አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
አእምሮ አልባ ዳኛ

በክፉ ህሊና እድልህን ዘግቶ በጉዳት ያጠቃህ፣
ታታሪውን ወጣት የነገን ተስፈኛ ለህልፈት ያበቃህ፤
ማን ይሆን ያ ክፉ ርህራሄ ያጣ?
ለምን ፈቀድክለት ደንብን ተከልሎ በጉዳተኛ ላይ ቂሙን እንዲወጣ?
እንዴት ዘነጋሃው አብራሃም ወንድሜ ግብግብ መሆኑን የኔና ያንተ እጣ?
ልብህ እያወቀው በምቀኞች መንደር በክፎዎች አንባ ልንኖር ተወልደን፣
ኮረኮንቹን መንገድ የጉዞን ጋሬጣ እሾሁን ተራምደን፣
የህብረተሰብ ሸጋታ አስተሳሰብ የሚቆልለውን የመከራ ቋጥኝ በጀግንነ አልፈን፣
በየህይወት ዘርፉ በትምህርት በስራ የገፉንን ሁሉ በወኔ አሸንፈን፤
ለድል የምንበቃ የእድሜልክ ታጋዮች መሆናችንን ልብህ እያመነው፣
አብራሃም ወንድሜ በክፉዎች ወጥመድ በእኩያኑ ሴራ መውደቅህ ለምነው?
ዳገት ቁልቁለቱን ያን ሁሉ መከራ አልፈኸው በብርታት፣
በአንዲት እርጉም አፍታ በከፋ ሰው ድርጊት በድንገት መረታት?

እስቲ ይሁን በቃ፣
በእውቀት አቅምህ ሳይሰንፍ አእምሮህ ጎልብቶ ሙሉ ሆኖ ልብህ፣
ማየት ብቃት ሆኖ ህሊና አልባ ዳኛ ሞት አስፈረደብህ።
ግን አይዞህ አልሞትክም ቃል ገብተንልሃል ሞትክን ላለመርሳት፣
በልባችን ነዷል ያቃጠለህ እሳት።

አይን አእምሮ በሚመስላቸው የእውቀትና ህሊና ድሆች ፍርደገምድል ፍርድ ራሱን ላጠፋው አይነስውር ወንድሜ አብራሃም ዱሬሳ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን ለመግለፅ ብዬ የፃፍኩት።

የህግ ባለሙያ እና የቀድሞው የፍሪካ እንዲሁም የኢትዮጵያ የአይነ ስውራን ፌደሬሽን ፕሬዘዳንት #አቶ ካሳሁን ይበልጣል።
ፍልሰቱ ከላይ ጀምሮ ነዉ።
~~~
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
★ባህር ዳር ምድብ ችሎት ዳኞች የነበሩት፦
#አቶ አለሙ ዩሐንስ
#አቶ ዳውድ አሊ
የዳኝነት ሙያን ተሰናብተው የጥብቅና ሙያን ተቀላቅለዋል።

የሲያድርና ዋዩ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የፍትሐብሄር የስራ ሂደት አስተባባሪ የነበረው #አቶ ግርማ ላቀው በ2015 ዓ.ም የዳኝነት ሙያን ለቀው ወደ ጥብቅናውን አለም ተቀላቅለዋል።

በባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበረውና ረዥም ጊዜ በዳኝነት ያገለገለው ጠንካራዉ #ዳኛ አቶ መንግስቱ አዱኛ የዳኝነት ሙያቸውን ለቀው የጥብቅና ሙያን ተቀላቅለዋል።