አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#ጥንቃቄ ስለ ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 መሰረት፣

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ፦
" ምናባዊ ንብረትን (ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ) ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ያልተሰጠው ድርጊት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ሕገ-ወጥ ተግባር እራሱን ይጠብቅ።

የኢትዮጵያ የገንዘብ መደብ ብር እንደሆነና በብሔራዊ ባንክ በሌላ አኳኋን ካልተፈቀደ በስተቀር በሀገሪቱ የሚከናወኑ ማናቸውም የገንዘብ ግንኙነቶች ሁሉ የሚከፈሉት በብር እንደሚሆን የብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 በግልጽ ይደነግጋል።

በተጨማሪም በክፍያ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 718/2003 መሠረት በየትኛውም የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድም ሆነ ሥርዓት ያለ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የገንዘብ ዝውውርም ሆነ ገንዘብ ነክ አገልግሎት መስጠት አይቻልም፡፡

ነገር ግን ከጥናት ለመረዳት እንደተቻለው በአሁኑ ወቅት ከህግ እውቅና ውጪ የክሪፕቶ ከረንሲ፣ እንደ ቢትኮይን እና የመሳሰሉት የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ አገልግሎት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ መጥቷል።

በተጨማሪም ይህ ተግባር ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ውጪ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር የሚደረግበት እና በተለይ በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።
#ጥንቃቄ❗️

በመዲናዋ ስልክ እየደወሉ እና የተለያዩ የማጭበርበር ዘዴዎችን በመጠቀም  ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦች  በመኖራቸው ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል።

ግለሰቦቹ በተለያየ ስልክ በመደወል እንኳን ደስ አላችሁ ሎተሪ ደርሷችኋል ሲስተም እያስተካከልን ነው፣ የሞባይሎትን አቅም ከ4G ወደ 5G እየቀየርን ነው ፣ከሌሎች ባንኮች ጋር ኦንላይን ሲስተም እየጀመርን  ነው በሚሉ እና በሌሎች ማደናገሪያዎች በመጠቀም የተለያዩ የማጭበርበር ወንጀል እንደሚፈጽሙ ታውቋል።

አንዳንዶቹ የማጭበርበሪያ ስልቶች  ግለሰቦች እንዲያምኑ በኤቲም ገንዘብ ያወጡበት ትክክለኛ ቀን ተነግሯቸው የወንጀሉ ሰለባ እየሆኑ የሚገኙ ሲሆን የግለሰቦች የባንክ ሚስጥር የሚወጣበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ምርመራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ተብሏል።

ወንጀሉ በልዩ ልዩ የአፈፃፀም ስልቶች እየተፈፀመ ከመሆኑም ባሻገር ስልክ በመንጠቅና ቴክኒካል የሆኑ ዘዴዎችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ አካውንት ወደ ቴሌ ብር በማስተላለፍ ወንጀሉ እየተፈፀመ ይገኛል፡፡

ህብረተሰቡ የማያውቋቸው የስልክ ጥሪዎች እና የጹሁፍ መልዕክቶች ሲደርሷቸው ተገቢውን ማጣራት ማድረግ እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
#tikvahethmagazine
https://t.me/lawsocieties
አሳሳቢው ወንጀል እና የአዲስ አበባ የራይድ ሹፌሮች
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በራይድ ታክሲ የትራንስፓርት አገልግሎት በሚሰጡ ሹፌሮች ላይ የሚፈፀም ግድያንና የከባድ ውንብድና ወንጀልን በተመለከተ የተጣሩ የምርመራ መዛግብትን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

በራይድና በሌሎች የትራንስፓርት አገልግሎት ድርጅቶች አማካኝነት የሚሰጡ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ለከተማው ማህበረሰብ ቀልጣፋ የሆነ ትራንስፖርት በመስጠት የከተማውን ማህበረሰብ ችግር በመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል፡፡

አገልግሎቱ በትራንስፓርት ዘርፉ ከሚሰጠው ጥቅም ባሻገር ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት በዚህ ዘርፍ ተሰማርተው ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን በሚደግፉ አሽከርካሪዎች ላይ በተለያየ ጊዜ አሰቃቂ #ወንጀሎች ተፈጽመዋል፡፡
ወንጀሎቹ ከተፈፀሙበት ጊዜ ጀምሮ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ከተሰጠው ስልጣንና ተግባር አኳያ፤ በተቋሙ የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ በርካታ የወንጀል ምርመራዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በቅርቡም ከነሀሴ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከዐቃቤ ህግና ከመርማሪ ፖሊሶች የተውጣጣ የጋራ ቡድን በማዋቀር 9 የምርመራ መዝገቦችን በማደራጀት ጥልቅ የሆነ ምርመራ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በምርመራ ግኝቱ ማረጋገጥ እንደተቻለውም በራይድ የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ሹፌሮች ላይ የወንጀል ተግባሩን የሚፈፅሙት የውንብድና ቡድኑ አባላት አብዛኛውን ጊዜ ወንጀሉን ከመፈፀማቸው በፊት የትራንስፖርት አገልግሎት ፈላጊ በመምሰል፣ መልካም ግንኙነት በመፍጠር ተበዳይ በሆኑት ሹፌሮች ላይ እምነት እንዲያድርባቸው ካደረጉ በኋላ አብዛኛውን ጊዜ ከአዲስ አበባ ወደ ዝዋይ መስመር በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ ከተሞች የትራንስፓርት አገልግሎት እንዲሰጣቸው ያደርጋሉ፤ በኋላም አገልግሎቱን ወደ ሚያገኙበት አካባቢ ሹፌሮቹን በመውሰድ እና በአንዳንድ ሁኔታዎችም አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ ራቅ ወዳሉና ሰዎች ወደማይበዙባቸው ቦታዎች በምሽት በመውሰድ ሹፌሮቹን ለሽንት አቁምልን በማለት ካስቆሙ በኋላ ወንጀሉን የሚፈጽሙ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡

