያወጣለት ለፍርድ ቤት ማመልከት ይችላል፡፡ ይሁንና የእርማት ጥያቄው ነገሩ ከተሰራጨበት ቀን ጀምሮ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ የቀረበ እንደሆነ ብቻ የሚስተናገድ ስለመሆኑ አዋጁ ይደነግጋል፡፡

ዋቢ፡- የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 48
ባልና ሚስት በባህል ተጋብተው በ 1989 አመተ ምህረት አንዲት ሊጅ ወልደው ተፋትተዋል። ሚስት ልጇን ብቻዋን አሳድጋለች፤ ባልም ሌላ ትዳር መስርቶ ልጆችን አፍርቷል። እናት ልጇን ስታሳድግ በጥረቷ ንብረት አፍርታ ቤትም ሰርታለጭ። በ 2008 አመተ ምህረት ይህ ሰው ያኛዉን ትዳሩን አፍርሶ እና በጠና ታሞ ከመጀመሪያ ባለቤቱ ጋ እርዳታሽን እፈልጋለሁ በማለት ከቤቷ ይገባል፤ የጋራ ልጅ ስለነበረቻቸዉ በርህራሄ ያስጠጉትና አስታመዉት ከዳነ በኋላ አብረው ሲኖሩ ሶስት አመታትን አሳለፉ። እናም አባት ሁልጊዜ ከቤቱ ባለኩል አድርጊኝ የሚል ጥያቄ ያቀርብላት፤ እሷም ባለመስማማት ትመልሰው ነበር። ቆይተዉ ትርፍ ቦታ ስለነበረዉ ጥቂት ዶርሞችን አብረዉ እያሉ ሰርተዋል። ሁልጊዜ ባለ እኩል ካላደረግሽኝ እያለ ፤ ካልተስማምሽም እያለ ያስፈራራትም ነበር። ከዚህ በኋላ ጥያቄዉን አልቀበለዉ ስትል፤ ከእርሷ እዉቅና ዉጪ የራሱ የሆኑ ሰወችን ይዞ ፤ ገንዘብ እንዳጋባላት እና ከቤቱ ባለቤትነት እንዳስገባችዉ የሚገልጽ ዉል ጽፎ እነዚያን ሰወች ከቤት ይዞ በመምጣት እንድትፈርምለት ይጠይቃታል። ነገር ግን በሃሳቡ ባለመስማማቷ ሳትፈርም ቀረጭ። በዚህ የተናደደዉ ሰዉየዉ ሌሊት በ ተተኳሽ መሳሪያ ያስፈራራታል። ከዚያም ቤቷን ጥላ ወደቤተሰቦቿ ትሄዳለች። ከዚያም የቤት እቃዉን ሁሉ አዉጥቶ ከወሰደ በኋላ ክስ ይመሰርትባታል። ክሱም እሱ በሌለበት ቤቱን እንደዘረፈችዉ ያስረዳል።
አሁን አብረው ያፈሩትን ሃብት ሳይቆጥር ጥራ ግራ የሰርችዉን ቤት እኩል ታካፍለኝ ብሎ ከሷት ይገኛል።
ከሙያ አንጻር የሆነ ነገር በሉኝ።
በዚህ ጉዳይ ጥብቅና የሚቆምልኝም ሰው እፈልጋለሁ!
አመሰግናለሁ
https://www.abyssinialaw.com/discussions/2022-11-12-14-03-47