የምርመራ ግኝቱ እንደሚያመላክተው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡትን አሽከርካሪዎች በጋራ በመሆን በስለት በመውጋት፣ በገመድ አንገታቸውን በማነቅና በሽጉጥ ተኩሰው #በመግደል #አስክሬናቸውን በመጣል ተሽከርካሪዎቹንና ሌሎች ንብረቶችን እንደሚወስዱ ተረጋግጧል፡፡

በቡድን የተደራጁ የወንበዴ ቡድኖች በሹፌሮቹ ላይ ጥቃት በመሰንዘር የሚያሽከረክሩትን ተሽከርካሪና ሌሎች ንብረቶች ከወሰዱ በኋላ የወሰዱትን ተሽከርካሪ በዝቅተኛ ዋጋ ያለምንም ህጋዊ ሰነድ በመግዛት አይነታቸውን በመቀየር፣ ታርጋ በመለጠፍ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሌላ የተደራጀ ቡድን መኖሩም በምርመራ ተረጋግጧል፡፡ የምርመራ ቡድኑ በዚህ የውንብድና ቡድን ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹን ወንጀል ፈፃሚዎንና በውንብድና ተግባር የተወሰዱ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

ምርመራቸው በተጠናቀቁና ክስ በተመሰረተባቸው መዝገቦች ላይ እንደታየው ቡድኑ ሶስት የሚሆኑ ሰዎችን በመግደል ሟቾች ሲያሽከረክሩት የነበሩትን ተሽከርካሪና ሌሎች ንብረቶችን የወሰዱ ሲሆን በዚህም ሂደት ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ህይወት ጠፍቷል፡፡ በተመሳሳይም በሌሎች ምርመራቸው በሂደት ላይ ባሉ መዝገቦችም ንብረት ከመዘረፉ ባለፈ የሰው ህይወት መጥፋቱ ተረጋግጧል፡፡

የምርመራ ቡድኑ ባደረገው እልህ አስጨራሽና ጠንካራ ምርመራ በዚህ የወንበዴ ቡድን ውስጥ ሆነው ወንጀሉን በተደራጀ ሁኔታ ሲፈፅሙ የነበሩ ሰዎችን በመያዝ ከተደራጀው 9 የምርመራ መዝገቦች ውስጥ 6 መዝገቦችን በማጠናቀቅ በ12 ተከሳሾች ላይ እስከ ሞት ፍርድ ድረስ በሚያስቀጣ በከባድ የውንብድና ወንጀልና በህገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል ክስ የተመሰረተ ሲሆን በቀጣይም ምርመራቸው እየተከናወኑ በሚገኙ መዝገቦች ላይ ጥልቅ ምርመራ በማድረግ አጥፊዎችን በህግ የማስጠየቅ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በራይድና በሌሎች ድርጅቶች አማካኝነት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሹፌሮች በቡድን በመሆን አገልግሎት በሚጠይቁ ሰዎች ላይ #ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡

አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜም ስለደንበኛው ሙሉ መረጃ መጠየቅና መያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ ውጭ ወይም አዲስ አበባ ውስጥም ሆኖ ጭር ወዳለ ቦታ አገልግሎት በሚጠይቁ ሰዎች ላይ አጠራጣሪ ሁኔታ ካዩባቸው ለጥንቃቄ የሚረዱ ተግባራትን በመፈፀም፣ በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላቶች መረጃዎችን በመስጠት፤ በተደጋጋሚ እንደሚታየውም አገልግሎት በመስጠት ሂደት የተለየ ግንኙነት የሚፈጥሩ ደንበኞች ላይ ትውውቅ አለን በሚል መዘናጋት መፈጠር የሌለበት መሆኑን እና መሰል ክስተቶችም ሲያጋጥሙ ማህበረሰቡ አገልግሎቱን ለሚሰጡ ሹፌሮች ድጋፍ እንዲያደርግና ለፀጥታ አካላት መረጃ በመስጠት የዘውትር ትብብር እንዲያደርግ ስንል እንጠይቃለን፡፡
የፕሬስ መግለጫ
ከፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ
https://t.me/lawsocieties
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Please #Share በማድረግ ሂይወትን እንታደግ 🙏
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👉